አባ መቃርስ - ክፍል - 2 / Aba Mekars Part - 2 Ye Kidusan Tarik

Ойын-сауық

ክፍል ሁለትን ስላዘገየሁባችሁ በጣም ይቅርታ ብሎክ እየተደረገ ስለተቸገርኩ ነው፡፡
ታላቁ ቅዱስ መቃርስ
ታላቁ ቅዱስ መቃርስ ወይም ቅዱስ መቃሬ 'ጽድቅ እንደ
መቃርስ' የተባለለት: የመነኮሳት ሁሉ አለቃ: ከ80 ዓመታት
በላይ በበርሃ የኖረ: በግብፅ ትልቁን ገዳም ወይም አስቄጥስን
የመሠረተ: ከ50,000 በላይ መነኮሳትን ይመራና
ይመግብ የነበረ ፍፁም ጻድቅ ነው::
በ4ኛው መቶ ክ ዘመን አርዮሳውያን ደጉን ታላቅ አባት
በሰንሰለት አስረው ከግብፅ ወደ እስያ በርሃ ከጉዋደኛው
ቅዱስ መቃርዮስ እስክንድርያዊ ጋር አሰድደውታል:: በዚያ
ለ2 ዓመታት ስቃይን ከተቀበሉ በሁዋላ በአረማውያን ፊት
ድንቅ ተአምር አድርገው አረማውያንን ከነንጉሳቸው
አጥምቀዋል::
በተሰደዱባት ሃገርም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም
አጠራሩ ይክበርና እመቤታችንን: ቅዱሳን ሐዋርያትን:
አዕላፍ መላእክትን: በተለይ ደግሞ ቅዱሳኑን ዳዊትን:
ዮሐንስ መጥምቁንና ወንጌላዊውን: ማርቆስን: ዼጥሮስን:
ዻውሎስን አስከትሎ ወርዶ ተገልጦላቸዋል:: በቅዱስ
አንደበቱም የምሕረት ቃል ኪዳን ገብቶላቸዋል::
ታላቁ ቅዱስ መቃርስና ባልንጀራው መቃርዮስ ከ2
ዓመታት ስደትና መከራ በሁዋላ ስደት በወጡባት ዕለት
መልዐኩ ኪሩብ በክንፉ ተሽክሞ ወደ ግብፅ
መልሷቸዋል:: በወቅቱም ጻድቁን ለመቀበል ከ50,000
በላይ የሚሆኑ ልጆቻቸው መነኮሳት በዝማሬ ወጥተዋል::
ስለ ታላቁ ቅዱስ መቃርዮስ ቅድስና ለመጻፍ መነሳት
በረከቱ ብዙ ነው:: ግን 'ዓባይን በጭልፋ' እንዲሉ አበው
ከብዛቱ የተነሳ የሚዘለቅ አይሆንም::
ቅዱስ መቃርስ ከዘመናት በላይ በቆየበት የበርሃ
ሕይወቱ:-
1.አባ ብሶይ: አባ ባይሞይ: አባ ሳሙኤል: አባ በብኑዳን
ጨምሮ እርሱን የመሰሉ ወይም ያከሉ ቅዱሳንን ወልዷል::
2.ለሕይወታችን መንገድ የሚሆኑንን ብዙ ቃላትን
ተናግሯል::
3.ከገዳማት እየወጣ በብዙ ቦታዎች ቅዱስ ወንጌልን
ሰብኩዋል::
4.አጋንንትን ድል ከመንሳት አልፎ እንደ ባሪያ ገዝቷቸዋል::
5.ለዓይንና ጀሮ ድንቅ የሆኑ ብዙ ተአምራትን ሰርቷል::
በእነዚህና ሌሎች ምክንያቶችም ቤተ ክርስቲያን "ርዕሰ
መነኮሳት ወይም የመነኮሳት ሁሉ አለቃ" ስትል ትጠራዋለች::
በ97 ዓመቱ መጋቢት 27 ቀን ሲያርፍ መላእክት ብቻ
ሳይሆን አጋንንትም ስለ ድል አድራጊነቱ ዘምረውለታል::
