//የቤተሰብ መገናኘት//"የተለያየንበት ቦታ እየሄድኩ ለዘመናት አለቅስ ነበር እህቴ..." ከ53 ዓመት በኋላ የተገናኝው ቤተሰብ ድንቅ ታሪክ /በቅዳሜን ከሰአት

Ойын-сауық

ወ/ሮ ታየችወርቅ አጎናፍር ከዚህ ቀደም በስቱዲዮ ተገኝተው እህትና ወንድሞቿን ፈልገው የነበረ ሲሆን ዛሬም ከስቱዲዮ ውጪ አቅራዎቹ በሀና ፉሪ አካባቢ በመገኘት ከእህትና ወንድም ጋር እንዲሁም ከሌሎች ቤተሰቦቿ ጋር ተኛኝተዋል
In today's family reunion segment, Tayech Werke Agonafere comes to the studio searching for her long-lost sister and brothers. Today, she reunites with them and other family members in the beautiful Hana Furi area outside the studio.
አፋላጊ ላይ ቀርበው ቤተሰባቸውን ከፈለጉ ሰዎች መካከል ተፈላጊው ሲገኝ የምናገናኝበት ፕሮግራም ነዉ ።
"We facilitate connections for individuals seeking their families through Afalagi. Join us for this program dedicated to reuniting loved ones."
Saturday afternoon infotainment show with magazine format; lifestyle, tea time guests, book review, music, cooking segment, and many more…, every Saturday at @2:00 PM only on EBS TV. #SaturdayAfternoonShow_EBSTV Subscribe to EBS worldwide: linktr.ee/ebstelevision EBS TV - Established in 2008 in Silver Spring, MD, USA, EBS TV is the first privately owned Ethiopian TV to provide a niche transmission programming that targets the booming Ethiopian market globally. #Ethiopia #EthiopianTvShow #EBSTV #EBSTVWorldwide #EthiopianBroadcastingService # You're#1choice
Follow us on:
tiktok www.tiktok.com/@ebstv.tv?_t=8...
Facebook: bit.ly/2s439TS
Telegram: t.me/ebstvworldwide
Website: ebstv.tv

Пікірлер: 647

  • @user-pb5tq6ow1z
    @user-pb5tq6ow1z5 күн бұрын

    የጎንደሬው ልጅ ደግሞ ይቅረብ የምትሉ በላይክ አሳዩኝ በጣም የሚያሳዝን ልጅ ነበር ከምንስ ደርሱ ይሆን

  • @user-zd1rk7xt3t

    @user-zd1rk7xt3t

    5 күн бұрын

    Awe Yemir Efuuu Ene Yimetalu Bemalet Begugut Neber Mitebikew😢😢😢

  • @ancanv1578

    @ancanv1578

    5 күн бұрын

    ተውየዛንልጅእባ።እንበሥለት።የኔሆደባሻ

  • @semiraadem2865

    @semiraadem2865

    5 күн бұрын

    ብዙ ጊዜ የዚህ የጎንደሬው ልጅ ይቅረብልን ስትሉ አያለሁ ምኑ ጠፍቶበት መጥቶ ነው እኔ ልጁን አላየሁትም ብዙ ጊዜ ሲኮመት ግን አያለሁኝ አላህ ያገናኘው

  • @user-zd1rk7xt3t

    @user-zd1rk7xt3t

    5 күн бұрын

    @@semiraadem2865 እናቱ ውደ😥😥😥

  • @taybat536

    @taybat536

    5 күн бұрын

    እናቱ ናት ሲያሳዝን ስሙ ደግሞ ዘር ፈልግ​@@semiraadem2865

  • @Ruqeyyaabintmuslim152
    @Ruqeyyaabintmuslim1525 күн бұрын

    ዛሬ የመጀመራ ነኝ ላይክ አርጉኝ

  • @tigistteketel3363

    @tigistteketel3363

    5 күн бұрын

    Demrige

  • @Maziyteka

    @Maziyteka

    5 күн бұрын

    ደምሪኝ

  • @tigistteketel3363

    @tigistteketel3363

    5 күн бұрын

    Demraschlhu demririge

  • @almedenderkiyab9126

    @almedenderkiyab9126

    5 күн бұрын

    konjo subscribe adergen sewedshe

  • @ufgryfhrfhxvxhdfir7321

    @ufgryfhrfhxvxhdfir7321

    5 күн бұрын

    ❤❤❤❤❤❤❤🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉

  • @wendubuna9885
    @wendubuna98855 күн бұрын

    ebs በጣም እያናደደኝ አሁን ለሁለተኛ ጊዜ ነው የDNA ውጤት ስታስቀሩ የመጀመሬያዋ ያቼ ከፈረንሳይ የመጣችው ዛሬ ደግሞ ከሆላንድ የመጣው ልጅ እኛ እየጠበቅ ነው

  • @YoditEMBAYE-xk1gq

    @YoditEMBAYE-xk1gq

    5 күн бұрын

    Me also

  • @natanemu9304

    @natanemu9304

    5 күн бұрын

    ትክክክክክክክል

  • @alemkebede5848

    @alemkebede5848

    5 күн бұрын

    አረ አትናደዱ ጊዜ ለኩሉ።

  • @tigistmisganaw1532

    @tigistmisganaw1532

    5 күн бұрын

    Betam ewnet temelkachn alemakber new

  • @gravitymobile7558

    @gravitymobile7558

    5 күн бұрын

    አንቺ /አንተ እናንተ እንዳሰባችሁት መሆን አለበት ብላችሁ አታስቡ በጣም ሥራ ይበዛባቸዋል ፡፡

  • @user-xf7is5yp5m
    @user-xf7is5yp5m5 күн бұрын

    የጎንደሩን ልጅ አቅርቡትና ይረዳ ቢያንስ ቢያንስ ትምህርቱን ይማር ።

  • @kinfeayele-sp3mc
    @kinfeayele-sp3mc5 күн бұрын

    ጥላሁን ከሆላንድ የመጣው DNA ከተሰጠ ወር አለፈው ከምን ደረሱ ሌላ ደሞ ዘር ጠይቅን ድጋሚ ቢቀርብ ምን አልባት የሱን ፕሮግራም እናቱ የምታይበት አጋጣሚ አላገኘችም ይሆናል

