ቅዱስ ስምኦን (ጫማ ሰፊው) - ክፍል 2 / Saint Simon - Part 2
Ойын-сауық
ቅዱስ ስምኦን (ጫማ ሰፊው
ተአምረ ማርያም ላይ ከተጻፉት እና በትርጓሜ ወንጌልም ላይ በማቴ5÷29 ለሚገኘው ቃል እንደ ታሪካዊ ማስረጃ ከሚቀርቡት ታሪኮች አንዱ የስምዖን ጫማ ሰፊው ታሪክ ነው፡፡
በ979 ዓም የፋጢማይድ ሥርወ መንግሥት ግብጽን በሚያስተዳድርበት ወቅት በከሊፋ አል ሙኢዝ ሊ ዲን ኢላህ አል ፋጢሚ ዘመን እንዲህ ሆነ፡፡
ለሥልጣን ሲል ወደ እስልምና የተቀየረ ያዕቆብ ኢቢን ቂሊስ የሚባል አንድ አይሁዳዊ ነበር፡፡ ይህ አይሁዳዊ ምንም እንኳን ለሥልጣን ሲል እስልምናን ቢቀበልም ልቡ ግን ከአይሁድ ጋር ነበር፡፡ ክርስቲያኖችንም በጣም ይጠላ ነበር፡፡ ይህ ጥላቻው የመጣው በከሊፋው ዘንድ በሚወደድ እና እርሱ ይቀናቀነኛል ብሎ በሚያስበው በአንድ ክርስቲያን ምክንያት ነበር፡፡ ይህ ክርስቲያን ቁዝማን ኢቢን ሚና ይባል ነበር፡፡
ከሊፋ አል ሙኢዝ ደግ፣ ምክንያታዊ እና በሰዎች ነጻነት የሚያምን ዕውቀትንም የሚወድድ መሪ ነበር ይባላል፡፡ ምሁራን ሲከራከሩ መስማት የሚወድድ ሌላው ቀርቶ የእስልምና ምሁራን እስልምናን ከሚቃወሙ ሰዎች ጋር በነጻነት እንዲከራከሩ የሚፈቅድ ሰው ነበረ፡፡
ይህንን ጠባዩን የሚያውቀው ያዕቆብ ሙሴ የተባለውን የአይሁድ ረቢ ጠርቶ ከፓትርያርኩ ጋር እንዲከራከር እና ፓትርያርኩን እንዲያሳፍረው መከረው፡፡ ሙሴም ጥያቄውን ለከሊፋው አቀረበ፡፡ ከሊፋውም ለፓትርያርኩ መልእክት ላከ፡፡
በቀጠሮው ቀን በወቅቱ የእስክንድርያ ፓትርያርክ የነበረው አብርሃም ሶርያዊ በሃይማኖት ዕውቀቱ እና ትምህርቱ የታወቀውን ሳዊሮስ ዘእስሙናይን ይዞት መጣ፡፡ ሳዊሮስ ዘእስሙናይ «በከሊፋው ፊት ይሁዲን መናገር መልካም አይደለም» አለው፡፡
ይህንን ቋንቋ ሙሴ በሌላ ተርጉሞ «አላዋቂ ብለህ ሰደብከኝ» ሲል ተቆጣ፡፡
ከሊፋ አል ሙኢዝም «መከራከር እንጂ መቆጣት አያስፈልግህም» አለው፡፡
ያን ጊዜ ሳዊሮስ «አላዋቂ ብዬ የተናገርኩህ እኔ ሳልሆን ያንተው ነቢይ ኢሳይያስ ነው» ብሎ በትንቢተ ኢሳይያስ 1÷3 ላይ ያለውን ጠቀሰ፡፡ ከሊፋው ገረመውና «እንዲህ የሚል የእናንተ ነቢይ አለ?» ሲል ሙሴን ጠየቀው፡፡ ሙሴም «አዎ አለ» አለው፡፡ አባ ሳዊሮስም «እንዲያውም እንስሳት ከአንተ እንደሚሻሉም ገልጧል» አለው፡፡ ይሄን ጊዜ ከሊፋው ሳቀ፡፡ ክርክሩም እንዲቆም አዘዘ፡፡
ይህ ሁኔታ ያዕቆብን አበሳጨው፡፡ ራሱ ባመጣው ጣጣ በከሊፋው ፊት መዋረዱም ቆጨው፡፡ ስለዚህም ክርስቲያኖቹን የሚያጠቃበት ሌላ መንገድ መፈለግ ጀመረ፡፡ ሙሴንም አንዳች ጥቅስ ከወንጌል እንዲፈልግ ነገረው፡፡