ታላቁ ቅዱስ መቃርስ ካረፈ በሁዋላ ከክቡር ሥጋው
ብዙ ተአምራት ይታዩ ነበርና የሃገሩ ወይም የሳስዊር ሰዎች
ሊወስዱት ፈለጉ:: ሳስዊር ማለት ቅዱሱ ተወልዶ
ያደገባት: ወላጆቹ ወይም አብርሃምና ሣራ ይባላሉ የኖሩባት ቦታ
ናት:: የምትገኘውም ግብጽ ውስጥ ነው::
በምድረ ግብጽ: በተለይም በገዳመ አስቄጥስ የአባ
መቃርስን ያህል ክቡርና ተወዳጅ የለምና የሃገሩ ሰዎች
የነበራቸው አማራጭ መስረቅ ነበር:: መሥረቅ ኃጢአት
ቢሆንም እነሱ ግን ስለ ፍቅር: አንድም ለበረከት ወይም በረከትን
ሲሹ አደረጉት::
ወደ ሳስዊርም ወስደው: ቤተ ክርስቲያን በቅዱሱ ስም
አንጸው በክብር አኖሩት:: በዚያም ለ160 ዓመታት
ተቀመጠ:: በ7ኛው መቶ ክ-ዘመን ግን ተንባላት
ወይም እስላሞች መጥተው ቤተ ክርስቲያኑን አጠቁ:: በዚህ
ጊዜም ሕዝቡ የጻድቁን አጽም ይዘው ሸሹ:: በሌላ ቦታም
እንደ ገና በስሙ ቤተ ክርስቲያን አንጸው በዚያ አኖሩት::
በእነዚህ ሁሉ ዓመታት የመንፈሳዊ አባታቸውን ሥጋ
ያጡት የገዳመ አስቄጥስ ቅዱሳን ያዝኑ ይጸልዩ ነበርና
ልመናቸውን ፈጣሪ ሰማ:: አባ ሚካኤል ሊቀ ዻዻሳት
በነበረበት ዘመን: ከገዳሙ ለሌላ ተግባር ወደ ሳስዊር
የተላኩ አበው ከታላቁ አባት ቤተ ክርስቲያን ሲደርሱ
ሰውነታቸው ታወከ::
ይዘው ለመውሰድ ሙከራ ቢያደርጉ ሊሳካላቸው
አልቻለም:: ምክንያቱም የቤተ ክርስቲያኑ ጠባቂ ደወል
ደውሎ ሕዝቡን ሁሉ ጠርቶ ነበርና:: ሕዝቡና ሃገረ ገዢው
የሆነውን ሲሰሙ "የቅዱሱን ሥጋ ብትነኩ እንገላቹሃለን"
ብለው ሰይፍ: ዱላ: ጐመድና ጦር ይዘው መጡባቸው::
መነኮሳቱ ግን ባዷቸውን ሊመለሱ አልፈቀዱምና ሌሊቱን
ሲያለቅሱና ሲጸልዩ አደሩ:: መንፈቀ ሌሊት በሆነ ጊዜም
ታላቁ መቃርስ በግርማ ወርዶ መኮንኑን "ለምን ወደ ልጆቼ
እንዳልሔድ ትከለክለኛለህ?" ሲል በራዕይ ተቆጣው::
በዚህ ምክንያትም መነኮሳቱ የቅዱሱን ሥጋ ተቀበሉ::
ሕዝቡም በዝማሬና በማሕኅሌት: ከብዙ እንባ ጋር
ሸኟቸው:: ታላቁ መቃሬ ወደ ገዳሙ ሲደርስም ታላቅ ደስታ
ተደረገ:: ቅዱሳን ልጆቹ ከመንፈሳዊ አባታቸው ተባርከው
በክብር አኑረውታል::
አምላከ ቅዱሳን የታላቁ ቅዱስ መቃርስን ትሕትናውን:
ትእግስቱንና ቅንነቱን ያድለን:: በበረከቱም ይባርከን::
ምንጭ ››› " ዝክረ ቅዱሳን Saints Of The Orthodox Church " የፌስቡክ ገፅ - %E1%8B%9D%E1...
ይህን መንፈሳዊ ፊልም አዘጋጅተውና ተርጉመው ላቀረቡልን ቃለ ሕይወት ያሰማልን፡፡

