Amharic Audiobook | በአሉ ግርማ | የፍፃሜ መጀመሪያ | መጥፋቱን (ሞቱን) የተነበየበት ሥራዉ | Bealu Girma | Milketa tv

Ойын-сауық

ሠላም ተወዳጆች፡- ተስፋሁን እባላለሁ፤ ይህ የኔ ቻናል ነዉ፤ በርካታ ጥበባዊ ሥራዎችንና ጠቃሚ ሐሳቦችን እየሠራሁበት እገኛለሁ፤ ቤተሰብ በመሆን አብረን እንድንማማርና ዘና እንድንል በኢትዮጲያዊ አክብሮት ጋበዝኳችሁ፡፡
||||
Music By:- OrangeHead - Background Music for Content Creators
"Peaceful Piano" is a calm, relaxing and smooth vibes track, this track might suit for study, inspiring or nature documentary videos background music.
► Download on my Patreon : bit.ly/3gfpR1S
||||
Music :Peaceful Piano
Music produced by OrangeHead
Watch : • [No Copyright Music] P...
Website : www.orangehead.net
/////

Пікірлер: 14

  • @desalegndawit9182
    @desalegndawit91824 ай бұрын

    መንግስቱ ሃ/ማርያም የምትባል ያገር በሽታ ነፍስህ አይማር ! የዚህን ብሩክ ሰው ቤተሰብና አድናቂዎቹን እንዳደድማህ ዘር ማንዘርህ እየደማ ይኑር !አይሳቅ ! አሜኬላ ይሁን !

  • @bornrebel7657
    @bornrebel76573 ай бұрын

    ምርጡ ደራሲ--በዓሉ ግርማ። በደደቦችና ጨካኞች የጠፋ ውዱ ደራሲ ነብስህን በገነት ያኑራት። መንግስቱ ጀግና ነው ለምትሉ ሰዎች ግን ከአውሬና ከሂትለር ደጋፊዎች ለይቼ አላያችሁም።