  • @Zizuyosan

    @Zizuyosan

    2 күн бұрын

    እሱን ላይ እኮ ነወ። ግን የት ደረሱ

  • @queenzuzu710

    @queenzuzu710

    Күн бұрын

    Yes👏

  • @Abi-kc6kk
    @Abi-kc6kk5 күн бұрын

    የዛሬው ይለያል 😢😢😢😢😢😢 የፈጣሪ ፈቃድ ተመስገን የኔ ጌታ ደስ ሲሉ ❤❤❤❤❤❤ የደጉ ዘመን ፍጥረት ምንም ሳይሆኑ ተገናኙ ቅን የዋህ ስለሆኑ ፈጣሪ እድሜ ጨምሮ አገናኛቸው ተመስገን የኔ ጌታ

  • @TigistMamo-or1pu
    @TigistMamo-or1pu5 күн бұрын

    አየለች አዳቺ አይነት ደጋግ የባል ዘመድ ያብዛልን

  • @sn-jn3eg

    @sn-jn3eg

    5 күн бұрын

    ከሚን ወላሒ በተለይ በዚህ ዘመን😢😢😢

  • @Damenu-mx1ch

    @Damenu-mx1ch

    4 күн бұрын

    አሜን እውነትነው

  • @tigstetekle768
    @tigstetekle7685 күн бұрын

    አምላኬ ሆይ እባክህ ለዚህ ደግ ህዝብ ስትል ሰላሙን መልስ ሰዉ ሰርቶ ሚበላበት ልጁን ሚያሳድግበት ይሁንልን

  • @EyzakAbrham-vb7hh

    @EyzakAbrham-vb7hh

    5 күн бұрын

    Amen 🙏

  • @sarasaragetachwe9732

    @sarasaragetachwe9732

    5 күн бұрын

    አሜን ፫

  • @hiruth9501

    @hiruth9501

    5 күн бұрын

    Amen❤

  • @yenenhemisganaw863

    @yenenhemisganaw863

    3 күн бұрын

    አሜን

  • @SamriKebede

    @SamriKebede

    2 күн бұрын

    አሜን

  • @sameraheb4449
    @sameraheb44495 күн бұрын

    የጎንደር ልጂ ድጋሜ ይቅረብ. አባካችሁ🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉

  • @gravitymobile7558

    @gravitymobile7558

    5 күн бұрын

    ምንድነው የጎንደሩ ልጅ የምትሉት አካባቢው ጦርነት አይደል እንዴት ነው ፕሮግራሙን የሚሰሩት ትንሽ አታስቡም

  • @Djdffs

    @Djdffs

    5 күн бұрын

    ምን ችግር አለው አወ ያቅርቡልን ስለነሱ አንች ምን አደከመሸ​@@gravitymobile7558

  • @naimadeneke

    @naimadeneke

    4 күн бұрын

    እኔም ከአይምሮሄ አልጠፋም 😢 ልጄን ነው ሚመሰለኝ እግዚአብሔር ይርዳው

  • @amma4705

    @amma4705

    4 күн бұрын

    አወ መቅረብ አለበት ተረሣእኮ

  • @sameraheb4449

    @sameraheb4449

    4 күн бұрын

    @@gravitymobile7558 እና አያሳዝንም እኔ መቼም ቅዳሜ ሲደርስ አሁን ተገኜች እያልኩ ነበር ግን እግዚአብሔር ሲፈቅድ ነው ሁሉም ነገር በእውነት የዛ ልጂ ነገር ሆዴን ነው ያላወሰው እስኪ አስቡ ከስሙ ይጀምራል እኮ. ዘር ጠይቅ የፈጠረው አምላክ ከእናቱ ጋ. ያገናኜው

  • @taybat536
    @taybat5365 күн бұрын

    አልሀምዱሊላህ ምስጋና ይገባዉ ለአለማቱጌታ እንኳን ደስ አላችሁ

  • @HelenD545
    @HelenD5455 күн бұрын

    እንኳን ደሕና መጣችሑ እኔስ ቅዳሜ በደረሠ ቁጥር እንባዬ የሚቀድመኝ የዘርጠይቅ ጉዳይ ነው የጎንደሩ ልጅ 😥እምን ደርሦ ይሖን

  • @zindzind3952

    @zindzind3952

    5 күн бұрын

    ወላሂእኔም

  • @negamekonnen8056
    @negamekonnen80565 күн бұрын

    ከሁሉ በፊት እናቶቻችንን የረዳ ደስታቸውንም ላሳየን ህያው እግዚአብሔር ክብር ምስጋና ይሁንለት። ኢ ቢ ኤሶችንም እግዚአብሔር ይባርካችሁ በርቱ

  • @EyzakAbrham-vb7hh

    @EyzakAbrham-vb7hh

    5 күн бұрын

    Amen Egziabhare yemsegen ❤❤❤

  • @ZeenahZeenah-zv8uq
    @ZeenahZeenah-zv8uq5 күн бұрын

    እኛ እንደሆነ ሲየላቅሱ ከነሱበላይ መልቀስ በያ ሰምንቱ ያአላህ ሁሉም ነገር እሱ በፈቀደዉ ግዜ እንጂ አይሆን ሱብሃን አላህ በስትርጅነ ሰበሰበቹ ማሸአላህ በጣም ደስ ብሎነል

  • @user-ny9fw9re3k
    @user-ny9fw9re3k5 күн бұрын

    ሰለ ውነት ለዚህ ፕሮግራም ቃል ያጥረኛል የበለጠ ደግሞ የወንድሜን ልጅ ብታገናኙኝ በጣም ደሰ ይለኛል እንሻላህ አገር ሰገባ እንሸ አላህ

  • @arbsieyasin4127
    @arbsieyasin41274 күн бұрын

    ይሄን የቤተሰቦች የማገናኘት idea የፈጠረው ሰው ግን ይባረክ!!!

