የአሁን ሃይል The Power of Now Book Summary In Amharic | Book Review in Amharic Ethiopia

The power of now(የአሁን ሃይል) መጽሃፍ፣ መንፈሳዊና ስነ ልቦናን አጣምሮ የያዘ መጽሃፍ ሲሆን፣ ሰዎች ከራሳቸውና ከሌሎች ጋር እንዴት ጤናማ ግንኙነት ሊኖራቸው እንደሚችል በስፋት ያቀርባል።
የመጽሃፉ ጭብጥ፣ አሁን ያለው ጊዜ ብቻ ነው እውነተኛና ጠቃሚ(only the present moment is real and matter.) ይላል። ያለፈውና የወደፊቱ በሃሳባችን የተፈጠሩ ናቸው። ሰዎች ህይወታቸውን እንዲቆጣጠሩ(control) መጠየቃቸው የሚያመጣው ትርፍ ቢኖር ህመምና ቅዥት ብቻ እንደሆነ ይገልጻል።
እንዲሁም በ አሁን ጊዜ (in the present moment)ራሳቸውን እንዲይዙ(እንዲሆኑ) ለመርዳት የመዝናናትና የማሰላሰል(meditation) ዘዴዎችን እንዲጠቀሙ ይጠቁማል።
ሙሉ መጽሃፉን ለማንበብ 👉 t.me/henokhirboro
▼ FOLLOW ME ▼
• Instagram : instagram.com/
• Facebook : / henokhirboro
• Telegram : t.me/henokhirboro
• TikTok : www.tiktok.com/henokhirboro
--------------------------------------------------------------------------------------------------------------
መግቢያ፥-
የዛሬ የመጽሃፍ ቅምሻችን እ አ አ በ1999 ለሁለተኛ ጊዜ በታተመ ወቅት የጋዜጠኞች ቁንጮና ንግስት በሆነቹ opera wenfrey ሊነበቡ ከሚገባቸው የክፍለ ዘመኑ ድንቅ መጽሃፍ ስትል ከመረጠችው በኋላ በሰሜን አሜሪካ ብቻ እስከ 2009 ባለ ጊዜ ውስጥ ከ3 ሚሊየን copy በላይ ለመቸብቸብ በቅቷል።
በ New York times(በመጽሃፍት ሽያጭ) bestselling books በመባል አንደኝነት ደረጃን መቆጣጠር የቻለና፣ ከ 33 በላይ በሚሆኑ የውጭ ቋንቋዎች ተተርጉሞ ፣ ተወዳጅነትን ያተረፈውን የ ኢካርት ቶሌ the power of now (የ አሁን ሃይል) የሚለው መጽሃፍ ነው።
ስለ ደራሲው(ኢካርት ቶሌ)፥-
በመግቢያ ላይ የሰማችሁት አሳዛኝ ታሪክ የዚህ መጽሃፍ ደራሲ የ ኢካርት ቶሌ ነበር። ቶሌ ትውልዱ ጀርመናዊ ሲሆን የመንፈሳዊ፣ ሜታፊዚክስ፣ እንዲሁም የself-help መጽሃፍት ደራሲ ነው።