  • @semiraweleyewa3586
    @semiraweleyewa35863 ай бұрын

    ምርጥ ደራሲ ትልቅ አሻራ ጥሎልን አልፏል ሁሉም ገዳዮቹን ስፀየፋቸዉ እኖራለሁ እሱግን ጀግና ግሩም ደራሲ ነዉ

  • @HopeTube
    @HopeTube Жыл бұрын

    አሪፍ ድምፅ አሪፍ አቀራረብ

  • @segenetmedia
    @segenetmedia2 жыл бұрын

    ሁሌም ማጣጣም የምፈልገው ስራ ተስፍሽ ሁሌም ተናፋቂ ስራህ ዘመን ይሻገራል

  • @ambaw1004

    @ambaw1004

    2 жыл бұрын

    ተስፍሽ(ትኅሣሱ) ይህንን ሥራ ይዘህ ሥለመጣህ አንጀቴ ቅቤ ጠጣ ፤ ይህ ሥራህ እጅጉኑ በጣም አድርጌ ለምወደዉ ለደራሲ በአሉ ግርማ መታሰቢያ ቢሆን ብዬ ተመኘሁ ! እባክህ ከቻልክ "የቀይ ኮከብ ጥሪ" አልያም "ደራሲው" ከቻልክ በአንተ ትንፋሽ ብትቀድስልን እባክህ አስብበት ? በአንድ ወቅት ወዳጄ አስቻለዉ ተጁ ይህንን ጽሁፍ ልኮልኝ ነበር ፤ አንተም መጨረሻ ላይ በጭልፋ ካስቀመስከን ጋር ትንሽ የሚደግፍ ጽሁፍ መስሎ ስለታየኝ ለትዉስታ እንዲቀመጥ እንዲህ ቆርጬ *Copy paste* አድርጌዋለኹ ፤ በአሉ ግርማ(የጽሁፉ ምንጭ ያልታወቀ) የብዙዎች አንደበት በተዘጋበት ፤ ፍርሀትና ልቅሶ በሰፈነበት ዘመን ብዕሩን በማቅናት ያንን ቀውጢ ግዜ በብዕሩ የዳሰሰ ኢትዮጽያዊ ጸሀፊ ቢኖር በዓሉ ግርማ ነው። ይህ ብዕር የዶለዶመው አንደበቱም የተዘጋው ሀሙስ የካቲት 24/1976 ዓ/ም ከቀኑ 11:30 ከቤቱ ከወጣ በኋላ ተመልሶ ቤተሰቦቹን ማየት ሲሳነው ሲሆን፡ ህይወቱ እንደ ብዕሩ ዛሬም ሚስጥር ሆናለች። በጊዜው የነበረው መነግስት እጁ እንደሌለበት ለማሰተባበል የማፈላለጉ ስራ እንዲቀጠል ለይስሙላ ቢያዝም ከመንግስት የተደረገ ምንም ጥረት አልነበረም። በቤተሰቦቹ ክትትል በእለቱ ይነዳው የነበረው መኪና በደብረዘይት መንገድ ቆሞ የተገኘ ሲሆን ይህን እውቅ ፀሀፊ ምን እንድበላው ዛሬም መልስ አለተገኘም። ከመጥፋቱ ሰባት ወራት በፊት ከየመደርደርያው እየተለቀመ የተማገደው የደራሲው መጽሀፍ ፤ከማስታወቂያ ሚኒስተር ስራው ተገልሎ እቤት እንዲቆይ መደረጉ ። አበዮቱን መንጋጋ ውስጥ እኮነው የከተክተው የሚለውን ቅሬታ ከኮኔሬል መንግስቱ መስማቱ የመሰወሩን ሚስጥር ግልጽ ያደርገዋለ። በዓሉ መስከረም 10/1931 ዓ/ም በኢሊባቡር ክፈለሀገር ክህንዳዊው አባቱ ና በወቀቱ ሀበታም ከነበሩ ቤተሰቦች ከተወለዱ እናቱ ወ/ሮያደኔ ቲባ በኢሊባቡርmጠቅላይ ግዛት ሱጺ ቦሩ በምትባል አነስተኛ የገጠር መንደር የተወለደ ሶሆን አባቱ ቤተሰባቸውን ወደ አዲስ አበባ ለማዛወር ሞክረው የእናቱ ቤተሰቦች ባለመስማማታቸው ከእናቱ ጋር ኢልባቡር እንዲቀር ከአባቱም ጋር የጠበቀ ገንኙነት አንዳይኖረው ሆኗል። በኢልባቡር ከአያቱ ጋር የጠበቀ ግንኙነት እንደነበረውና በጊዜው ስለነበሩት ምምህሩ በተደጋጋሚ ከማውራት ሌላ ስለ ኢሊባቡር ህይወቱ ብዙም አያወራም ነበር። የአንደኛ ደረጃ ትምህርቱን እዚያው በትውልድ ሀገሩ ሱጺ ከአጠናቀቀ በኋላ ወደ አዲስ አበባ በመመጣት በልዕለት ዘነበወርቅ ትምህርትቤት ትምህርቱን መከታተል ጀመረ በጊዜው በሚሰጠው ፈተና ክፍተኛ ውጤት በማግኘቱ በ1943 ዓ/ም ጀነራል ዊንጌት ትምህርትቤት የመግባት ዕድል ለማግኘት ችሏል። በጀነራል ዊንጌት በጎበዝ ተማሪነቱ ፤ ተማሪዎችን ለአመጽ በማነሰሳት ችሎታው ሲታወቅ ስነጽሁፍን የሀይወት መርህ ለማድረግ የመጀመሪያውን ጥሪ የተቀበለበት ግዜ እንደሆነ ይነገራል። በእዲስ አበባ በነበረበት ግዜ አንደወላጅ የተንከባከቡትን የቅርብ ቤተሰብ ስም በመውስድ በዓሉ ግርማ በሚለው መጠሪያ ይጠራ የጀመረው የኮሌጅ ተማሪ ሆኖ ነበር። በዓሉ ግርማ በ1954 ዓ/ም ከአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ በፖለቲካ ሳይንስና በጆርናሊዝም የመጀመርያ ድግሪውን ሲያገኝ በትምህርት ላይ እያለ ለኢትዮጺያ ሄራለድ ጋዜጣ በሪፖርተርነት እንዲሁም በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ በጊዜው ይታተም ለነበረው NEWS and VIEWS ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ሆኖ ሲያገለግል የንጉሱን ሥርዓት የሚነቅፉ ጽሁፎችን በማቅረቡ ከመንግስት የተሰወረባቸው ግዚያት ነበሩ። ትምህርቱን እንደጨረሰ የስኮላርሽብ እድል በማግኘቱ በፖለቲካ ሳይንስ ና ጆርናሊዝም የማስተርስ ዲግሪውን East Lansing Michigan ከሚገኘው በርክሊ ዩንቨርስቲ አግኝታል። በስራ ዓለም በ1955 የዛሬይቱ ኢትዮጺያ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ በ1957 የመነነና የአዲስ ሪፖርት ምፅሄቶች ዋና አዘጋጅ በ1960 የኢትዮጺያን ሄራለድ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ከ1962 - 1966 በጋዜጣው ህይወት ታሪክ ለመጀመርያና ለመጨረሻ ግዜ ታማኝነት ባገኘው የአዲስ ዘመን ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ በ1969 የማስታወቂያ ሚኒስተር ቋሚ ተጠሪ ሆኖ ሲያገለገል በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ተጋባዝ መምህር በመሆን በ creative writing ሙያ በርከት ያሉ ባለሙያዎችን ለማፍራት ችሏል። በስራ ዓለም ተግባቢ ና ሰርቶ ማሰራት የሚችል ፤ በሙያው የተመሰገነ እንደነበረ አብረውት የሰሩት ይናገራሉ። ጋዜጦች ላይ በሚያቀርቡ ጸሁፎች የተናሳ የደሞዝ መቆረጥ ና ከስራ መባርር የመሰሉ ችግሮችም ደርሰውበታል።