  • @Firstmove01
    @Firstmove015 күн бұрын

    እውነት ለመናገር አንድ የምወደው ፕሮግራም ይሄ ብቻ ነው ግን ሰው በጉጉት የሚጠብቃቸውን ታሪኮች ወይ የዘገዩበትን ምክንያት አለዛም ከቀረም ስርዓት ባለው መልኩ ማሳወቅ ሲገባችሁ ለእናንተ ፕሮግራም ፍጆታ ብቻ አውላችሁ ፀጥ እባካችሁ ለተመልካች ክብር ይኑራችሁ

  • @nigusadis7992

    @nigusadis7992

    5 күн бұрын

    ሰውንቀዋል. በጣምብዙግዜተጠይቀዋል. መልስየለም

  • @samimmsamimm7281

    @samimmsamimm7281

    5 күн бұрын

    ትክክል😢😢

  • @meronbesha9903

    @meronbesha9903

    5 күн бұрын

    ትክክል

  • @HsksnsHaovs

    @HsksnsHaovs

    5 күн бұрын

    እና ምንም አዲስ ነገር ሳይኖር ምላሽ ይስጡ ነዉ ምትሉት.....እነሱ የድርሻቸዉን እየተወጡ ነዉ የኛ ሰዉ እንደሆነ ሚስጋና ቢስ ነዉ😢

  • @user-rt7ns2rn6s

    @user-rt7ns2rn6s

    5 күн бұрын

    አረ ምስጋና ቢስ አንሁን ጉድ እኮ ነው እነሱ አዲስ ካለ እስሰመጨረሻ ይጓዛሉ

  • @gionabayethiopia7325
    @gionabayethiopia73255 күн бұрын

    በወለጋ እና በኦሮሞ ክልል ውስጥ የተገደሉትእና ነዋሪ እንዳይሆኑ እና የመኖሪያ ቦታ የተነፈጉ ሰዎች ልክ እንደዚህ በአንድም በሌላም መንገድ ወደዚያ የተጓዙ ሰዎች ናቸው። እግዚአብሔር መልካም ማድረግ የሚፈልግ ልቦና እና እርስ በርሳችንም ፍቅርን ይስጠን🙏🙏🙏

  • @genetonelove518

    @genetonelove518

    2 күн бұрын

    Ye Oromia tos wuch donkoro

  • @SemiraGetahun

    @SemiraGetahun

    2 күн бұрын

    ​@@genetonelove518ክፍታችሁ ሞልቶ ፈሰሰ አላህ ያጥፍችሁ😢

  • @TsehayLemma-lp7mm
    @TsehayLemma-lp7mm5 күн бұрын

    ኢቢኤሶች ምንም የሚባል ነገር የለም ቃላት ያጥራል የዚህ ሁሉ እናቶች አባቶች አምላክ ፀጋ በረከቱን ያብዛላችሁ እድሜ ከጤና ይስጣችሁ ምርቃታቸው ይጠብቃችሁ

  • @FevenDesta-vw7fv

    @FevenDesta-vw7fv

    Күн бұрын

    0:54 Uuuuuii😅

  • @tagewdasolomon555
    @tagewdasolomon5555 күн бұрын

    በስላሴ ስም ሰው በገዛ ሀገሩ ስደተኛ ይሆናል እንዴ በጣም አሳዘኑኝ እናቴ እስከዛሬ ብቻቼውን ያሳለፋት እህት ወንድም እያላቼው በናፉቆት ተሰቃይተው የእናት እንጉርጉሯቼው ደሞ ልክ እንደ እናቴ ያንጎራጉራሉ እንኳን ደስ አልዎት

  • @aminaahmed-zz9dj
    @aminaahmed-zz9dj5 күн бұрын

    ወሏሂ በጣም ውስጥ የሚነካ ፕሮግራም ነው ማሻ አሏህ እንኩዋን ደስ አሏችሁ ለመላ ቤተደቦቻችሁ አልሀምዱሊሏህ በጣም ደስ ብሎኛል

  • @user-lx4bk8ot9m
    @user-lx4bk8ot9m5 күн бұрын

    ያረቢ የኔሥ አጎት መቼ ይሁን የማገኘዉ መች ይሁን የኛም ይህን አይት ማእረግ የሚደርሠን ያረብ

  • @user-gp5wv2hw8x
    @user-gp5wv2hw8x5 күн бұрын

    ወይኔ ዮንዬ የቤቱ ድምቀት ስወድህ 🥰🥰🥰🥰🥰እረጅም እድሜ ከጤና ጋር አብዝቶ ይስጥህ 🥰🥰🥰

  • @beletetigist9830
    @beletetigist98305 күн бұрын

    አርጅተው እንኳን ቁንጅናቸው ያስታውቃል እንኳን ደስ አላችሁ ❤ ያመጣሻቸው አህት ተባረኪ በብዙ🙏

  • @OmAnwar-dd9kx
    @OmAnwar-dd9kx5 күн бұрын

    ምንም የማይሰለች ፕሮግራም በጣም ተወዳጅ ነው የኢቢኤስ አዘጋጆች ፈጣሪ ረጅም እድሜ ከጤና ጋር ይስጣችሁ ሁሉም እየመረቃችሁ ነው ማንም የሚወዳደራችሁ የለም በጣም አመሰግናችህዋለሁ በጣም ይገርማል በጣም ከብዙ ዓመት በህዋላ በህይወት መገናኘት ትልቅ ደስታ እንክዋን ደስ አላቸው እናንተንም እንክዋን ደስ አላችሁ ።

