Ethiopia

Ойын-сауық

በአሉ ግርማ ከፃፋቸው እጅግ ተወዳጅ ድርሰቶቹ አንዱ ነው። "ደራሲውደራሲው "
ደራሲው "ን ከሌሎቹ ዘመን ተሻጋሪ ሥራዎቹ ለየት የሚያደርገው በአሉ ለዚህኛው ድርሰቱ ብዕሩን ያነሳው በዘመኑ የነበረውን ኢትዮጵያዊ ደራሲ በሌላ መነፅሩ ሊያሳየን መሆኑ ነው። ወደር የማይገኝለት ሽቅርቅሩ ዘናጩና ጥንቁቁ በዓሉ ግርማ በብእሩ ከትቦ እንካችሁ ያለንን የዘመኑን ደራሲ ያየበትን ድንቅ ክህሎት በእኛ የሚለካ ባይሆንም በተቻለን አቅም ክብር ሰጥተን ለመተረክ ሞክርነዋል።
አንተ የጥበብ ልጅ ሆይ ነብስህ በሰላም ትረፍ።
ተራኪዎች
አንተነህ አስረስ፣
ብሌን ሳሙኤል፣
ቤርሳቤህ ፈረደ
እና ሌሎችም።
ኢትዮእማ ቲዩብ
Ethioemma Tube April, 2022.
ፍሉት ማጀቢያ--ሀና ምትኩ

Пікірлер: 22

  • @kiyatsegaye3106
    @kiyatsegaye3106 Жыл бұрын

    Excellent work... thanks Bealu Girma, and the artists for narrating the book. Its said Sirak's story is Gash Sebhat G/Egziabher's life story.

  • @ethioemmatube

    @ethioemmatube

    Жыл бұрын

    thankyou u got it

  • @merongedlu8929
    @merongedlu89292 жыл бұрын

    እናመሰግናለን ቆንጆ ቅዳሜ ልጀምር ነው

  • @chagnimediaoffical
    @chagnimediaoffical2 жыл бұрын

    ምርጥ ስራ ከምርጥ ከያኒያን ጋር ሲገናኝ ደስ ደስ ደስ ይላል!....አንትሽ አድምተህ ነው የምተርከው/የምተውነው ብል ይቀለኛል…/ የድምጽ ኤዲቲንጉ ደግሞ አምብሽ እጅግ ጥንቁቅና አዳዲስ ስታይል የምታሳየን ስለሆንክ እና ስላወኩህ ኩራት ይሰማኛል…ሌሎችም በዚህ ስራ የተሳተፉት ተዋንያን ድምጻችሁ ከለሩና ስሜት ውስጥ የምትገቡበት መጠን ገራሚ ነው…..ደራሲው ደራሲው….ቡም ያበደ ስራ ነው!

  • @ethioemmatube

    @ethioemmatube

    2 жыл бұрын

    ክብረት ይስጥልኝ

  • @keludifamilyshow
    @keludifamilyshow2 жыл бұрын

    እንኳን ጥበብ ላንበረከከችው የጥበብ አፍቃሪ የጥበብን ጣእም ላላወቀ ለማወቅም ላልጣረ የጥበብ ከራማ እንዲታረቀው ብሎም የተፀናወተውን የጥላቻ መንፈስ ከላዩ ላይ ግፍፍ የምታደርገው ውድ ክቡር መተኪያ የሌለህ በዓሉ ግርማ እውነት ውስጥ ዘልቆ የሚገባው እና ስሜትን የሚቆጣጠረው ተሠጥኦህ በህይወቴ ሲያስደምመኝ ይኖራል ፤አንትሽ ወንድሜ ካንተ ብዙ ተምሬያለሁ አጃይብ ነው ትረካህ ሳይሆን ትወናህ መድረኩን ከጫፍ እስከጫፍ የተቆጣጠርክ መሪ ተዋናይ ለመሆንህ ስራህ ያሳብቃል። በጥልቀት ሳደምጥህ እኔም እንዳንተ የጥበብ ከራማው ወለል ብሎ በተከፈተልኝ ብዬ ሲራክ እስክንድር መፅሀፉን እንደጀመረ ሲነግረው ቅናት ወረፍ እንዳረገው እኔንም ሞክሮኝ ነበር። ከምር ትችላለህ ለዚህ እንቁ የኢትዮጵያ ልጅ በአንተ አንደበት መተረኩ ክብር ነው እንዲሁም ሌሎች አጋሮችህ በቃ በጥበብ የበሠለ ሠው አያጠራጥርም። እኔን ያማለለኝ በዛሬው ትእይንት የሠብለ እና የሲራክን መገናኘት ተከትለው የሚዥጎደጎዱት የፍቅር አማልክትን ከያሉበት የሚሠበስቡት ውብ የቃላቶች ድርደራ የአረፍተ ነገሮች አሠካክ አጀብ ነው። የቱን ጠቅሼ የቱን ልተወው እውነትም ሲራክ ወጣት ወጣት እየተጫወተ ነው በከባድ ሁኔታ ከህይወት ጋር ፍቅር ወድቋል ያስደምማል ግን ደግሞ መጨረሻው ያስፈራል የእስክንድር ስጋት እኔም ጋር አለ 👉ሴቼንቶ ግን ምንድነው ውይይት የምንለው ወይስ ሌላ? እናት ሀገር ወይም ሞት ሶሻሊስት ኮሚኒስት ብቻ የቱ ይሆን ለአንዲት ሀገራችን የጠቀማት እምባዋንም ያበሠላት ?የእንቁጣጣሹ ድባብ ዋው እንዴት ይመስጣል እኔም በአደይ አበባ መሀል እንሾሽላ ሞቄ የተከበብኩ መሠለኝ በመጨረሻም የወቅቱ የሙዚቃ ንግስት ብዙዬ ልቤን አርዳዋለች ደራሲውን ይህን በመሠለ ብቃትና ድባብ ስላቋደሳችሁን ፈጣሪ ከማያልቀው በረከቱ ያቋድሳችሁ ኑሩልን እናመሠግናለን🙏🙏

