የዕብራውያን መልእክት ታሪካዊ ዳራ | የዕብራውያንመልእክት ለምን ተጻፈ?

በዚህ ቪድዮ የዕብራውያን መልእክት በዐዲስ መንገድ
ይመልከቱ! ታሪካዊ ዳራውን በመረዳት የዕብራውያን
መልእክትን በተሻለ መልኩ ይረዱ፤ መልእክቱንም
ለሕይወትዎ እና ለመጽሐፍ ቅዱስ ጥናትዎ ተግባራዊ
ያድርጉ፡፡ የዕብራውያን መልእክትን፣ የመጀመሪያዎቹ
ተደራሲያን በደረሰባቸው የስደት ታሪካዊ መቼት
ውስጥ ማንበቡ፣ ሊያጋጥሙን በሚችሉ ችግሮች
ውስጥ ኹሉ በኢየሱስ በማመን እንድንጸና መልእክቱ
ያበረታናል፡፡
የመጽሐፍ ቅዱስን ታሪክና በሕይወታችን ላይ
የሚፈጥረውን ተጽዕኖ በሥነ ጽሑፋዊና ታሪካዊ
ዐውዶቹ ውስጥ በተሻለ ለመረዳት በምናደርገው በዚህ
ጕዞ ላይ ተቀላለቀሉን፡፡ ይህ በመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት
ውስጥ ጠቃሚ የኾነው የትርጕም አካል ሲኾን
መጽሐፍ ቅዱሳዊ አስተሳሰብና የኑሮ ዘዬ እንዲኖርዎ
ያግዞታል፡፡ ቪድዮዎቻችን በኹሉም የዕድሜ ክልል
ለሚገኙና መጽሐፍ ቅዱስን መማር ለሚሹ ኹሉ
የሚኾኑ ናቸው፡፡ እነዚህን ቪድዮዎቻችንን በመጠቀም
የግልና የቡድን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናትዎን ያሳድጉ፡፡
www.thebibleeffect.com
FACEBOOK: / experiencethebibleeffect
INSTAGRAM: / thebibleeffect
ተኣማኒ የኾኑ ክርስቲያናዊና መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጽሑፎች፣ ቪድዮዎችና መጻሕፍት ለማግኘት www.Yeamlak.com ድረ ገጽን ይጎብኙ
#የዕብራውያንመልእክት #መጽሐፍቅዱስጥናት #ዐዲስኪዳን
ምዕራፎች
0፡00 መግቢያ፡ ኢየሱስን መከተል ከባድ ሊኾን ይችላል
0፡23 በሮም የነበረችው የመጀመሪያዋ ቤተ ክርስቲያን
2:05 ስደትና ፈታኝ አማራጭ
3:53 ለዕብራውያን የተጻፈ ደብዳቤ
5:11 የሕይወት ተዛምዶ፣ በአስቸጋሪ ወቅት የእኛ ትኩረት

Пікірлер: 4

  • @thebibleeffectamharic
    @thebibleeffectamharic8 ай бұрын

    የሕይወት ተዛምዶ ጥያቄዎች 1) ኀጢአትን ከሠራኽ ወይም እግዚአብሔርን እንዳሳዘንህ ከተሰማኽ በኋለ “ወደ ርሱ ትቀርባለኽ?” ወይስ “ከርሱ ታፈገፍጋለኽ?” ለምን? 2) ኢየሱስ ርኅሩኅ ሊቀ ካህናት መኾኑ (ዕብራውያን 4፥15)፣ የሚፈተኑትን መርዳት የሚችል መኾኑ (ዕብራውያን 2፥18)፣ እንዲሁም ምሕረትንና ጸጋን የሚሰጥ መኾኑን (ዕብራውያን 4፥16) ማወቅ ምን ያስተምርኻል? 3) በዕብራውያን 11 የተዘረዘሩትን የብሉይ ኪዳን ገጸ ባሕርያትን ዐስቡ? ስለ እነርሱ ምን ምን ታሪኮችን ታስታውሳላችኹ? ኹሉም መልካል ታሪክ ያላቸው ናቸውን? እነዚህን ሰዎች በተመለከተ እውነተኛ እምነት ምን እንደሚሠራ ምን እንደማይመስል ምን ይነግራችኋል? 4) ሰዎች ለኢየሱስ ታማኝ ኾነው እንዲቀጥሉ ለማድረግ እንዴት ማበረታታት እንደምትችሉ የዕብራውያን መልእክት ጸሐፊ ምን ሊያስተምራችኹ ይችላል?

  • @edengobezayehu6236
    @edengobezayehu62368 ай бұрын

    እግዚአብሔር ይባርካችሁ !!! 🙏🙏🙏

  • @thebibleeffectamharic

    @thebibleeffectamharic

    8 ай бұрын

    አመሰግናለሁ!! መጽሐፍ ቅዱስን በማጥናትህ እግዚአብሔር ይባርክህ!

  • @hiyabhiruy
    @hiyabhiruy8 ай бұрын

    ያሚዬ እግዚአብሔር ይባርክህ

Келесі