እ አ አ 1977 በ 29 አመቱ በ አንድ ምሽት ከገጠመው እሱ) መንፈሳዊ ልምምድ) ከሚለው መገለጥ የተነሳ ፣ ውስጣዊ ለውጥ በማግኘቱና ከነበረበት ከባድ የጭንቀት በሽታ ከዳነ በኋላ ስሙን ከ ኤልሪክ ወደ ኤክህርት በመለወጥ በ አለም ዙሪያ ተወዳጅ የሆነውን የመጀመሪያ መጽሃፉን the power of now(የአሁን ሃይል) 1997 በቅቷል።
The power of now(የ አሁን ሃይል) መጽሃፍ መንፈሳዊና ስነ ልቦናን አጣምሮ የያዘ መጽሃፍ ሲሆን፣ ሰዎች ከራሳቸውና ከሌሎች ጋር እንዴት ጤናማ ግንኙነት ሊኖራቸው እንደሚችል በስፋት ያቀርባል።
ራስን የማሰላሰል(self-reflection)ና በ አሁን ጊዜ የመገኘት ጽንሰ-ሃሳብ(present in the moment) መርሆችን ቀለልባሉ ምሳሌዎች ያሳያል።
የመጽሃፉ ጭብጥ፥-
አሁን ያለው ጊዜ ብቻ ነው እውነተኛና ጠቃሚ(only the present moment is real and matter.) ይላል። ያለፈውና የወደፊቱ በሃሳባችን የተፈጠሩ ናቸው። ሰዎች ህይወታቸውን እንዲቆጣጠሩ(control) መጠየቃቸው የሚያመጣው ትርፍ ቢኖር ህመምና ቅዥት እንደሆነ ይገልጻል።
እንዲሁም በ አሁን ጊዜ (in the present moment)ራሳቸውን እንዲይዙ(እንዲሆኑ) ለመርዳት የመዝናናትና የማሰላሰል(meditation) ዘዴዎችን እንዲጠቀሙ ይጠቁማል።
ከእነዚህም መካከል ብዙ ተግባራትን በማስቀረት፣ ፍጥነት መቀነስ፣ ከተፈጥሮ ጋር ጊዜ ማሳለፍ፣ እንዲሁም ስለ ወደፊቱ ያለ ጭንቀቶችን መተው ያካትታል።
የመጽሃፍ ሁለት ቁልፍ - ጽንሰ ሃሳቦች
የመጀመሪያው 1 እኛ አእምሮ አችን አለመሆናችን ነው። (we are not our mind)
አብዛኞቻችን አውቀን(consciously) አእምሮአችንን አንጠቀምም።
ይልቁንም አእምሮአችን በማያቋርጥ ሃሳቦች እኛን ይቆጣጠረናል። ብዙ ጊዜም በእኔነት(ego-self) እንመራለን። Egoአችን ስለራሳችን ያለን አመለካከት ካለፈው ልምምዳችን እየቀዳ ፣ መሆን ስለምንፈልገው ደግሞ ከመጪው ጊዜ ይመገባል። ስለ ራስህ ያለህ አመለካከት ያለፈው ህይወት ድምር ውጤት ከሆነና መጪውን ጊዜም ከዚህ መነሻ የምታይ ከሆነ በጊዜ ቅዥት ውስጥ ገብተሃት። አላፊውም ሆነ መጪው ያለው አእምሮው ውስጥ ነው።
አብዛኛው ጉልበታችንን የምናሳልፈው ባለፈው አሊያም በመጪው ጊዜ ላይ እንጂ በአሁኑ ጊዜ አይደለም።
ብዙ ጊዜ እምቅ አቅማችንና ሃይላችን የሚያልቀው ከ አሁን (present moment)
ይልቅ በ አለፈው(ልንለውጠው በማንችለው) ወይም በመጪው(በማናውቀውና እርግጠኛ መሆን በማንችልበት) ላይ መሆኑ ያሳዝናል።
ብዙዎቻችን አሁን ላይ የለንም(Absent) ነን። በአእምሮአችን ሃሳብ አለም ያለፈው ጊዜ ላይ አለኢያም ደግሞ ስለመጪው በማሰብና በመጨነቅ እንቆያለን። በዚህም ሁልጊዜ የ አሁንን ሃይል በማባከን ተጠምደናል።
