የሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ታሪካዊ ዳራ | ሐዋርያት ሥራ ለምን ተጻፈ?

በዚህ ቪድዮ ውስጥ የሐዋርያት ሥራ መጽሐፍን በዐዲስ መንገድ ያጥኑ! ሐዋርያት ሥራ መጽሐፍንና የቤተ ክርስቲያንን ታሪካዊ ዳራ በማጥናት ጠለቅ ያለ ግንዛቤ ያግኙ እንዲሁም መልእክቱን በሕይወትዎና በመጽሐፍ ቅዱስ ጥናትዎ ውስጥ ተግባራዊ ያድርጉ፡፡ የሉቃስ ወንጌልም ሆነ የሐዋርያት ሥራ መጻሕፍት የኢየሱስ እውነተኛ ተከታዮች የኢየሱስን የምሥራች በሁሉም ስፍራዎች በማዳረስ ያኖሩትን አሻራ ያሳያሉ፡፡ ከእነርሱም፣ ኢየሱስን መምሰልንና የእግዚአብሔርን ተልእኮ በዓለም ውስጥ ለመፈጸም ለመንፈስ ቅዱስ መገዛት ቊልፍ መሆኑን እንማራለን፡፡
መጽሐፍ ቅዱስን፣ ታሪኩን እና በሕይወታችን ላይ ያለውን በጎ ተጽዕኖ በተሻለ መንገድ ለመረዳት ሥነ ጽሑፋዊ ዐውዱንና ታሪካዊ ዐውዱን ለማጥናት በምናደርገው ጉዞ ውስጥ ተቀላለቀሉን፡፡ መጽሐፍ ቅዱስን በጥልቀት በማጥናት ሂደት ውስጥ ይህ አስፈላጊው የትርጉም ክፍል ሲሆን መጽሐፍ ቅዱሳዊ አስተሳሰብና መጽሐፍ ቅዱሳዊ ኑሮ እንዲኖራችሁ ያግዛችኋል፡፡ የምናዘጋጃቸው የመጽሐፍ ቅዱስ ቪድዮዎች ለሁሉም ዕድሜ የሚሆኑ ናቸው፡፡ እነዚህን ቪድዮዎች በመጠቀም የግልና የቡድን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናትዎን ያሳድጉ፡፡
WEBSITE:
www.thebibleeffect.com
FACEBOOK:
/ experiencethebibleeffect
INSTAGRAM:
/ thebibleeffect
ተኣማኒ የኾኑ ክርስቲያናዊና መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጽሑፎች፣ ቪድዮዎችና መጻሕፍት ለማግኘት www.Yeamlak.com ድረ ገጽን ይጎብኙ
#የሐዋርያትሥራመጽሐፍ #የመጽሐፍ ቅዱስጥናት #አዲስኪዳን
ምዕራፎች
0:00 መግቢያ፡ የእግዚአብሔር ተልእኮ
0:39 ሉቃስ፡ ብቁ የሆነ ደራሲ
1:43 የሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ዓላማ
2:50 ኢየሱስን መምሰል፡ ጸሎት
3:13 ኢየሱስን መምሰል፡ መንፈስ ቅዱስ
3:42 ኢየሱስ መምሰል፡ መጽሐፍ ቅዱስ
4:07 የሐዋርያት ሥራ ቤተ ክርስቲያንና አሕዛብ
5:54 የሐዋርያት ሥራ ቀዳሚ ተደራሲያንና የሮም ሕግ
7:37 የሕይወት ተዛምዶ፡ የእግዚአብሔርን መንግሥት እንዴት እንገንባ፡፡

Пікірлер: 1

  • @thebibleeffectamharic
    @thebibleeffectamharic2 ай бұрын

    የሕይወት ተዛምዶ ጥያቄዎች 1. በሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ውስጥ የኢየሱስን ምሳሌነት እንዴት ነው የተከተሉት? ቤተ ክርስቲያን ይህን ሥራቸውን እንዴት ነው ማስቀጠል ያለባት? የሐዋርያትን ምሳሌ በመከተል ረገድ ራሳችንን ልናጠናክር የሚገባው እንዴት ነው? 2. የሐዋርያት ሥራ መጽሐፍን ስታነብቡ መንፈስ ቅዱስ ለተጠቀሰባቸው ቦታዎች ከፍተኛ ትኩረት ስጡ፡፡ በዚህ መጽሐፍ ውስጥ የኢየሱስ መልካም ዜና በየስፍራው እንዲዳረስ መንፈስ ቅዱስ የተጫወተውን ሚና እንዴት ታዩታላችሁ? ዛሬስ በእኛ ዘመን በሕይወታችን መንፈስ ቅዱስ ምን ዐይነት ሚና ሊጫወት ይችላል? 3. ሐዋርያት የኢየሱስን ምሥራች በየስፍራው ለማዳረስ የተጠቀሟቸው ልዩ ልዩ ስልቶች ምንድን ናቸው? ከእነዚህ ስልቶች ውስጥ ዛሬ እኛ ብንጠቀማቸው ውጤታማ ሊሆኑ ይችላሉ ብላችሁ የምታስቧቸውን ጥቀሱ፡፡ ለምን?

Келесі