Пікірлер: 471

  • @yeznakassahun780
    @yeznakassahun780 Жыл бұрын

    የአባታችን የፃዲቁ አባ መቃርስ በረከት ይድረሰን አሜን አሜን አሜን

  • @HananHanan-ld3cw
    @HananHanan-ld3cw Жыл бұрын

    የአባታችን የአባ መቃርስን ጥንካሬና ጽናት ይስጠን አሜንንን

  • @hanamariyam829
    @hanamariyam8296 жыл бұрын

    የአባ መቃርስ በረከቱ እና ረዲዐቱ ይደርብን የህን አዘጋጅተው ላቀረቡልን እግዚአብሔር ፀጋውን ያብዛላቸው

  • @zebaasrat9290
    @zebaasrat92905 жыл бұрын

    እግዚአብሔር ይመስገን የአባ መቃርስ አምላክ ሆይ እባክህ እኔንም በምሕረትህ ጎብኝኝ ክብር ምስጋና ለድንግል ማርያም ልጅ ይሁን አሜን

  • @netsanetsoimon8355
    @netsanetsoimon83552 жыл бұрын

    እግዚአብሄር ይመስገን ቃለ ህይወት ያሰማልን አባታችን በረከታቸው ይደርብን አሜን አሜን አሜን

  • @sessilbein857
    @sessilbein8572 жыл бұрын

    እግዚአብሔር ይመስገን አሜን ለአባቶቻቺን ቃለህያ ወትን ይስማልን ፀጋው ይብዛላቹ

  • @tewahedoreligion1855
    @tewahedoreligion18553 жыл бұрын

    ቃል ህይወት ያሰማልን ያባቶቻችን ረደኤት በረከት ይደርበን አሜን፫

  • @user-we4dp1mg9e
    @user-we4dp1mg9e6 жыл бұрын

    አሜን አሜን አሜን ቃል ህይወት ያስማልን የፃዲቁ አባታችን አባ መቃርስ ረድኤታቸው በረከታችው ፀሎት ልመናቸው አይለያን አሜን!! ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ለዘላለም ትኑር አሜን!!

  • @loveisgood

    @loveisgood

    4 жыл бұрын

    Amen ❤❤❤

  • @user-ns9cg9uk4x

    @user-ns9cg9uk4x

    4 жыл бұрын

    Amen amen amen

  • @user-no9zc3zt1z

    @user-no9zc3zt1z

    Жыл бұрын

    አሜን አሜን አሜን

  • @user-nw3fi1kw8r
    @user-nw3fi1kw8r6 жыл бұрын

    አሜን አሜን አሜን የአባቶቻችን የእናቶቻችን ረድኤት በረከት ይደርብን የአባታችን የአባ መቃርስ ረድኤታቸው በረከታቸው ልመናቸው አይለየን አሜን

  • @Burafkr19
    @Burafkr199 ай бұрын

    አሜን አሜን አሜን ቃለ ህይወት ያሰማልን የፃዲቁ አባታችን የአባ መቃርስ ረድኤታቸው በረከታቸው ፀሎተ ልመናቸው አይለየን አሜን !!!!! ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ለዘላለም ትኑር አሜን

  • @user-jp1mi1ik6y
    @user-jp1mi1ik6y4 жыл бұрын

    አባ በረከቶቱን ይደርብን አባ ይሰብን በፅሎቶን በመቅበዝበዝ ላይ ነው ያለሁኝ እባክን የሰራዊት ጌታየ ሆይ 😭😭😭

  • @user-wy8ge6wr5y
    @user-wy8ge6wr5y4 жыл бұрын

    አሜን አሜን አሜን ቃለ ሕይወት ያሰማልን የፃድቁ የአባ መቃርስ ረዴት በረከታቸው ምልጃና ፀሎታቸው አይለየን አሜን

  • @biniyammulugeta587
    @biniyammulugeta5872 жыл бұрын

    አሜን የአባታችን የአባ መቃርስ ረድኤትና በረከታቸው በህዝበ ክርስቲያኑ ላይ ይደርብን

  • @iskechagetchew2701
    @iskechagetchew27014 жыл бұрын

    የ አባ መቃርዮስ ረዴት በረከታቸው ይደርብን ቀለ ህይወት ያሰማልን የአገልግሎት ዘመናቸውን ይባርክልን 🙏❤️⛪⛪⛪🙏❤️🙏❤️

  • @mesitawtikorma8468
    @mesitawtikorma84683 жыл бұрын

    ያባታችን ያባ መቃርስ እረዴታቸው በረከታቸው ይደርብን በእወነት አሜን፫

  • @user-ji2wv2xt1z
    @user-ji2wv2xt1z6 жыл бұрын

    አሜን አሜን አሜን የአባታችን የቅዱስ የአባ መቃርስ በረከት ፆሎቶችው ይደርብን ተዋህዶ ለዘላለም ትኑር ቃለሄውት ያስማልን

  • @Ggg-vs1iy
    @Ggg-vs1iy11 күн бұрын

    የአባታችን ደአባ መቃርስ ረደት በረከት ምልጃና ፀሎት አይለየን አሜን⛪👏⛪👏🙏🙏👏

  • @yeketashfera7094
    @yeketashfera70946 жыл бұрын

    ያባታችን በረከታቸው ይድረሰን ምልጃቸው አይለየን ኦርቶዶክስ ለዘላለም ትኑር አሜን።

  • @tgstlove2384
    @tgstlove23845 жыл бұрын

    አሜን አሜን አሜን በእውነቱ ቃለ ህይወት ያሰማልን የአባታችን የአባ መቃርስ በረከት ረድኤት ምልጃ ፀሎት አይለየን አሜን አሜን አሜን

