ቅዱስ አባ ዮሐንስ ሐጺር ክፍል - 1 / Kidus Aba Yohannes Hatsir Part -1
Ойын-сауық
ይህን መንፈሳዊ ፊልም አዘጋጅተው ላቀረቡልን ሁሉ ቃለ ሕይወት ያሰማልን፡፡
+" ቅዱስ አባ ዮሐንስ ሐጺር "+
በቤተ ክርስቲያን ያሉ አበው ሊቃውንት እንደሚሉት ከቅዱሳን በቁመቱ የአባ አርሳኒን ያክል ረዥም አልነበረም:: እርሱ እንደ ዝግባ ቀጥ ያለ ነበር:: በዚያው ልክ ደግሞ የቅዱስ ዮሐንስን (ዛሬ የምናከብረውን) ያህል አጭር አልነበረም:: በዚህ ምክንያት ይሔው ለዘለዓለም "ዮሐንስ ሐጺር - አጭሩ አባ ዮሐንስ" ሲባል ይኖራል::
+ሊቃውንትም ቁመቱንና ቅድስናውን በንጽጽር ሲገልጡ:-
"ሰላም ሰላም ዕብሎ በሕቁ:
ለዮሐንስ ሐጺር ዘነዊኅ ሒሩተ ጽድቁ" ይላሉ:: "ቁመቱ እጅግ ያጠረ: ጽድቁ ግን ከሰማይ የደረሰ ቅዱስ ዮሐንስን ሰላም ሰላም እንለዋለን" እንደ ማለት ነው::
+ቅዱሱ የተወለደው በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን በምድረ ግብጽ ነው:: ወላጆቹ ምንም ከሥጋዊ ሃብት ድሆች ቢሆኑም ባለ መልካም ክርስትና ነበሩና በጐውን ሕይወት አስተምረውታል:: ወደ ምናኔ የገባው ገና በ18 ዓመቱ ሲሆን የታላቁ አባ ባይሞይ ደቀ መዝሙር ሆኖ ተጋድሎንና ትሕርምትን ተምሯል::
+ቅዱስ ዮሐንስ ሐጺር በወቅቱ ከነበሩ ቅዱሳን ከቁመቱ ባሻገር በትሕትናው: በትእግስቱና በመታዘዙ ይታወቅ ነበር:: አባ ባይሞይ ይጠራውና ያለ ምንም ምክንያት ደብድቦ ያባርረው ነበር:: እርሱ ግን "ምን አጠፋሁ?" ብሎ እንኩዋ ሳይጠይቅ "አባቴ ሆይ! ማረኝ?" እያለ ከእግሩ ሥር ይወድቅ ነበር::
+ለብዙ ጊዜ በተመሳሳይ ሲደበድበው: እርሱም እርሱው ተደብድቦ: እርሱው ይቅርታን ሲጠይቅ ኖረ:: አንድ ቀን ግን እንደ ልማዱ ሊገርፈው ሲሔድ 7ቱ ሊቃነ መላእክት ከበውት አይቶ ደንግጦ ተመልሷል::
+አባ ባይሞይ ይሕንን ሁሉ የሚያደርገው ጠልቶት ወይ ክፉ ሆኖ አይደለም:: አንድ ሰው የሌላኛውን ግፍ መቀበል ካልቻለ ሰይጣንን ድል አይነሳም የሚል ትምሕርት ስለ ነበረ ነው እንጂ::
+አንድ ቀን ቅዱስ ዮሐንስ ወደ መምሕሩ ቀርቦ "አባቴ ጅብ ካገኘሁ ምን ላድርግ?" ሲል ጠየቀው:: (የአካባቢው ጅብ መናጢ ነበር) አባ ባይሞይ ግን "ይዘህልኝ አምጣው" አለው:: ትዕዛዝ ነውና ቅዱሱ ወደ በርሃ ወርዶ: ጅብ አልምዶ ይዞለት መጥቷል::
+ሌላ ቀን ደግሞ አባ ባይሞይ ቅዱስ ዮሐንስን ጠራውና ተፈልጦ የወደቀ ደረቅ እንጨት ሠጠው:: "ምን ላድርገው አባ?" አለው:: "ትከለውና እንዲያፈራ አድርገው:: ከዚያ አምጥተህ አብላኝ" ሲል መለሰለት:: ይህ ነገር ከተፈጥሮ ሥርዓት ውጪ መሆኑን እያወቀ ቅዱስ ዮሐንስ "እሺ" ብሎ ወስዶ ተከለው::