  • @ambaw1004

    @ambaw1004

    2 жыл бұрын

    ደራሲው የደራሲያንና የተደራሲያንን ሙግት በሰፊው የሚታይበት ሲሆን ደራሲው እውነተኛ ደራሲ ለመሆን ያለውን ጥብቅ ፍላጎት“ ከምፈጥረው ገፀ ባህርያት አጥብቄ የምጠብቀው ማህበራዊ ድፍረት፤ ትህትና ፤ ፍቅር ፤ ሀቀኝነት፤ ቀጥተኛ መሰዋትነት በእኔ ባህሬ ውስጥ የት አለ ?’’ “ መጻፍ አልቻልኩም ሀቁ ይህ አይደለም ሀቁን ክእራሴ እደብቀዋለው ፤ መጻፍ አልቻልኩም ጊዜዬን በከንቱ ነው የማጠፈው የምለው ነገር የለኝም ቢናረኝም ምን እንደሆነ አላውቅም ባውቅም በቃላት ልገልጸው አልቻልኩም ቃላት መግለፅ ያለባቸውን አይገልፁም ያሾፋሉ። ” እያለ ከእራሱ ጋር የከፈተው ጦርነት ዘመኑ ምን ያህል የፍርሀት ዘመን እንደነበር የሚያሳይ ሲሆን በወቅቱ በሀገሪቱ ወስጥ የነበረውን ፖለቲካዊ ቅራኔ “ ሱሪ ባንገት አውልቅ ምርት! ምርት! አረነጓዴ ዘመቻ ውይይት ክብብ፤ ውግዘት ፤እርግማን፤ መኮነን፤መጠቆም ፤ ማጋለጥ ፤ መዋጮ ለእናት ሀገር ጥሪ ፤ ለመልሶ ማቋቋም ” በሚመስል አገላለጽ የገለጸው ሲሆን የተረት ስፈርን ነዋሪዎች የዕለት ተዕለት ኑሮ በከተማ ቤት አዋጅ ምክንያት የተፈጠረውን ችግር በመዘርዘር በሀገሪቱ የሰፈነውን ማህበራዊ ውድቀት ያወጋበት መፅሀፍ ነው። ደራሲው 1 -በጋሀዱ ዓለመና በተስፋ ዓለም መካከል ያለውን ልዩነት አጉልቶ የሚያሳይ 2-ሰፊ ያስተሳሰብ ለዩነት በማህበረሰቡ ውስጥ እንዳለና መንኛውም ለውጥ ከዚህ አስታሳሰብ መመንጨት እንዳለበት የሚጠቁም 3-የሀገሪቱን የኑሮንና የኢኮኖሚ ውድቀት የማህበረሰቡን የዕለት ተዕለት ህይወት በመኖር እንድናየው ያደረገበት 4-በሀገሪቱ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚ አቅጣጫ ላይ የማረምና የማስተማር አቀራረብ የሚታይበት 5-በጊዜው የነበረው ስርዕት ከእራሱ አስተሳሰብ ጋር እንደሚጋጭ ያጋለጠበት 7 የመናገር ፤ የመጻፍ ፤ የማንበብ ነዓነት ከግል ነፃነት እንዴት እንደሚነፃፀር ያስተማረበትና በወቅቱ ጸሀፊያን ያለባቸውን ችግሮች በሰፊው የሚያትትበት ነው። ኦሮማይ ንግግር ፤ ንግግር ብዙ ንግገር ትንሽ ስራ ግምገማ ፤ ግምገማ ብዙ ግምገማ ትንሽ ውጤት ፤ መፈክር ፤መፈክር ነጋ ጠባ ዘመቻ እድገት በህብረት ብሎ ዘመቻ ፤ ለጦርነት ዘመቻ ፤ የኢኮኖሚ ግንባታ ዘመቻ ፤ ማሀይምነት ለማጥፋት ዘመቻ ፤ የቁጥጥር