  • @user-vu1sc3oy7v
    @user-vu1sc3oy7v2 жыл бұрын

    የአባታችን የአባ መቃርስ መልጃና ፆለት ልመና አይለየን አሜን ፫

  • @martatube73
    @martatube735 жыл бұрын

    የአባ መቃርስ በርከታቸው ይደርብን ተመስገን ጌታ ሆይ 💒

  • @seblieyobawyt990
    @seblieyobawyt9904 жыл бұрын

    የአባቶቻችን በረከት በሁላችን ይደር አሜን❤🙏🙏🙏

  • @user-ii1bb6si9x
    @user-ii1bb6si9x3 жыл бұрын

    አሜን አሜን አሜን ቃለ ህይወት ያሰማልን የአባ መቃርስ ጸሎት እና በረከት ከሁላችን ጋር ይሁን🙏🙏🙏

  • @christianmsgana2580
    @christianmsgana25806 жыл бұрын

    የቅደሳን እናቶች እና አባቶቻችን እረድኤት በረከታቸው ይደርብን አሜን

  • @user-sc6pf7mu4p
    @user-sc6pf7mu4p10 ай бұрын

    አሜን አሜን አሜን ቃለህይወት ያሰማልን የባታችን የባ መቃርስ እረዲኤት በረከት በሁላችንም ላይ ይደርብን❤❤❤

  • @enatmesfin
    @enatmesfin4 жыл бұрын

    ቃል ሕይወት ያሰማልን አባቶች ለምናችሁ ጸሎታችሁን አይለየን አመሰግናለሁ

  • @ogbamicaelangesom3240
    @ogbamicaelangesom32405 жыл бұрын

    እግዚኣብሄር ይመስገን ጸጋውን ያብዛላችሁ! የኣባ መቃርስ በረከታቸውን ይደርብን!

  • @mesklove4771
    @mesklove47715 жыл бұрын

    አሜን ቃለ ህይወት ያሠማልን ያአባ መቃርስ በረከት በሁላችንም ላይ ይደር ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ለዘላለም ትኑር

  • @seyumayelee8421
    @seyumayelee84214 жыл бұрын

    አሜን አሜን አሜን ፀሎታቸውና በረከታቸው በሁላችን ላይ ይደርብን

  • @user-hw7wx8cz2q
    @user-hw7wx8cz2q4 жыл бұрын

    የቅዱሳን በረከት አይለየን አሜን ፫🙏🙏🙏💒

  • @user-rw1is9sr1o
    @user-rw1is9sr1o6 жыл бұрын

    አሜን አሜን አሜን የአባታችን የአባ መቃርስ በረከታቸው ምልጃና ጥበቃቸው ከህዝበ ክርስቲያን ጋር ለዘላለም ይኑር ።።።።።።

  • @lamitaaoun2290

    @lamitaaoun2290

    6 жыл бұрын

    የንግስት ልጂ. I have been in a While ያውም ያማላጇ

  • @zebnasemawmengesha6812
    @zebnasemawmengesha68126 жыл бұрын

    ያባታችን ያባ መቃርስ እረዴታቸው በረከታቸው ይደርብን በእውነት

  • @bghftggicd5769

    @bghftggicd5769

    4 жыл бұрын

    Amen amen Amen 😭⛪🙏

  • @bghftggicd5769

    @bghftggicd5769

    4 жыл бұрын

    AMEN amen Amen ⛪😭🙏

  • @asresalemnew4521

    @asresalemnew4521

    3 жыл бұрын

    Amen

  • @betibeti72

    @betibeti72

    2 жыл бұрын

    ያባታችን በረከታቸው ይደርብን 😭😭😭😭🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏😭😭😭😭😭🙏🙏🙏

