የግብፃዊቷ ቅድስት ማርያምና የአባ ዞሲማ ታሪክ / St Mary The Egyptian & Aba Zosima - ሙሉ ታሪክ

Ойын-сауық

† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን †
† ሚያዝያ 6 ስንክሳር †
† ቅድስት ማርያም ግብፃዊት †
= ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በዚህች ዕለት እነዚህን ታላላቅ ቅዱሳን ታስባለች:-
በዚች ቀን በበረሀ የምትኖር ግብፃዊት ማርያም አረፈች። ይቺም ቅድስት ከእስክንድርያ አገር ሁና ወላጆቿ ክርስቲያን ናቸው። እድሜዋ አስራ ሁለት አመት በሆናት ጊዜ የመልካም ስራና የሰው ሁሉ ጠላት ሸንግሎ አሳታት በእርሷም የማይቆጠሩ የብዙዎችን ነፍስ አጠመደ እርሱ ሰይጣን ስለ ዝሙት ፍቅር ያለ ዋጋ ስጋዋን እስከ መስጠት አድርሷታልና ።
በዚህም በረከሰ ስራ ውስጥ ኖረች በየእለቱም የኃጢአት ፍቅር በላይዋ ይጨመርባት ነበር። ሰውን የሚወድ የእግዚአብሄርም ቸርነት ወደ ክብር ባለቤት ወደ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መቃብር ሊባረኩ ወደ ኢየሩሳሌም ለመሄድ የሚሹ ሰዎችን ገለጠላት።
ከእሳቸውም ጋራ ትሄድ ዘንድ ልቧ ተነሳሳ ከብዙ ሰዎችም ጋራ በመርከብ ተሳፈረች። ባለ መርከቦችም የመርከብ ዋጋ በጠየቋት ጊዜ ስለ መርከብ ዋጋ ያመነዝሩባት ዘንድ ሰውነቷን ሰጠቻቸው ኢየሩሳሌምም እስከ ደረሰች ይህን ስራ አልተወችም።
የክብረ ባለቤት በሆነ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መቃብር ወደ አለች ቤተ ክርስቲያን ትገባ ዘንድ በወደደች ጊዜ መለኮታዊት ኃይል መግባትን ከለከለቻት። እርሷም ከሚገቡ ሰዎች ጋራ ትገባ ዘንድ ብዙ ጊዜ ደከመች ነገር ግን ከለከላት እንጂ የጌታ ኃይል አልተዋትም።
ከዚህም በኃላ ስለ ረከሰ ስራዋ አሰበች በልቧም እያዘነችና እየተከዘች ወደ ሰማይ ወደ እግዚአብሄር አይኖቿን አቀናች በማንጋጠጥዋም ውስጥ አምላክን የወለደች የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያምን ስእል አየች።
በፊቷም አለቀሰች ፍጥረቶችን ሁሉ የምትረጅአቸው አምላክን የወለደሽ እመቤቴ ተዋሽኝ ከሁሉ ሰዎች ጋራ ገብቼ የመጣሁበትን ስራዬን የፈፀምኩ እንደሆነ ያዘዝሽኝን ሁሉ እኔ አደርጋለሁ ብላ በማመን ለመነቻት።
ቤተ ክርስቲያን ፈጥና ገባች በገባችም ጊዜ የበአሉን ስራ ፈፀመች። ከዚህም በኃላ አምላክን ወደ ወለደች ወደ እመቤታችን ወደ ከበረች ድንግል ማርያም ስእል ተመልሳ ወደ እርሷ መሪር ልቅሶ እያለቀሰች ረጅም ፀሎትን ፀለየች ነፍሰዋን ለማዳን እርስዋ ወደ ወደደችው ትመራት ዘንድ አምላክን ከወለደች ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ስእል ከዮርዳኖስ በረሀ ብትገቢ አንቺ እረፍትንና ድኀነትን ታገኚ አለሽ የሚል ቃል ወጣ።
ከእመቤታችን አምላክን ከወለደች ከቅድስት ድንግል ማርያም ስእል ይህን ቃል ተቀብላ ወድያውኑ ወጣች። በውጪም አንድ ሰው አግኝታ ሁለት ግርሽ ሰጣትና አምባሻ ገዛችሸት።