የ አሁን እርግጠኛ ልትሆንበትና እውነት(real) የሆነ ጊዜ ነው። ህይወት ሁሌ የምታስጨንቀንና የምታስፈራራን በማናውቀውና እውን ባልሆነ በመጪውና በወደፊት ጊዜ ላይ ቆማ ነው። በትላንትናና በዛሬ ላይ ምንም ስልጣን እንደ ሌላት ታውቃለች። ማንም ሰው ስለመጪው እንጂ ስላለፈው ሊጸጸት ይችል ይሆናል እንጂ ሊጨነቅ አይቻልም። ዛሬም ቢሆን በእጅ ያለች ቀን ናት አሁን ደግሞ ከዛሬ ይልቅ ሃይል አላት።
ሁለተኛው 2 እራሳችንን ከ አእምሮአችን እንዴት ነጻ እናደርጋለን(how do we free ourselves from our minds?) አእምሮህን(የምታስበውን ሃሳብ) በንቃት ተከታተል(observe your mind)
ይህ ማለት (የምታስበውን አስብ) እንደሚሉት ማለት ነው። ካለፈው ጊዜ ትኩረትህን ሰብሰብ በመጪው ጊዜ በሃሳብ ከመንጓዝ ለሃሳብህ ሉጋም አበጅለት። ከማያስፈልጉ የትላንት ትዝታዎች ከማታውቀው ከመጪው ጊዜ ፍርሃት አእምሮህ በአሁን ላይ ይሁን። ትኩረትህን በ አሁን ላይ መሰብሰብን ተማር።
አእምሮህ በትላንት እንዲያላዝን ፣ በመጪው ደግሞ በፍርሃት እንዳይቆዝም ሁሌ አሁን ላይ አድርገው።
ስሜትህን ተመልከት(watch your emotion)የሰው ልጅ በቀን ከ 60.000 በላይ ሃሳቦች እንደ ሚያስብ ጥያቶች ያሳያሉ። እነዚህን ሁሉ ሃሳቦች መቆጣጠርና በንቃት መከታተል እጅግ በጣም ከባድና አድካሚ ነው። ሁሉንም ሃሳቦች መከታተል ስለማንችል፣ ሀሳቦች በስሜት(emotion)በኩል እራሳቸውን ስለሚገልጡ፣ ስሜታችንን(emotion)ናችንን በንቃት መከታተል እንችላለን። ይህም አእምሮ አችን አሁን ላይ እንዲሆን ለማስገዛት ይረዳናል።
ለ አሁን ተገዛ (surrender to the present) አንዳንድ ያለፉ የህይወት ልምምዶቻችን ህመምን እና አሉታዊ ውጤትን ይፈጥሩብናል። በዚህም አሉታዊ ሃይል ይጨምራል። ለ አሁን መገዛት እጅ መስጠትን፣ ድክመትን ወይም ሁሉን መተው ማለት አይደለም። ይልቁኑ ጤናማ ያልሆኑና አሉታዊ የትላንት መርዛማ ትዝታዎች ያለፈው ጊዜ ላይ ባሉበት መጣል እና ከ አሁን ሃይል ጋር መገናኘት ነው።
-----------------------------------------------------
የመጽሃፉ ደራሲ አሳዛኝ ታሪክ - 00:00
መግቢያ - 02:31
የመጽሃፉ ጭብጥ - 04:14
እኛ አእምሮአችን አይደለንም - 05:12
ከአእምሮ ነጻ መውጣት - 07:14
የምታስበውን አስብ - 07:29
ስሜትህን ተመልከት - 08:09
ለአሁን ተገዛ - 08:50
ማጠቃለያ - 09:24
ስንብት - 10:19