  • @gigitubeweloo
    @gigitubeweloo5 күн бұрын

    😢ይገርማል😢የጎንደሩን ልጅ ሁሌም አስበዋለሁ😢😢😢😢

  • @Elham-gw7gm

    @Elham-gw7gm

    4 күн бұрын

    ወላሂ እኔም 😢😢😢

  • @user-zv4hn6hb1e
    @user-zv4hn6hb1e5 күн бұрын

    ያረቢ እናቴ ታላቅ ወንድሟ ከጠፋባት ከ 35 አመት በላይ ሆነዉ ካሳዉ አሊ የባላል ቅርርቶና ዋሽንት ይወድ ነበረ ትላለች ሁሌ ዋሽንት ስትሰማ ታለቅሳለች ሲከፋት እያንጎራጎረች የወንድሟን ስም እየጠራች ታለቅሳለች እናቴ ብትቀርብና ወንድሟን ልጆቹን ብታገኝ ደስ ይለኝ ነበረ ግን ማን ወደከተማ ያመጣልኛል እኔም ስደት ሆንኩኝ ብቻ ኢንሻአላህ ስመለስ

  • @user-rt7ns2rn6s

    @user-rt7ns2rn6s

    5 күн бұрын

    ማቅረብ ትችያለሽ በዘመድ እዲመጡ አድርጊ

  • @dsfd8981

    @dsfd8981

    4 күн бұрын

    የኔም እናት ታላቅ ወንድሟ ከጠፋ ቆየ እሷም እንደዛ 😢😢😢

  • @HayaaaHayaa33

    @HayaaaHayaa33

    4 күн бұрын

    ነይውሰጥ

  • @HayaaaHayaa33

    @HayaaaHayaa33

    4 күн бұрын

    ነይ በውሰጥ የኔ አባት ከሳው አሊ ይባላል እህቱ ጥፍታበታለች ለርዥም አመት

  • @hdxz7664
    @hdxz76645 күн бұрын

    የሆላንዱ ልጅ ውጤት ብይነገረን❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤

  • @ill5552
    @ill55525 күн бұрын

    ሱብሀን አሏህ ለአሏህ ምን ይሳነዋል ማሻአሏህ በጣም ደስ ይላን ሁሉም ነገር ፈጣሪ በፈቀደው ሰአት ሆናል አልሀምዱ ሊላህ አላኩልሀል የዛሬዎቹ ደሞ በኡነት ይለያሉ ደስስስስስ ሲሉ🌹🌹

  • @Bt-Y2XLO
    @Bt-Y2XLO5 күн бұрын

    በጉጉት የምንጠብቀዉ የቅዳሜ ከሰዓት ፕሮግራም !!የቤተሰብ መገናኘት እነደእኔ የሚያስደስተዉ!?

  • @tigistteketel3363

    @tigistteketel3363

    5 күн бұрын

    Demrige🙏

  • @temabrand3382
    @temabrand33825 күн бұрын

    የጎንደሩልጅ አድራሻው ጠፋ ኤብዮሶች❤❤ አሳውቁን አንደኛናቹ

  • @YebaleworkAsamenew
    @YebaleworkAsamenew5 күн бұрын

    እንኳን ከሞት የተረፋት ተገናኙ እንባዬን መቆጣጠር አቃተኝ መችም በመሀል ያረፈ ይኖራል ብዬ ነው አዛውንቶች ናቸው እንኳን ደስ አለን ለሁላችንም ተመስገን

  • @user-bg5rh4ui4f
    @user-bg5rh4ui4f5 күн бұрын

    በጣም የምወደዉ እና በጉጉት የምጠብቀዉ ፕሮግራም ነዉ ይከ❤እኳንም ተገናኛችሁ የሰዉ ደስታ ያስደስተኛል ያስለቅሰኛል😭😭😭

  • @nimatmuusaa-wr8oz

    @nimatmuusaa-wr8oz

    5 күн бұрын

    Eneem indanchi 😢

  • @b.6015
    @b.60155 күн бұрын

    😢😢😢😢😢😢😢 ማሻ አላህ ያየጎደር ልጅ ግን እናቱ ጠፍታ ቀረች 😢😢😢😢

  • @SmilingKelpie-or9bn

    @SmilingKelpie-or9bn

    4 күн бұрын

    አገኛታታልእካ

  • @embatmekrya1596
    @embatmekrya15965 күн бұрын

    ፀጊ ጎበዝ እግዚያብሔር መልስ አለው ቢዘገይም እውነት ነው

  • @My-Fano-Amahara
    @My-Fano-Amahara5 күн бұрын

    #የሸዋ ደብረብርሃን ነን ሲሉ ልቤ ስንጥቅ አለ🥰 ተመስገን እንኳን በህይወት ተገናኛችሁ🙏🥰 ደሞ ደስስስ ሲሉ ትልልቅ ሰዎች ሳይ ደስስስ ነው የሚለኝ🥰

  • @user-sq2fe2lh2b

    @user-sq2fe2lh2b

    5 күн бұрын

    Enem yihn lbs ayeshew yenetelawun tletun dizaynun sntalabet yewalnewun ye shewa yegna new blew😮😮