ሙሴ በመጨረሻ በማቴ 17÷20 ያለውን «የስናፍጭ ቅንጣት ታህል እምነት ቢኖራችሁ ይህንን ተራራ ከዚህ ተነሣ ብትሉት ይሆናል» የሚለውን አገኘ፡፡ ለያዕቆብም ነገረው፡፡ ያዕቆብም ወደ ከሊፋው በማምጣት «በክርስቲያኖች መጽሐፍ ላይ እንዲህ ስለሚል ይህንን ፓትርያርኩ ያሳየን» አለው፡፡ ከሊፋው ተገረመ፡፡ ፓትርያርኩንም ጠርቶ ጠየቀው፡፡ አብርሃም ሶርያዊ ይህ ቃል በእውነት እንዳለ ነገረው፡፡
ከሊፋውም «በእውነት የክርስቲያኖች ሃይማኖት እውነት ይሁን ውሸት ለመፈተኛ ይህ ጥሩ አጋጣሚ ነው፡፡ ይህንን ማድረግ ካቃታቸው ግን ሕዝቡን እያታለሉ ነውና መቀጣት አለባቸው» ብሎ አሰበ፡፡
ከሊፋ አል ሙኢዝ ለአባ አብርሃም አራት ምርጫ አቀረበለት
1. የሙካተምን ተራራ ከምዕራብ ወደ ምሥራቅ ማዛወር ወይም
2. እስልምናን ተቀብሎ ክርስትናን መተው ወይም
3. ግብጽን ትቶ ወደ ሌላ ሀገር መሄድ ወይንም
4. በሰይፍ መጥፋት
ፓትርያርክ አብርሃም ውሳኔውን ለማሳወቅ የሦስት ቀን ጊዜ ጠየቀ፡፡ ከከሊፋው ዘንድ ከወጣ በኋላም ጳጳሳቱን፣ መነኮሳቱን፣ ካህናቱን፣ ዲያቆናቱን እና ምእመናኑን ሰበሰበ፡፡ ያጋጠመውንም ነገር ነግሮ በመላዋ ግብጽ የሦስት ቀን ጾም እና ጸሎት አወጀ፡፡
በሦስተኛው ቀን ማለዳ ቅድስት ድንግል ማርያም ለአባ አብርሃም ሶርያዊ ተገለጠችለት፡፡ «ይህንን ነገር የሚያደርግልህ አንድ ሰው አለ፡፡ ወደ ከተማው ገበያ ስትወጣ አንድ ዓይና የሆነ በገንቦ ውኃ የተሸከመ ሰው ታገኛለህ፡፡ እርሱ ይህንን ተአምር ያደርግልሃል» አለቺው፡፡
አባ አብርሃም ወዲያው ከመንበረ ጵጵስናው ወጥቶ ወደ ከተማው ገበያ መንገድ ጀመረ፡፡ በመካከሉም አንድ በገንቦ ውኃ የያዘ ሰው አገኘ፡፡ ያም ሰው አንድ ዓይና ነበረ፡፡ ጠራውና ወደ ግቢው አስገባው፡፡ የሆነውንም ነገረው፡፡
ያ ሰው «እኔ ኃጢአተኛ ነኝ፤ ይህ እንዴት ይቻለኛል» አለው፡፡
አባ አብርሃምም ያዘዘቺው ድንግል ማርያም መሆንዋን ነገረው፡፡
ያ ሰው ስምዖን ጫማ ሰፊው ይባላል፡፡ አንዲት ሴት እየደጋገመች መጥታ «ይህንን ዓይንህን እወድደዋለሁ» ብትለው ጫማ በሚደፋበት ጉጠት አውጥቶ የሰጣት እርሱ ነው፡፡
«አባቴ ሕዝቡን ወደ ተራራው ሰብስብ፡፡ እኔ ከአንተ አጠገብ እሆናለሁ፡፡ በአራቱም አቅጣጫ አንድ መቶ አንድ መቶ ጊዜ ኪርያላይሶን በሉ፡፡ ከዚያም ስገዱ፡፡ ከስግደቱ በኋላ ስታማትብ ተራራው ይነሣል » አለው፡፡
አባ አብርሃም ወደ ከሊፋው ሄዶ ተራራውን እንደሚያነሡት ነገረው፡፡
ኅዳር 15 ቀን 975 ዓም ሙስሊሞች፣ ክርስቲያኖች፣ አይሁድ፣ ሌሎችም ተሰበሰቡ፡፡ በአራቱም አቅጣጫ ጸሎተ ዕጣን ተደርሶ ኪርያላይሶን ተባለ፡፡ ከዚያም ሕዝቡ ሁሉ ሰገዱ፡፡ ከስግደት ተነሥተው ጸጥ ሲሉ ኃይለኛ ድምፅ ተሰማና ተራራው ካለበት ተነሣ፤ ፈቀቅም አለ፡፡ እንደገና ሰገዱ፤ አሁንም ተነሥቶ ፈቀቅ አለ፡፡ ለሦስተኛ ጊዜ ሰገዱ ተነሥቶ ወደ ምሥራቅ ሄደ፡፡ በዚህ ጊዜ ከሊፋው በከፍተኛ ድምፅ ጮኸ፡፡ «በቃ፣ በቃ በዚህ ከቀጠለ ከተማዋ ትፈርሳለች» አለ፡፡ ክርስቲያኖቹ በደስታ አምላካቸውን አመሰገኑ፡፡ ከሳሾቻቸው አፈሩ፡፡ ስምዖን ጫማ ሰፊው ግን ጠፋ፡፡