  • @user-mi3oe8ye7n
    @user-mi3oe8ye7n5 жыл бұрын

    እሜን እሜን እሜን ቃለ ህይወት ያሰማለን የፃድቁ እባታችን እባ መቃርዮስ በረከት ረዲኤት ይደርብን እሜን

  • @user-cb2tr4cd9m
    @user-cb2tr4cd9m10 ай бұрын

    አሜን አሜን አሜን ቃለ ህይወት ያሰማልን ያባታችን አባ መቃርስ እረድት በረከታቸው ይደርብን ሁላችን ህዝበ ክርስቲያን❤❤❤

  • @user-op5mv6iw1w
    @user-op5mv6iw1w6 жыл бұрын

    የአባታችን አባ መቃርስ ረእደት በረከታቸው ከሁላችን ጋር ይሁን አሜን አሜን አሜን

  • @fasikalebanon6024
    @fasikalebanon60242 жыл бұрын

    አሜን,አሜን,አሜን,የአባታችን,የአባ,መቃርስ,የቅዱሰን,እረዴኤታቸው,በረከታቸው,ይደርብን,አሜን,አሜን,አሜን,👏👏👏

  • @tsedaytseday9415
    @tsedaytseday94154 жыл бұрын

    አሜን አሜን አሜን የአባቶቻችን በረከት ይደርብን🙏

  • @zmeraazmera6355
    @zmeraazmera6355 Жыл бұрын

    የአባታችን መቃርስ በረከት ይደርብን ቃለ ህይወት ያሠማልን👏

  • @user-xc7lm2jr9c
    @user-xc7lm2jr9c Жыл бұрын

    የአባታችን መቃርስ ርዴት በርከታቸው ይደርብን 🤲🤲🤲🤲

  • @wolatemikealwolatemikeal1103
    @wolatemikealwolatemikeal11036 жыл бұрын

    አሜን ፫ የአበቶቻችን ረዴት በረካታችው አይለየን በፀሎታችው እኛ በሪያዎችህ እና ደካሞች ነንና አቤቱ ስለ አባ ማቃርስ ብለህ እኛ ደካሞችን ማረን ይቅር በለን

  • @Uyyy-fu3xh
    @Uyyy-fu3xhАй бұрын

    የአባታችን የአባ መቃርስን ጥንካሬና ጸናት ይስጠን ረድኤታቸው በረከታቸው ፀሎተ ልመናቸው አይለየን ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ለዘላለም ትኑር አሜን አሜን አሜን ❤❤❤

  • @firehiwettuaumay5670
    @firehiwettuaumay56703 жыл бұрын

    ቃል ሂወት ያስማልን አሜን ፫ የአባቶች የቁዱሳን በረከታቸው ን እና ረዲኤታቸውን በሁላችን ህዝበ ክርስትያን ይሁን አሜን፫

  • @brtigete1875
    @brtigete18756 жыл бұрын

    አሜን አሜን አሜን ቃለ ህይወት ያሰማልን የአባቶቻችን በርከት አይለየን ወደኛ እንዴደርስ የምታርጉት እግዚአብሔር ይስጥልን

  • @user-xv1cb4jw9h

    @user-xv1cb4jw9h

    4 жыл бұрын

    Brti Gete ገጠ

  • @user-fq7of6rw7n
    @user-fq7of6rw7n3 жыл бұрын

    የአባታችን የአባ መቃርስ በረከታቸው ይደርብን አሜን ይህንን አዘጋጅታችሁ ላቀረባችሁልን ፀጋዉን ያብዛላችሁ አስተማሪ ነዉ ❤❤❤

  • @Tsgetsge-fq3zb
    @Tsgetsge-fq3zb6 жыл бұрын

    የአባ መቃርስ በረከት ያሳድርብን የቅዱሳን አምላክ አሜን ፫

  • @abebatesemma5632
    @abebatesemma56328 ай бұрын

    የቅዱሳን አምላክ ልዑል እግዚአብሔር ይክበር ይመስገን አሜን የቅዱሳን አባቶቻችን በረከት ረድኤት የጸሎታቸው አይለየን አሜን ቃለ ህይወት ያሰማልን

  • @MekuanintBirru
    @MekuanintBirru4 ай бұрын

    የአባታችን ቅዱስ አባ መቃርስ ረድኤት በረከታቸው ይድረሰን በጸሎታቸው ይማረን

  • @hananhp4217
    @hananhp42178 ай бұрын

    አሜን አሜን አሜን የፃድቁ አባ መቃርስ እረድኤት በረከታቸዉ ይደርብን ስለ ቅድሳኑ ብሎ አምላካችን ለሀገራችን ኢትዮጵያ ምህረት ቸርነቱን ይላክላት 🤲🤲🤲🤲🤲

  • @user-qu8wd6mp8x
    @user-qu8wd6mp8x6 жыл бұрын

    የፃድቁ በረከት ይደርብን አምላኬ ሆይ አሁንም መልካም። ፃድቅ ስው አስነሳልን። ለሀገራችን ሰላም ይውረድን አሜን

  • @user-th6nb3kj8x

    @user-th6nb3kj8x

    3 жыл бұрын

    የፃዲቁ በረከት ይደርብን አምላኬ ሆይ አሁንም አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን

  • @teduadaayal2841
    @teduadaayal28412 жыл бұрын

    ሰለሁሉም ነገር እግዚአብሔር ይመስገን ጌታየ መዳህኒቴ እየሱስ ክርስቶስ ሆይ በልቤ ውስጥ ንገስ እባክህን በአቭ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አፅናኝ ሰይጣንን በዙሪያዬ አርቅልኝ አሜን አሜን አሜን🙏🙏🙏