+ከዚያም ለ2 ዓመታት ሳይታክት ውሃ አጠጣው:: ውሃውን የሚያመጣበት ቦታ ደግሞ 10 ኪሎ ሜትር ያህል ከገዳሙ ይርቅ ነበር:: ቅዱሱ ላቡን እያፈሰሰ አሁንም ማጠጣቱን ቀጠለ::
+በ3ኛው ዓመት ግን ለምልሞ አበበ: ደግሞም አፈራ:: ካፈራው በኩረ ሎሚም ወስዶ ለመምሕሩ "አባቴ! እንካ ብላ" ብሎ ሰጠው:: አባ ባይሞይ ግን ማመን አልቻለም:: እጅግ አደነቀ: አለቀሰም::
+ወዲያው ያን ፍሬ ታቅፎ ወስዶ ለገዳሙ መነኮሳት አላቸው- "ንሱ ብሉ: በረከትንም አግኙ:: ይህ የዛፍ ሳይሆን የመታዘዝ ፍሬ ነው:: ቅዱስ ዮሐንስ አባ ባይሞይ ቢታመም ለ12 ዓመት አስታሞታል::
+መምሕሩ ከማረፉ በፊትም መነኮሳቱን ሰብስቦ የቅዱስ ዮሐንስን እጅ አስጨበጣቸው:: "ይህ የያዛችሁት እጅ የሰው ሳይሆን የመልአክ እጅ ነው" ብሏቸው ዐርፏል:: ቅዱስ ዮሐንስም ከዓመታት ቆይታ በሁዋላ የገዳሙ አበ ምኔት ሆኖ አገልግሏል:: ብዙ ነፍሳትንም ለቅድስና ማርኩዋል::
+መላእክት ንጽሕናው ደስ ስለሚያሰኛቸው አብረውት ይውሉ ነበር:: ሲተኛም በተራ በተራ ክንፋቸውን ያለብሱት ነበር:: ምጽዋትን በጣም ስለሚወድ ሰፌድ እየሰፋ ይሸጥና ገንዘቡን ለነዳያን ያን ያካፍል ነበር::
+አንድ ቀን እንደ ልማዱ ወደ ገበያ ወጥቶ ሳለ ተደሞ (ተመስጦ) መጣበት:: ሰማያት ተከፍተው: ቅዱሳን ሊቃነ መላእክት ሚካኤልና ገብርኤል በግርማ በጌታ ፊት ቆመው ተመለከተ::
+"እጹብ: እጹብ" እያለ ሲያደንቅ አንድ ገዢ መጥቶ "ባለ እንቅብ ዋጋው ስንት ነው?" ቢለው "እኁየ ሚካኤልኑ የዓቢ ወሚመ ገብርኤል - ከሚካኤልና ከገብርኤል ማን ይበልጣል?" ብሎታል:: ገዢውም ደንግጦ "እብድ መነኩሴ" ብሎት ሔዷል::
+ቅዱስ ዮሐንስ ሐጺር ወደ ባቢሎን (የአሁኗ ኢራቅ) ሒዶ ከተመለሰ በሁዋላ በበርበሮች ምክንያት ከአስቄጥስ ወደ ቁልዝም ተሰዷል:: በዚያም በአባ እንጦንስ በዓት ውስጥ ዐርፏል:: ለ400 ዓመታት በዚያው ቆይቷል::
+በ825 ዓ/ም ግን በአባ ዮሐንስ ፓትርያርክ ዘመን ክቡር ሥጋው ወደ ገዳመ አስቄጥስ ተመልሷል:: ቅዱሱ ያረፈው ጥቅምት 20 ቀን ሲሆን ዛሬ ሥጋው የፈለሠበት ነው:: በዚህ ዕለትም የቅዱስ ዮሐንስ ሐጺርና የታላቁ ቅዱስ መቃርስ ሥጋ በተገናኙ ጊዜ ግሩም ተአምር ተደርጉዋል:: ወደ ቤተ ክርስቲያኑ ሲገባም ታላቅ የብርሃን ጐርፍ ሲፈስ ታይቷል::
+ሰማያዊ መዓዛም አካባቢውን ሞልቶታል:: ከዻዻሳቱ አንዱ እባረካለሁ ብሎ የቅዱስ ዮሐንስን ሥጋ ቢገልጠው አካባቢው ተናወጠ:: መባርቅትም (መብረቆች) ተብለጨለጩ:: ደንግጠው ቶሎ ቢያለብሱት ጸጥታ ሆኗል:: በዚህ ሁሉ ደስ ያላቸው አበው ቅዱሱን በዝማሬ ሲያወድሱት ውለዋል::
ምንጭ - ዝክረ ቅዱሳን የፌስቡክ ገጽ
/ %e1%8b%9d%e1%8a%ad%e1%...
