ፓራሻት ትፃቬ(ኦሪት ዘፀአት 28፣2)፦ "የተቀደሰውንም ልብስ ለክብርና ለጌጥ እንዲሆን ለወንድምህ ለአሮን ሥራለት።"

በእግዚአብሔር እርዳታ ቅዳሜ የሚነበበው ሳምንትዊ የኦሪት ክፍል ከኦሪት ዘፀአት ምዕራፍ 27 ቁጥር 20 እስከ ምዕራፍ 30 ቁጥር 10 የሚነበብ ሲሆን፤ ፓራሻት ትፃቬ በመባል ይታወቃል። ይህ ሳምንታዊ የኦሪት ክፍል እንዲህ ሲል ይጀምራል፦ "አንተም መብራቱን ሁልጊዜ ያበሩት ዘንድ ለመብራት ተወቅጦ የተጠለለ ጥሩ የወይራ ዘይት እንዲያመጡልህ የእስራኤልን ልጆች እዘዛቸው። በመገናኛው ድንኳን ውስጥ በምስክሩ ታቦት ፊት ባለው መጋረጃ ውጭ አሮንና ልጆቹ ከማታ እስከ ማለዳ ድረስ በእግዚአብሔር ፊት እንዲበራ ያሰናዱት፤ በእስራኤል ልጆች ዘንድ ለልጅ ልጃቸው የዘላለም ሥርዓት ይሁን።" ኦሪት ዘፀአት (27፣20_21) ከዚህ የተፃፈው ይህ የኦሪት ትዕዛዝ፤ ቤተ መቅደሱ በነበረበት ጊዜ እና በውስጡ ዘውትር ሲበራ የነበረውን መብራት በንፁህ(በጠለለ) የወይራ ዛይት እንዴት ማብራት እንዳለባቸው የሚገልፅ ትዕዛዝ ነው። ከዚህም በመቀጠል ተፅፎ የምናገኘው ርዕስ ጉዳይ፤ ካህናት በቤተ መቅደሱ የሚያገለግሉበት ልዩ አልባሳት እንዴት መዘጋጀት እንዳለባቸው ነው፦"የተቀደሰውንም ልብስ ለክብርና ለጌጥ እንዲሆን ለወንድምህ ለአሮን ሥራለት።" በዘውትር መብራቱ እና በካህናት ልዩ አልባሳት አሰራር ያለው ቅደም ተከተል አገላለፅ ሁኔታ ሊቃውንቶችን የሚከተለውን ጥያቄ እንዲያነሱ ሳያስገድዳቸው አልቀረም። በአለፈ ሳምንት በአነበብነው ሳምንታዊ የኦሪት ክፍል፤ አጠቃላይ የተንቀሳቃሽ ድንኳኑን እቃዎች አሰራር የተገለፀበት ሁኔታ ስለነበረ፤ ግዴታ በዚህ ሳምታዊ የኦሪት ክፍልም፤ ባለፈው ሳምንት የተጀመረውን ርዕሰ ጉዳይ በመቀጠል፤ የካህናት አልባሳት አንዱ የድንኳኑ መገልገያ ቁስ ስለሆነ በመጀመሪያ ስለ ልዩ ልብሱ አሰራር መገለፅ ነበረበት። ሁሉም የድንኳኑ ቁሳቁሶች እንዴት እንደሚሰሩ ካሰርዳና ሁሉም ነገር ከተዘጋጀ በኋላ በድንኳኑ ምን ማድረግ (እንዴት መብራቱን ማብራት) እንዳለባቸው መግለፅ ነበረበት። ለምሳሌ በዚህ ኦሪት ክፍል መግቢያ ላይ እንደተገለፀው፤ የዘውትር መብራቱ በጠለለ የወይራ ዛይት እንዴት መብራት እንዳለበት መፃፍ ሲገባው፤ የድንኳኑ ቁስቁሶች በሙሉ እንዴት እንደሚሰሩ እያንዳንዱ ገልፆ ሳይጨርስ፤ በመካከል ስለ መብርቱ መግለፁ ለምን አስፈለገ?