  • @ethioemmatube

    @ethioemmatube

    2 жыл бұрын

    አንድ ክፍል ባለፈ ቁጥር ሁላችንም ያንቺን አስተያየት እንጠብቅ ጀመረ እኮ።ቋንቋሽ ልብ ያሞቃል ።በተመስጦ የሚያዳምጥ ሰው መጽሀፉን ከተራኪው በላይ ያውቀዋል ለዚህ ምስክሩ አንቺ ነሽ ።ክብረት ይስጥልን

  • @ambaw1004

    @ambaw1004

    2 жыл бұрын

    ከሉዲዬ ! የጥበብ ዛር ከነ ምርቃናዋ ሠፍራብሻለች ማለት ነው? ጥበብ በግራና ቀኝ ትክሻዋ እየታከከች በተሰናኘችው የቃላት ውቅር ጣፍጣ፤ እንደ ሰጎን እንቁላሎች በአሸዋው ዳር ዳር በሚበትናቸው በሚያማምሩ ህብረቀለማት፤ ባሸበረቁ አልማዛዊ የስልጠተ መሳሪያ ፈርጦች እየተገለጸ.. ሰጥ ለጥ በሎ የከተብሽዉን ማንበብ እንዴት እንደሚያረካ ኮመንትሽን ያነበበ የደረሰበት ያውቀዋል ። ከሉዲዬ ከዚህ ቀደም ነግሬሽ ነበር የበዓሉ ስትሰሚ የምትከትብዉ ሀሳብ የኪነት ዛርሽ እንደተነሳብሽ ያሣብቃል፤ ወደታሪኩ ሥንመለስ አንቺ የጠነቆልሽዉን በመደገፍ ፤ የሢራክዬ በፍክር መክነፍ አላማረኝም፤ ሁለት ካርታ ሥቦ መጫወቱ አስፈርቶኛል ፤ እስኬዉ ጥሩ ሀሳብ ፈልቆለታል፤ በተቃራኒው ጌጤ ዛሬ በጣም ተረጋግታለች አይመስልሽም ? ብቻ ምርጥ ነበር ••••

  • @keludifamilyshow

    @keludifamilyshow

    2 жыл бұрын

    @@ethioemmatube እኔም ከልብ አመሠግናለሁ አንትሽ ወንድሜ ይህንን ድንቅ የጥበብ ማእድ ስቋደስና የሚያስደምመውን የአተራረክ ብቃት ስሰማ ከልጅነቴ ከኢለመንተሪ ሀይስኩል ከዚያም በኋላ የታሸሁበት ብዙ ያየሁበት የተውኔት ፍቅር ያገረሽብኛል ለዛም ነው እያንዳንዶቹ ካራክተሮች ውስጥ ሳላስበው ዘልቃለሁ ክበርልኝ ወንድም አለም🙏🙏🙏

  • @keludifamilyshow

    @keludifamilyshow

    2 жыл бұрын

    @@ambaw1004 አምብዬ ውስጤን ሁሌም በደንብ ትረዳዋለህ ወንድሜ የቀድሞ ያገረሽብኛል የጥበብ ከራማ ዛር ወዘተ በለው ያንዘፈዝፈኛል😂የዛሬውን አካሄድ በሚገባ ገልፀኸዋል ግን ጌጤ ሳትሆን ፅጌ ለማለት ፈልግህ መሠለኝ😉 አምብዬ የሙዚቃ ምርጫህ ግን ተወው በቃ አደንዝዞኛል አቤት የድሮ ሮማንቲክ ሙዱ ልዩ ነበር