Пікірлер: 427
በእውነቱ ቃለህይወት ያሰማልን ፀጋውን ያብዛላችሁ እኛንም በሀይማኖት ያፀናን
የቅዱሳን አባቶቻችን ረድኤት በረከታቸው ይደርብን ለሰሩት ለተረጎማችሁልን እግዚአብሔር አምላክ ፀጋውን ያብዛላችሁ ተስፋ ርስተ መንግስተ ሰማያትን ያውርስልን
@lemlemlemey
Ай бұрын
Cr
ጸሎታቸዉ እና በረከታቸዉ ከኛጋር ይሁን ኣሜን።
*የአባቶቻችን በረከታቸው ይደርብን*
የቅዱሳን አባቶቻችን በረከታቸው ይደርብን ፀሎታቸው ይጠብቀን እሽ ማለት ታላቅ በረከትን ታስገኛለችና አምላከ ቅዱስ ዮሐንስ ሐፂር ለእኛ እሽ የሚል ልቦና ያድለን አሜን
@serk-ke7xt
5 ай бұрын
አሜን🙏🙏🙏
ስለሁሉ ነገር ለኡል እግዚአብሄር የተመሰገን ይሁን የቅዱሳን አባቶቻችን በረከትና ረዲኤት ይደርብን!!
@debebemehirete7863
6 жыл бұрын
የማርያም ባርያ ነኝ
@selamhagerey4778
5 жыл бұрын
Selam
@user-xj3ql4xz5z
5 жыл бұрын
ጥቅምት ፳ የረፍቱመታሠቢያ እንኳን አደረሣችሁ በረከቱይደርብን
@user-fe5qk2mc6y
5 жыл бұрын
Amen Amen Amen Amen
@user-dj5bc1yi3b
5 жыл бұрын
አሜን አሜን አሜን
አሜን አሜን አሜን የቅዱሳን አባቶቻችን በረከት ይደርብን አቤቱ አምላኬ ሆይ የትህትና ልብን አድለኝ አይቶ መተውን ሰምቶ መቻልን አድለኝ አሜን
ምነኛ መታደል ነው በዝ መፈሳዊ ፊልሜ መሳተፎ ሰወች የባየውሀንስ በረከት ያደረብን አሜን አሜን አሜን 💒💒💒💒🙏🙏🙏🙏
እግዚአብሔር ቃለ ህይወት ያስማልን እግዚአብሔር ሆይ የቃለሳይሁን የትግባር ከርስቲያን እንሁን ዘንደ ፍቃድህ ይሁንል። አሜን ፫
ሰለማይነገር ስጦታው እግዚአብሔር ይመስገን የቅዱስ አባ ይሖንስ በርከታችው በሁላችንም ላይደርብን አቤቱ የቅዱሳን አክላክ ለኛም ለሀጢተኞቹ እምነትን ስጠን
አቤቶ እግዚአብሔር ሆይ ትግስት ስጠኝ እንካን ይህን ያክል ተፈትኝ ሲደክመኝ እንኳን የማማርር ነኝ ትግስቱን ስጠኝ
@hanagosaye8136
3 жыл бұрын
ልክ እኮ ነው እኛ ትንሽ ሲደክመን ፈጣሪን እናማርራለን ቅዱሳን ግን የደረሰባቸውን እንግልት ግፍ ስናይ ለነሱ ፅናቱን ሰቷቸዋል የነሱ በረከት ይደርብን
አሜን አሜን አሜን ቃል ህይወት ያሰማልን🙏🙏🙏💙😢😢😢
qale hiwot yasemale amen
አባ ዮሐንስ ሐዲር በረከታቸው ይደርብን ትግስታቸውን መታዘዛቸውን ለኛም ያድለን አሜን አሜን አሜን
Amen amen amen .. bereketna redet qdusabatachin yohabs ayleyen amen.