አባ አብርሃም በብርቱ አስፈለገው፡፡ ከዚያ በኋላ ግን ሊያገኘው አልቻለም፡፡ አባ አብርሃም ሶርያዊ ይህንን የድንግል ማርያምን ተአምር ለማስታወስ ከነቢያት ጾም ጋር ተያይዞ እንዲጾም አዘዘ፡፡ በገና ጾም የመጀመርያዎቹ ሦስት ቀናት ይህንን ተአምር ለማስታወስ የምንጾማቸው ናቸው፡፡
ዛሬ ተራራው ከሦስት ቦታ ተከፍሎ ይታያል፡፡ ከምዕራብም ወደ ምሥራቅ ሸሽቷል፡፡ «ሙከተም» ማለትም «የተቆራረጠ» ማለት ነው ይባላል፡፡ ይህ ተራራ ዛሬ በአሮጌዋ ካይሮ ይገኛል፡፡
ከዚህ ተአምር በኋላ ከሊፋ አል ሙኢዝ ለቤተ ክርስቲያን ብዙ ነገር አድርጓል፡፡ አያሌ የፈረሱ አብያተ ክርስቲያናት ተጠግነዋል፡፡ አዳዲሶቹም ተሠርተዋል፡፡ ይህ ተአምር የግብጽ ፓትርያርኮች ታሪክ በተሰኘው ጥንታዊ መጽሐፍ እና በሌሎችም መዛግብት ተመዝግቧል:: በተአምረ ማርያም ላይ የምናገኘው ታሪክ ከእነዚህ ጥንታውያን መዛገብት የተገኘ ነው፡፡ በሌላም በኩል ተራራው እና በአሮጌዋ ካይሮ የመዓልቃ ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን ዙርያ የተደረጉ የአርኬዎሎጂ ቁፋሮዎችም ይህንን መስክረዋል፡፡
በኋላ ግን ቦታው ሆን ተብሎ የካይሮ የቆሻሻ መጣያ ተደረገ፡፡ ክርስቲያኖቹ ወደ አካባቢው የሚጣለውን ቆሻሻ በመጥረግ ታሪኩ እንዳይጠፋ ታገሉ፡፡ በመጨረሻም ነገር ሁሉ ለበጎ ነውና ቆሻሻዎቹን እንደገና ለአገልግሎት በማዋል /ሪሳይክሊንግ/ መጠቀም ጀመሩ፡፡ ዛሬ ለብዙዎች የሥራ እድል ከፍቶላቸዋል፡፡
የአል ሙከተም ተራራ ተፈልፍሎ የስምዖን ጫማ ሰፊው ቤተ ክርስቲያን ተሠርቷል፡፡ የቤተ ክርስቲያኑ መቅደስ ክፍት ነው፡፡ ወንበሩ 25000 ምእመናን ይይዛል፡፡ የስምዖን ዐጽምም በመዓልቃ ቤተ ክርስቲያን በተደረገው ቁፋሮ ተገኝቶ በዚሁ የተራራ ቤተ ክርስቲያን በክብር አርፏል፡፡
----------------------------------------
ዲ.ን ዳንኤል ክብረት
Пікірлер: 299
ናይ ኣቦና ቅድስ ስምኦን ን ኣቦታትና .ንብዓት.ፆሎት .ቃል ኪዳን ምስ ኩላትና ይከን. ኣመላከ እስራኤል ነዚ ቅድስ ኣቦ ክረአ ዝፈቀድካለይ ኣመላክ ክብሪ ምስጋና ንዓካ ይኩን ኣሜን
አሜን አሜን አሜን ቃለ ህይወት ያሰማልን የቅዱሳን በረከት ይደርብን ❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤
ኣሜን ኣሜን ኣሜን ቃለ ህይወት ያሰማልን 🙏🙏🙏
_ቃለ ህይወት የስመዐልና ብሓቂ እግዚአብሔር ኣምላክ ንፅህ ልቢ ያዓድለና ናይ ተግባር ሰባት ይግበረና_
