ቅድስት ዮስቲና እና ቅዱስ ቆጵርያኖስ - ክፍል 2 / Saints Justina and Cyprian - Part 2 - Ye Kidusan Tarik

Ойын-сауық

💗 ቅዱሳን ቆዽርያኖስ እና ዮስቴና 💗
ቆዽርያኖስ ማለት አገር ያስጨነቀ የሶርያ ጠንቅ ዋይ (መተተኛ) የነበረ ሰው ነው:: ከሥራዩ ብዛት የተነሳ አጋንንትን የሚፈልገውን ያዛቸው ነበር:: በዚያ ሰሞን ታዲያ ወደ #አንጾኪያ ሔዶ የለመደውን ሊሠራ አሰበ:: እንዳሰበውም ሔደ::
በአንጾኪያ ደግሞ ስም አጠራሯ የከበረ: ክርስትናዋ የሠመረ: ድንግልናዋ የተመሠከረና ደም ግባቷ ያማረ አንዲት ወጣት ነበረች:: ስሟም #ዮስቴና(የሴቶች እመቤት) ይባላል:: እንዲህ ነው ስምና ሥራ ሲገጣጠሙ::
በወቅቱ ደግሞ የእርሷ ጐረቤት የሆነ አንድ ሰው በቁንጅናዋ ተማርኮ 'ላግባሽ' ቢላት 'አይሆንም' አለችው:: ምክንያቱም እርሷ መናኝ ናትና:: በጥያቄ አልሳካልህ ቢለው በሃብት ሊያታልላት: 'እገድልሻለሁ' ብሎ ሊያስፈራራት: በሥራይ (በመስተፋቅር) ሊያጠምዳት ሞከረ::
ነገር ግን አልተሳካለትም:: ምክንያቱም ሟርት በእሥራኤል ላይ አይሠራምና:: በመጨረሻ ግን ወደ #ቆዽርያኖስ ሔዶ "አንድ በለኝ" አለው:: ቆዽርያኖስም "ይሔማ በጣም ቀላል ነው" ብሎ ወዲያው አጋንንትን ጠራቸው:: "ሒዳችሁ ያችን ወጣት አምጡልኝ" ሲልም ላካቸው::
አጋንንቱ ወደ ቅድስት ዮስቴና ሲሔዱ ግን #መላእክት ወርደው ቤቷን በእሳት አጥረውታል:: ተመልሰው "አልቻልንም" አሉት:: እርሱም "አንዲት ሴት ካሸነፈቻችሁማ እኔም ክርስቲያን እሆናለሁ" ብሎ አስፈራራቸው:: አጋንንቱም በማታለል አንዱ ሰይጣን እርሷን መስሎ ሌሎቹ ደግሞ አስረውት መጡ::
ቆዽርያኖስ ይህን ሲያይ ደስ ብሎት "ሠናይ ምጽአትኪ ኦ ዮስቴና እግዝእቶን ለአንስት - የሴቶች እመቤት ዮስቴና እንኩዋን ደህና መጣሽ" ሲል: ስሟ ገና ሲጠራ ደንግጠው አጋንንት እንደ ጢስ ተበተኑ::
"ለዛቲ ቅድስት በኀበ ጸውዑ ስማ:
ከመ እንተ ጢስ ተዘርወ መስቴማ" እንዳለ መጽሐፍ::
ቆዽርያኖስም በሆነው ነገር ተገርሞ "ስሟን ሲጠሩ እንዲህ የራዱ ወደ እርሷማ እንዴት ይቀርባሉ" ብሎ ተነሳ:: መጽሐፈ ሥራዩን በሙሉ አቃጠለ:: ሃብቱንም ለነዳያን አካፍሎ ሒዶ #ክርስቲያን ሆነ:: የሚገርመው ድንግል ነበርና ከብዙ ተጋድሎ በሁዋላ ዲቁናና ቅስናን ተሾመ::
አምላክ መርጦታልና የቅርጣግና (Tunisia) ዻዻስ ሆኖ ተመርጦ የክርስቶስን መንጋ በትጋት ጠብቁዋል:: ቅድስት ዮስቴናም ገዳም አንጻ: ደናግሉን ሰብስባ ንጽሕናን ስታስተምር ኑራለች:: በመጨረሻም መስከረም 21 ንጉሡ ዳኬዎስ ክርስቶስን ካልካዳችሁ በሚል ብዙ አሰቃይቶ አንገታቸውን አሰይፏል::
ቸር አምላክ በኃይለ መስቀሉ ሃገራችንን ከክፉው ሁሉ ይጠብቅልን:: የቅዱሳኑን ጸጋ ክብርም አይንሳን:: አሜን
ምንጭ ››› "ገድለ ቅዱሳን Gedle Kidusan Acts of Saints" የፌስቡክ ገፅ የተወሰደ
አዘጋጅተው ላቀረቡልን ቃለ ሕይወትን ያሰማልን፡፡ አሜን

