ደራሲው derasew 10 ድርሰት በአሉ ግርማ Bealu Girma አማርኛ ትረካ audio book 2022

Ойын-сауық

በአሉ ግርማ ከፃፋቸው እጅግ ተወዳጅ ድርሰቶቹ አንዱ ነው። "ደራሲውደራሲው "
ደራሲው "ን ከሌሎቹ ዘመን ተሻጋሪ ሥራዎቹ ለየት የሚያደርገው በአሉ ለዚህኛው ድርሰቱ ብዕሩን ያነሳው በዘመኑ የነበረውን ኢትዮጵያዊ ደራሲ በሌላ መነፅሩ ሊያሳየን መሆኑ ነው። ወደር የማይገኝለት ሽቅርቅሩ ዘናጩና ጥንቁቁ በዓሉ ግርማ በብእሩ ከትቦ እንካችሁ ያለንን የዘመኑን ደራሲ ያየበትን ድንቅ ክህሎት በእኛ የሚለካ ባይሆንም በተቻለን አቅም ክብር ሰጥተን ለመተረክ ሞክርነዋል።
አንተ የጥበብ ልጅ ሆይ ነብስህ በሰላም ትረፍ።
ተራኪዎች
አንተነህ አስረስ፣
ብሌን ሳሙኤል፣
ቤርሳቤህ ፈረደ
እና ሌሎችም።
ኢትዮእማ ቲዩብ
Ethioemma Tube may, 2022.
ፍሉት ማጀቢያ--ሀና ምትኩ

Пікірлер: 45

  • @THuB21
    @THuB21 Жыл бұрын

    በጣም እናመሰግናለን ለድንቅ አቀራረባችሁ❤❤❤

  • @aziye
    @aziye8 ай бұрын

    በጣም ደስ የሚል የተዋጣለት ትረካ ነበር በዚህ ስራ የተሳተፋችሁ ተባረኩ ከቁጥር አትጉደሉ💚🥰

  • @ambaw1004
    @ambaw10042 жыл бұрын

    በዓሉ ግርማ ስለ ደራሲው ልብወለድ መፃፍ ይፈልግና ጋሽ ስብሐት ጋር ይሄዳል ፤ "ሲቢ ስለ ደራሲ መፃፍ ፈልጌ ነበር ፤ እራሴን ሞዴል ባደርግ ልክ አይመጣልኝም ፤ ስለዚህ ስለአንተ እንድፅፍ ፍቀድልኝ" "በጣም ደስ ይለኛል" አለ ስብሐት። ስብሐት ማስታወሻ ላይ ለዘነበ ሲያጫውተው፦ "አየህ በዓሉ ብዙ አንባቢ አለው ፤ዝነኛ ደራሲ ነው፤ እኔ ማንም አያውቀኝም ፤ በአሉ በነፃ ማስታወቂያ ልስራልህ እያለኝ ነው ፤ ይህንን የበዓሉን መጽሐፍ ያነበቡ አንባቢያን እኔንም ለማንበብ ሰፍ ብለው ይጠብቃሉ።" (ስብሐት ሁሌም ነገሮችን ቀለል አድርጎ በአዎንታዊ ጎኑ የሚመለከትበት ባህሪው ሁሌም ይደንቀኛል) ልብወለዱ በዚህ መልኩ ተጠነሰሰ። ስብሐት ያወራል፤ በአሉ ማስታወሻ ይይዛል፤ በየመሐሉ ጥያቄ ይጠይቃል፤ ስብሐት ይመልሳል። ቀስ በቀስ ጥራዙ ዳጎስ እያለ መጣ፤ ደራሲው ነፍስ መዝራት ጀመረ፤ ስብሐት ገፀባህሪ ሆነ። ደራሲው ተወለደ። መጽሐፉ አልቆ ስብሐት አንብቦት እንዲህ አለ፦ "የኔ ታሪክ 50% ቢሆን ነው። የቀረውን የበዓሉ ምናብ የወለደው ነው። በጣም ቆንጆ አድርጎ ነው የፃፈው"

