የያዕቆብ መልእክት ታሪካዊ ዳራ | የያዕቆብ መልእክት ለምን ተጻፈ

በዚህ የመጽሐፍ ቅዱስ ማስተማሪያ ቪድዮ ውስጥ የያዕቆብ መልእክትን በዐዲስ መልክ ይማሩ። የያዕቆብ መጽሐፍን ከታሪካዊ ዳራው አንጻር በጥልቀት ለመረዳት ጥረት በማድረግ መልእክቱን በግል
ሕይወታችሁና በመጽሐፍ ቅዱስ
ጥናታችሁ ውስጥ ተግባራዊ አድርጉ። የመጀመሪያዎቹ ተደራሲያን የገጠሟቸውን መከራዎችና ታሪካዊ ኹነት በመረዳት ማንበብ የፍትሕ መጓደል በሚያጋጥመን ጊዜም እንኳ በጥበብ እንድንመላለስና የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት ኾነን እንድናድግ ያበረታታናል።
መጽሐፍ ቅዱስን፣ ታሪኩንና በሕይወታችን ውስጥ የሚያመጣውን
ለውጥ በተሻለ መንገድ ለመረዳት እንዲሁም ሥነ ጽሑፋዊ ዐውዱንና ታሪካዊ ዐውዱን ለመረዳት በምናደርገው ጒዞ ዐብራችሁን እንድትጓዙ እንጋብዛችኋለን። መጽሐፍ ቅዱስን በማጥናት ሂደት ውስጥ ይህ እጅግ ጠቃሚው ክፍል ሲሆን መጽሐፍ ቅዱሳዊ አስተሳሰብና ኑሮ እንዲኖረን ያግዘናል። የምናዘጋጃቸው ቪድዮዎች በሁሉም ዕድሜ ክልል ለሚገኙና የተለያየ የመጽሐፍ ቅዱስ ዕውቀት ደረጃ ላላቸው ሁሉ የሚጠቅሙ ናቸው።
www.thebibleeffect.com
FACEBOOK: / experiencethebibleeffect
INSTAGRAM: / thebibleeffect
ተኣማኒ የኾኑ ክርስቲያናዊና መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጽሑፎች፣ ቪድዮዎችና መጻሕፍት ለማግኘት www.Yeamlak.com ድረ ገጽን ይጎብኙ
#የያዕቆብመልእክት #ዐዲስኪዳን #የመጽሐፍቅዱስጥናት
ምዕራፎች
00፡00- መግቢያ የኢየሱስ ደቀ መዝሙር በመሆን ማደግ
00፡26 መጀመሪያዪቱ የአይሁድ ቤተ ክርስቲያን
2፡51 ሐዋርያው ያዕቆብ
3፡45 መልእክተ ያዕቆብ
4፡28 በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ በርትቶ ማደግ

Пікірлер: 3

  • @thebibleeffectamharic
    @thebibleeffectamharic Жыл бұрын

    የሕይወት ተዛምዶ ጥያቄዎች 1) በሕይወቴ ውስጥ የሚያጋጥሙኝን ፈተናዎች መቋቋም የምችለው እንዴት ነው? በእነዚህ ጊዜያት ውስጥ ርዳታ የማገኘው ከየት ነው? 2) ያዕቆብ ጥበብን በተመለከተ ምን ይላል? ያዕቆብ በገለጸው የጥበብ መንገድ መመላለስ የምችለው እንዴት ነው? 3) (ያዕቆብ 3፥1-12)ን ዛሬ ቀኑን ሙሉ አስቡት። አንደበቴ መላ ሥጋዬንና ነፍሴን በየትኛው አቅጣጫ እየመራው ነው? 4) (ያዕቆብ 4፥13-16) ለወደፊት ያሉኝን ዕቅዶቼን ሁሉ ለእግዚአብሔር አስገዝቻለሁን?

  • @MasaMasa-ql7pu
    @MasaMasa-ql7pu9 ай бұрын

    ❤ጌታ ኢየሱስ ይባርክህ ❤

  • @thebibleeffectamharic

    @thebibleeffectamharic

    9 ай бұрын

    ስለተመለከቱ እናመሰግናለን! ለእርስዎ ጠቃሚ እንደነበረ ተስፋ ያድርጉ! በረከት!

Келесі