አሜን አሜን አሜን ቃለ ህይወት ያሰማልን🙏🙏🙏💙😢😢😢
Amen amen amen kalehiwet yasemaln yekudus smon bereket riedaiet yderben
amen amen amen kbriy leamlak smh ykber ymesgen lezelalemu amen
Amen Amen Amen Yee Kidusa simone Barktu Yee Darben Amen Amen Amen
AMEEN AMEEN AMEEN kale heyoten yasamalen ye Abatichen barakati ye darabeni ⛪✝️📚💯💯💯💯👏👏👏👏🍇🍇🍇
አሜን አሜን አሜን የቅዱሳን በረከታቸዉ ይደርብን 🙏🙏🙏
አሜን አሜን አሜን የቅዱሳኑ በረከታቸው ትድረሰን
አሜን አሜን አሜን አሜን ቃል ህይውት ያሠማልን፡፡ የቅዱሣን በረከታቸው ይደረብን😭😭 የእወነት በጣም ደሥ የሚል መንፈስን የሚያድሥ ነው፡፡ኦረቶዶክሥ ተዋህዶ ለዘላለም ፀንታ ትኑረ፡፡ ተረጉማችሁ ለምትለቁልን እግዚአብሔረ ይባረካችሁ፡፡በረቱልን በዚህ ፌልም ብዙ ነፍስ ትድናለች፡፡ አሜን አሜን አሜን
Ame AME ame
አሜን አሜን አሜን ቃላ ህይወት ያሰማልን❤
Aemennnnnnn nay aebotatna bereketin xelotin aeb hizbi kirstyan yihder🛐🙏🛐🙏🛐🙏🛐🙌🙌🙌🙌💖💖💖
አሜን አሜን አሜን ቃለ ህይወት ያሰማልን ያባታችን በረከታቸወ የደርብን አሜን፫
አሜን ቃለሂወት ያሰማልን በረከቱ ይድረሰን
አሜን አሜን አሜን ቃል ሂወት የስማዐለን
ናይ አቦና ስምኦን ጸሎቶም አይፈለየና አሜን በረከቶም ይሕደረና አሜን
ተመስገን ተመስገን ተመስገን የኔ ገይታ በእውነት የነዚህ ኣባቶች ፀሎት ኣይለየን🙏😢⛪
@BelayneshNigatu
28 күн бұрын
Amen amen amen 🤲🤲🤲🤲
ቃለሂወት ያሰማልን እናመሰግናለን
አሜን አሜን አሜን አሜን ቃለሂወት ያምስል ን
እግዚያብሔር፣ይመስገን፣አሜን፣አሜን፣አሜን፣የቅድስ፣ስሞኦን፣በረከቱ፣ረዴቱ፣ከእኛ፣ጋር፣ይሁን፣አሜን፣እሜን፣አሜን
ቃል ህይወት ያሰማልን አሜን አሜን አሜን 🙏🙏🙏❤
በእውነት ቃለ ህይወት ያሰማልን መምህር በድሜ በፀጋ ይጠብቅልን 🙏🙏🙏
አሜን አሜን አሜን ቃል ህይወት ያሰማልን ቅዱስ ሳምኦን በርከታቸው ይደርብን
አሜን ቃለ ህይወትን ያሰማልን🎉🎉🎉
አሜን አሜን አሜን በእውነት ቃለሕይወትን ያሰማልኝ የቅዱሳን አባቶች ረድኤት በረከታቸው በሁላችን ላይ ይደርብን ሀገራችን ላይ ያለውን ችግርና ፈተና ያርቅልን🤲🤲🤲🥰🥰
የአባታችን በረከታቸው ይደርብን❤
አሜን አሜን አሜን ቃለ ህይወት ያሰማልን ያባቶቻችን በረከት ይደርብን
የቅዱሳን በረከት ይደርብን
Abate KEDUSE SEMEON Radeat Baraketh Yedareben AMEN AMEN AMEN!!!