  • @user-cv8nr9rz2o

    @user-cv8nr9rz2o

    4 күн бұрын

    😂ልክ እንደ እኔ ሀገሬ ደብረብርሀን🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉❤❤❤❤

  • @yalem2598
    @yalem25985 күн бұрын

    የውንየ ጸግየ ስላየኋቹህ ደስ ብሎኛል ዛሬ ጠብቀን የነበር የባለፈው ልጅ ከውጭ የመጣው ከናቱጋ ዲኤንኤ የሰጠው የነሱን ነበር አይደርስም እንዴ

  • @Firstmove01

    @Firstmove01

    5 күн бұрын

    በሰው ጊዜ ይቀልዳሉ

  • @jemilamohd8602
    @jemilamohd86025 күн бұрын

    ሲለቅሱ ማለቅሰው ነገረሰ ሲሰቁ መሳቅ ድሰ ሲሎ በአላህ

  • @user-fz5cl3rv7d
    @user-fz5cl3rv7d5 күн бұрын

    እር ምን ታምር የት ነሽ የጎደሩ ልጅ እናት የት ነሽ😢😢😢😢😢😢

  • @fatumamohammed-ye1rr
    @fatumamohammed-ye1rr5 күн бұрын

    አየለች ቅጣው አላህ ዘመንሽን ሁሉ ይባክልሽ የፈለግሽውን ነገር አላህ ያሳጣሽ መልካም ነት ለእራስ ነው እንደ አንች አይነት ደግ የባል ቤተሰብ ያብዛል አላህ Ebs ሚዲያ 🎉ሁል ጊዜም ያብብብ ከፍ ይበል አላህ ድርጂቱ ከፍ ያድርገው ከነእ ሰራተኞቹ❤ ❤❤❤

  • @meseretdibabe8020
    @meseretdibabe80205 күн бұрын

    ያልሞተ ስው ይገናኛል የሚባለው ለካ እውነት ነው❤❤❤

  • @user-yp4zc3kt7e
    @user-yp4zc3kt7e4 күн бұрын

    ሸዋ አይታማም ደሞቼ እንኳንም ተገናኛችሁ ልጆቻችን እንዳይጋቡብን እናስተዋውቃለን አለ የተባረከ ዘር ebs ተባረኩ🎉🎉🎉🎉🎉🎉❤❤❤❤❤❤❤

  • @ruq1716
    @ruq17165 күн бұрын

    ❤❤❤ ባለታሪኮቹ ሳያለቅሱ እኔ በእምባ የምታጠበዉ ነገር 😂😂

  • @michaletesfalase8016
    @michaletesfalase80165 күн бұрын

    በኡነት Ebs እግዚአብሔር ይባርካቹ እኔ ኤርትራዊ ነኝ የናንተ ፕሮግራም ሁሌን እከታተላለሁ በጣም ጥሩ ስራ ነው የምትሰሩ እግዚአብሔር ከናንተ ጋ ይሁን ❤❤❤

  • @Aberash-hd1uz
    @Aberash-hd1uz5 күн бұрын

    እግዚአብሔር አምላክ ሆይ ተመስገን የዚህን ቤተሰብ ደስታ እዲህ እዲሆን የፈቀድክ አሁንም ተጠፋፍተው ያዘኑትን በሰላም አገናኛቸው❤❤❤❤

  • @BH-id8px
    @BH-id8px2 күн бұрын

    የዛሬው ይብሳል እማዬ እድሜ ከጤና ይስጦት እንኳን ደሳላችሁ ቤተሰብ ዘመድ ኤቢዬስ ኑሩልን

  • @user-fu8ok1fr9m
    @user-fu8ok1fr9m5 күн бұрын

    በዚህ ዕድሜ መገናኘት ደሰ ይላል ከነናፍቆት ሰቀቀን ከሚያልፉ ደሰ ይላል ተመሰገን😊

  • @asnitubechannel4469
    @asnitubechannel44695 күн бұрын

    ነገሮችን ሁሉ በጊዜዉ ዉብ አርጎ ሰራዉ🙏🏾 እንኳን ደስ ደስ አላችሁ

  • @hshshshshshsh4959
    @hshshshshshsh49595 күн бұрын

    አየለች እግዛበሔር ይጥሺ ዘመንሽኡሉ ይባረክ እንደአንች አይነት የባል ዘመድም ይብዙ❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤

  • @user-sh7gs2zy8c
    @user-sh7gs2zy8c4 күн бұрын

    ደስ ሲሉ የአላህ የኔ እናቶች እኳን ሳትገነጣጠሉ በሰላም ተገናኛችሁ

  • @nigusadis7992
    @nigusadis79925 күн бұрын

    ከሆላድየመጣው የናትናልጅ. ውጤትስየጥላሁን.

