ፓራሻት ትሩማ፦ "በመካከላቸውም አድር ዘንድ መቅደስ ይሥሩልኝ።"(ዘፀአት 25፣8) እንዴት ለእግዚአብሄር ቤት መቅደስ መስራት ይቻላል?

"እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። ሰማይ ዙፋኔ ነው፥ ምድርም የእግሬ መረገጫ ናት፤ የምትሠሩልኝ ቤት ምን ዓይነት ነው? የማርፍበትስ ስፍራ ምንድር ነው?" ትንቢተ ኢሳያስ(66፣1)
በእግዚአብሔር እርዳታ ቅዳሜ የምናነበው ሳምንትዊ የኦሪት ክፍል ከኦሪት ዘፀአት ምዕራፍ 25 ቁጥር 1 እስከ ምዕራፍ 27 ቁጥር 19 የሚነበብ ሲሆን፤ ፓራሻት ትሩማ ይባላል። ይህ ሳምንታዊ የኦሪት ክፍል እንዲህ ሲል ይጀምራል። “እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ ሲል ተናገርው። ስጦታ ያመጡልኝ ዘንድ ለእስራኤል ልጆች ተናገር፤ በገዛ እጁ ሊሰጠኝ በልቡ ከሚያምረው ሰው ሁሉ መባ (ቁርባን) ተቀበሉ። ከእነርሱም የምትቀበሉት መባ ይህ ነው። ወርቅ፤ ብር፤ ናስም፤ሰማያዊና ሐምራዊ ቀይም ግምጃ፤ ጥሩ በፍታም፤ የፍየልም ጠጉር፤ ቀይ የአውራ በግ ቁርበት፤የአቆስጣ ቁርበት፤ የግራርም እንጨት፤ የመብራትም ዘይት፤ ለቅብዓት ዘይትና ለጣፋጭ ዕጣን ቅመም፤ መርግድም፤ ለኤፎድና ለደረት ኪስ የሚደረግ ፈርጥ። በመካከላቸውም አድር ዘንድ መቅደስ ይሥሩልኝ። እኔ እንደማሳይህ ሁሉ፤ እንደ ማደሪያው ምሳሌ እንደ ዕቃውም ሁሉ ምሳሌ፤ እንዲሁ ሥሩት። ከግራር እንጨትም ታቦትን ይሥሩ፤ ርዝመቱ ሁለት ክንድ ተኩል፤ወርዱም አንድ ክንድ ተኩል፤ ቁመቱም አንድ ክንድ ተኩል ይሁን። በውስጥና በውጭም በጥሩ ወርቅ ለብጠው፤ በእርሱም ላይ በዙሪያው የወርቅ አክሊል አድርግለት። አራት የወርቅ ቀለበቶችም አድርግለት፤ እነርሱንም በአራቱ እግሮች ላይ አኑር፤ በአንድ ወገን ሁለት ቀለበቶች፤ በሌላው ወገን ሁለት ቀለበቶች ይሁኑ፤ በዚህ ፓራሻ ውስጥ አብዛኛው ተፅፎ ያለው የእግዚአብሔርን የድንጋይ ጽላቶች (ሚሽካን) ከምን አይነት ዕቃዎች እንደሚሠራ፤ ርዝመቱ ምን ያህል እንደሆነ፤ ቁመቱም ስንት እንደሆነ በብዙው ይተነትናል”። ለምሳሌ፦ አንድ ይሁዲ ሰው ብዙ ዓመት ውጭ አገር ከቆዬ በኃላ ከዕለታት አንድ ቀን በፋክስ መስሪያ ቤት ወደ እስራኤል አገር ለመሄድ ይጠራል። ይህ ሰውዬም ይህን ሲሰማ በጣም ይደሰታል። ከዚያም ቀጥሎ ያለውን ንብረት በሞላ ሽጦ ከጨረሰ በኃላ በዛን ዘመን መኪና አልነበረም፤ መርከብ ብቻ ነው የነበረ። ይህ ሰው ንብረቱን ተቀብሎ ከጨረሰ በኃላ ወደ መርከቡ ቤተሰቡን ይዞ ይገባል። ነገር ግን ጤና የለለው ሰው በሞላ ከመርከቡ መሰቀል የለበትም ብለው ህግ አውጀዋል። ይህ ይሁዲም ከመርከቡ ከመሰቀሉ በፊት እሱና ቤተሰቦቹ ምርመራ ያከናውናሉ። ነገር ግን የዚህ ይሁዲ ልጆች የተወሰኑት ጤና ስላልነበራቸው ከመርከቡ መሳፈር አልቻሉም። ምክንያቱም ጤና የለለው ሰው ከመርከቡ ከተሰቀለ ለጤናማው ሰው በጣም አስጊ ይሆናል በማለት የመርከቦች ባለቤት ከለከሉ። ይህ ሰውዬም እነዚህን ልጆች ትቶ እያለቀሰ ተለያቸው። እነሱም እኛ ሁልጊዜ ከዚሁ ዘላለም እንኖራለን፤ ከመርከቡም መሰቀል አንችልም በማለት ተስፋ ቆርጠው በእልቅሶ ተለያዩ። ተምሳሌ በዚህ ዓለም በጎ ሥራ ለሰው በጣም ጠቃሚ ነው። ይህ ማለት አንድ ሰው በሕይወት ሲኖር በጎ ሥራ የሚሠራ ከሆነ ምሳሌ ኦሪትን የሚማር ከሆነ፣ ሀይማኖትን የሚጠብቅ ከሆነ፣ የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ ሳያዛንፍ የሚጠብቅ ከሆነ፤ አይበለውና ሲሞት ይህ በሞላ በሕይወቱ ያከናወናቸው በጎ ተግባራቶችና ሥራዎች በሞላ ወደ ሰማይ አብረውት ይሄዳሉ። አይ እንደዚያ ይሁዲ ሰውዬ ግማሽ ልጆች ታመው ከመርከቡ ሳይገቡ እንደቀሩት እኛም በሕይወታችን ለነፍሳችን ጠቃሚ ነገር ካልሠራንላት በሰማይ ላይ ጥሩ ልታገኝ ወይም ገነት መግባት አትችልም። ስለዚህ በሕይወታችን ስንኖር ጥሩ ተግባራቶችን ለማድረግ እንሞክር።

Пікірлер: 3

  • @zemachtaklea6628
    @zemachtaklea66284 ай бұрын

    በርቱልን ብርቱ ቀጥሉበት በዚህ ሐሳብ

  • @user-bu8sg9kb6o
    @user-bu8sg9kb6o4 ай бұрын

    Dase yamele temhirt naw hulam endzhi ya egziyabharn kale betstmrn teru naw edema ena tan ysthi

  • @zemachtaklea6628
    @zemachtaklea66284 ай бұрын

    ሰላም ጤና ይስጥልን የተከበራችሁ የተወደዳችሁ ይህ ትምህርት ቀላል አይደለም ስለዚህ የኦሪት ክፍሎች እንደዚህ በማስተማር ቀጥሎበት የሁላችንም ትምህርት ለማወቅ ያቀረበችዎት ሀሳብ የእግዚአብሔርን ቃል ማወቅ አስፈላጊ ነው መልካም ይሁንላችሁ አሜን

Келесі