ፓራሻት ሚሽፓቲም:- የሀጢአት ክፉ ጉቦ የበሽታ ክፉ ተስቦ።

በእግዚአብሔር እርዳታ ቅዳሜ የምናነበው ሳምንትዊ የኦሪት ክፍል ከኦሪት ዘፀአት ምዕራፍ 21 ቁጥር 1 እስከ ምዕራፍ 24 ቁጥር 18 የሚነበብ ሲሆን፤ ፓራሻት ሚሽፓቲም ይባላል።
በሚቀጥለው ቅዳሜ የሚነበበው ሳምንታዊ የኦሪት ክፍል በብዙ ማህበረስባዊ ርዕሰ ጉዳዮች የሚያተኩር ሳምታዊ የኦሪት ክፍል ሲሆን፤ በዚህ የኦሪት ክፍል ከሚገኙት የተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች፤ ሰፋ ያለውን ቦታ ይዞ የሚገኘው ርዕስ የፍርድ ሥርዓት ሲሆን፤ ይህን የፍርድን ሥርዓት ለመረዳት ደግሞ በሁለት ከፍሎ ማየት ይቻላል፦
የመጀመሪያው የፍርድ ሥርዓት፦ ከሳሽና ተከሳሽ በዳኛ ላይ ተቋቍመው ያልተግባቡበትን ጉዳይ ለዳኛው በማቅረብ እና ዳኛው ነገሩን አመዛዝኖ፣ መርምሮ ለተበዳይ ካሣ፤ ለአጥፊ ደግሞ ቅጣት የሚሰጥበት ሥርዓት ብያኔ ነው።
ሁለተኛው የፍርድ ሥርዓት ደግሞ፦ አንድ ሰው ከዚህ አለም ከተለየ በኋላ፤ ከእግዚአብሔ ፊት ቀርቦ፤ በዚህ ዓለም በነበረበት ጊዜ የሰራው መልካምና መጥፎ(ሀጢአት) በአንድ ተመዝኖ፤ መልካም ለስራ ጥሩ ሽልማት የሚሰጥበት፤ መጥፎ ለሰራ ደግሞ ቅጣት የሚሰጥበት የፍርድ ሥርዓት ይሆናል። ሁለተኛውን ሥርዓት ከአንደኛ የፍርድ ሥርዓት ለየት የሚያደርገው፤ የሰው ልጅ ነብሱ እና ስጋ ከተለያዩ ወይም ከእግዚአብሔር ፊት የሚካሄደው ፍርድ ሥነ ሥርዓት፤ ዝንፈት የለለበት ሲሆን፤ በዚህ አለም የሚካሄደው ፍርድ ግን በጉቦ፣ በዘመድና በስልጣን በመመካት ወይም በመተዋወቅ ሁኔታ ፍርዱ ሊዛነፍ ይችላል። ስለዚህ በዚህ በይሁዳዊያ እምነት መሰረት፤ ዳኞች ፍርድን እንዳይዛቡ እንዲህ ተብሎ ተፅፏል፦ "ማማለጃን አትቀበል፤ ማማለጃ የዓይናማዎችን ሰዎች ዓይን ያሳውራልና፥ የጻድቃንንም ቃል ያጣምማልና።" ኦሪት ዘፀአት(23፣8) የሀጢአት ክፉ ጉቦ የበሽታ ክፉ ተስቦ እንዲሉ፤ የጉቦ (የሙስና ) ሀይል አይንን ይሰውራል። ስለዚህ ጎቦ መቀበል ትልቅ ተፅኖ ስለሚያሳድር፤ የዳኛውን ፍርድ የማጣመም እና የፍድ ሚዛን ችሎታውን በማዛባት ትክክለኛ ፍርድ እንዳይፈርድ ያደርገዋል። የኦሪት ሊቃውንቶችም ዳኞች ከዚህ ዓይነት ስህተት እንዳይደርሱ፤ ከፊቱ ለፍርድ የሚቀርብ ሰው ጠዋት ሰላም ቢለው፤ በዚያ ሰው ፍርድ ላይ ዳኛ ሆኖ መቀመጥ እንደለለበት ያስጠነቅቃሉ። ከዚህም በተጨማሪ በሚድራሽ ታንሁማ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ "አለም ፀንታ እንድትኖር ከፈለጋችሁ፤ ትክክለኛውን ፈርድ ፍረዱ። የኖህ ትውልድ የጠፋውም፤ ፍርድን ሰለ አጣመሙ ነው።" ራቢ ሽሙኤል ባር ናህማኒ በራቢ ዮናታን ስም እንዲህ ይላሉ፦ "እያንዳንዱ ፈራጅ እውነተኛ ፍርድን በእውነት ከፈረደ የእግዚያብሔር መንፈስ በህዝበ እስራኤል ዘንድ እንዲያድር ያደርጋል።"

Пікірлер: 1

  • @zemachtaklea6628
    @zemachtaklea66284 ай бұрын

    እናመሰግናለን❤❤

Келесі