ከዚያም በኃላ የዮርዳኖስን ወንዝ ተሻግራ ፅኑእ ተጋድሎ እየተጋደለች በበረሀው ውስጥ አርባ ሰባት አመት ኖረች ሰይጣንም አስቀድማ በነበረችበት በዝሙት ጦር ይዋጋት ነበር።
እርሷ ግን በተጋድሎ ፀናች ከዚያም ከገዛችው አምባሻ ብዙ ቀን ተመገበች። ሁለት ሁለት ቀን ሶስት ሶስት ቀን ፁማ ከዚያ አምባሻ ጥቂት ትቀምስ ነበር በአለቀም ጊዜ የዱር ሳር ተመገበች።
በዚያችም በዮርዳኖስ በረሀ እየተዘዋወረች አርባ አባት አመት ሲፈፀምላት እንደ ገዳሙ ልማድ የከበረች አርባ ፆምን ሊፈፅም ቅዱስ ዘሲማስ ወደዚያች በረሀ መጣ። በሱ ደብር ላሉ መነኲሳት ልማዳቸው ስለሆነ በየአመቱ ወደ በረሀ ወጥተው የከበረች የአርባ ቀን ፆም እስከ ምትፈፀም በፆምና በፀሎት ተፀምደው በገድል ይቆያሉ ።
ስለዚህም ዘሲማስ ወደ ዮርዳኖስ በረሀ በወጣ ጊዜ የሚፅናናበትን ያሳየው ዘንድ እግዚአብሄርን ለመነው። በበረሀውም ውስጥ ሲዘዋወር ይቺን ቅድስት ሴት ከሩቅ አያት የሰይጣን ምትሀት መሰለችው በፀለየም ጊዜ ከሰው ወገን እንደሆነች ተገለጠለችለት።
ወደርሷም ሄደ እርሷ ግን ከእርሱ ሸሸች ወደርሷም ይደርስ ዘንድ ከኃላዋ በመሮጥ ተከተሉት። ከዚህም በኃላ ዘሲማስ ሆይ ከእኔ ጋራ መነጋገር ከፈለግህ ጨርቅን በምድር ላይ ጣልልኝ እከለልበት ዘንድ ብላ በስሙ ጠራችው።
በስሙ በጠራችውም ጊዜ እጅግ አድንቆ ጨርቁን ጣለላት ያን ጊዜም ለብሳ ሰገደችለት እርሱም ሰገደላት እርስበርሳቸውም ሰላምታ ተሰጣጥተው በላዩዋ ይፀልይላት ዘንድ ለመነችው እርሱ ካህን ነውና ካህን ሰለሆነ።
ከዚህም በኃላ ገድሏን ታስረዳው ዘንድ ቅዱስ ዘሲማስ ለመናት ከእርሷ የሆነውን ሁሉ ከመጀመሪያው እስከመጨረሻው ነገረቸው። እርሷም በሚመጣው አመት የክብር ባለቤት የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ስጋውንና ደሙን ከእርሱ ጋራ ያመጣላት ዘንድ ለመነችው እርሱም እሺ አላት።
አመትም በሆነ ጊዜ ስጋውንና ደሙን በፅዋ ውስጥ ያዘ ደግሞ በለስ ተምርንና በውኃ የራሰ ምስርን ይዞ ወደርሷ ወደ ዮርዳኖስ በረሀ መጣ ቅድስት ማርያምን በዮርዳኖስ ወንዝ ዳር ስትሄድ አያት ወደርሱም ደርሳ እርስበርሳቸው ሰላምታ ተሰጣጡ በአንድነትም ፀለዩ ከዚህም በኃላ ስጋውንና ደሙን አቀበላት።
በለሱን ተምሩንና ምስሩንም አቀረበላትና ትመገብለት ዘንድ ለመናት ስለ በረከት ከምስሩ በእጇ ጥቂት ወሰደች። ደግሞም በሁለተኛው አመት ወደእርሷ ይመለስ ዘንድ ለመነችው ።ሁለተኛ አመትም በሆነ ጊዜ ወደዚያ ወደ ዮርዳኖስ በረሀ መጣ ያቺ ቅድስት ሴት ሙታ አገኛት በራስጌዋም ድኀዪቱን ግብፃዊት ማርያምን ከተፈጠረችበት አፈር ውስጥ ቅበራት የሚል ፅሁፍ አገኘ።ከፅሁፉ ቃልም የተነሳ አደነቀ።
ያን ጊዜም ከግርጌዋ አንበሳን ሲጠብቃት አየ እርሱ መቃብርዋን በምን እቆፍራለሁ ብሎ ያስብ ነበር በዚያም ጊዜ ያ አንበሳ በጥፍሮቹ ምድሩን ቆፈረ የከበረ ዘሲማስም በላይዋ ፀሎት አድርጎ ቀበራት ።
ወደ ገዳሙም ተመልሶ ለመነኮሳቱ የዚችን የከበረች ግብፃዊት ማርያምን ገድሏን እንዳስረዳችው ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ ነገራቸው እጅግም አደነቁ ምስጉን ልኡል እግዚአብሄርንም አመስገኑት። መላው እድሜዋም ሰማንያ አምስት ሆኗታል።
የእናታችን በረከት በሁላችን ላይ ይሁን አሜን፡፡