Пікірлер: 926

  • @user-zx3fs2sq3q
    @user-zx3fs2sq3q6 жыл бұрын

    Hadiya Nura እግዚአብሔር ይቅር ይበለሽ የማትናወጥ የማትነቃነቅ በኢየሱስ ክርስቶስ በደሙ ያነፃትን ሀይማኖታችን ናት !!!! ወደ ትክክለኛ መንገድ እግዚአብሔር ይምራሽ ይህን ሁሉ ታምራት እያያችሁ ዛሬም እራሳችሁን እየሸወዳችሁ ትኖራላችሁ የሚያድነውን አምላክ የያዘ መቼም አይወድቅም!!! በዚህም እጅግ ደስ ይላችኋል፥ ነገር ግን በእሳት ምንም ቢፈተን ከሚጠፋው ወርቅ ይልቅ አብልጦ የሚከብር የተፈተነ እምነታችሁ፥ ኢየሱስ ክርስቶስ ሲገለጥ፥ ለምስጋናና ለክብር ለውዳሴም ይገኝ ዘንድ አሁን ለጥቂት ጊዜ ቢያስፈልግ በልዩ ልዩ ፈተና አዝናችኋል። እርሱንም ሳታዩት ትወዱታላችሁ፤ አሁንም ምንም ባታዩት በእርሱ አምናችሁ፥ የእምነታችሁን ፍፃሜ እርሱም የነፍሳችሁን መዳን እየተቀበላችሁ፥ በማይነገርና ክብር በሞላበት ሐሤት ደስ ይላችኋል። 1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 1:6-9 ከእግዚአብሔር የተወለደ ሁሉ ዓለምን ያሸንፋልና፤ ዓለምንም የሚያሸንፈው እምነታችን ነው። 1 የዮሐንስ ወንጌል 5:4 ውድ የተዋህዶ ልጆች እንኳን ለብራሃነ ጥምቀቱ አደረሳችሁ አደረሰን መልኳም በዓል ይሁንላችሁ አሜን፫ " ያመነ የተጠመቀም ይድናል፥ ያላመነ ግን ይፈረድበታል።" (የማርቆስ ወንጌል 16:16)

  • @yekidusantarik

    @yekidusantarik

    6 жыл бұрын

    አሜን

  • @user-gd2dm1rl1k

    @user-gd2dm1rl1k

    6 жыл бұрын

    ድንግ

  • @vatefghhffghh7896

    @vatefghhffghh7896

    6 жыл бұрын

    ድንግል ማርያምን ይዞ የሰላም ጉዞ

  • @vatefghhffghh7896

    @vatefghhffghh7896

    6 жыл бұрын

    የቅዱሳን ታሪክ / Ye Kidusan Tarik

  • @user-vd8zt8fi6m

    @user-vd8zt8fi6m

    6 жыл бұрын

    ድንግል ማርያምን ይዞ የሰላም ጉዞ ቀድሞ ተዋህዶ መሆን እራሱ መታደል ነው አምላክ የጠፉ ወገኖቻቺንን ይመልስልን እኛንም ያጽናን

  • @hiewtdemelie6102
    @hiewtdemelie6102 Жыл бұрын

    ተመስገን ተመስገን ተመስገን አምላኬ ይህንን እንድንሰማይችን ስዓት ባርኮ ቀድሶ የሰጠን አምላካችን ልዑል እግዚአብሔር ይመስገን በረከታቸዉ ይደርብን

  • @AmanYouTube2024
    @AmanYouTube20244 жыл бұрын

    አቤቱ ጌታይ ቆጹርያኖስና ዬስትናን ከእሳት ነበልባል እዳንካችው እኛንም ከመናፉስት የእሳት ውጊያ አንተ ጠብቀን አሜን

  • @azebzam873

    @azebzam873

    10 ай бұрын

    አሜን አሜን አሜን

  • @user-nc5ki3pr1w

    @user-nc5ki3pr1w

    5 ай бұрын

    አሜንአሜንአሜን🤲🤲🤲

  • @user-qo9eh9yf4e

    @user-qo9eh9yf4e

    3 ай бұрын

    አሜን አሜን አሜን❤❤❤

  • @alemtsehaysesaysisay7144
    @alemtsehaysesaysisay714410 ай бұрын

    ድንቅ ተአምር እና ታሪክ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታይ በመሆኔ ታላቅ ኩራት ይሰማኛል ጌታ ኢየሱስ ክብርና ምስጋና ይግባህእንዲሁም ብፅዕት እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እንዲሁም ቅዱሳኑ ሁሉ ምልጃችሁ ርዴታችሁ ብርከታችሁ እስከ አለም ፍፃሜ ከኛ ጋር ይሁን አሜን 😢❤

  • @mangestu4336
    @mangestu43365 жыл бұрын

    በመጀመሪያ ልዑል እግዚአብሔር ይህን የተቀደሰ የቅዱሳን ፊልም እንድናይ የፈቀደልን ፊጣሪ የተመሰገነ ይሁን አሜን የቅድሳን በረከትና ረድኤት ይደርብን አሜን ቃል ህይወት ያሰማልን

  • @adinatiku4380
    @adinatiku43803 жыл бұрын

    ለመግለጽ ቃላት ያጥረኛል ሀይለ እግዚአብሔር ከእኛጋ ይሁንአሜን

  • @user-yx9fo8xr8j
    @user-yx9fo8xr8j4 жыл бұрын

    የቅድስት ዮሲቲና እና የቅድስ ቆጵርያኖስ ጸሎታቸው ና በረከታቸው ይደርብን ኣሜን ኣሜን ኣሜን ኣምላኬ ሆይ እንየ ሃጽያተኛ ልጅህ ይቅር በለኝ እንደ ድንጋይ የደረቀ ልበይ መንፈስ ቅድስ ኣሳድርበት😢😢😢😢