  • @zadyearsamalij1092
    @zadyearsamalij1092Ай бұрын

    የአባ መቃርስ በረከት ይደርብን አሜን የአባ መቃርስ አምላክ ሆይ ማረኝ ይቅር በለኝ ኦ ጌታ ሆይ አድነኝ አዘጋጅታችሁ ላቀረባቹልን እግዚአብሔር ይስጥልን ጸጋውን ያብዛላችሁ

  • @user-qp8hp3id7j
    @user-qp8hp3id7j6 жыл бұрын

    አሜን ለአባ መቃረስ ፃሎት አይለየኝ አሜን ቃል ህይወት ያሠማልን

  • @user-pc8ig9ez4h
    @user-pc8ig9ez4h5 жыл бұрын

    አባቶቻችን እረድኤት በረከት ይደርበን አሜን አሜን አሜን

  • @fanayekebede5921
    @fanayekebede59216 жыл бұрын

    አሜን አሜን አሜን የአባ መቃርስ እረድኤት በረከት ፀሎትና ምልጃ ከእኛ ከህቦች ብሎም ባገራችን የኢትዮጵያ ላይ ፀንቶ ይኑር አሜን

  • @helenhelen349
    @helenhelen349 Жыл бұрын

    አሜን አሜን አሜን ቃል ህይወት ያሰማልን የአባታችን አባ መቃርስ እረዴታቸው በረከታቸው ይደረብን ይድርሰን አሜን

  • @user-zr5df2vn2y
    @user-zr5df2vn2y6 жыл бұрын

    አሜን የአባታችን አባ መቃርስ በረከታቸው ረኤደታቸው አይለየን!

  • @birukyeshambel1046
    @birukyeshambel1046 Жыл бұрын

    የአባ መቃሪዮስ በረከታቸው አይለየን ። የምህረት አምላክ በምህረትህ እርዳን።

  • @user-lq9vm2ft9c
    @user-lq9vm2ft9c2 жыл бұрын

    የፃድቁ አባ መቃርስ እንድሁም የቅዱሳን ረዴት በረከታቸው በህዝበ ክርስቲያኖች ላይ ይሁን አሜን አሜን አሜን

  • @mdet2995
    @mdet2995 Жыл бұрын

    የአባታችን አባ መቃርስ በረከት ይደርብን ላዘጋጁልን ቃለ ህይወት ያሠማልን

  • @user-yd8rg1pw4b
    @user-yd8rg1pw4b2 ай бұрын

    የአባ መቃርስ በረከታቸው ይደርብን አሜን ቃለ ሂወት ያስማልን አሜን

  • @user-ko7lb2fu8i
    @user-ko7lb2fu8i5 жыл бұрын

    አሜን አሜን አሜን ቃለህይወት ያሰማልን የአባታችን የአባ መቃርስ በረከታቸው አይለየን

  • @emafekre7829
    @emafekre78292 жыл бұрын

    አባ መቃርሰ አባቴ ረድኤትዎት በረከትዎት አይለየን ላሥተረጎማችሁልን ዘመናችሁ ይባረክ

  • @netsanetbirhanu2470
    @netsanetbirhanu2470 Жыл бұрын

    ያላሰባችሁትን ሲሰይ ፀጋ ይሰጣችሁህ

  • @niceboy7269
    @niceboy72696 жыл бұрын

    የአባቶቻችን በረክት ልመናቸው ሁል ግዜ ከኝ ከህዝበክርስቴኑ ጋር ይሁን አሜን

  • @user-ve4tn9zp3y
    @user-ve4tn9zp3y Жыл бұрын

    አሜን አሜን አሜን ቃል ህይወት የስሚልና የፃዱቁ አባታችን አባ መቃርስ ረድኤታቸዉ በረከተችንዉ ኣይለያን

  • @user-jo3ou8yt3p
    @user-jo3ou8yt3p6 жыл бұрын

    አሜን አሜን አሜን ቃል ህይውት ያስማልን አሜን የአባ መቃርስ በረክት ከሁላችን ጋር ይሁን

  • @user-tu7du7xi1c
    @user-tu7du7xi1c2 жыл бұрын

    አሜን አሜን አሜን ቃለ ሂወት ያሰማልን የአባ መቃርስ ፆለት ልመናቸው ረድኤት በረከታቸው ይደርብን

  • @heedaakeedas5626
    @heedaakeedas56262 жыл бұрын

    አሜን አሜን አሜን ቃልህይወት ያሰማልን የአባ መቃርስ በረከትና እረድኤት ጾሎት ልመናችሁ አይለየን

  • @sarahamod7584
    @sarahamod7584 Жыл бұрын

    አሜን አሜን አሜን አባ መቃርስ ሆይ ነፍሳችን አደራ በሰማይ ፀሎት በረከታቸው አይለየን ሀገራችን ኢትዮጵያ ሰላም ያድርግልን

  • @bertyeshet2229
    @bertyeshet2229 Жыл бұрын

    የአባታችን የአባ መቃርስ በርከታቸው ይደርብን አዘጋጅተው ላቀርቡልን አባቶቻችን ቃለ ህይወት ያሰማልን የአባቶቻችን በርከት ይደርብን