  • @selam801
    @selam8015 ай бұрын

    በአሉ ግርማ በጣም እምወደው ደራሲ ይሄ መጽሐፉ ደሞ በይበልጥ በጣም ወደድኩለት❤😊

  • @grmbyn1
    @grmbyn12 жыл бұрын

    ተባረኩ:: ሌሎችም ምርጥ ምርጥ ድርሰቶችን እንደምታስኰመኩሙን ተስፋ አለኝ::

  • @kesisserebeazezew7287
    @kesisserebeazezew7287 Жыл бұрын

    Thank you very much for this work I love it.

  • @dawitsiltan5109
    @dawitsiltan51092 жыл бұрын

    ግሩም አቀራረብ ነው ዋው ምስሉ አይኔ ላይ መጣ እናመስግናለን 👍

  • @kiyatsegaye3106
    @kiyatsegaye3106 Жыл бұрын

    A great job 👏. It's beyond narration ... you took us back to the 70s E.C. socio-economic life of Ethiopian people.

  • @ferhanmohammed2877
    @ferhanmohammed28772 жыл бұрын

    Betam new menamesegnew

  • @samiraseid9324
    @samiraseid93242 жыл бұрын

    Thank you so much for amazing story book reading you are well appreciated always

  • @danielghebre
    @danielghebre2 жыл бұрын

    ደስ የሚል ትረካ እና ቀጥሉ እናመሰግናቸዋለን

  • @tameegiddisa3941
    @tameegiddisa3941 Жыл бұрын

    በዓሉ ግርማ የምወደው ደራሲ ነው የእሱን ሰራ እንዲግሩም አድርገው ሰላቀረብ እጀግ ደሰ ብሎኛል በርቱልን አመሰግናለው!!!

  • @Yosi-xv7sv
    @Yosi-xv7sv5 ай бұрын

    በርቱ

  • @Habeshawi26
    @Habeshawi26 Жыл бұрын

    ✌🏾🙏🏽

  • @ferhanmohammed2877
    @ferhanmohammed28772 жыл бұрын

    Qetel qetel

  • @MahletFantahun
    @MahletFantahun2 жыл бұрын

    ተባረክልኝ! ተባረኩልኝ!

  • @nolinoli9641
    @nolinoli9641 Жыл бұрын

    በጣም አመሰግናለሁ!!

  • @user-cf6zx2sq5n
    @user-cf6zx2sq5n5 ай бұрын

    ይህን ድንቅ መፅሐፍ እንዲህ ባመረ ጥምረትና የድምፅ ጥራት ስለተረካችሁልን ክብረት ይስጥልኝ እያልኩ በድምፅና በምስል የተሳተፋችሁ ሁሉ ክበሩለን በዚሁ ጥምረት ሌላ ስራ እንጠብቃለን ከትረካነቱ ባሻገር ትወናም ነበረውና እናመሰግናለን በርቱ ❤️🙏❤️

  • @meazabeza2806
    @meazabeza28062 жыл бұрын

    እጅግ በጣም አመሰግናለሁ ሚገርም አተራረክ🙏💚💛❤️

  • @EsmaelM-ze8nk
    @EsmaelM-ze8nk7 ай бұрын

    በአሉ አልሞተም በአሉ መቼም አይሞትም። ትውልድ እስከ አለ በአሉ አለ። ጋሽ ስብሀት ለኛ ሼክስፒር አችን ነው። ሁለቱንም በጣም እወዳቸዋለሁ።