ቃለህወትያሰማልን.አሜንአሜንአሜን
ቃል ህይወት ያስማልን
እልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልል እግዚአብሔር ይመስገን🙏🙏🙏አሜን አሜን አሜን🙏🙏🙏
ቃለሕይወት ያሠማልን አሜን አሜን አሜንክብርለናተለአባቶቻችንይሑን
በእውነት እንዴት ያለ ተአምር ነው አቤቱ ጌታ ሆይ ትሁት አድርገኝ ይህንን የምትሰሩልን እግዝአብሔር ይባርካችሁ
Amn amn yekdus smeon bereket ydereben zend amn 🙏🙏🙌🙌
አሜን፡በረከቱ ይደርብን
ቃለህይወት ያሰማልን የቅዱስ ስምኦን በረከት በሁላችንም ላይ ይደርብን
በረከታቸው ይደርብን ❤❤❤❤😢😢😢😢
እረዴታቸው በረከታቸው ይደርብን አሜን አሜን 🙏🙏🙏🙏🙏
ቃል ህይውት ያሠማልን የቅዱሣን በረከታቸው ይደረብን አሜን አሜን🥰🥰❤❤😍😍
Amen amen amen
አሜንአሜንአሜን እግዚቤህር ይመሰገን
ቃለ ህይወት ያሰማልን አሜን 😭😭
በረከታቸው ይድረሰን!!!
አሜን አሜን አሜን ቃለ ህይወት ያሰማልን የአባታችን የስሞኦን በረከት ይደርብን አሜን፫ ግሩም ነው
አሜን አሜን አሜን ቃለ ህይወት ያሰማልን ጎዶልያስ
ቃለሂወት ያሰማልን ያባቶቻችን እረዴት በረከት ይደርብን አሜን ፫ ኦርቶዶክስ ለዘላለም ጸንታ ትኑር
@hannasalam672
Жыл бұрын
አሜን አሜን አሜን❤❤
ቃልይሆትያስማልን
ቃለ ህይወት ያሰማልን
❤❤❤አሜን አሜን ቃለሕይወት ያሠማልን
አሜን አሜን አሜን ክርስቲአን ያርከኝ ጌታየ አመሰግንሀለሁ
Kale heywot yasemalen tsagahun yabizalachu tebareku AMEEN AMEEN AMEEN ✝️✝️✝️
ቃለ ህይወት ያሠማልን የሰማነው በልቦናችን ይፃፍልን🤲 ለአባቶቻችን እድሜና ጤና አብዝቶ ይስጥልን👏🕊👏🕊
እግዚአብሔር ከብር ምሰጋና ለንተይሁን የቅዱሳን አምላክ በረከታቸው ይድርሰን
በረከታችሁ ይድረሰን
Kebere neamelke 🤲🤲🤲⛪⛪⛪
አሜን አሜን አሜን❤❤❤
ተመስገን የኔ ጌታ
ቅዱሥ አባታችን የቅዱሥ ሥምኦን በረኬት እረዴትሕ ይደርብን አሜን
አሜን አሜን አሜን ቃለ ህይወት ያሠማልን የአባቶቻችን በረከት ትድረሰን😢🥰🥰🥰❤️❤️❤️
አሜን አሜን አሜን 🙏🙏
ቃለህይወት ያሠማልን የቅዱሣኑ አባቶቻችን ኧረዴታቸዉ በረከታቸዉ ይደርብን አሜን
በረከታችሁ ይደርብን
ቃለ ህይወት ያሰማልን የአባቶቻችን ፀሎት በረከት አይለየን አሜንንንን••••• በጣም ልብን ደስስስስ የሚያሰኝ ታሪክ ነው እህት ወንድሞቼ አሁን እርጉዝ ነኝ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ወንድ ከሆነ እምወልደው "ስምዖን" እለዋለሁ ስሙን •••••!!!
