ስምኦንና ልደቱ SIMON AND THE BIRTH DAY WRITTEN AND NARRATED BY DAWIT ALEMU

/ @dawitalemu470
በምስራቃዊ የኢየሩሳሌም ክፍል የሚኖር አንድ ስምኦን የተባለ ሰዉ ዘወትር አንድ ጸሎት ይጸልይ ነበር፡፡
‹‹አምላክ ሆይ የኢስራኤልን ድህነት ሳታሳየኝ አትግደለኝ!፡፡›› እያለ፡፡
አንድ እለት ማታ ስምኦን በጥልቅ እንቅልፍ ዉስጥ ሰጥሞ መልአኩ ወደ እሱ መጣ፤እንዲህም አለዉ…
‹‹ስምኦን ሆይ ጸሎትህ ተሰምቷል፡፡ኢየሱስ ክርስቶስ ሳይወለድ ከቶዉኑ ይቺን ምድር አትሰናበትም፡፡››
መጀመሪያ ስምኦን በሰማዉ ነገር ክፉኛ ደስ አለዉ፡፡ልቡ ሀሴት አደረገች፡፡ችግሩ ግን የመጣዉ ወደኋላ ነዉ፡፡ቢጠብቅ ቢጠብቅ ኢየሱስ አይወለድም፡፡የእድሜ እኩዮቹ አረጁ፤ሞቱ፡፡እሱ ግን አንድ ፍሬ ልጅ እንደሆነ አለ፡፡የልጆቹ እኩያ አረጁ፤ሞቱ፡፡እሱ ግን ገና ያልነጣ ጺሙን እየላጨ አለ፡፡የልጅ ልጆቹ እኩያ አረጁ፤ሞቱ፡፡እሱ ግን……
‹‹ኤጭ ! አሁንስ››››ይል ጀመር፡፡ሰለቸዉ፡፡
‹‹ለካ ህይወት የምትጣፍጠዉ አጭር ስትሆን ነዉ!፡፡›› በህይወት አታካችነት ተማረረ፡፡መበሰጫጨት አበዛ፡፡(የታግዷል ዘመን ሕይወቱን አወሳስቦበትም ሊሆን ችላል)
ብቻ ስምኦን ይናደድ አበዛ፡፡በዚያ ላይ ደግሞ ፤‹‹ይሄ ሰዉዬ ምንድነዉ ?! አያረጅም እንዴ?!››የሚሉ ድምጾች ከወዲህ ወዲያ ያወክቡት ጀመር፡፡
‹‹ድሮ ድሮኮ ነዉ ይሄንኑ አክሎ የምናዉቀዉ፡፡››እያሉ ጣት የሚጠቋቀሙበት በዙ፡፡ከዚያስ?

Пікірлер: 4

  • @mahlitzewdu8709
    @mahlitzewdu8709 Жыл бұрын

    አይአይአይ አተራረክ ፓ!!!! ምርጥ ነው

  • @dawitalemu470

    @dawitalemu470

    Жыл бұрын

    አመሰግናለሁ ማሂ!

  • @gatik6455
    @gatik645510 ай бұрын

    ye russian short stories... where are they??

  • @hallelujah9090
    @hallelujah90902 ай бұрын

    እንደ ዳዊት የምወደው ተራኪ የለም።ፋናን ማዳመጥ አልወድም የዳዊት ትረካዎች ግን አያመልጡኝም። ዩቲዩብ ላይ የዳዊት ትረካዎች ግን እምብዛም የሉም

Келесі