  • @hfjg3350
    @hfjg3350 Жыл бұрын

    ለነዮወስቲና የደረሰ እግዚአብሄር ለኛም ይድረስልን አሜን🙏

  • @berihugebremedhin497
    @berihugebremedhin4974 жыл бұрын

    የቅዱሳን እናቶቻችን እና የቅዱሳን አባቶቻችን በርከት አይለየን አሜን ቃለ ህይወትን ያስማልን ማዳምጠው ባጣምጠው የማልጠግበው ኦ!!አምላኬ ላንተ እና ለአንተ እንድኖር እርዳኝ

  • @masumajman3232

    @masumajman3232

    8 ай бұрын

    Ameen Ameen Ameen Bareketechewuu ka gara yihuni

  • @ayalneshlove5718
    @ayalneshlove57183 жыл бұрын

    በረከታቸው ይደርብን እኛንምአሜን በ ፫ሐይማኖታችን ያፅናን

  • @user-xr2dw6rp2i
    @user-xr2dw6rp2i5 жыл бұрын

    አሜን ፫, አምላክ ቅዱሳን እኔን ሀጢያተኛዋ ልጅህን እርዳኝ 😢😢😢😢

  • @mintamirchaile87
    @mintamirchaile873 жыл бұрын

    ኦርቶዶክስ በመሆኔ እግዚአብሄር ክብርና ምስጋና ላንተና ለእመቤታችን እንዲሁም ለፃድቃን ለሰማዕታት እስከ አለም ፍፃሜ ይሁን

  • @mamey7142
    @mamey71423 жыл бұрын

    በእውነት ቃለ ህይወት ያስማልን አሜን የቅዱሳን ምልጃ ፀሎታቸው በረከታቸው አይለየን አሜን

  • @enatmesfin
    @enatmesfin5 жыл бұрын

    ክርስቲያን ያደረገኝ አምላክ ክብር ምስጋና ይድረሰው ለድንግል ልጅ #እግዚያአብሄር ቃል ሕይወት ያሰማልን ምልጃችሁ አይለየን በጸሎት አስቡን አሁን ባለንበት ሁኔታ በእምነታችን ልንጸና ይገባል ከ ዲዮ ቂሊጢያኑስ የባሰ የኦርቶዶክስ ጠላቶች መናፍቃን ተነስተዋሉና መድሃኒአለም በሀይማኖት ያጽናን በ video የተሳተፋችሁት ሁሉ እግዚአብሔር ይስጣችሁ በረከታቸው ይደርብን።

  • @Linda-ee5kv
    @Linda-ee5kv3 жыл бұрын

    እግዚአብሔር ይመስገን በረከታችሁ ይደርብን አሜን አሜን አሜን

  • @haymiyetwhdolije5711
    @haymiyetwhdolije57115 жыл бұрын

    ተዋህዶችን ለዘላለ ጸንታ ትኑሪልን

  • @alemaraya3502
    @alemaraya35026 жыл бұрын

    የተወደዳችሁ የክርስቶስ ባለሞሎች እግዚአብሄር ይስጥል የቅዱሳኑ በርከት እርዴኢት ይደርብን አሜን

  • @yekidusantarik

    @yekidusantarik

    6 жыл бұрын

    አሜን

  • @tekestt9185

    @tekestt9185

    5 жыл бұрын

    እግዚአቤረከነንትጋያሁ

  • @sarasoso3865

    @sarasoso3865

    3 жыл бұрын

    አሜን አሜን አሜን

  • @eyerusalemmulu3913
    @eyerusalemmulu39133 жыл бұрын

    አሜን አሜን አሜን ቃለ ህይወት ያሰማልን የቅዱሳን በረከታቸው ይደርብን እሄ እንድናይ የፈቀደ የአባቶቻችን እግዚአብሔር ይመስገን ምስጋና ለእናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አሜን፫

  • @user-zp6qv7jv9q
    @user-zp6qv7jv9q3 жыл бұрын

    ስለ ሁሉም ነገር እግዚአብሔር ይመስገን

  • @tadelugesesew7935
    @tadelugesesew79352 жыл бұрын

    እመብርሀን እናታችን እንደ ዮስቲና ልቦናችንን ትክፈትልን አሜን አሜን አሜን

  • @ayaleerta3248
    @ayaleerta32483 жыл бұрын

    አሜን ቃለ ህይወትን ያሰማልን ለሁላችሁም

  • @fanuailnegash1802
    @fanuailnegash18025 жыл бұрын

    አሜን አሜን አሜን የአባታችን እና የእናታችን የሁሉም ቅዱሳን በረከት ረዴኤታቸው በእውነት ይደርብን አሜን አይለየንም በጸሎታችንም ይማሩን አሜን አሜን አሜን

  • @elelelelel3034
    @elelelelel30343 жыл бұрын

    ቃለህይወትን ያሰማልን በእድሜ በፀጋ ይጠብቅልን ለመንግስቱ ለእርስቱ ያብቃልን አሜን በረከታቸው ይደርብን

  • @user-hm8cz6mw6w
    @user-hm8cz6mw6w3 жыл бұрын

    አሜን አሜን አሜን የቅዱሳን ፀሎት ከኛ ጋር ይሁን 🙏🙏🙏

  • @user-ql5qj5tr7g
    @user-ql5qj5tr7g5 жыл бұрын

    የቅዱሳን በረከታቸው ይደርብን በጸሎት ልመናቸው ይማረን ያስበን አሜን ጌታሆይ እኛንም ደካማ ባርያወችህን በእምነትና በምግባር አጽናን