@mangestu4336
5 жыл бұрын
የበኪ እናት ዉይ የኔ እናት እመቤታችን ታገላግልሽ እህቴ እንደ ፍላጎትሽ ይሰጥሻል ፈጣሪ
@yekidusantarik
5 жыл бұрын
አሜን እግዚአብሔር ያሰብሽውን ይስጥሽ
@habshihabshi7549
5 жыл бұрын
እህቴ ቡእውነት የቅድስት ሙራኤል ጸሎት የልብሺን ትሥጥሺ ውይይይይይይእመብርሀን ትዳብስሺ
@user-kl5hn1ss7h
5 жыл бұрын
አሜንንንንንንን
@user-jk3uc1gn5t
3 жыл бұрын
@@user-kl5hn1ss7h ወለድሽ
አሜን አሜን አሜን
ስለ ሁሉም ነገር እግዚአብሔር ይመስገን የአባታችን ቅዱስ ስምኦን በረክፕት ከሁላችን ጋር ይሁን አሜን ተርግማችሁ ላቀረባችሁ እግዚአብሔር እድሜ ጤና ይስጣችሁ እናመሰግናለን
ኣሜን ኣሜን ኣሜን
ቃለ ሂወት ያሰማልን ያባታችን በረከታቸው የደርብን አሜን
Egziabeher yemesgen bewunt qale hiwoten yasemalen tsega berketachewu ayileyen Amen Egziabeher yixebeqelne Amen
እግዚአብሔር ይመስገን ሁሉ የሚቻለው አምላክ ያባቶቻችን እረዴት በረከታቸው ይደርብን አሜን❤❤❤
ኣሜን ተዋህዶ መሆን መመረጥ ነው እንደዝህ ኣድርጋቹሁ ስላቀረብላችሁልን እናመሰግናለን ክብር ምስጋና ለ እግዚኣብሔር ይሁን🙏🙏🙏🙏
ኣሜን ኣሜን ኣሜን ቃለ ህይወት የስመዐልና ክብራት ኣቦታትና በረኸቱን ፀግኡን የብዘሐልኹም እግዚኣብሄር ኣምላኽ🍃📖🍃
የቅዱሳን ረደኤት በረከት ይደርብን
እግዚአብሔር ይመስገን
አሜንበረምጋይባሃል
ኣሜንንንንንንንንንንንን ቃል ሂወት የስማልና በረከቶምን ጸሎቶምን ናይ ቅድሳን ኣይፈለየና።
አሜን አሜንአሜን🙏🙏🙏
ስለ ሁሉም ነገር እግዚአብሔር ይመስገን
amen amen amen kale hiwet yasemalen ye kudusan berket ena tslot ayleyn
ክብር ምስጋና ይሁን ለሉኡል እግዚአብሔር
ቃለህይወትያሰማልን።እዝጋብሄርይመስገንይህንንበርከትእንድናይለርዳንአምላካችንምስጋናይድርሰው
የቅዱስ ስምኦን በረከቱን ረዴኤቱን ይደርብን ኣሜን ኣሜን ኣሜን
እግዚአብሄር የተመሰገነ ይሁን
አሜን አሜን አሜን ቃልህዉትያስማልን የአባታችን እርደትና በርከት ከሁላችንም ይደርብን
በርታቸዉ ይደርብን❤❤❤አሜን
ስለ ሁሉም ነገር እግዚአብሔር ይመስገን ጌታ ሆይ ስምህ ካለም ጫፍ እስከ አርያም የተመሰገነ ይሁን አሜን የቅዱሳኑ እርድኤት በርከታቸው አይለየን አሜን ፫ ለሁላችሁም ቃለ ህይወት ያሰማልን
የቅድሳን አምላክ እግዚአብሔር ይመስገን በርከታቸው ይደርብን!
አሜንአሜን አሜን
Thanks GOD ❤
ጌታ ሆይ ላንተ ምን ይሳንሀል ክብርና መጎስ ላንተ ይሁን
Amen
ቃለ ሂወትን ያሰማልን የናታችን የንፅህት ድንግል ማርያም ልጅ ጌታችን መዳኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ስሙ ከአፅናፍ እስከ አፅናፍ የተመሰገነ ይሁን የቅዱስን በረከት አይለየን
አሜን😭
የቅዱሳኑ እረዴትና በረከታቸው ይደርብን አሜን አምላከ ቅዱሳን ይርዳን ይቅር ይበለን
የቅዱሳን አባቶቻችን በረከታቸው እረድኤታቸው አይለየን አሜን፫
EGZIABHIER YMESGEN 🙏🙏🙏🤲🤲🤲❤️❤️❤️
አሜንንንን