Пікірлер: 289

  • @user-ub4oh9id3z
    @user-ub4oh9id3z3 жыл бұрын

    የግብፃዊቷ ቅድስት ማሪያም በረከቷ ይደርብን የአባ ዞሲማ ረዴት በረከታቸው ይደርብን አሜን🙏

  • @addaagsa6706

    @addaagsa6706

    2 жыл бұрын

    አሜን አሜን አሜን በእዉነት

  • @hgtu

    @hgtu

    Жыл бұрын

    አሜን አሜን አሜን🙏

  • @aboaomr5163

    @aboaomr5163

    4 күн бұрын

    አሜን

  • @SofiaJemal-rk1sf
    @SofiaJemal-rk1sfАй бұрын

    የግብፃዊቷ ማርያም እና የአባ ዞሲማስ በረከት ይደርብን አሜን

  • @aboaomr5163

    @aboaomr5163

    4 күн бұрын

    አሜን

  • @Ggg-vs1iy
    @Ggg-vs1iy19 күн бұрын

    የግብፃዊቷ የቅድስት ማርያም ና የአባ ዞሲማ ረደት በረከት ምልጂና ፀሎት አይለየን አሜን አሜን አሜን💚💚💚💚💛💛💛💛❤❤❤❤👏🙏👏😢😢😢😢😢😢😢😢😢

  • @user-wk2jw5bi6v
    @user-wk2jw5bi6v3 ай бұрын

    የእናታችን ቅድስት ማርያም ግብጻዊት እዲሁም የሌሎቹ የሁሉም ቅዱሳን በረከታቸዉ ይደርብን በጸሎታችን ይማረን❤

  • @YordanosF
    @YordanosF3 жыл бұрын

    እናቴ ቅድስት ማርያም ግብፃዊት ያንቺን ፅናትንና የልብ መሰበር ለልጅሽ እንዲያድለኝ በፀሎትሽ አስቢኝ አባ ዞሲማ በረከትዎ በልጅዎት ላይ ይደርብኝ!

  • @user-sd6nh3ri2n

    @user-sd6nh3ri2n

    2 жыл бұрын

    አሜን አሜን አሜን ለንስሀ ሞት ያብቃን

  • @user-jp1mi1ik6y

    @user-jp1mi1ik6y

    2 жыл бұрын

    አሜን አሜን አሜን

  • @imdove7849YouTube

    @imdove7849YouTube

    2 ай бұрын

    Amen Amen Amen

  • @aboaomr5163

    @aboaomr5163

    4 күн бұрын

    አሜን

  • @hairo3250
    @hairo3250 Жыл бұрын

    የአባታችን እና የግብፃዊቷ ማርያም በረከታቸው ጸሎታቸው ይድረሰን 🙏🙏🙏

  • @aboaomr5163

    @aboaomr5163

    4 күн бұрын

    አሜን

  • @FhFv-bn5ui
    @FhFv-bn5ui4 ай бұрын

    የአባታችን ቅዱስ ዞሢማ እና የቅድሥት ማርያም በረከታቸው ይደርብን የኛንም ፍጻሜአችንን ያሣምርልን አሜን

  • @user-ns9hh5uc4u

    @user-ns9hh5uc4u

    4 ай бұрын

    አሜን፫

  • @meticar4025
    @meticar40256 ай бұрын

    የድንግል ማርያም የአስራት ልጆች ወዴት ናችሁ አቤት ይሄኔ ዓለማዊ ቢሆን 😢😢😢😢😢😢 እግዚአብሔር አምላክ ልቦና ያድለን ለሁላችንም ማስተዋሉን ይስጠን አሜን፫ 🙇‍♀️🙇‍♀️🙇‍♀️🙏🌹🌹