  • @user-lw2rd1cc5w
    @user-lw2rd1cc5w3 жыл бұрын

    እህት ወንድሞች ፀጋ እግዚአብሔር ይብዛላቹሁ በቤቱ ያፀናቹሁ አሜን

  • @user-kd9vn5nu2k
    @user-kd9vn5nu2k4 жыл бұрын

    አሜን አሜን አሜን የቅዱሳን ረድኤት በረከት ምላጃ አይለየን😭😢😢

  • @mdntsis395
    @mdntsis3956 жыл бұрын

    የኦርቶዶክስ እምነት ለዘላለም ትኑር ኦርቶዶክስ መሆን መመረጥ ነው

  • @toyoererertoyoererer1874

    @toyoererertoyoererer1874

    6 жыл бұрын

    Mdnt Sis አሜን አሜን አሜን

  • @gebremedhingebreyesu2727

    @gebremedhingebreyesu2727

    5 жыл бұрын

    Amne amne amne

  • @sintklemma

    @sintklemma

    5 жыл бұрын

    Hol I99 OP d9098i😑🙂🙂😅😱😳🤒🤒😱😱😳🤒🤒🤒😬

  • @user-sk6zl7yi8y

    @user-sk6zl7yi8y

    5 жыл бұрын

    Amen Amen Amen

  • @user-bi1nx1wr3y

    @user-bi1nx1wr3y

    5 жыл бұрын

    Amennn

  • @user-xg3tw6uv4z
    @user-xg3tw6uv4z3 жыл бұрын

    ውይ ደስ ሲል መግልፅ ያቅተኛል እግዚአብሔር ይመስገን ስለሁሉም ነገር የቅዱሳኑ በርከት አይለየን አሜን ፫

  • @user-ry6nk8yw9m
    @user-ry6nk8yw9m5 жыл бұрын

    ተዋህዶ ለዘላለም ትኑር እግዚአብሔር አጽራረ ቤተክርስቲያንን ያስታግስልን ይህንን የቅዱሳኑን ታርክ ለተረጎማችሁልን እግዚአብሔር ሰማያዊ ዋጋን ይስጥልን ለእኛም አስተዋይ ልቦን ይስጠን

  • @user-xd3ey7zn1l
    @user-xd3ey7zn1l4 жыл бұрын

    አሜንየቅዱሳን በርከታቸው ይደርብን ተዋህዶ መሆን በምንኛ መመርጥ ነው🙏🙏🙏

  • @biskutzeleke9111
    @biskutzeleke91113 жыл бұрын

    Amen Amen Amen Amen kale hiwetin yasemalin yesmanewun yasadirbin Amen

  • @user-hm6mw7bb1l
    @user-hm6mw7bb1l6 жыл бұрын

    የቅዱስ አባታችን ቆጲያኖስና የቅድስት እናታችን ዮስቲና በረከት ይደርብን አሜን ፫

  • @mulukebede1817
    @mulukebede18173 жыл бұрын

    ፆለታቸውና በረከታቸው ይደሪበን ተመስገን ኣሜላኬ ሆይ ለኛም ምረትሀህ ላከልን ኣሜን ኣሜን ኣሜን

  • @user-uh6tz8uz2b
    @user-uh6tz8uz2b2 жыл бұрын

    ቃለ ህይወት ያሠማልን ፀጋውን ያብዛላችሁ

  • @brtumulat2138
    @brtumulat21384 жыл бұрын

    እግዚአብሔር ይመስገን በእውነት በረከታቸው ረድኤታችው ምልጃ ፀሎታችው ይደርብን ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ለዘለአለም ትኑር አሜን

  • @helenhaftom1525
    @helenhaftom15254 жыл бұрын

    ቃለይወትይሰማልን🙏🙏🙏🙏

  • @fgghjfhhhj9655
    @fgghjfhhhj96555 жыл бұрын

    ፀጋውን ያብዛላችሁ እግዚአብሔር ስራው ድንቅ ነው ትክክለኛውን መንገድ ይምራን አሜን

  • @meseretasafe3095
    @meseretasafe30952 жыл бұрын

    የቅዱሳኑ በረከታቸው ይደርብን አምላኬ ሆይ እኔንም በሀጢያት የጠፋሁትን ባሪህን ልቦናየን አብራልኝ መልካሙን መንገድ ምራኝ ማስተዋል ጥበቡን አድለኝ😭😭😭😭

  • @user-nc5ki3pr1w

    @user-nc5ki3pr1w

    5 ай бұрын

    አሜንአሜንአሜን🤲🤲🤲🙏🙏🙏

  • @user-by3ii6tr7y
    @user-by3ii6tr7y2 жыл бұрын

    ኣሜን ኣሜን ኣሜን በረከታችው የቅድስት ዮስቲና እና የቅዱስ ቆጸርኖስ ይደርብን 🙏🙏🙏🙏🙏🤲🤲🤲

  • @user-tj5go1im5q
    @user-tj5go1im5q5 жыл бұрын

    ናይ ብሓቂ ቃለ ሂወት ይስመዐልና ፁቡቅ ትምህርቲ እዩ ኦሮቶደክስ ልዘላኣልም ትንበር ኣሜን ኣሜን ኣሜን

  • @user-wc3sl3km1l
    @user-wc3sl3km1l6 жыл бұрын

    አሜን የቅዱሳን በረከታቸው ይደርብን በእውነት በጣም እናመሰግናለን እኛም የሰማነውን 30 60 100 ያማረ ፍሬ እንድናፈራ ይርዳን አሜን