ቅዱስ ዮሃንስ አባቴ በረከትዎ ይደርብን እንዳተ ታዛዠ ባደረገኝ ልዑል እግዚአብሔር ይመስገን 🙏
አሜን አሜን አሜን ቃል ህይወት ያሰማልን በረከታችሁ ይደርብን አባታችን ልቦናዬ ክፈትልኝ አቤቱ የድንግል ማርያም ልጅ እየሱስ ክርስቶስ አቤቱ ልቦናዬን ክፈትልኝ
Fetenan malef lebego new Abetu amlakachin lik inde yihwans tigstun siten amen amen
ቃልሂወት ያስዐልና ፡ናይ ቁዱሳን ኣቦታትና በረከት ረዲኤት ምስ ኩላትና ደቂ ተዋህዶ ይኹን ኣሜን ኣሜን ኣሜን
በእውነት እዲህ ለምታቀርቡልን የቅዱሳን አምላክ ይጠብቃችሁ አሜን አሜን አሜን የጻዲቁ በረከት ይደርብን!!
በእውነት እንዲህ እየሰራችሁ ለምታቀርቡልን እግዚአብሔር አምላክ ሰማያዊ ዋጋ ይስጥልን ቸሩ መድሀኒአለም ያገልግሎት ዘመናችሁን ያርዝምልን
@reda6328
5 жыл бұрын
zewudinesh Dggifa ኣሜን. ኣሜን. ኣሜን
@reda6328
5 жыл бұрын
ኣሜን. ኣሜን. ኣሜን ማር
@reda6328
5 жыл бұрын
ኣሜን. ኣሜን. ኣሜን
@tallybayan4380
Жыл бұрын
አሜን
@user-uc9ox9es6c
3 ай бұрын
አማን አሜን አሜን 😢
የአባታችን ቅዱሰ ይሁዋንሰ ሀፂር በረከት ይደርብን አሜን አሜን👏
በውነት የአባቅዱስ ዮሐንስ ሀጺሩ በረከታቸው ይድርሰን በውነት እግዚአብሔር ከዳማችን ይጠብቅል አምላክችን
የቅድሳን አባቶቻችን እርዴት በርከት ይደርብን አሜን አሜን አሜን
Amen amen amen kelheyot yasemaln berketachw yederbn
አሜን የፃድቁ በረከት ይደርብን
በረከታችሁን ይደርብን ይከተለን አሜን አሜን አሜን
Amen amen amen amen amen amen amenamen amem amen amen amen amen amen amen amen amen amen amen amen amen amen amen amen
ቃለ ህይወት ያሰማልን የአባታችን የቅዱስ ዮሐንስ በረከት ይደርብን
አሜን የቅዱሳን የመላይክት የሠማአታት በረከት እረደታቸው ይደርብን
አሜን የአባታችን በረከት አይለየን። መምህሬ ወንድሜ ይሄንን የህይወት ምግብ ስላቀረብክልን ቅዱስ እግዚአብሔር አብዝቶ ጤና እና እድሜ ይስጥክ።
ስለሁሉም ነገር ልኡል እግዛብሄር የተመሰገነ ይሁንየቅዱሳን አባተቻችን በረከት ረዲኤት አይለየን
በእውነት የቅዱሳን በረከት ይደርብን ቃለ ህይወት ያሰማልን አሜን አሜን አሜን 🤲🤲ብዙ ትምህርቶች አስተማሪ ነው እግዚአብሔር ይስጥልን
በእዉነት ቃል ህይወት ያስማልን የቅድስን ረድኤት እና በርክት ይድሪብን አሜን አሜን አሜን አባትየ ልእል እግዚአብሔ ሆይ የአንተ የወድድ እና ሕቅ የራስ የምብላ ሁሌ በፍተና ግዜ ነወ እና በየበርህ የሎ እህት ወንድሞችየ ለገንዘብ የተሰደድ በሰላም ውደ አሰብት አደርስች አባት በችሪነትህ ገብኝችዉ አሜን አሜን አሜን