  • @user-cc8dx3ti7z

    @user-cc8dx3ti7z

    4 ай бұрын

    አሜን አሜን አሜን😢🙏

  • @sablaayele8859
    @sablaayele88593 жыл бұрын

    አሪፈ ትመህረተ ነው የእግዚብሔረ ቤተስቦች እባካቺሁ ግቡና ትማሩ

  • @belinshmohg4688

    @belinshmohg4688

    3 жыл бұрын

    አወአሪፍነውማሬዋ💒💒🇪🇹🇪🇹🙏🙏🙏

  • @habshyalhabshy8495

    @habshyalhabshy8495

    3 жыл бұрын

    አሜንአሜንአሜ

  • @firiyotfiritawaahidoo3921

    @firiyotfiritawaahidoo3921

    Жыл бұрын

    Hunet new Betam tiliq Timirtnew igzehiber yimasgen

  • @user-hg9yp5ud3p

    @user-hg9yp5ud3p

    6 ай бұрын

    ኣሜንኣሜንኣሜን❤❤❤

  • @endashawchaka9847

    @endashawchaka9847

    3 ай бұрын

    እውነት ነው የቅዱሳኑ በረከት ይድረሰን 🤲🤲🤲

  • @user-qp1np2um9t
    @user-qp1np2um9t3 ай бұрын

    የግብፃዊቷ ማርያም እና የኣባ ዞሲማ በረከት ከሁላችን ይሁን አሜን ፫😢

  • @user-nl4lb8sw2f
    @user-nl4lb8sw2f11 ай бұрын

    ኣሜን ፆሎታቸው ወበረከታቸው ይደረብን❤❤❤ ተመስገን ጌታሆይ ቃለ ህይወት ያሰማን ተመስገን ኣምላኬ❤❤❤

  • @user-di7kl8we6f
    @user-di7kl8we6fАй бұрын

    🤲🤲🤲😭የግብፀዊቷ የቅድስት ማርያም እዲሁም የሁሉም በረከታቸሁ እደሪብን❤❤❤❤❤🤲🤲🤲🤲🤲

  • @elroitube27
    @elroitube27Ай бұрын

    ዛሬ የዕረፍት መታሰቢያ ባዕልዋ ነው የአባ ዞሲማስ እና የቅድስት ማርያም ግብፃዊት በረከታቸው ይደርብን

  • @kokab597
    @kokab5975 ай бұрын

    የእወነት እግዚአብሔር የሁለቱን ቅዱሣን በረከት ያሳድርብን አሜን ❤❤❤❤❤❤❤

  • @tesman2627
    @tesman262718 күн бұрын

    አሜን አሜን አሜን የቅድስት ማርያምና የአባ ዞሲማ በረከታቸው ይደርብን

  • @eyosigoitom213
    @eyosigoitom2132 жыл бұрын

    ለእግዚአብሔር የሚሳነው የለም 🙌🏽❤️። በረከታቸው ይደርብን❤️🙌🏽❤️

  • @fatmaman2519
    @fatmaman2519Ай бұрын

    አሜን አሜን አሜን የቅዱሷኖቹ በረከት ከሁላችንም ጋር አይለየን አሜን🙏🙏🙏🙏

  • @user-rq9fx7qh5z
    @user-rq9fx7qh5z3 жыл бұрын

    አሜን አሜን አሜን የአባታችን የአባ ዞሲማ እና የእናታችን ግብጻዊቷ ቅድስ ማሪያም በረከታቸው ይደርብን ጌታ ሆይ አቤቱ ወደኔ ወደ ኃጢአተኛዋ ልጅህ ተመልከት 😢😢😭😭😭

  • @user-xs2qq5ql4z
    @user-xs2qq5ql4zАй бұрын

    አሜን 🙏 አሜን 🙏 አሜን 🙏 እናቴ ድንግል ማርያም እናቴ የጌታይ እናት የእኛም እናት ሁሌም ተመስገን እናትቴ ማርያም ማረን ይቅር በይን እናቴ ይቅርታ እናቴ ማረን አመላኬ ሆይ እኛንም አስብን አመላኬ ሆይ ማረን አባቴ አሜን 🙏❤🤲🤲🤲❤🙏

  • @hananhp4217
    @hananhp42177 ай бұрын

    የናታችን ግብፃዊቷ ቅድስት ማርያምና ያባታችን የአባ ዞሲማ በረከታችሁ እረድኤታችሁ አማላጅነታችሁ ይደርብን👏👏👏

  • @hanakukuhana4575
    @hanakukuhana4575Күн бұрын

    አሜን የቅዱሳኑ በረከት ምልጃ አይለየን 🙏🙏🙏✝️❤✝️❤✝️❤

  • @comcell3831
    @comcell3831Ай бұрын

    የግብጻዊቷ የቅድስት ማርያም በረከቷ ይደርብን የሁሉም ቅዱሳን በረከታቸው ይደርብን አቤቱ ጌታ ሆይ ለንሰሐ አብቃኝ😢😢😢

  • @aboaomr5163

    @aboaomr5163

    4 күн бұрын

    አሜንአሜንአሜን😢

  • @user-sd6nh3ri2n
    @user-sd6nh3ri2n2 жыл бұрын

    አሜን አሜን አሜን ቃለ ህይወት ያሰማልን የአባታችን ዞሲማና የቅድስት ማርያም በረከታቸው ይደርብን🙏 ለእኛም እንደ እናታችን ቅድስት ማርያም ለንስሐ ሞት ያብቃን😭😭😭😭