የሚድራሽ ራባን መፅሀፍ በመርኮዝ፤ ሊቃውንቶች የቤተ መቅደሱን ዋና አላማ እንደሚቀጥለው በይነውታል፦ እግዚአብሔርም ለሙሴ እንዲህ አለው፤ "ተወቅጦ የተጠለለ ጥሩ የወይራ ዘይት እንዲያመጡልህ የእስራኤልን ልጆች እዘዛቸው።" ኦሪት ዘፀአት (27፣20_21) ከላይ በተፃፈ ትዕዛዝ ላይ ስንመለከት፤ እንደሁል ጊዜው እንዲያመጡ እዛዛቸው አልተባለም። ነገር ግን እንዲያመጡልህ ነው ተብሎ የተፃፈው። ስለዚህ ኦር ሀይም የተባሉት ሊቃውንት እንደሚቀጥለው ያስረዳሉ፦በዚያን ጊዜ የነበሩ ሰዎች የእግዚአብሔር መንፈስ በሙሴ አማካይነት በተሰራው ድንኳን እንደማይውል ሙሴን ስለ አላመኑት፤ ለአንተ ያመጡታል ሲል፦ ይህን የጠለለ የወይራ ዛይት ሲያመጡልህ እና በምዕራብ ያለው መብራት ለሁል ጊዜ ሲበራ፤ የእግዚአብሔር መንፈስ በእነርሱ ላይ ይሆናል። ከዚህም የተነሳ የእርሱ ነቢይነት ትክክል እንደሆነ፣ የእግዚአብሔር መንፈስ በሰማይ ብቻ ሳይሆን በምድርም እንደሚሰፍን ለማስረዳት ስለፈገ እንደሆነ ይገልፃሉ። በዚህም ምክንያት እግዚአብሔር የጠለለውን የወይራ ዛይት ወይም በመብራቱን ለእራሱ አስፈልጎት ሳይሆን፤ እኔ እናንተን ከአህዛብ እጅ ለማውጣት(አውጥቼ ብሩህ የሆነ ህዝብ) እንዳደረኳችሁ፤ እናንተም ይህን የወይራ ዛይት ወስዳችሁ መብራት ስታበሩ፤ ቤተ መቅደሱም በዚህ አለም ለሚገኙ ፍጥረታት ሁሉ ያበራል። ከዚህም የሰው ፍጥረት ወደ ፈጣሪው በመመለስ፤ እና ለእርሱ ብቻ ያገለግላል። ስለዚህ የቤተ መቅደሱ ዋና አላማ፤ ለአለም ብርሀን ሆኖ በረከትን፣ ስኬታማነትን፣ ደስታን፣ ወ.ዘ.ተ ለእስራኤል ልጆች ብቻ ሳይሆን ፤ ንጉስ ሰለሞን ቤተ መቅደሱን ሲያስመርቅ እንደፀለየው፦ "ከሕዝብህም ከእስራኤል ወገን ያልሆነ እንግዳ ታላቁን ስምህን፥ ብርቱይቱንም እጅህን፥ የተዘረጋውንም ክንድህን ሰምቶ ስለ ስምህ ከሩቅ አገር በመጣ ጊዜ፥ መጥቶም ወደዚህ ቤት በጸለየ ጊዜ፥ አንተ በማደሪያህ በሰማይ ስማ፤ የምድርም አሕዛብ ሁሉ ስምህን ያውቁ ዘንድ እንደ ሕዝብህም እንደ እስራኤል ይፈሩህ ዘንድ፥ በዚህም በሠራሁት ቤት ስምህ እንደተጠራ ያውቁ ዘንድ፥ እንግዳው የሚለምንህን ሁሉ አድርግ። " መጽሐፈ ነገሥት ቀዳማዊ (8፣ 42_43) ሁሉም የሰው ልጆች የዚህ ብርሀን ተካፋይ ይሆናሉ። "አገሪቱም ፀሐይና ጨረቃ ያበሩላት ዘንድ አትሻም። የእግዚአብሔር ክብር አብርቶላታልና ብርሃኑም በጉ ነውና።" እንደሚባለው እግዚአብሔር በተቀደሰችው ምድር እና በህዝበ እስራኤል ላይ በርሀኑ(መንፈሱን) ሁል ጊዜ በማዋል፤ ለዘላለም ይጠብቃቸዋል።

Пікірлер: 3

  • @user-kt8sl6if5f
    @user-kt8sl6if5f4 ай бұрын

    ተችሎ ደሰ ይላል ውይይታችሁ 🍀🍀🌱🌷🌷

  • @user-qv5uk5dc3u
    @user-qv5uk5dc3uАй бұрын

    יישר כוח ጠንካሮቻችን : - በጣም ደሰ የሚል ትምህርት ነው የምታስተምሩት ። 🔯

  • @user-kt8sl6if5f
    @user-kt8sl6if5f4 ай бұрын

    ኦሪትን ሚከተል ያቀዋል በውነት ደስ ብችሁኛ ተችሎ ያባትህን ስም አላቀውም ❤🎉

Келесі