አሜን አሜን አሜን ቃለሂወት ያሰማልን የአባታችን በረከት እረዴት ይደርብን ለሀገራችን ሰላም ፍቅር አንድነት የድንግል ማርያም ልጅ ቅዱስ እግዚአብሔር ያድልልን አሜን
@sarasara-ov7gx
6 жыл бұрын
ሂሩት ፈለቀ አሜን።አሜንአሜን ።የቅዱሳን ሰመአታት የፃድቃንሰመአታት ፆለት ልመናቸዉ በረከትአቸዉ አለየን ቃለህዉትነረ ያሰማልን የማታልፈዉን እረሰተ መግሰተ ሰመአታትን።ያወርሰልን።በደጁ አፅናን ሀፃታችንነረም።ይቅርበለን አቤቱ
ኣሜን ኣሜን ቃለ ህይወት ያሰማን የቅዱሳን ታሪክ ለምታቀርቡልን እግዚአብሔር ኣምላክ ጸጋዉን ያብዛላቹ
የአባ የውሀንስ በረከታቻውን ይደርብን አሜን ቃለ ህይወት ያሰማልን አሜን።
የአባታችን አባ ዮውሃን በረክት ረድኤት አይለየን ኣሜን አሜን አሜን
የቅዱሳን በረከት እረዴታቸው ይደርብን ተርሜወች እግዚአብሔር ፀገውን ያብዛላቹህ
እግዚአብሔር ይመስገን ለሁሉም ነገር እሂን ለመስማት ላበቃኝ እናመስግናለን ወድሜ የአባታችን አባ #ዮሐንስ በረከቱ ይደርብን አሜንንንንንንንንን
የቅዱስ አባ ዮሃንስ ሐጲረ ምልጃውና ፆለቱ እና በረከቱ ከኛጋ ይሁን አሜን ፫
ቃለ ህይወት ያሰማልን ፀጋዉን ያብዛላችሁ የቅዱሳኑ ቡረከተ ረድኤት ይደርብን
የቅድሳን በረከት ይደረብን አሜን አሜን አሜን አምላክ የሐንስ አንተ ታውቃለህ
የቅዱሳን አባቶቻችን ረድኤት እና በረከት ይደርብን ።
የኣባታችን የቅዱስ የሀንስ በረከት ረድኤት ይደርብእን አሜን፫
@alhajjalhajj2581
4 жыл бұрын
የአባታችን የቁድሳን ይኋንስ ረደኤቱ ያድረሰን አሜን አሜን አሜን
@ttigistttigist2200
3 жыл бұрын
አሜንአሜንአሜንንን
የቅዱስ ይዋንስ በረከት ረድኤል በላያችን ላይ ይደርሳል እሄንን መንፈሳዊ ቢድዮ ለሁለተኛ ግዜ ሳየው መንፈሳዊ ድራማ እንዴት ደስ ይላል
የቅዱሳንን ኗረከተ ያሳድርብን ቃለ ህይወት ያሰማልን🙏🙏🙏🙏🙏
የቅዱሳን አባቶቻችን ፀሎት ረድኤት በረከታቸው ከሁላችንም ጋር ይሁን ይህንን የቅዱሳንን ፊልም የምትሰሩ ሁሉ እግዚአብሔር አምላክ ዋጋችሁን ይክፈል አሜን
የቅዱሳን በረከታቸው ይደረብን ቃለ ህይወት ያደማልን እግዚአብሔር ይስጥልን
የአባታችን የአባ ዮሐንስ በረከት ይደረብን የኔጊ ሰው ይበለን 🤲🤲🤲
የቅዱሳናት በርከታቸው ረድኤታቸው ይደርበን አሜን፫
አሜን አሜን አሜን የቅዱሳን በረከታቸው ፀሎታቸው ይጠብቀን
ቃለ ህይወትን ያሰማልን በእውነት ; የአብርሀም የያዕቆብ የስሀቅ እንዲሁም የእነዚህ ብሩካን ቅዱሳን የ እግዚአብሔር ባለሟሎች በረከታቸው ረድኤታቸው ምልጃቸው በእኛ በህዝበ ክርስትያን ላይ ይደርብን አሜን።