  • @aboaomr5163

    @aboaomr5163

    4 күн бұрын

    አሜን😢

  • @tigist19
    @tigist193 жыл бұрын

    በረከቱ ይደረብን 🙏💜 አትጥፉብን ቶሎቶሎ ልቀቁልን 🙏💜

  • @meticar4025
    @meticar40256 ай бұрын

    አሜን፫ ቃለህወትን ቃለበረከትን ያሰማልን 🙏🙏 ጸሎት ልመናቸው በሁሉም ህዝበ ክርስቲያን ላይ ይደርብን አሜን፫ 🙇‍♀️🙇‍♀️🙇‍♀️🙏🌹🌹 😢

  • @user-sw3ou7nu7t
    @user-sw3ou7nu7t2 ай бұрын

    የእናታችን ማራም ግብፄውይ ረዴቷ በረከቷ ይደርብን አሜን አሜን አሜን❤❤❤❤

  • @nodthil6934
    @nodthil6934Ай бұрын

    የቅዱሣን እናቶቻችን አባቶቻችን ረድኤት በረከት አይለየን

  • @AsterabebeAwek
    @AsterabebeAwek17 күн бұрын

    የቅዱሳን በርከታቸው ይደርብን ፆለታቸው አይለየን

  • @hulukasu5356
    @hulukasu53564 ай бұрын

    አሜን በእውነት ረዴቴ በረከትቸው የደርበን በፀሎታቸው የማሪን ❤❤❤🙏🤲🤲🥰🥰

  • @user-to9gr4vq2e
    @user-to9gr4vq2e4 ай бұрын

    የቅዱሳን በረከት እረዴት ይደርብንአሜን

  • @Rozi199
    @Rozi19910 ай бұрын

    ግብጻውይቷ ቅድስት ማርያም በረከቷ ይደርብን

  • @asteryosef6196
    @asteryosef61962 жыл бұрын

    የግብፃዊቷ ቅድስት ማርያም በረከቷ አይለየን አሜን የአባ ዞሲማ በረከታቸው አይለየን አሜን አሜን አሜን

  • @afomiatube41
    @afomiatube4127 күн бұрын

    የቅድስት ማርያም በረከቷ ይደርብን❤❤❤❤

  • @tube-hk8nt
    @tube-hk8nt8 ай бұрын

    ሰላም ለቅድስት ቤተክርስቲያን ሰላም ለሀገራችን ኢትዮጵያ ሰላም ለአለም አቤት ምንኛ መታደል የአባ ዘሲማና የግብፃዊቷ ማርያም በረከታቸውን በሁላችን ላይ ይደር😢

  • @Zagoy7952
    @Zagoy79523 жыл бұрын

    አሜን አሜን አሜን ቃለ ህይወትን ያስማልን በእድሜ በፀጋ ይጠብቅልን የቅዱሳን ምልጃና ፀሎት አይለየን አሜን፫

  • @netsanetsoimon8355
    @netsanetsoimon83553 жыл бұрын

    እግዚአብሄር ይመስገን ቃለ ህይወት ያሰማልን አሜን አሜን አሜን

  • @user-zq3nc4ny6k
    @user-zq3nc4ny6k3 жыл бұрын

    አሜን አሜን አሜን በረከታቸው ይደርብን

  • @Hameremedia21
    @Hameremedia21Ай бұрын

    ቃለ ሕይወት ያሰማልኝ በረከቷ ይደርብን

  • @user-md6bi9be8n
    @user-md6bi9be8nАй бұрын

    አሜን የቅዱሳኑ በረከት ይደርብን አሜን አሜን አሜን!!!

  • @fairoozfairooz3607
    @fairoozfairooz36072 жыл бұрын

    አሜን አሜን አሜን የቅድስት ግብፃዊት እና የቅዱስ ዞስማስ በረከታች ፀሎታች በኛ ለይ ፀንቶ ይኑር ለይኩን ለይኩን ለይኩን

  • @yewonkeshtukidusgebralante8990
    @yewonkeshtukidusgebralante89903 жыл бұрын

    የእናታችነ የቅድስት ማርያም በረከቷ ፅናቷን የአባ ዞሲማ በረከታቸዉ ፀሎታቸዉ ይደርብን የቅዱሳን አምላክ ሆይ እኔን ሀጥያተኛዋን ከበደሌ አንፃኝ