  • @user-wt8mq9ho8l
    @user-wt8mq9ho8l6 ай бұрын

    አሜን አሜን አሜን የአባታችን መቃርሰ ረድኤት በረከት አይለየን 🙏

  • @nigat4478
    @nigat44782 жыл бұрын

    የአባታችን አባ መቃርስ በረከት ረድኤታቸዉ አይለየን አሜን

  • @sarahmohammed8130
    @sarahmohammed81302 жыл бұрын

    አሜን አሜን አሜን ቃለ ህይወት ያሰማልን የፃድቁ አባ መቃርስ ረድኤት በረከቱ ይደርብን አሜን፫

  • @teduadaayal2841
    @teduadaayal28412 жыл бұрын

    አሜን አሜን አሜን ቃለሂዎት ያሰማልን ያሰማን የቅዱስ አባ መቃርስ በረከት ፀሎት ልመና ይድረሰን አሜን አሜን አሜን🙏🙏🙏🙏🙏

  • @kabrneshayitodameitydamety8966
    @kabrneshayitodameitydamety89663 жыл бұрын

    ሁላችንም ቸሩ እግዚአብሔር ይቅር ይበለን ይህንኑ ላዝጋችሁልን ወንድሞቻችን ቃለህይወት ቃል ብርክትን ያስማልን የአባታችን የቅዱስ አባ መቃርስ ርዕደት ብርክቱ ከመላው ሕዝብ ክርስቲያን ጋር ይሁን አሜን

  • @user-cc8dx3ti7z
    @user-cc8dx3ti7z5 ай бұрын

    አሜን አሜን አሜን ቃለ ህወይት ያሰማልን የአባታችን ዬአባ መቃርስ ፆሎት ልመናዉ አይልይን ...😢🙏🙏

  • @brtukanleake1591
    @brtukanleake15912 ай бұрын

    እግዚአብሄር ይመስገን ቃል ሂዎት ያሰማልን የ አባ መቃርስ በረከት ይደርብን✝️⛪️✝️❤❤❤

  • @fatmaman2519
    @fatmaman25192 ай бұрын

    አሜን አሜን አሜን የአባቶቻችን እሬዴት ና በረከታቸው ይደርብን🙏🙏🙏🙏

  • @user-uu2mf7jr7i
    @user-uu2mf7jr7i4 жыл бұрын

    የኣባ መቃርስ ፀጋና በረከት ከኛ ከኦርቶዶክስ ተዋህዶ ይሁን ኣሜን ኣሜን ኣሜን

  • @rahelmamo4970
    @rahelmamo49702 жыл бұрын

    የአባ መቃርስ አምላክ እግዚአብሄር ይክበር ይመስገን አባቴ ረድኤት በረከቶት ይደርብን

  • @dfhd3103
    @dfhd31032 жыл бұрын

    አሜን የአባ መቃርስ በረከቱ እረዴኤት ይደርብን አሜን ቃለሂወት ቃለበርከት ያሠማልን ፀጋውን ያብዛላችሁ የአገልግሎት ዘመናችሁን እግዚአብሔር አምላክ ያስርዝምልን አሜን አሜን እግዚአብሔር ይመስገን የቅዱሳን እርዴኤት በረከታቸው ይደርብን አሜን