  • @kebebushtweld8215

    @kebebushtweld8215

    5 күн бұрын

    እኔም የዚ ልጅ ዉጤት ምነዉ ምነዉ እያልኩ ነዉ የኔ ጣፋጮች

  • @user-kv9bs9zk5f
    @user-kv9bs9zk5f5 күн бұрын

    የእግዚአብሔር ስራው ድንቅ ነው ስለሁሉም ነገር እግዚአብሔር የተመሠገነ ይሁን በእውነት

  • @FatumaTube-dp1sl
    @FatumaTube-dp1sl5 күн бұрын

    እልልል እንኳን ደስ አላችሁ ደስ ይላል ግን የጎንደሩ ልጅ ቤተሰብ ሳይገኙ ቀሩ የኔ አባት አላህ በሰላም ያገናኛችሁ❤❤❤❤

  • @etlmawmoges5058
    @etlmawmoges50585 күн бұрын

    እንኳን ደስ አላችሁ ማሪያምን በጣም ነው ደስ ያለኝ የተለያዩ ሁሉ እግዚአብሄር እንደዚህ አገናኝቷቸው ደስታ ያሰማል❤❤❤❤❤❤❤❤

  • @hirutwedajo6984
    @hirutwedajo69845 күн бұрын

    እቴቴዬ እማምዬ እታባዬ እንኳን ደሰ አላችሁ ረጅም እድሜ ይስጣችሁ ቸሩ መድኃኔአለም

  • @ZeenahZeenah-zv8uq
    @ZeenahZeenah-zv8uq5 күн бұрын

    ሰዉን ያለመሰጋነ አላህን አያመሰግንም E B C ያምር በርቱ አላህ የግዛቹ

  • @semirahussen574
    @semirahussen5744 күн бұрын

    የአላህ ልባን የነካኝ ታሪክ አንድ ሀገር ተቀምጦ እስከዝ ዲረስ እስከሚረጅ😭😭😭😭😭💔💔💔💔

  • @rhamtistore9583
    @rhamtistore95835 күн бұрын

    እውነትም ፅሀይ ይውጣላችሁ ተባረኩ ኢቢስ የኔ አብሮ ማልቀስ😢😢😢❤❤🎉🎉🎉🎉

  • @user-ok9fz5pl6j
    @user-ok9fz5pl6j5 күн бұрын

    እንደ ዛሬ አልቅሸ አላዉቅም የኔ ናት እንኳን ደስ አላችሁ በጣም ደስ ይላል

  • @MeraMekonnen

    @MeraMekonnen

    5 күн бұрын

    Enem........weyyyy

  • @alemkebede5848

    @alemkebede5848

    5 күн бұрын

    እኔም።

  • @tigistabdisa-ob4sx
    @tigistabdisa-ob4sx5 күн бұрын

    እግዚአብሔር ይመስገን ክብር ለአምላካችን ለመድኅኒአለም እንኳን ደስ ያላችሁ

  • @user-ve7in7go6m
    @user-ve7in7go6m5 күн бұрын

    Uuufff kanii hardhaa adduma mattii addaan faca'aanii hundaa rabbii waliin haa gahuu 😭😭😭❤️🤲

  • @berhanudagnew4402
    @berhanudagnew44025 күн бұрын

    የአዲስ አበባ ሕዝብ ለተቃሞ ሰልፍ እሚወጣው ማደንዘዣ የሆኑት መጠጥ ቤቶች ፡ ጭፈራ ቤቶች እና እነርሱ መዝናኛ የሚሉዋቸው ከተዘጉበት ብቻ ይመስለኛል ።

  • @ZeenahZeenah-zv8uq
    @ZeenahZeenah-zv8uq5 күн бұрын

    አራ የከነደዉ ልጅ ይቅራብልን እነትነ ልጅ እማማ አርጅቶወሉ እነ ልጀቸዉ ከሆነ እንዲደሰቱ እበከቹ ዲኤኑን ዉጤት አምጡልን በሚቀጥለዉ እሱ ይቅራብልን

  • @mymunahussen1263
    @mymunahussen12635 күн бұрын

    አላህ ሆይ የተነፋፈቀን ሁሉ አንተ አገናኘው ያረብ እንኳን ደስ አላችሁ ሁላችሁም

  • @matiwosfufanekera
    @matiwosfufanekera5 күн бұрын

    የጠፌ ሰዉ ስገኝ ሁሉም ሰዉ እደሠታል እኔ ግን 20 ዓማት የላቃሥኩ ነኝ ይበከቹ ልጃን ፈልጉልኝ የልጃ ስም ቃልክደን ማቲዎስ ፉፋ የእናቱዋ ሰም ብራሐን አያለዉ ስዩም ትግራይ ክልል አፈልጉኝ

  • @zuzumohammed8947

    @zuzumohammed8947

    5 күн бұрын

    አላህ ያገናኛችሁ እማ

  • @MashoKahsay-cv5sm

    @MashoKahsay-cv5sm

    4 күн бұрын

    ትግራይ የት አካባቢ እንደ ሆኑ የቦታው ስም እምታውቅ ከሆነ ንገረኝ❤❤

  • @nazretnazret8929
    @nazretnazret89294 күн бұрын

    እግዜአብሔር ይመስገን እተኮ ቸርነትህ ብዙነው የድንግል ማርያም ልጅ 🙏🙏🙏

  • @ZEthiopia-ng2oe
    @ZEthiopia-ng2oe5 күн бұрын

    በሳምንቱ ቤተሰባቸውን ያገኛሉ ብይ ነበር ነገር ግን በሳምንቱ ባይሆንም በ3 ሳምንት ይሄው እንዳልኩት ቀርበዋል እንኳን ደስ አሎውት እናታችን🙏

  • @alemkebede5848
    @alemkebede58485 күн бұрын

    ኢ ቢ ኤሶች ቃል አጣሁላችሁ ደስታ ኬቤታችሁ አይራቅ የብዙዎች የደስታ ምንጭ ናችሁና ተባረኩልን በጣም ነው ያስለቀሱኝ ዛሬ እናቶቼ እንኳን ደስ አላችሁ።

  • @rabimhammed119
    @rabimhammed1195 күн бұрын

    ያአላህ ይሄ ሁሉ ቤተሰብ እያለ በናፍቆት ሲቃጠሉ መኖር እንኳን ደስ አላችሁ ሁላችሁም ኢቢኤስ ምርጥ ፕሮግራም ክበሩልን 🎉🎉🎉❤❤❤❤