  • @yaredenayared8873
    @yaredenayared8873Ай бұрын

    ጉደኛ ነው በትረካ ፊልም አሳያችሁን ድንቅ ችሎታችሁን አለማድነቅ ድድብና ነው።

  • @teddysiyoum5612
    @teddysiyoum56122 жыл бұрын

    Big thanks to all of you!! 💚💛❤️ 🙏🏾🙏🏾🙏🏾

  • @bezawitfantahun5565
    @bezawitfantahun55652 жыл бұрын

    ምርጥ ምርጥ ተራኪዎች ;ምርጥ ማጀቢያሙዚቃ ወደር የሌለው አቀራረብ እናመሰግናለን ።

  • @ethioemmatube

    @ethioemmatube

    2 жыл бұрын

    ክብረት ይስጥልን

  • @yohanslily4245
    @yohanslily4245 Жыл бұрын

    ከልብ አመሰግናለሁ በሌላ ሰራ እንጠብቃለን 🙌🏼💚💛❤️

  • @Neba-b
    @Neba-b2 жыл бұрын

    cheers !👍👍👍

  • @zer5667
    @zer56672 жыл бұрын

    በጣም ጥሩ ነበር አመሰግነዋለሁ

  • @merongedlu8929
    @merongedlu89292 жыл бұрын

    ውድ ወገኖች እኔ በግሌ በጣም ከልቤ አመሰግናችኋለሁ። ጥንቅቅ ያለ ስራ ነው የምትሰሩት በርቱ

  • @ethioemmatube

    @ethioemmatube

    2 жыл бұрын

    እኛም እናመሰግናለን ሸርሽሩት ለይኩት ኮምቱት።እንበዛለን ገና

  • @Degsewtube
    @Degsewtube Жыл бұрын

    ሰላም ጤና ይስጥልኝ ለዚህ ቤት ኦ ገራሚ ትረካ ነው የእዮብ ዮናስ ታናሺ ወንድም መሆን አለብህ👌

  • @ethioemmatube

    @ethioemmatube

    Жыл бұрын

    እናመሰግናለን።በእዮብ ተገርተን በምክሮቹ አድገን ነው ።ልክ ነሽ

  • @samm8405
    @samm840510 ай бұрын

    C'est la vie= ሴ ላ ቪ

  • @tegegnyimerkassa4813
    @tegegnyimerkassa48132 жыл бұрын

    🇨🇦🇨🇦🇨🇦🙏💚💛❤️

  • @samm8405
    @samm840510 ай бұрын

    ያነበብኩት ከ 30 ዓመት በፊት ነው :: ተረት ሰፈርን ቀበሌ 15/16 ን በምናቤ አየቃኘሁ... ምስጋናዬ ይድረስ

  • @zewidekebede7449
    @zewidekebede74497 ай бұрын

    በጣም ወደድኩት ቀጥልበት ደሞ 4:08 ሌላ

  • @semiraweleyewa3586
    @semiraweleyewa35863 ай бұрын

    ግሩም ነዉ ደራሲዉ ተሰጥቶታል በጣም ቀልብ እሚወስድ ድርሰት 3 ድርሰቶቹን አዳምጫለሁ በጣም የወደድኩትና ያከበርኩት ደራሲ ነዉ አቅራቢወቹም ሁላችሁንም አመሰግናለሁ እንዲህ ባማረና ለጆሮ ተስማሚ በሆነ ትረካ ስላስደመማችሁኝ ሁሉንም በተግባራ ነዉ ያስደመጣችሁን ዋዉ ነዉ ይልመድባችሁ ።