  • @Mama-zw8hv
    @Mama-zw8hv3 жыл бұрын

    እግዚአብሔር ሆይ በነዚህ ቅዱሳን ፀለት በረከትም በኛላይ አሳድር ይቅር ባይ አምላክ ሆይ ሁሉ ይሚቻልህ ይቅር በለኝ ማርኝ እኔ በሀጣት የበሰበስኩ የሸተትኩ ልጅህን ይቅር በለኝ አሜን፫

  • @user-hj6xm3sr2g
    @user-hj6xm3sr2g6 жыл бұрын

    ተመስገን ጌታ ሆይ ካንቴ የምሳኖዉ ነገር የለም ተመስገን።መንግስህ ለዘላለም የተመሰገነ ፣ ከፊ ከፊ ያለ፣ይህን።እሰግድላሃሎዉ አመሰግናሃሎህ እልልልልልልልልልልልልልልልልልልል አጥንት የምያለመልም ዝማረ መላእክት ያሰማልን እልልልልልልልልልልልልልልልል።እድመ ከጤናጋ ይስጣቹ መንግስትም ያዉርሳቹ።ኣርቶዶክስ ሃይማኖትየ የጥንት ነሽ ያባት እና እናትየ ማህቴብየ አልበጥስም ትኖራለች ለዘላለምየ።

  • @wlitesanebet1719
    @wlitesanebet17195 жыл бұрын

    ቅዱሳን እናቶቻችን አባቶቻችን ፆለታችሁ አይለየን አሜን እዴት መታደል ነው ኦርቶዶክስ መሆን

  • @zitobewke4121

    @zitobewke4121

    Ай бұрын

    እኔመታደልነው

  • @user-nq3rg7cs1m
    @user-nq3rg7cs1m2 жыл бұрын

    የቅዱሳን አባቶቻችን እና እናቶቻችን አምላክ ለእኛም ይርዳን የቅዱሳን በረከት ይደርብን አሜን

  • @marta6335
    @marta63355 жыл бұрын

    አሜን የቅዱሳን በረከት ይደርብን በእውነት

  • @micomico2708
    @micomico27085 жыл бұрын

    የቅዱሳን አባቶቻችንና እናቶቻችን በረከታቸው ይደርብን በእውነት ቃለህይወት ያሰማልን

  • @user-pl7ty9jt9i
    @user-pl7ty9jt9i6 жыл бұрын

    የቅዱሳን አባቶቻችን በርከታቸው ይደርብን ይሄንንም ፈልም ላቀርቡልን ለድካማቸው የልፍት ዋጋቸውን እግዚአብሔር ይክፈላቸው በእድሜ በጤን ያቆይልን .አሜን ለንሰሀ ሞት ያብቃን !

  • @shwyshwy5929
    @shwyshwy59295 жыл бұрын

    የቅደሳን አምላክ ይክበር ይመስገን

  • @user-vu1sc3oy7v
    @user-vu1sc3oy7v2 жыл бұрын

    ሰለ ሁሉም ነገር እግዚአብሔር ይመስገን ይህን እንድናይ ሰለፈቀድክልን እናመሰግንሀለን አሜን ቃለ ህይወትን ያሰማልን ፀጋውን ያብዛላችሁ አሜን የቅዱሳን አባቶቻችን እና እናቶቻችን በረከት ፆለትና ልመናቸው አይለየን አሜን

  • @user-kr4np9rz2i
    @user-kr4np9rz2i5 жыл бұрын

    የቅዱሳኑ እረድኤት እና በረከት ይደርብን አሜን ከበረከታችሁ ይደርብንንን እሴተ ማርያም ብላችሁ በፆለታችሁ አስኝ ሀጥያተኛል እህታችሁ

  • @HosamHosam-vk8xy
    @HosamHosam-vk8xy5 жыл бұрын

    አሜን የቅዱስኖች ላክ ይጠብቀን ቃለህይወትን ያሰማን በእዳሜ ቡፀጋ ይጠበቀን አሜን

  • @thegreatantony5060
    @thegreatantony50603 жыл бұрын

    ሰላም ለቆጵርያኖስ ሰማዕተ ኢየሱስ ፌማ በጤገነ እሳት ውዑይ አባላቲሁ ዘሀማ ምስለ ሠለስቱ ዕደው ዘተሳተፍዎ ፃማ ወሰላም ለዮስቴና በኀበ ጸውዑ ስማ ከመ እንተ ጢስ ተዘርወ መስቴማ።

  • @zamadiyasalkaw7800
    @zamadiyasalkaw78006 жыл бұрын

    አሜን አሜን አሜን ቃለ ህይወትን ያሠማልን አቤቱ አምላኬ ሆይ የኔንም ልብ ወደአተ እደታሥብ መልካም ፍቃድህ ይሁንልኚ

  • @webshettaddse3443
    @webshettaddse34435 жыл бұрын

    እግዚአብሔር ስራው ድንቅ ነው በእውነት ቃለህይወትን ያሰማልን ፀጋውን ያብዛላችሁ የቅዱሳን በረከታቸው ይደርብን አሜን እግዚአብሔር ይስጥልን ውድ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች

  • @hnaanabdualla4830
    @hnaanabdualla48306 жыл бұрын

    Amen Amen Amen

  • @getachewkahsu6994
    @getachewkahsu69944 жыл бұрын

    Amen Amen Amen qal hiwet yesmalnha Egziabher amelak ymasgen

  • @user-vi2zj9ps9b
    @user-vi2zj9ps9b5 жыл бұрын

    አሜን ቃለሂወትን ያስማልን የቅዱሳን ረድኤት በረከት ይደርብን ተዎህዶ ለዘላለም ይኑር ኑር ክብር ለድንግልማርያም ልጅ ለእየሱሰክርስቶስ

  • @betselotmuche1553
    @betselotmuche15536 жыл бұрын

    Amen.Amen.Amen.kale.hiwot.yasemaln

  • @user-rw3iy3sj6k
    @user-rw3iy3sj6k6 жыл бұрын

    በረከት ጾሎት ናይ ቅድስቲ የስታና ኣይፈለና እግዚአብሄር ጎይታ ሰራዊት ብምሕረቱ ይራየና ኣብ እምነትና የጽንዓና ንኩሉ ወገናቺን ኣሜን

  • @dyd5174

    @dyd5174

    4 жыл бұрын

    አሜን አሜን አሜን

  • @kokobbkokob497

    @kokobbkokob497

    4 жыл бұрын

    Amen Amen Amen

  • @atalelechhailu3166
    @atalelechhailu31664 жыл бұрын

    Amen Amen Amen Bereketachehu Yedereben

  • @user-ut6fi2cf6n
    @user-ut6fi2cf6n3 жыл бұрын

    አሜን አሜን አሜን በረከታቸዉ ይደርብን

  • @user-dr5xe1il2o
    @user-dr5xe1il2o3 жыл бұрын

    እግዚአብሔር ስራው ድንቅ ነው እኛንም በእምመታችን ያፅናን በረከታቸውን ያሳድርብን🙏🙏🙏🙏🙏

  • @user-ur3yx7hk6q
    @user-ur3yx7hk6q6 жыл бұрын

    እህት ወድሞቼ እዲህ የቅድሣን ህይወት እንማርበት ዘንድ በዚህ መልከ አዘጋጅታችዉ ሠላቀረባቹ አመሠግናለዉ አምላክ ያገልግሎት ዘመናቹዉን ያርዝመዉ በቤቱ ያፅናቹ እኛም 3060100እድናፈራ የቅዱሣኑን እህይወት እንጀምር ዘንድ አምላክ ይርዳን በፀሎታቹዉ አሥቡኝ ወለተ ሠንበት ነኝ

  • @yekidusantarik

    @yekidusantarik

    6 жыл бұрын

    አሜን

  • @destadesta4885

    @destadesta4885

    6 жыл бұрын

    Amen amen amen

  • @sadagirma8833

    @sadagirma8833

    6 жыл бұрын

    አሜን አሜን አሜን

  • @sosnamaharena6162

    @sosnamaharena6162

    5 жыл бұрын

    +Desta Desta p

  • @Newaccount-sr3wh

    @Newaccount-sr3wh

    5 жыл бұрын

    ስለማይነገር ስጦታህ እግዜ አብሄር ይመስገን የሰማእታት በርከት በሁላችን ላይ ይደር አሜን አሜን አሜን

  • @user-qh5xs4kn6g14
    @user-qh5xs4kn6g14 Жыл бұрын

    በረከታችው ይደርብን ሌኔ ሃጥያተኛው ወለተ ኪሮስ ብላቹ በፀሎት ኣስቡኝ የድንግል ማርያም ልጆች

  • @libneshtirulo8753
    @libneshtirulo87535 жыл бұрын

    Amen amen amen barkatachu yerdan

  • @user-cw4yu5gj4k
    @user-cw4yu5gj4k3 жыл бұрын

    በናተ ፆሎት እኔን ሀጢተኛዋን ልጃችሁን ይማረኝ

  • @user-tj2yz2ru4v
    @user-tj2yz2ru4v6 жыл бұрын

    Amennn Egziabher ymesgen mn ysanewal

  • @zena4992
    @zena499222 күн бұрын

    አቤቱጌታ ሆይ ከእናታችን ከቀድስት ዮስቲና ካባታችን ቆጽርያኖስ አባታችን በረከት እረዴት አካፍለን በዘመናች ከሚአሳድደን እሳት አውጣን