  • @ahmadjadiga1802
    @ahmadjadiga18025 күн бұрын

    ማሻአላህ ልዬ ቀን ሁል ጊዜ ደስታ ይሁንላችሁ❤

  • @yeshitegegne9994
    @yeshitegegne99945 күн бұрын

    የዛሬዉስ ፡ ተለየብኝ ፡ እግዚአብሄር ፡ ይመስገን

  • @AbushAb-fg2gc
    @AbushAb-fg2gc4 күн бұрын

    ይህን comment የምታነቡ ሁሉ፡ ለኔም ፀልዩልኝ #እናቴን እንዳገኝ፡፡ ከተለያየን 33 ዓመት ሆነን ፡

  • @user-kn6bd1sl9d

    @user-kn6bd1sl9d

    2 күн бұрын

    Egzeabher yerdah

  • @user-zo9kz2ev5z
    @user-zo9kz2ev5z5 күн бұрын

    ደስታም ያስለቅሳል ማልቀስ ሳልፈልግ አስለቀሱኝ

  • @herutmengistu1947
    @herutmengistu19474 күн бұрын

    እንኳን ደስስ አላቹህ ከዚህ ሁሉ የናፍቆት ህመም በሰላም ተገናኛቹህ❤🙏

  • @zinabmohamammd3146
    @zinabmohamammd31465 күн бұрын

    በእውነት ስለ ማይሳነው ነገር እግዚአብሔር ይመስገን❤❤❤እልልል እንኳን ደስ አላችሁ❤❤❤

  • @asnabelayneh7228
    @asnabelayneh72285 күн бұрын

    እግዚአብሔር ይመስገን ስለ ሁሉም ነገር ያስመዘገብሻቸው ቅን ልብ አለሽ ዘርሽ ይባረክ እንደ አንቺ ያሉትን ያብዛልን አንቺ ባትኖሪ ኖሮ ተለያይተው ይቀሩ ነበር እግዚአብሔር ቀሪ ዘመናችሁን የፍስሃ ያድርግላችሁ እማዬ እድለኛ ነዎች

  • @user-wd6zy3ew5s
    @user-wd6zy3ew5s5 күн бұрын

    በተሰብ ሁሉም ቆንጆ ናቸዉ አንድ አይነት ናቸዉ

  • @hshdhdh5295
    @hshdhdh52955 күн бұрын

    የኔ ነገር ሲደሱም ማልቀስ ሲከፉም ማልቀስ አይይ ናፍቆት 10 አመቴ ቤተሰብ ከተለየሁ እማየ 😢😢😢😢 ❤❤❤

  • @umueimran
    @umueimran5 күн бұрын

    ውይ አደኛነኝ እኳንደስአላችሁ እዳው ሳምንትበመጣቁጥር የጎደሬውንልጅነው እምጠባበቀው እባካችሁ እደገናይቅረብ😢😢😢😢😢😢😢😢😢

  • @HelenD545

    @HelenD545

    5 күн бұрын

    በጣም😢 ቢቀርብ መልካም ነው

  • @SamriKebede
    @SamriKebede2 күн бұрын

    የድሮ ሰዎች በጣም ክፉ ናቸው ቤተሰብ አያገናኙም እኔ ለምሳሌ እናቴ ከአባታችን ተለያይታ አ አ ለአባቴ ዘመድ ሰጠችኝ ግን 25 ዓመት ሙሉ ከቤተሰብ ሳያገናኙ አፍነው ስራ ያሰሩኝ ነበር ካለደመወዝ ስለዚህ የዛ ግፍ ነው

  • @rehanamohammad5319
    @rehanamohammad53195 күн бұрын

    ሰላም ብያለዉ ያአላህ ኢቤሶች እድሜጤና. ለሁላቹም ተመኝዉ የተጠፋፉትን መገነኝት ቀለል ነገር አይደለም በጠም የምከተተለዉ ፒሮጊራም ነዉ እባዬን መቁጠጠር አልችልም

  • @Damenu-mx1ch
    @Damenu-mx1ch4 күн бұрын

    እሰይ የኔ እናት እንኳን ደስአሎዎት❤❤❤ የጎንደሩ ልጅ እባካችው እንደገና አቅርቡት

  • @DhgdDhgfe-zj9li
    @DhgdDhgfe-zj9li5 күн бұрын

    እኳን ደስአላችሑ የተገናኛችሑት ግን የምገርሙ ናችሑ ተመልካቹ የተለቀቀው ሌላ የምታወሩት ሌላ የጎደሩም የውጪ አገሩም ከመጣ ወዴት ይወስዱታል አቤት የኛሕዝብ 🤔🤔🤔🤔🤔🤔🤔🤔 በተረፈebs በጣም ጥሩስራነው ከአላሕ በታች በርቱ ዮውኔ ፀጊ በርቱልን የናቶችያባቶች ምርቃን እራሱ በብር አይገዛም በተረፈ አላሕዬ ሐገራችንን ለዚሕ የዋሕ ሕዝብ ሰላሟን መልስልን አማራ እስላም ሳትል ያረብ 🤲🤲🤲🤲