  • @mekdi1921
    @mekdi1921 Жыл бұрын

    የአባ መቃርስ በረከቱ ይደርብን በምልጃው ከመከራ ሥጋ ወነፍስ ያድነን🙏 አሜንንን

  • @sjddgkgf8204
    @sjddgkgf82042 жыл бұрын

    አሜን አሜን አሜን አምላካችን እየሱስ ክርስቶስ ይክበር ይመሥገን ያአባታችን ያባመቃርስ በረከታቸው ፀሎታቸው ይደረብብን

  • @user-oc8lk7kj2i
    @user-oc8lk7kj2i4 ай бұрын

    በእውነት በረከታቸው ረደኤታቸው ይደርብን የሰማንውን በልቦናችን ይሳልብን ❤❤ ፆለት ልመናቸው ይድረሰልን አሜን አሜን አሜን❤❤

  • @smerhsoso7490
    @smerhsoso74905 ай бұрын

    ናይ ኣቦና መቃርስ ፆሎቶምን በረከቶምን ኣይፈለየና

  • @alemneshalemu1599
    @alemneshalemu15994 жыл бұрын

    የአባታችን፡የአባ፡መቃርስ፡በርከቱ፡ልመናዉ፡ፆሎቱ፡ለእኔም፡ለቤተሰቦቸም፡ይደርብን

  • @samrayoutube7826
    @samrayoutube7826 Жыл бұрын

    አሜን አሜን አሜን ቃል ህወት ያስማልን🙏🙏🙏💒💒💒✝️🛐✝️🛐🛐📖📖📖❤❤❤❤❤❤💚💛❤️

  • @xbgg5952
    @xbgg595210 ай бұрын

    አሜን አሜን አሜን የአባታችን የቅዱስ የአባ መቃርስ በረከት ፆሎቶችው ይደርብን❤

  • @user-ip4uw9jm3x
    @user-ip4uw9jm3x6 жыл бұрын

    እግዚአብሄር አምላክ ለሁላችሁም ቃለ ህይወት ያሠማልን አሜን የፃድቁ አባ መቃር በረከት ይደርብን አሜን፫

  • @user-he9um6ty1y
    @user-he9um6ty1y6 жыл бұрын

    አሜን አሜን አሜን ቃለ ህይወት ያሰማልን ጸጋና በረከቱ ያደልልን የአባ መቃርስ እና የሁሉም ቅዱሳን አባቶች ጸሎት ልመናቸው በረከት ረዲአታቸው አይለይብን አሜን አሜን አሜን

  • @nadaahmed3993
    @nadaahmed39935 жыл бұрын

    እግዚአብሔር ሆይ እንደኔ በደል፥ሳይሆን እንዳንተ ይቅርታ የቅድሳኖችህ ምልጃ በረከት አይለየኝ ድንግል ማርያም ሆይ በእምነቴ እፀና ዘንድ በልጅሽ መስቀል ደጋግመሽ ባርኪኝ።አሜን፥አሜን፤አሜን።

  • @user-cp4xf3lk8t
    @user-cp4xf3lk8t7 ай бұрын

    አሜን አሜን አሜን ያባመካርስ እረዴታቸው በረከታቸው ምልጃቸው ይደርብን

  • @michaelmehari1053
    @michaelmehari10533 жыл бұрын

    በረከትን ረዲኤትን ኣማላዲነትን ናይ ኣባ መቃርስ ይሕደረና ብጸለትኩም ካብ ሓጥኣተይ ፍትሑን አሜን አሜን አሜን!

  • @user-sz8ry9xu9l
    @user-sz8ry9xu9l2 жыл бұрын

    አሜን አሜን አሜን ቃለ ህይወት ቃለ በርከት ያሰማልን የቅዱሳን የፀድቃን የስመዕታት የአባታችን የአባ መቀርሳ በርከት ረዴኤት አይለየን አሜን የሰማነዉን በልቦናችን ያሳድርብን አቤት ደስስስስ ማለቱ እግዚአብሔረ አምላከ በቃላችን ያፀናን የተግባር ሰዉ ያድርገን አሜን

  • @shitayehabteyes1689
    @shitayehabteyes1689 Жыл бұрын

    የአባ መቃርስ በረከታቸው ምልጃቸው አይለየን ይርደን በእውነት የሄን ላቀረባችሁልን እግዚአብሔር ይስጥልን።

  • @mooodeal1909
    @mooodeal19092 жыл бұрын

    የአባቶቻችን እና የእናቶቻችን የቅዱሳን በረከታቸው ይደርብን

  • @user-ji5rd2fb2h
    @user-ji5rd2fb2h2 жыл бұрын

    ኣሜን ኣሜን ኣሜን ቃለ ሂወት ያስማልን የኣባታችን ኣባ መቃርስ በረከታቸው በኛ ላይ ይደርብን

  • @SamsungAs-lo8bc
    @SamsungAs-lo8bc11 ай бұрын

    አሜን አሜን አሜን የቅዱስ መቃርስ እረድኤት በረከት ይደርብን

  • @lamlankam6633
    @lamlankam66336 жыл бұрын

    አሜን አሜን አሜን ቃለህይወት ያሰማልን ያሰማን የቅዱሳኑ ረድኤት በረከት ይደርብን በእውነት ደስስስስ የሚል ነው እግዚአብሔር ይስጥልን ሁላችንንም በቤቱ ያፅናን እማምላክ አትለየን በያለንበት ትጠብቀን

  • @user-tb5uv7jo7p
    @user-tb5uv7jo7p5 жыл бұрын

    ኣሜን ኣሜን ኣሜን የአባ ማቃርዮስ በረከትና ረድአታቸው ኣይለየን

Келесі