  • @user-vu6tx2rx6y
    @user-vu6tx2rx6y2 ай бұрын

    በረክታቸው ይደርብን

  • @TigistTariku-qo6in
    @TigistTariku-qo6in2 ай бұрын

    አሜን አሜን አሜን የቅዱሳኑ ረድኤት በረከታቸው ይደርብን ስለነሱ ብሎ ይታለቀን አምላከ ቅዱሳን ይለመነን ከስተታችን የምንመለስበት እድሜ ለንሰሀ ይስጠን

  • @brinebekle5939
    @brinebekle5939Ай бұрын

    የግብፃዊቷ ማሪያም በርከት ይደርብን

  • @flamedino15
    @flamedino153 жыл бұрын

    አሜን አሜን አሜን የቅዱሳን አባቶቻችን እናቶቻችን በረከታሽው ይደርብን ቃል ህይወት ያስማልን። በዕድሜ በጤና በፀጋው ይጠብቃችሁ። አሜን አሜን ይቆየን

  • @tewabechbelay1655

    @tewabechbelay1655

    2 жыл бұрын

    በረከታቸው ይደርብን የአባቶቻችን አሜን

  • @3sgroup460

    @3sgroup460

    2 жыл бұрын

    ቃለህወትን ያስማልን የቅዱሳኑ በርከታችው ይደርብን አሜን አሜን አሜን አሜን

  • @asterabate7743
    @asterabate7743 Жыл бұрын

    የግባፃዊቷ ቅድስት ማርያም በረከት ረደኤቷ አይለየን እኛንም ለንሰሀ ሞት ያብቃን የአባ ዞሲማስ ቡራኬዎት አማላጅነታቸዉ አይለየን

  • @sarakonjo2971
    @sarakonjo29712 ай бұрын

    የቅዱሳኑ በረከት ይደርብን አሜን

  • @user-li3yy3vy7h
    @user-li3yy3vy7h3 жыл бұрын

    _አሜን አሜን አሜን ይሁን ይደረግልን _የቅዱሳኑ በረከታቸዉ እረድኤታቸዉ ይደርብን_

  • @user-ht7if5fo7p
    @user-ht7if5fo7p2 ай бұрын

    እግዚአብሔር ይስጥልን በጣም ትልቅ ትምህርት ነዉ ለወጣቶች ያገኘንበት ግን እባካችሁ በጣም ብዙ የቅዱሳን ታሪኮች በትግርኛ የተተረጎሙ አሉና እባካችሁ በአማርኛ ተርጉሙልን