  • @mnnj6080
    @mnnj60806 жыл бұрын

    ሁሉን ቻይ ለሆነው ለህያው እግዚአብሄር ክብርና ምስጋና ይሁን አሜን አምላክ ሆይ ማረን ይቅርበለን አሜን

  • @messymessy8882

    @messymessy8882

    5 жыл бұрын

    ሰለሁሉም ነገር እግዜአብሔር ይመስገን አሜን

  • @nigmanigma2760
    @nigmanigma27605 жыл бұрын

    ቃለ ህይወትን ያስማልን ያስማነ አሜን አሜን አሜን ኤርቶዶክስ ለዘላለም ነው እምነት ፁኑ ነች

  • @user-cw4yu5gj4k
    @user-cw4yu5gj4k3 жыл бұрын

    እግዚአብሔር ሆይ የተዋሕዶ እምነት ተከታይ እድሆን ስለመርጥኸኝ ክብር ምሥጋና ላተ ይሁን

  • @AsahaduChannel
    @AsahaduChannel6 жыл бұрын

    TEWAHIDO LEZELALEM TINURE

  • @yordiberhe6496
    @yordiberhe64966 жыл бұрын

    amen amen amen qal hewet yasemaln

  • @user-fu8sw2nl9x
    @user-fu8sw2nl9x5 жыл бұрын

    ኣሜንንን የቅዱሳን ጾሎት ና በረከት ከኛ ጋ ይሁንን

  • @user-kr4ge5gk5s
    @user-kr4ge5gk5s6 жыл бұрын

    አሜን አሜን አሜን ቃለ ህወት ያሰማልን። ኦርተዶክስ ለዘላለም ትኑር ክብር ለድንግል ማርያም ልጂ ለየሱስ ክርስቶስ ይሁን አሜን ፫

  • @bezyeentwlijibezyeentwlij2177
    @bezyeentwlijibezyeentwlij21775 жыл бұрын

    Amen Amen Amen kale hiyot yasemalin Amen ye kudist baraket yedarbin Amen

  • @user-td9tb8zl7j
    @user-td9tb8zl7j5 жыл бұрын

    እግዛብሄር አያል ነው ስሙ ዛሬም ነገም ዞትርም ይክበር ይመስገን አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን

  • @ebabu8698
    @ebabu86985 жыл бұрын

    እግዚአብሔር በምነት አፅናን እግዚአብሔር ስምህ ለዘላለም የተመስገነ ይሁን አሜንንንን

  • @user-ri1qh5zn2g
    @user-ri1qh5zn2g2 жыл бұрын

    አሜን አሜን አሜን ቃል ህይወት ያሰማልን በእውነት አቤቱ የድንግል ማርያም ልጅ እየሱስ ክርስቶስ ፍቅር ያሸንፈኝ ልቦናዬን ክፈትልኝ

  • @umeshraee9152
    @umeshraee91526 жыл бұрын

    እግዚአብሄር አምላክ እስከመጨረሻ እንድንጸና ቅዱስ ፍቃዱ ይሁንልን ቃለ ሂወት ያሰማልን አሜን አሜን አሜን

  • @user-ip4uw9jm3x
    @user-ip4uw9jm3x6 жыл бұрын

    አሜን አሜን አሜን ቃለ ህይወት ያሠማልን

  • @sara-sq4fe
    @sara-sq4fe5 жыл бұрын

    አሜን ቃለህይወትን ያሰማልን በድሜ በፀጋ ይጠብቅልን ተዋህዶ ኦርቶዶክስ ለዘላለም ትኑር ያመነ የተጠመቀ ይድናል

  • @Zet2023-fs1tt
    @Zet2023-fs1tt2 ай бұрын

    አሜን ፫ ስለ ቃሉ የቃሉ ባለቤት ልሑል እግዚያብሔር የከበረና የተመሰገነ ይሁን

  • @user-he9um6ty1y
    @user-he9um6ty1y5 жыл бұрын

    አሜን አሜን አሜን በእውነት የህወትን ቃል ያሰማልን እግዚአብሔር አምላክ ጸጋና በርከቱ ያድልልን የቅዱሳን በረከት ረዲኤታቸው ምልጃ ጸሎታቸው አይለየን አሜን ፫ በዚህ ፊልም የተሳተፋቹ ሁሉ እግዚአብሔር በቤቱ ያጽናቹ

  • @user-qj7hv4cw6r
    @user-qj7hv4cw6r6 жыл бұрын

    እግዚአብሔር ምን ይሳነዋል ውደ የኔ እኔም የሱ! የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ልጅ ክርስቲያን በመሆኔ እጅግ ደስስስስስስስስስስ ይለኛል! ውበትም ሀሰት ነው ደም ግባትም ከንቱ እግዚአብሔርን የምትፈራ ሴት ግን እርሷ ትመሰገናለች! “ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ፣ የእግዚአብሔርም ልጅ እንደ ሆነ ታምኑ ዘንድ፣ አምናችሁም በስሙ ሕይወት እንዲኖራችሁ ይህ ተጽፎአል”። (ዮሐ. 20:31) በእውነት ይህን መንፈሳዊ ህይወትን የሚያድስ አዘጋጅታችሁ ስላቀረባችሁልን እግዚአብሔር አምላክ ያገልግሎት ዘመናችሁን ያርዝምልን!!!!!! ከቅዱሳኑ በረከት ረድኤት አማላጅነት አይለዬን!

  • @baha6976

    @baha6976

    5 жыл бұрын

    Amen amen amen

  • @awettesfu5266

    @awettesfu5266

    4 жыл бұрын

    Tsbuk

  • @fatimamhmdhhjuio3789

    @fatimamhmdhhjuio3789

    4 жыл бұрын

    AMEEN AMEEN AMEEN yaa Goofataa Galanii sii haa Ta'uu!!!!