ዘመቻ ፤ አሁን ደግሞ የኤርትራን ችግር ለመፍታት ዘመቻ ነጋ ጠባ ስብሰባ ፤ ጠዋት ስብሰባ ፤ ማታ ስብሰባ ፤ የማያቋርጥ የስብሰባ ህይወት የኢትዮጺያ ችግር ሁሉ ባአዋጅና በዘመቻ እንደ በጋ ጉም በኖ የሚጠፋ ይምስላቸዋል መሰረታዊ ችግራችን የአይምሮ ድህነት መሆኑን ያዋጅ ፤ የማጠናቀሪያ አዋጅ ጋጋታ ፤ ዘመቻ ብሎ ጭጭታ ትርምስ መተራመስ ተተራመሶ መሞት በማለት በጊዜው በጥናትና በዝግጅት ላይ ያልተመሰረተው የሀገሪቱ ሀብት በተገበረበት በቀይ ኮከብ ዘመቻ የማስታወቂያ ሚኒስትሩ ተወካይ ፀጋዬ ሀይለማሪያም ታሪክ ላይ ያነጣጠረውና የታሪኩ ተራኪ እራሱ ደራሲው መሆኑን በየምዕራፉ እያስተዋወቀ በደራሲው በእውን የታየው ፤ የተደረሰውና የተተረከው ኦሮማይ በኢትዮጺያ ታሪክ ታሪካዊና ህይወትን መሳይ ድንቅ ነገር የተሰዋበት ድንቅ መዕሀፍ ነው። በዚህ መፅሀፍ በጊዜው የነበረውን የኤርትራን ችግር ፤ሴቶችን በመድፈር፤ ካለመንም ፍርድ የሞት ቅጣት በመፈፀም ፤ ወጣቱን በማስበርገግ የብህራዊ ጦር ፤ የ15ኛ ብርጌድ ፤ ህብረት ዕዝ ፤ ከደርግ ምርመራ አፋኝ ጓድ ፤ የህዝብ ድርጅት ጊዚያዊ ጽህፈት ቤት የመሳሰሉ ቡድኖች ለችግሩ መባባስ ምክንያት እንደሆኑ በግልፅ ያስቀመጠ ሲሆን ውታደሩ ከአመራሩ በተለየ መልኩ ሀገሩን የሚወድ ለሀገሩም የተሰዋ ቢሆንም ጦርነቱ ፖለቲካዊ መፍትሄ ያልተፈለገበትና አዝማቾቹም ከሀገራቸው ይልቅ እራሳቸውን የሚወዱ ችሎታውና ብቃት የሌላቸው ለጦርነቱም የነበራቸው አመለካከት በጣም የቀለለ የኤርትራም ህዝብ በባለስልጣኖች በደረሰበት ስቃይ ከሻቢያ ጋር ለማበር መገደዱን ሀገሪቱም የማትችለው ጦርነት ላይ መዘፈቋንአስቀምጧል። የወቅቱን ባለስልጣኖች በገፀባህሬ መልክ በመሳል እውነተኛ ማንነታቸውን ፤ ልግል ጥቀማቸው የሚያደርጉትን መሯሯጥ ፤ ለስልጣን ያላቸውን ጥም ለጦርነት ሳይሆን ባአስመራ ሴቶች ላይ ለመዝመት የመጡ ዝሙተኞች እንደነበሩ በድፍረት ፅፎታል። የፍጻሜ መጅምሪያ በበዓሉ ግርማ በግዜው በማስታወቂያ ሚንስተር ይታተም በነበርው የካቲት ምዕሄት ላይ ብቸኛ የታተም አንስተኛ መጻጻፍ ሲሆን የታሪኩ ገፀባህሬ ህሊና የሚባል ሰው ሲሆን ህሊና ጠጪና ስለ ዕውነት ና ሀቀ ኝነት ለመጸፍ ከእራሱ ጋር በሚያደርገው ትግል ስለነበረው ተስፋና ሰስለነበረበት ፍርሀትነና በጊዜው ሰለ መሰወሩ በኋላም ተመልሰው የሚያደርጉትን ጭውወት የሚተርክ ሲሆን መዕሀፉ በዓሉ ግርማ ክህሊናው