@kalukalury4783
6 жыл бұрын
አሜን
ያባቶቻችን በረከት ይደርብን በፀሎታቸው ይማረን አሜን አሜን አሜን
የቅዱሳን በረከት ይደርብን ቃለ ህይወትን ያሰማልን
የቅዱሳን በረከታቸው ይደርብን እግዚያብሄር ሆይ ባንተ የሚቀና ልቦና ስጠን
የቅዱሳን በረከት በኛላይም ይደር አሜን
የቅዱሳን እረድኤት በረከታቸው ይደርብን
አሜን ቃል ሂወት ያሰማን ለሁላችንም የአባታችን ረደኤት በረከት ይደርብን አሜን
የቅዱሳን አባቶቻችን እረዴት በረከታቸው አይለየን የቅዱሳን አምላክ አገራችንም ሰላም ያድርግልን ቸሩ መዳህኔአለም አሜን፫
የአባታችን የአባ ዪሐንስበርከታቸውና ረዴታቸው አይለየን
አሜን አሜን አሜን ቃለህይወት ያሰማልን
አሜን አሜንአሜን በርከታቸው ይደርብነ ⛪️⛪️⛪️✝️✝️✝️✝️⛪️❤️❤️❤️🥰🥰🥰🥰🎤🎤🎤🎤🎤🤲🤲🤲🤲🤲🤲🌻🌻🌻🌻🌻👏👏👏
ኣየየየ ኣቦታተይ ቡሩካት ጸሎትኩምን ረዲኤትኩም ይሕደረና ነዛ ዓለም ተተው ኢላ ክትከይድ ዝገበርኩን ብጸሎት ንስካትኩም ኢኩምሞ ጸሎትኩም ኣይፈለየና!!! ኣሜንንንንንንንንንንን ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ንዘልኣለም ትንበር ኣሜን።
@user-mk4qc4cf3s
4 жыл бұрын
Amen.
@mirrym8719
4 жыл бұрын
Amen amen amem
የቅዱሳን አባቶቻችን በርከታቸዉ ይደርብን አሜን በእዉነት እሆን እደሰማ ለፈቀድክልኝ አምላኬ እግዚአብሔር ይመስገን
ቃለ ህይወትን ያስማልን በእውነት ለሁላችንም
ዝማሬ መላእክት ያሰማልን ለዘላለም አሜን ፫ በረከት እና ቸርነት ይደብርልን
አምላከ ቅዱሳም እግዚአብሔር ይክብር ይመስገን ስሙ የአባታችን በረከታቸው ይድርብን አሜንንን በትንሹ እኮ ታዘዥች ያድርገን እኛም በእውነት ♥♥♥ ቃለ ህይወት ያሰማልን ተስፋ መንግስተ ሰማያትን ያዋርስልን አሜንንን ♥♥♥
ቃለህይወት ያሰማልን ያባቶቻችን በረከት ይደርብን አሜን ለተረጎማችሁልንም አባቶች ፀጋውን ያብዛላችሁ
@user-mk4qc4cf3s
4 жыл бұрын
Amen
ኣሜን ኣሜን ኣሜን ቃለ ህይወት የስመዐልና ናይ ኣቦና ቅዱስ የውሃንስ በረኸቶምን ረድኤቶምን ፀሎቶምን ምስ ኩላትና ኣሜን🍃
አሜን ቃለ ህይወት ያሰማልን የቅዱሳን ሁሉ በረከታቸው ይደርብን
ቃለህይወት ያሰማልን ያባቶቻችን በረከታቸው ይደርብን የነሱን ፅናት እምነት በልባናችን ያሳድርብን
የቅዱሳን በርከት በእኛ ላይ ይደርብን አሜን አሜን አሜን
ክብር ምስጋና ለናተ ይሁን ቅዱሳን ሰማዕታት ቅዱስ ቃለ በረከታቸው እኛ ላይ ይደር እናም ለእናተ ይህን በረከት እና ትምህት ላስተማራችሁን እግዚአብሔር እድሜና ጤና ይስጣችሁ
@athbaa1615