  • @user-vw4xe6fb9z
    @user-vw4xe6fb9z6 жыл бұрын

    አሜን ቃለህይወትን ያሰማልን

  • @kokalama1004
    @kokalama1004Ай бұрын

    አሜን ተመስገን ይህን ላደረገ ልኡል እግዚአብሔር ይክበር ይመስገን የሁላችንንም ታሪክ ይቀይርልን በዝች በቀናች ሀይማኖት ያፅናን

  • @mlashugmedhin4983
    @mlashugmedhin49835 жыл бұрын

    የቅዱሳኑ በረከት ረድኤት ይደርብን

  • @user-um4xs2vr6o
    @user-um4xs2vr6o6 жыл бұрын

    አሜን የቅዱሳኑ በረከታቸው ይደርብን እኛንም በቤቱ አጽናን

  • @christianmsgana2580
    @christianmsgana25806 жыл бұрын

    የቅዱሳንን እናቶች የቅዱሳን አባቶች በረከት ይደርብን ምልጃቸዉ አይለየን አሜን

  • @bizaumolosaber40

    @bizaumolosaber40

    6 жыл бұрын

    አሜን በረከታቸው ይደርብን

  • @yayshmazengya7812

    @yayshmazengya7812

    6 жыл бұрын

    Kaliheyiwe Yasemaling Bekalu Lemilewite Yabekani Yekidusanu Berikite Yiderebine

  • @user-cu2ik1cy5d

    @user-cu2ik1cy5d

    5 жыл бұрын

    Amen amen amen bereketachew yederben

  • @sraayele840

    @sraayele840

    4 жыл бұрын

    እግዚአብኤር ታላቅ ነሁ ክብር ለእግዚአብኤር

  • @user-mu3zy5kw8t

    @user-mu3zy5kw8t

    3 жыл бұрын

    የቅዱሳን በረከት ምልጃና ፀሎታችሁ ከሕዝብ ክርስቲያን ጋር ይሁን አሜን፫

  • @BK-rw6pt
    @BK-rw6pt9 ай бұрын

    የእመቤታች የቅዳሜ ቅዳሴ ትርጓሜ ላይ ሰሟ ሰምቼ ታሪኳን ለመስማት ጓግቼ አየዋት ጠንካሬ የእምነት ሴት❤

  • @kibrealemye8319
    @kibrealemye83196 жыл бұрын

    ኦርቶደክስ ሀይማኖት ለዘላለም ትኖራለች እህት ወድሞች ያግልግሎታችሁን እግዚያብሄር ይባርክላችሁ ቅዱሳኑች በቸርነትና በምህርታቸው ይጠብቁን አሜን ወደር የሌለው ደስታይሰማኛል ፊልሞን ሳይ

  • @user-yz6cf7vv2w
    @user-yz6cf7vv2w6 жыл бұрын

    አሜን ቃለ ህይወት ያሰማልን የቅዱሳን በረከታቸዉ ይደርብን

  • @ilovemyfamilyft5747

    @ilovemyfamilyft5747

    6 жыл бұрын

    ፍቅር ይታገሳል جرين هواس amean

  • @frecll9925
    @frecll99256 жыл бұрын

    አሜን በረከታችሁ ይደርብን አይለየን ያገልግሎት ዘመናችሁን ያርዝምልን::

  • @GGg-zh1ku

    @GGg-zh1ku

    5 жыл бұрын

    አሜን፫

  • @weynhagerannafaki7263
    @weynhagerannafaki726310 ай бұрын

    የቅዱሳን በረከት ለኛም ይሁንልን ትክክለኛዉን መንገድ ይምራን በቤቱ ያጽናን አሜን አሜን አሜን ጌታዬና አምላኬ ሆይ አመሰግንሀለኩ

  • @belihunmalede9132
    @belihunmalede91326 жыл бұрын

    አሜን ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ርድኤት በረከት ያካፍለን የቅዱሳንን በረከት ያከፍለን ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ለዘላለም ትኑር !!!

  • @user-og9bp5zp4r
    @user-og9bp5zp4r6 жыл бұрын

    አሜን (3)በረከታቸው ይድረሰን

  • @tizitaderes9126
    @tizitaderes91266 жыл бұрын

    አሜን አሜን አሜን ቃለህይወትን ያሰማልን በርቱልን በእውነት እስከዛሬ ባለማወቄ ከመፈሳዊ ውጭ ድራማና ፊልም ሳይ ቆይቻለው በደዚህ አይነት መንፈሳዊ በመጀመሩ በጣም ደስብሎኛል አመሰግናለው

  • @user-lo8jn3gi3u

    @user-lo8jn3gi3u

    6 жыл бұрын

    ቃለህይወት ያሠማልን በረከታቸው ይደርብን

  • @user-lo8jn3gi3u

    @user-lo8jn3gi3u

    6 жыл бұрын

    ተዋህዶ እቁ ነሽ

  • @hidatwelday2212

    @hidatwelday2212

    5 жыл бұрын

    🙏💒🙏💒🙏💒🙏💒🙏💒🙏💒🙏💒😢💒😢💒😢😢💒😢💒😢💒😢👏💖👏💙👏❤👏💚👏💛👏💜👏

  • @user-hc6fz2jr8m

    @user-hc6fz2jr8m

    5 жыл бұрын

    Tizita Deres እግዚአብሔር ይመሰግን

  • @user-ii8lx8tp1v

    @user-ii8lx8tp1v

    5 жыл бұрын

    @Hiruty KuwaitAmen .

Келесі