  • @ambaw1004

    @ambaw1004

    2 жыл бұрын

    @@keludifamilyshow ከሩቅ ሆኖ፤ ከሰማይ ጋር የተሰፋ ከሚመስልሽ አውላላ መካከል.፤ የጥበብ እስትንፋስ፤ እንደ ኤፍራጥስ ንፋሳት፤ እንደ ቢሾፍቱ ቆሪጦች ተመስላ፤ እየጠራችሽ ነይ ነይ ••••እያለች••• በላይሽ ላይ ሰፍራለች፡፡ የስሙን ዕርማት ተቀብያለሁ ፤ እና ከሉዲዬ ሙዚቃዎቹ ከልብ የተሞዘቁ ሥለመሆናቸው እሙን ነው፤

  • @user-fg6pb2or5k
    @user-fg6pb2or5k2 жыл бұрын

    እንደተለመደዉ እናመሰግናለን 👍

  • @grmbyn1
    @grmbyn12 жыл бұрын

    Part 9 please?

  • @ambaw1004
    @ambaw10042 жыл бұрын

    ዉድ ደራሲ በዓሉ ግርማ አንተን አለማድነቅ አይቻልም፤ እንዲህም ያለ የሥነ - ጽሁፍ ኪነት የለም፤ ወዝ በጥራት ከኢትዮጵያ አልፎ የአለም ዙፋን ላይ በኩራት የሚቀመጥ፤ ውልውል ወይራ ስራ፤ አፋችንን አስከፍቶ ዝንብ የሚያስገባ የኢትዮጵያን ሥነ - ጽሁፍ ኪነትን ኢትዮጵያዊነትን የሚያደምቅ የሚያደማምቅ የድብርት ደመናን የሚበትን መጽሐፍ ። *Ufaaaa* በዓሉ እንወድሀለን፤ ይባላል ምንም ጥዑም ምግቢ ቢያቀርቡልህ አቀራረቡ ካላማረ ምግቡ አይበላም፤ ተራኪ አንተነህ አሥረስ የዉብዳር እናም ሌሎች ተራኪያን ለሁላችሁም ትልቅ ክብር አለኝ ፤ ለኪነት ተሰጥታችሗል ፤ እዋይ ተከስተ አንትሽ ድሮም በትወና ልዕልናህ አደንቅህ ነበር ፤ አሁን ደግሞ ይህንን ትረካ በትንፋሽህ እፍ ብለህ ነፍዝ የዘራህበት አንተዉ ነህ፤ የ ጋሽ በዓሉ ግርማ ነፍስ በአንተ እረክታለች ወዳጄ ልቤ ። ለኪነት መሰጠት እዚህ ድረሥ ሲደርስ አሁን ላይ ግብዐተ መሬቱን እያሥፈጸሙ ላሉ ሁሉ የትምህርት በትር ነው አበቃሁ።

  • @ethioemmatube

    @ethioemmatube

    2 жыл бұрын

    ወዳጄ ልቤ ዘፈኖቹን ከየት ፈልፍለህ እንደምታመጣቸው የውቤ በረሀዋ አድባር ትወቀው።ይህን ስራ አንተ ባትሸልመው እንዲህ አይዋብም ነበር።ትንሿን መስመር ትረካ ክብር ሰጥተህ በቅንብር ከፍ የምታደርጋት አንተ ነህና በተራኪዎቹ ስም በጣም እናመሰግናለን

  • @ambaw1004

    @ambaw1004

    2 жыл бұрын

    @@ethioemmatube አንትሽዬ ለኪነቱ ማደግ የበኩላችንን ጠጠር ማቀበል ግዴታም ጭምር ነው! ክብሩ ለኔ ነው

  • @gethug.3028
    @gethug.30282 жыл бұрын

    ትረካ በባለሙያዎች ሲተረክ እንዴት ዉብ እንደሆነ አሳይታችሁናልና እድሜ ከጤና ጋር ይስጥልን:: ደራሲው ክፍል 8 ከተለቀቀ ሁለት ሳምንት አለፈው ክፍል 9 ግን ጠፋ:: በደህና ነው? እባካችሁ ልቀቁልን

  • @ethioemmatube

    @ethioemmatube

    2 жыл бұрын

    እናመሰግናለን ስለዘገየን ይቅርታ እየጠየቅን ዛሬ ክፍል 9 ይለቀቃል

  • @baryawbaryaw1390
    @baryawbaryaw1390 Жыл бұрын

    ግሩም አተራረክ ነው።

Келесі