5 жыл бұрын
Aemn amen aemn aemn
ቃለ ህይወት ያሰማልን ከቅዱሳን በረከት ያካፋለን
በእዉነት ቃለ ህይወት ያሠማልን ፀጋዉን ያብዛላችሁ በረከታቸዉ ይደርብር❤❤❤⛪❤❤❤
የቅድሳን በረከታቸው ይደርብልን የፊልሙን አቀናባራውዮንና ደራስውን በአጠቃላይ የተሳተፋችሁ በእውነት ቃለህወት ያሰማልን ጸጋውን ያብዛላችሁ አሜን ፫ ስለአስተላለፍለክሉንም በእግዚአብሄር ስም አመሰግናለው መልካሙን ይስጣችሁ
አሜን አሜን አሜን ቃለህይወትን ያሰማልን የቅዱሳኑ በረከታቸው ይደርብን አሜን
በረኸት ቑዱስ ዮውሐንስ ሐጺር የካፍለና ቃለ ሂወት የስምዓልና አሜን !!!
ቃለ ህይወት ያስማልን እግዚአብሔር ፀጋውን ያብዛላቸው አሜን ፫
@mekdiiyetewahedolijmekdii4080
5 жыл бұрын
አሜን ቃል ህይወት ያሰማልን
@betibeti72
2 жыл бұрын
🙏🙏🙏🙏😭😭😭😭😭😭😭🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏😭😭😭😭😭😭😭😭😭
የኣባ የውሃንስ- ሓጺር ጸሎትና በረከት ይድረሰን
እግዚአብሔር ይመስገን። የአባቶቻችን ፅጋና በርከት ከሁላችን ጋይ ይሁን በእውነ ት ላቀረባችሁልንም ለሁላችሁም ቃለ ህይውፕትን ያስማልን አሜን የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ለዘላለም ትኑር
የቅድሳን በረከታቸውይደርብን ፀጋውን ያብዛላቹ ለምታቀርብልን ወንድሞቼ
የቅዱሳኑ በረከታቸው ይደርብን አሜን አሜን አሜን
እናመሰግናለን ቸሩመድካኒያለምበላይኛዉይክፈላችህትልቅትምህርትነዉ
ጌታ ሆይ ተመስ ገን ያለተ ሂወት ባዶናት በረከታቸው ይደርብን
@gbbj4463
3 жыл бұрын
E
የቅዱሳን ረድኤት በረከታቸው ይደርብን
የቅዱስ ዳዊት በረከት እረእዴ ት ከሁላችን ጋይደርብን አሜን
amen amen amen ykdus aba yohans redet berket bhulachen lay2yder
የቅዱሳን በረከት ይደርብን የቅዱሳን ሂወት ድንቅ ነው
ቃለ ህይወት ያሰማልን ረድኤት በረከቱ ያድለን አሜን ፫
ቃለ ህይወት ያሰማልን የቅዱሳን በረከታቸው ይድረሰን አሜን፫
በረከታቸው ይደርብና የአባታችን ዮዎሃንስ
እግዚኣብሔር ይስጥልን ወንድም እናመሰግናለን
ቃለህይወትን ያሰማልን የቅዱሳን በረከት ይደርብን
መዳንት። እግዚአብሔር። ዮሐንስ እና ጌታ እጥብቅህ
በእወነት ቃል ህይወት ያሰማለን ኣሜን
አሜን አሜን አሜን ቃለ ህይወተን ይስማለን 🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
ቃለ ሕይወት ያሰማልን ከቅዱስ ዮሐንስ ሐጺር ረድኤት በረከት ይክፈለን
አሜንንን የቅዱሣን ረድኤታቸውና በረከታቸው ይደርብን ቃለ ሂወት ያሠማልን