  • @ethioemmatube

    @ethioemmatube

    3 ай бұрын

    ክብረት ይስጥልን

  • @etshuncho2673
    @etshuncho2673 Жыл бұрын

    ዘመን የማይሽረው አስገራሚ አተራረክ

  • @keludifamilyshow
    @keludifamilyshow2 жыл бұрын

    "ደራሲው የመጨረሻው ክፍል" አጃይብ ነው ጥበብን ከእፍታው እንድናጣጥመው ጠረኗንም እንድምገው የእርካታውም ተቋዳሽ እንድንሆን ምንያህል ተጠባችሁ ለፍታችሁበት እዚህ ላደረሳችሁን ሁሉ ምሳጋናዬ የትየለሌ ነው ቀላል አይደለም ከካራክተር ጥናት እስከ ድምፅ ትወና ሪከርድና ኤዲቲንግ ይህን የመሠለ ጥርት ያለ ስራ ለማቅረብ የብዙዎች ትብብርና ህብረት ይጠይቃል ይህንንም ተወጥታችሁታል።በድጋሚ ግዝፍ ያለ ምስጋናዬን አቀርባለሁ።ስቀጥል አጨራረሡ እጅግ ማራኪ ነው ተወዳጁ ጋሽስብሃት የነበረው ስብእና ገራሚ ነበር የማይቻለውን የቻለ ጀግና ፃህፍት የመልካም ልብ ባለቤት ፅጌን ከዛ ከድንጋይ የጠጠረ ውስብስብ ባህሪዋን እንዲህ በማይታመን ሁኔታ ምቹ ምድር ማድረጉ አስደምሞኛል እኔነኝያለ ቡጢ ቀምሶ የሠብለንና የባሏን ሊበጠስ የደረሠ የግንኙነት ገመድ ማጥበቁ ድንቅ ነው ጥበብ የእውነተኛ አለም ነፀብራቅ ይላሉ ይህ ነው ተናግረን የማንጨርሠው አድንቀን የማንጠግበው ነበር ።ሌላም እንጠብቃለን 💐💐👌

  • @ethioemmatube

    @ethioemmatube

    2 жыл бұрын

    አንቺም ከጅምሩ እስከፍጻሜው ዳጎስ ያለ ሀሳብ እየሰጠሽን አብረሽን ስለነበረሽ ዳጎስ ያለ ምስጋና እናቀርባለን።ሌላም እናነባለን እንተርካለን ኧረ ገና እንበዛለን

  • @ambaw1004

    @ambaw1004

    2 жыл бұрын

    " ከ ዘጠኝ ወር በጋ ከሦስት ወር ክረምት ፤ እንዴት በመሥከረም በከሉዲ ልሙት ፤ ከሉዲአችን የመጻሒፍት ፍሬ ሐሳብን ጥንቅቅ ብሎ በማድመጥ፤ እንዲሁም የሙሀባ ካብ በመደረብ ፤ የሚገርም የሞራል እገዛ ነበር ሥታደርጊ የቆየሽዉ ። አንቺን ወደዚህ በመጋበዜ ኩራት ተሰምቶኛል ፤ በሁሉም ከያኒ ስም እራትና መብራት ይስጥልን ፤ ከሉዲዬ ሥለ በዓሉ ግርማ የምለዉ ከያኒ ስጋው እንጂ በስራው በኩል ስሙ አይሞትም በአንባቢ ( በአድማጭ ) ልብ ማሳ ውስጥ ምድር ላይ ዘርቶ በሄደው የጥበብ ዘር ፤ በትውልድ ታዛ ስር ለሚጠለሉ፣ ስራው ለመንፈስ ማደሻ ይሆን ዘንድ አዝምረው በልብ ጎተራ የሚጎተር የነፍስ እህል ናቸው። ከ " ደራሲው " ከተሰኘዉ ድንቅ መጽሐፉ ብዙ ቁም ነገር ቀሥሜበታለሁ፤ የሚገርመዉ ፍጻሜው እንዲህ ያማረ ይሆናል ብዬ አልገመትኩም ነገሮች ምሥቅልቅላቸው የወጣ ይመስል ነበር፤ ብቻ ትላንት ላይ ሆኖ ዛሬን የጠነቆለ ድንቅ መጽሐፍ ፤ ድንቅ ትዝታ ፤ አቦ በዓሉ ነፍስህ ህያዉ ትሁን •••• ከሉዲዬ ደግሞ - ክብረት ይስጥልን •••••

  • @cococake6803
    @cococake68032 жыл бұрын

    Where is the next part ? Be shene tagete ende

  • @ambaw1004

    @ambaw1004

    Жыл бұрын

    This is it

  • @cococake6803

    @cococake6803

    Жыл бұрын

    @@ambaw1004 weye what a terrible ending

  • @ambaw1004

    @ambaw1004

    Жыл бұрын

    @@cococake6803 how is that terrible?

Келесі