  • @user-qq7su4bq1b
    @user-qq7su4bq1b2 жыл бұрын

    በረከታቸው ይደርብን እኛንም ለስጋዉ ወደሙ ያብቃን

  • @user-dr5xe1il2o
    @user-dr5xe1il2o2 жыл бұрын

    አሜን አሜን አሜን ቃለ ህይወት ያሰማልን በረከታቸው ይደርብን አቤቱ ጌታሆይ እኛንም ለንስሀ አብቃን😭😭😭😭

  • @dghthhu3910
    @dghthhu39107 ай бұрын

    አሜን ለኔም ፅናትን ስጠኝ ጌታሆይ በፀሎታቸው ማርኝ😢😢

  • @user-uy8ps5yb2n
    @user-uy8ps5yb2n2 ай бұрын

    አሜን አሜን አሜን በርከታችው ይደርብን

  • @Werik-vz3vu
    @Werik-vz3vu2 ай бұрын

    እግዚአብሔር ይመስገን ስለ እናንተ ቅድስና እንድሰማ ስለረዳን

  • @meseretzike
    @meseretzike2 ай бұрын

    የሁሉ ፈጣሪ ሁሉን ቻይ ቸርና ሩህሩህ አምላክ እባክህ ምህረት አድርግልኝ😢😢😢😢😢😢😢😢😢😢😢😢😢😢😢😢😢😢😢😢😢

  • @aekuattube
    @aekuattube3 жыл бұрын

    ሳየው የሚያስለቅሰኝ ሳነበው የሚያስደነግጠኝ ገድል ነው በረከታቸው ይድረሰን

  • @tinaethio3885
    @tinaethio38854 ай бұрын

    ደጋግሜ ያየሁት የቅዱሳን ታሪክ

  • @user-ph8rl9yn2s
    @user-ph8rl9yn2s2 ай бұрын

    .በረከታቸዉ.የደረበን.ይቅርበለን❤❤❤❤❤❤

  • @fgradesfgrades5092
    @fgradesfgrades50922 ай бұрын

    አሜን አሜን አሜን በረከተቸው ይደርብን😢😢🙏🙏🙏

  • @Sara-dq3rz
    @Sara-dq3rz5 ай бұрын

    የአባቶቻችን እና የቅድስት ግብጽዊቷ ማርያምም ረድኤት በረከታቸው ይደርብን

  • @KrisenetMamo-fg3fm
    @KrisenetMamo-fg3fmАй бұрын

    አሜን በርከታቸዉ የደርብን

  • @tigstkiros-lm1zk
    @tigstkiros-lm1zk8 ай бұрын

    የቅድስት ማርያም በረከታ ይደርብን

  • @misawarku596
    @misawarku5962 жыл бұрын

    አሜን አሜን አሜን በረከታችሁ ይደርብን👏😭

  • @user-mk7up8gr6w
    @user-mk7up8gr6w6 ай бұрын

    አሜን አሜን አሜን የቅዱሳን በረከታቸዉ ይደርብን

  • @GEthio501
    @GEthio5015 ай бұрын

    እግዚአብሔር ይስጥልን የቅዱሳን እናቶቻችን እና አባቶቻችን እረድኤት በረከት ይደርብን ! እሜን ❤️🙏

  • @genitinishuatube6203
    @genitinishuatube62036 ай бұрын

    አቤት መታደል በረከታችሁ ይደርብን አቤቱ እኔንም መልሰኝ ለቅዱስ ቁርባን አብቃኝ ይቅር ባይ አምላክ🙏

  • @brokeragearoundaddisababa9344
    @brokeragearoundaddisababa93442 жыл бұрын

    ስንትዎቻችን የሰው ህይወት ያበላሸነው

  • @naseematariq2142
    @naseematariq21425 ай бұрын

    የአባቶቻችን አምላክ እግዚአበሔር ይመስገን❤

  • @user-ib4mr7wk3w
    @user-ib4mr7wk3w5 ай бұрын

    አሜን አሜን አሜን ቃል ህይወት ያሥማልን በረከታችሁ ይደርብን 🤲🤲🤲🤲🤲😢😢😢😢😢😢😢ለእኛም ለንሣሃ ሞት አብቃን 😭😭😭😢🤲🤲🤲🤲

  • @sjddgkgf8204
    @sjddgkgf82043 жыл бұрын

    አሜን አሜን አሜን

  • @user-cc4kc2uk4u
    @user-cc4kc2uk4u5 ай бұрын

    የቅዱሳን በረከታቸው ይደርብን🙏

  • @natimintesnot8065
    @natimintesnot80652 жыл бұрын

    አሜን! በረከታቸው ይደርብን! የእናታችን ቅድስት ግብፃዊት ማርያምን የንስሐ ፍሬ እንድናፈራ አምላክ ሁላችንንም ይርዳን!

  • @raheel368
    @raheel3683 жыл бұрын

    Amen የአባቶችህ አማልክ ሁልቺም የታብቃቹ ⛪️🤲😢

  • @yashiyashi1504
    @yashiyashi15042 ай бұрын

    አሜን አሜን አሜን ቃለሕይወትን ያሰማልን

  • @user-te3vx9mr9m
    @user-te3vx9mr9m3 жыл бұрын

    አሜን አሜን አሜን በረከታቸው ይድረሰን አሜን

  • @betibeti72

    @betibeti72

    2 жыл бұрын

    አሜን አሜን አሜን በረከታቸው ይድረሰን አሜን 🙏🙏🙏🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰

  • @Selam-rd6qv
    @Selam-rd6qv22 күн бұрын

    Amen bereketachew yiderbn

  • @ibrahimdingan4855
    @ibrahimdingan48552 ай бұрын

    በመጀመሪያ ቅዱሥ ትመግበኝ ዘንድአመሠግንሀለሁ ❤❤❤❤❤❤❤

  • @user-hy3rn9dr4r
    @user-hy3rn9dr4r8 ай бұрын

    አሜን በረከታቸዉ ለእኔ ለሀጢአተኛዋ ይድረሰን

  • @yewonkeshtukidusgebralante8990
    @yewonkeshtukidusgebralante89903 жыл бұрын

    አሜን ቃለ ህይወት ያሰማልን ይህንን አዘጋጅታችሁ ለምታቀርቡልን ሁሉ ሰማያዊ ዋጋን ይክፈልልን አሜን፫

  • @meronalimu1057
    @meronalimu10575 ай бұрын

    የቅዱሳን በረከት ይደረብንን😢😢

  • @taiguhayile2660
    @taiguhayile26602 ай бұрын

    አሜን አሜን አሜን❤❤❤❤

  • @tigistashuma6088
    @tigistashuma60885 ай бұрын

    እግዚያብሔር፣ይመስገን፣አሜን፣አሜን፣አሜን፣የፃድቃን፣የሰማይታት፣በረከታቸው፣ረዴታቸው፣ከእኛጋር፣ይሁን፣ለዘላለሙ

  • @brhanie6823
    @brhanie6823 Жыл бұрын

    አሜን አሜን አሜን የቅዱሳን በረከት እረድኤት አይለየን አሜን አሜን አሜን

  • @HANNA-qy5bl
    @HANNA-qy5bl3 ай бұрын

    የማረያም በረከት ምልጃው የአባ ዞሲና ምህረት ከና አይለየን አሜን 🙏🙏🙏🙏🙏🤲🤲🤲✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️