ጋር ተመልሶ እንደተገናኘና ከህሊናው ጋር በመታረቁ መሰወሩንና የሚደርስበትን ለመቀበል መዘጋጀቱን የነገረን ዘዴ ሊሆን እንደሚችል ጽሁፉን ያነበቡ ሁሉ ይገምታሉ። በአድማስ ባሻገር ጊዜው አላለፈም ይህይወትን ጥሪን ካወቅ ዘንድ ላአንድ ቀን እንኳን እራስህን ግልጽ በህልና ደውል ስለችግርና ስለ ብቸኝነት ለመዝፍን ፍላጎት የለኝም መጻፍ የምፈልገው ስለ ዓለም ውበትና ስለሰው ተፈጥሮ መሰረታዊ ጥሩነት እንዲሁም ሰው በራሱ የራሱን ደህንነት እንዳያገኝ ስለሚያደናቅፉት አካባቢዎች ነው። በቀይ ኮከብ ጥሪ ያለ ድርስት ሌላ ህይወት የለኝም ምኞቴ በድርሰት ለሰው ልጅ ደስታን ለማስገኝት ነበር ግን ለሰው ልጅ ደስታን ለመስጠት አልቻልኩም ለራሴም ደስታ አላገኘሁም ስለዚህ የመኖር ትርጉሙ አልታየኝም ባዶነት ይሰማኛል ባዶነትን ፍጹም የሚያደርገው ደግሞ ሞት ነው ፍጹም መሆን አለበኝ በሀዲስ እኔ የምወደው በሰው ልብ ተሰፋ ፍቅርና ቆራጥነት የሚያጠናቅር ውበት ያለው ቅኔ ነው። በደራሲው እኔ የምጽፈው ስለ ልበ ሙሉነት ስለ ድፍረት ነው ድፍረት ለሌለው ብዕር ወረቀት ባታበላሹ ይሻላል የሰው አካለና ነፈስ አንደ ስለሆነ የሚጸድቀውም የሚኮነነውም በራሱ ልብ ውስጥ ነው። በኦሮማይ የሚሞትበትን የሚያውቅ ማን አለ? በነፃነት ኖሮ በነፃነት ሞሞት የሻላል። ብዕሩ ዕውነትን ለመግለፅ በትግል ላይ እንደነበረች ፤ ስሜቱ ሰው ከማንም በላይ ክቡር መሆኑን እንደገለጸች ፤ ምኞቱ በብዕሩ ለወገኖቹ ደስታን መቸር መሆኑን ፤የድርሰት ፍቅሩ የልክፍት ያህል ከድርስት እንደተቃራኘ መኖሩን ደፋርና አዋቂ ታላቅ የስንዕሁፍ ሰው እንደነበረ በፁሁፎቹ ከእውነትና ክድርሰት ሊለየው የሚችል ሞት ብቻ እንደነበር ይህንንም ለመቀበል ዝግጁ መሆኑን ብብዕር ውጤቶቹ ቁልጭ አድርጎ ያሳየን ታዋቂው ደራሲ ዛሬ በህይወት ቢኖር ብዙ ስራዎችን ሊያካፍለን ይችል የነበረ ሲሆን የበርካታ ሰማዕታት አሟሟት ሚስጥር ሲገለጽየንጉሱ አዕም ከኮ/መንግስቱ ሐ/ማርያም ቢሮ ስር ተቆፍሮ ሲወጣ የ60ዋቹ የንጉሱ ባለስልጣኖች አፅም ከአዲሰ አበባ ከርቸሌ በፍለጋ ሲለቀም የእነ አቡነ ቴዎፋለዎስ አፅም ክልዑል አስራተ ካሳ መኖሪያ ግቢ ውስጥ በቁፋሮ ሲገኝ በዓሉ ግርማ የት ገባ? በመጭረሻ ለበርካታ ደራሲ በዓሉ ግርማን ለበርካታ ዓመታት መለስ ያላገኙትን ቤተሰቦቹን በተለይም ባሌቤቱንና ልጆቹን ለአንድ ደቂቃ በህሊና ጸሎት እንድናስባቸው እንጠይቃለን!

