የ1እና2 ቆሮንቶስ ታሪካዊ ዳራ - ክፍል 2

የ1 እና 2 ቆሮንቶስ መጽሐፍ ታሪካዊ ዳራ
በጳውሎስና በቆሮንቶስ በነበረችው ቤተ ክርስቲያን መካከል የነበረውን ግንኙነት ለማወቅ ያዘጋጀናቸውን ቪድዮዎች ይመልከቱ፤ ይህም የ1 እና 2 ቆሮንቶስ መጽሐፍ ለዘመናችን ያለውን ዘመን ተሻጋሪ እውነት በተሻለ ሁኔታ መረዳት እንድትችሉ ያግዛችኋል፡፡
በዚህ ክፍል 2 ቪድዮ ጳውሎስ የቆሮንቶስን ከተማ ለቅቆ ከሄደ በኋላ በዚያ በነበረችው ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ምን እንደተፈጠረ እንማራለን፡፡ ባህላቸው በኢየሱስ ላይ ያላቸውን እምነት እንዴት እንደቀረጸውና በቤተ ክርስቲያኒቱ ውስጥ ለተፈጠሩ ጥያቄዎችና ችግሮች ኹሉ እንዴት መንስኢ እንደኾነ እንመለከታለን፡፡ ጳውሎስም በ1 እና 2 ቆሮንቶስ መልእክታቱ እነዚህን ጥያቄዎችና ችግሮች በማንሳት ምላሽ ይሰጣል፡፡
www.thebibleeffect.com
FACEBOOK: / experiencethebibleeffect
INSTAGRAM: / thebibleeffect
ተኣማኒ የኾኑ ክርስቲያናዊና መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጽሑፎች፣ ቪድዮዎችና መጻሕፍት ለማግኘት www.Yeamlak.com ድረ ገጽን ይጎብኙ
#ቆሮንቶስ #TheBibleEffectAmharic #ፍቅር

Пікірлер: 2

  • @thebibleeffectamharic
    @thebibleeffectamharic Жыл бұрын

    ከ1 እና 2 ቆሮንቶስ ልናስተውላቸው የሚገቡ የሕይወት ተዛምዶ ጥያቄዎች፡፡ 1) አስተሳሰቤ፣ ዋጋ የምሰጣቸው ነገሮች ወይም ባህሪዬ ከመጽሐፍ ቅዱስ ይልቅ ባህሌንና ልማዴን የሚያንጸባርቀው በምን በምን ጉዳዮች ላይ ነው? (ለምሳሌ ክርሰቲያናዊ አንድነት፣ ጋብቻና ጾታዊ ግንኙነት፣ የግል መብቶች፣ እርስ በርስ መዋደድ፣ ትንሣኤ፣ ልግስና፣ ወዘተ.) 2) ጳውሎስ በ1ቆሮንቶስ 13 ላይ በገለጸው የፍቅር ሕይወት መመላለስ የምችለው እንዴት ነው? 3) በዙሪያዬ ባሉ ሰዎች ዘንድ የተሻልኹ ኾኜ ለመታየት ድክመቶቼን ለመደበቅ የምሞክርባቸው መንገዶች አሉ? ድክመቶቼን በመጠቀም የክርስቶስን ታላቅነት ማሳየት የምችለው እንዴት ነው?

  • @user-py7cr9cd9f
    @user-py7cr9cd9f4 ай бұрын

Келесі