  • @mirymirylove1767
    @mirymirylove17672 жыл бұрын

    amen amen amen

  • @user-ou2ho1vb3b
    @user-ou2ho1vb3b3 жыл бұрын

    *በረከታቸው ይድረሰን ቃለህይወትን ያሰማልን*

  • @user-is7go9vn7g
    @user-is7go9vn7g5 ай бұрын

    እግዚአብሄር አምላክ እኔን ሀጥዕ የሆንኩ ባሪያህን ታሪኬን ለውጠው የቅድት እናታችን እና የቅዱስ አባዞሲማበረከት አይለየን በጾለታቸው ይማረን አሜን አሜን አሜን😂😂😂😂😂😂🙏🙏🙏🙏🙏

  • @sofyass3973
    @sofyass39733 жыл бұрын

    አሜን አሜን አሜን🤲🤲🤲🤲

  • @Milat-or9ly
    @Milat-or9ly2 ай бұрын

    እውነት እኔንም ይምረኝ ይሆን አቤቱ ጌታዬ እየሱስ ክርስቶስ ሆይ ወዳንተ እቀርብ ዘድ እርዳኝ።ፈቃድህ ይሁንልኝ

  • @tigist19
    @tigist193 жыл бұрын

    አሜን አሜን አሜን ቃለ ሕይውት ያሰማልን🙏💒🙏💒🙏💒💜

  • @user-vm5ln7qe8l
    @user-vm5ln7qe8l3 жыл бұрын

    አሜን አሜን አሜን👏👏

  • @emujiru1797
    @emujiru17975 ай бұрын

    ግብፃዊቷ ማርያም የጌታን ቅዱስ ስጋና ቅዱስ ደሙን ከተቀበለች በኋላ በእለተ ሐሙስ በስቅለት ዋዜማ ከዚህ አለም በምት ተለየች 47 አመት ሙሉ ከሰይጣን ጋር ያላትን ፈተና ጨርሳ ሚያዚያ 14/ 4031 የ አረፈች የግብፃዊቷ ማርያም እና የአባ ዞሲማ በረከት ከሁላችን ጋር ይሁን አሜን 😢 ለሁላችንም አስተዋይ ልቦናን ያድለን 😢 አሜን አሜን አሜን

  • @brinebekle5939

    @brinebekle5939

    Ай бұрын

    አሜን አሜን

  • @user-dk6hs9bm2x
    @user-dk6hs9bm2x2 ай бұрын

    የአባ ዞሲማ ና የግብፅዊቷ ማሪያም ከረብር ምስጋና የገባቸው ረድኤታቸው ይደርብን አሜን🎉🎉🎉🎉🎉🎉❤❤❤❤❤❤🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉❤❤❤❤❤❤❤❤❤😊😊😊😊😊😊😊😊😊😊😊😊😊🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉❤❤❤❤❤❤❤❤😊😊😊😊😊😊😊😊😊😊🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤😊😊😊😊😊😊😊😊😊😊❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉😊😊😊😊😊😊😊😊😊😊😊🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤😊😊😊😊😊😊😊😊😊😊😊😊😊😊🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉😊😊😊😊❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤

  • @user-xb7ly8jk9y
    @user-xb7ly8jk9y3 ай бұрын

    አሜን

  • @shewakesete1167
    @shewakesete11675 ай бұрын

    Amen amen amen

  • @user-rq5vl7mm7z
    @user-rq5vl7mm7z3 жыл бұрын

    በረከታቸዉ ይደርብን ኣሜን

  • @meronbisrat4594
    @meronbisrat45942 ай бұрын

    Amen berketa yhderena ❤❤

  • @ililliiumamaa5210
    @ililliiumamaa52103 жыл бұрын

    Waqayyoo sagale jirenya Sii yaa dhagechisuu 😭😭😭😭😭

  • @rahealraheal1881
    @rahealraheal18813 жыл бұрын

    ቃለ ሂወት ያሰማልን መማህሮቻችን እጅግ በጣም እናመሰግናለን

  • @user-lp3vp3qx1e
    @user-lp3vp3qx1e3 жыл бұрын

    አሜን አሜን አሜን በርከታቸው ይደርብን

Келесі