  • @ambaw1004

    @ambaw1004

    2 жыл бұрын

    @@milketatv ምንም ችግር የለዉም ጓድ ተስፍሽ ያዉ ከላይ እንዳልኩ ይህ ኹላ መረጃ በአንድ ወቅት አስቻለው ተጁ (ፓጂ) ነበር ያጋራኝ ፤ ደራሲዉን እጅግ አብዝቼ ስለምወደዉ ማስታወሻ ኖት ላይ ይዤው ነበር ! እኔ ምልህ የጋሽ ስብኃት ገ/እግዝአብሔር ስራ ላይ ሐሣቤን ከትቤ አልፖስት አለኝ

  • @user-lz4oo6or5h
    @user-lz4oo6or5h2 жыл бұрын

    በርታ ተስፍሽ😘😘

  • @lemlemg542
    @lemlemg5422 жыл бұрын

    እናመሰግናለን ተስፍሽ

  • @aliyamohammedebirahim3031
    @aliyamohammedebirahim303111 ай бұрын

    ምርጥ አቀራረብ በምርጥ ድምጽ በምርጥ አተራረክ! መጽሀፍንማ አንተ ተርክ ተሰፍሽ 👌👍

  • @bekelegessesse2601
    @bekelegessesse26012 ай бұрын

    በተለይ ግን ደራሲው በሚለው መጽሐፉ ላይ የሚደርስበትን ጉዳት ትንቢት በደንብ አስቀምጧል።

  • @KukuBubu20
    @KukuBubu20 Жыл бұрын

    Because of that stupid leader we lost the best writer we miss u

  • @desalegndawit9182

    @desalegndawit9182

    4 ай бұрын

    May God pay him the tribute

Келесі