ከጋዜጠኛና ደራሲ በዓሉ ግርማ ጋር ከረጅም ዘመን በፊት ከአድማስ ባሻገርን ከጻፈ በኋላ የተደረገ ቃለ ምልልስ ( ክፍል 1)

ለምንድን ነዉ የምንኖረው? የህይወት ትርጉሙ ምንድን ነዉ?
እንወለዳለን፥ እድለኛ ከሆንን እናድጋለን፥ እናረጃለን፥ እንሞታለን። ከእንስሳ የተለዬ ህይወት አይደለም። ልዩነት ቢኖር የሰዉ ልጅ ስለ መኖር ያለዉ የማሰብ ችሎታ ብቻ ነዉ። ማሰብ ባይኖር ኖር ክፋን ለበጎ ለይቶ ለማወቅ ህሊናችን አይጨነቅም ነበር። ህይወት አጭርና ጅል ነገር ናት!
ግን ታስጨንቀናለች። የጭንቀቱ መሰረት የማሰብ ችሎታችን ነዉ። ሌላ አይደለም። የማሰብ ችሎታችን እፎይታ፥ ሰላም፥ ዘላለማዊ ፀጥታ! የሰዉ ዘር ሞኝ ነዉ። ጅል ነዉ። ለሚኖረዉ አጭርና ጅል ህይወት፥ ገና ለገና የማሰብ ችሎታ አለኝ ብሎ፥ ለእንስሳ ባህሪይዉ የረቀቀና የላቀ ትርጉም ሊሰጠዉ ይሞክራል።
መኖር ስቃይ ነዉ። ለማትረባ አጭር ህይወት ብዙ ስቃይ፥ መዋተት፥ መጨነቅ፥ መቃተት፥ መቡዋጠጥ፥ መንጠራራት፥ ትርጉሙ ምንድን ነዉ? ዞሮ ዞሮ ጥሪኝ መቃብር። ሞት ነዉ ዘላለማዊ ነገር። ሞት ዉበት ነዉ። የሰዉ ልጅ ግብ ነዉ። ግን እንፈራዋለን። ተወልዶ፥ አድጎ፥ አርጅቶ፥ መሞት መኖሩን እያወቅን ሞትን ልናመልጠዉ እንሞክራለን።
እና የሰዉ ልጅ የወል እብደት ምንጩ ይኸዉ ነዉ። በፍርሃት ጥላ ስር የሚኖር ሁሉ በዚህም ሆነ በዚያ እብድ ነዉ። የእያንዳንዱ ሰዉ የእብደት መጠን ወይም ደረጃ ጠባይ፣ ባሕርይ እንለዋለን....'' (በዓሉ ግርማ ) የቀይ ኮኮብ ጥሪ
ከጋዜጠኛና ደራሲ በዓሉ ግርማ ጋር ከረጅም ዘመን በፊት ከአድማስ ባሻገርን ከጻፈ በኋላ የተደረገ ቃለ ምልልስ እንድታዳምጡ እንጋብዛለን።
t.me/felegethiopia
blue.et/Felegethiopia
/ @felegethiopia
#ethiopian #author #bealugirma #admasradio ‪@mikejoys‬

Пікірлер

    Келесі