  • @EkramKader-gs5nn

    @EkramKader-gs5nn

    5 күн бұрын

    እኔ እራሱ አቃጠሉኝ ኮሜንት መፃፍ አልወድም አነባለሁ እንጂ

  • @EkramKader-gs5nn

    @EkramKader-gs5nn

    5 күн бұрын

    አሚንንንን ያረብ

  • @user-gn5wb1zi4o

    @user-gn5wb1zi4o

    5 күн бұрын

    ልጁ ስለሰዘነቸው ነው ምኮምቱቱ

  • @NurEkram

    @NurEkram

    5 күн бұрын

    እነሱ ያልመጣላቸው ነገር ምን ያርጉ አትጫጩ

  • @beranamagarsa9437
    @beranamagarsa94375 күн бұрын

    እንኳን ደስአላቹዉ ❤❤❤🎉🎉🎉በእዉነት እንደት ያስደስተል 🎉🎉🎉🎉🎉እልልልልልልል ኢቢስች ተባረኩልን🎉🎉🎉❤❤

  • @user-sr7pk8ee6t
    @user-sr7pk8ee6t5 күн бұрын

    ቅዳሜ በደረሠ ቁጥር ያየጎንደር ልጂ መጣደ እያልኩ እሮጣለሁ አረተውዳግም አቅርቡት በአላህ😢😢😢

  • @user-tc3hq6mf2w
    @user-tc3hq6mf2w5 күн бұрын

    እኳን በሰላም መጣቺሁ EBS ሶቺ የጎደሩልጂ ከምን ደረሰ 😢😢 😢😢

  • @FikreAbebe-xv8vm
    @FikreAbebe-xv8vm5 күн бұрын

    እሰይ ጎበዝ ያለው ይበቃል ስለሞተው ሳይሆን ያሉት አስደንቆኛል

  • @tegeset293
    @tegeset2935 күн бұрын

    የኔም እናት እህትና ወዳሟን አግታ እድህ በደስታ ብታለቅስ ኡፍ

  • @adelalbalooshi8054

    @adelalbalooshi8054

    5 күн бұрын

    ebs indikeribu arigachewu

  • @user-ew6qp1lt3g
    @user-ew6qp1lt3g5 күн бұрын

    መሻ አላህ እንኳን በሠላም ተገናኛችሁ

  • @Fatema-fv5bw
    @Fatema-fv5bw5 күн бұрын

    ሀሌ ገርማንት ሰፈሬን አያው ያደስታ ለቅሶ ደስ ሲል

  • @belaynehfantaye8486
    @belaynehfantaye84865 күн бұрын

    የሚገርመው፣ ይሄን ያክል ከሰሜን አማራ ከምዕራብ ወለጋ የተጋባ አብሮ የኖረ የተጋመደ ሕዝብ ለማጨራረስ የተኬደው ርቀት ሆሆሆሆ

  • @user-el6mj2yv8g

    @user-el6mj2yv8g

    4 күн бұрын

    ጨፍጭፈው ጨረሡኮ😢

  • @kwkw2678
    @kwkw26784 күн бұрын

    ታማስገን እንኳን ደስ አለችው ❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤ ያእውነት እያለቀስኩ ነው ያየሁት እኔም ወንድሜ ከጠፋ ሃያ አራት አማት ሆነው ፋጠር አምላክ ከስደት በሠለም ማልሶኝ እኔም ወንድሜን ለማግኛት ያብቀኝ ወንድሜ ስሙ ማገሸ ጉልማ ወይም ታሾማ ጉልማ ይባለል ትውልድ ቦታው ቀርሠ ይበለል 😢😢😢😢😢😢😢😢😢

  • @meseretdibabe8020
    @meseretdibabe80205 күн бұрын

    በጣም ደስ ይላል ዮኒ እግዚአብሄር ይስጣችሁ❤❤❤

  • @amma4705
    @amma47054 күн бұрын

    ማሽአላህ እድሜ ረጂም አድርጓችሁ ተገናኛችሁ ያለሠውይገናኛል

  • @Aberash-hd1uz
    @Aberash-hd1uz5 күн бұрын

    የዱሮዎቹ ችግር ቢለያቸው እዲህ ተነፋፍቀው ተፈላልገው ተገናኝተው ይላቀሳሉ ❤❤❤ያኹኑ ትውልድ ደሞ ስንት ሞልቶ ተርፎት በፍቅር መኖር አቅቶት ይባላል ይላቀሳል😢😢😢አቤት ልዩነት አቤቱ ልዑል እግዚአብሔር ሆይ የቀድሞዋን ኢትዮጵያን አምጣልን❤❤❤

  • @user-yz7ey9ws2m
    @user-yz7ey9ws2m5 күн бұрын

    ኢትዮጵያዊት ለዘላለም ኑሪ ፍቅር ሰላም አንድነት ይስጠን ቸር አምላካችን እግዚአብሔር ይመስገን እንኳን ደስ አላችሁ❤❤❤❤❤❤❤❤❤

  • @hawwaksa44
    @hawwaksa445 күн бұрын

    እማማ እንኳን ደሰ ያለሸ

  • @AbayeneshKenda21
    @AbayeneshKenda214 күн бұрын

    ኧረ የጎንደሩ ልጅ ይቅረብልን ሁሌም ቅዳሜ ከሰአት በደረሰ ቁጥር ልቤ ተጠልጥላ ባፌ ልትወጣ ነው በጣም የሚያሳዝን ልጅ ነው ዘርህን ፈልግ የተባለው የጎንደሩ ልጅ ይቅረብልን❤

  • @user-gt1mx3bd5m
    @user-gt1mx3bd5m5 күн бұрын

    የምር የደስታ ልቅሶ ነው አብሪያቸው ያለቀስኩት እነ ዮኒዮ ፈጣሪ አብዝቶ ይባርካችሁ 🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉❤

  • @user-wp4vb1xk2v
    @user-wp4vb1xk2v5 күн бұрын

    እንኳን ደስ አላችሁ ! የእኛ ህዝብ እንግዲህ እንደዚህ ነው ልትለየው የማትችል የተቀየጠ ህዝብ ነው የሚባለው ።

  • @Banchu-dz8vw
    @Banchu-dz8vw5 күн бұрын

    እግዚአብሔር ታሪክ ቀያሪ ነው እኮ ደስታና ለቅሶ እግዚአብሔር እድሜና ጤና ይስጣችሁ ኑሩ

Келесі