የፊልሞና መጽሐፍ ታሪካዊ ዳራ / የፊልሞና መልእክት ለምን ተጻፈ?

በዚህ ቪድዮ አማካኝነት የፊልሞና መጽሐፍን በዐዲስ መንገድ ያጥኑ። ታሪካዊ ዳራውን በማወቅ ስለ ፊልሞና መጽሐፍ ጥልቅ መረዳት ያግኙ እንዲሁም መልእክቱን በሕይወትዎና በመጽሐፍ ቅዱስ ጥናትዎ ተግባራዊ ያደርጉ። በሮም ግዛት ውስጥ የነበረውን ባርነት ጨምሮ የፊልሞና መጽሐፍን ታሪካዊ ሁኔታ ማወቅ ይህን መጽሐፍና መልእክቱን በተሻለ መንገድ ለመረዳት ያግዛል። የኢየሱስ ደቀ መዝሙር መሆን ማለት ከኢየሱስ የተቀበልነውን ይቅርታና ዕርቅ ለሌሎች ማሳየት ማለት ነው።
መጽሐፍ ቅዱስን፣ ታሪኩንና በሕይወታችን ውስጥ የሚያመጣውን ለውጥ በተሻለ መንገድ ለመረዳት እንዲሁም ሥነ ጽሑፋዊ ዐውዱንና ታሪካዊ ዐውዱን ለመረዳት በምናደርገው ጒዞ ዐብራችሁን እንድትጓዙ እንጋብዛችኋለን። መጽሐፍ ቅዱስን በማጥናት ሂደት ውስጥ ይህ እጅግ ጠቃሚው ክፍል ሲሆን መጽሐፍ ቅዱሳዊ አስተሳሰብና ኑሮ እንዲኖረን ያግዘናል። የምናዘጋጃቸው ቪድዮዎች በሁሉም ዕድሜ ላይ ለሚገኙና የተለያየ የመጽሐፍ ቅዱስ ዕውቀት ደረጃ ላላቸው ሁሉ የሚጠቅሙ ናቸው።
#ፊልሞና #ዐዲስኪዳን #የመጽሐፍቅዱስጥናት
www.thebibleeffect.com
FACEBOOK: / experiencethebibleeffect
INSTAGRAM: / thebibleeffect
ተኣማኒ የኾኑ ክርስቲያናዊና መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጽሑፎች፣ ቪድዮዎችና መጻሕፍት ለማግኘት www.Yeamlak.com ድረ ገጽን ይጎብኙ
ምዕራፎች
0፡00 መግቢያ - ውጤታማ ደቀ መዝሙር አድራጊነት ምንድን ነው?
0፡27 ለፊልሞና የተላከው ደብዳቤ ኹነት
1፡14 ባርነት በሮም መንግሥት ውስጥ
2፡11 ጳውሎስና አናሲሞስ
4፡04 ተግባራዊነት- የውጤታማ ደቀ መዝሙር አድራጊነት ማሳያዎች

Пікірлер: 4

  • @thebibleeffectamharic
    @thebibleeffectamharic Жыл бұрын

    የሕይወት ተዛምዶ ጥያቄዎች

  • @FesumeBafkadu
    @FesumeBafkadu

    Tebarku

  • @NerdiAsefa-si2jq
    @NerdiAsefa-si2jq21 күн бұрын

    ዋው እዴት ድቅ ነው

Келесі