Пікірлер: 76

  • @yodit587
    @yodit587 Жыл бұрын

    Thank you 🙏

  • @bezawittesfaye922
    @bezawittesfaye922 Жыл бұрын

    Keep up Henok. Enamesegnalen.

  • @eduofabera8738
    @eduofabera8738 Жыл бұрын

    Thank you so much bro

  • @hopeeleverlast3092
    @hopeeleverlast3092 Жыл бұрын

    Amazing Bro this is Wondering.....!

  • @biltek2030
    @biltek2030 Жыл бұрын

    thank you my brother, best explanation , clear and precise review. keep it up on !!!

  • @afomiaafomias4950
    @afomiaafomias4950 Жыл бұрын

    Thank you my Dear, BEST EXPLANTION ❤

  • @LucyTip
    @LucyTip Жыл бұрын

    Tnx a lot Mr Henok its Amazing 👍

  • @fikirhaile4461
    @fikirhaile4461 Жыл бұрын

    Thanks a lot👍

  • @mitikuabiyo9099
    @mitikuabiyo9099 Жыл бұрын

    U r really amazing bro..thank you for ur review..keep it up

  • @siye251
    @siye251 Жыл бұрын

    Amazing

  • @Elaweddngstudio1310
    @Elaweddngstudio1310 Жыл бұрын

    Thanks bro.

  • @lishantekabe8760
    @lishantekabe8760 Жыл бұрын

    Amazing book I have never read.... Thank you

  • @bemenettassew5191
    @bemenettassew5191Ай бұрын

    Thank you

  • @ngestiturebab9655
    @ngestiturebab9655 Жыл бұрын

    Thank you bro

  • @genettekle1239
    @genettekle1239 Жыл бұрын

    Thx

  • @hamelmalmesfin9918
    @hamelmalmesfin9918 Жыл бұрын

    በጣም አመሰግናለው ወንድሜ🙏 የሚገርም መጽሐፍ ነው❤️🙏

  • @kenenisabedasa
    @kenenisabedasa Жыл бұрын

    Amaizing broo this is great book now i am interested to read it thankyou very much for sharing such kind of useful informations

  • @eth806
    @eth806 Жыл бұрын

    amazing Bro!

  • @temu_rb7147
    @temu_rb7147 Жыл бұрын

    Nice of you dude

  • @getnetlakew3923
    @getnetlakew3923 Жыл бұрын

    I like it

  • @muludessetaw1166
    @muludessetaw1166 Жыл бұрын

    telek sera new...! tevarek.

  • @gammachuamantee3263
    @gammachuamantee3263 Жыл бұрын

    Wow

  • @temesgensebro7011
    @temesgensebro70116 ай бұрын

    Thanks Heni! Try to review "Emotional Intelligence" book by Daniel Goleman.

  • @mussafentaw8653
    @mussafentaw8653 Жыл бұрын

    እምትለቃቸው መፃሀፍቶቾ በትርጉም አልያም በትረካ እደዴት ማግኘት እችላለን ሰራዎችህን በጣም አነቃቂ ናቸው

  • @fuadabdulfeta5029

    @fuadabdulfeta5029

    Жыл бұрын

    tedel tube የአሁን ሀይል ብለህ ማግኘት ትችላለህ ።

  • @tube-yi8tg

    @tube-yi8tg

    Жыл бұрын

    ​@@fuadabdulfeta5029 በአማርኛ ተተርጉሞ በበመፅሀፍ ይሸጣል እንደ

  • @hilejamal4650
    @hilejamal4650 Жыл бұрын

    The way you approach and ur voice very nice and the concept also nice keep it up

  • @henokhirboro

    @henokhirboro

    Жыл бұрын

    Thank Hile

  • @emebetdesta7003
    @emebetdesta7003 Жыл бұрын

    👍

  • @yematagetaneh-ol3tr
    @yematagetaneh-ol3tr Жыл бұрын

    ❤❤❤

  • @mulukenw.mariam3193
    @mulukenw.mariam3193 Жыл бұрын

    Betam arif tireka newu ketilibet.....dimtsi desi yilala

  • @henokhirboro

    @henokhirboro

    Жыл бұрын

    Thank You Bro😀

  • @abebechkebede9528
    @abebechkebede952810 ай бұрын

    Selam lemanbeb betam efelfalhu pls kechalc bamargia yetergime pls

  • @yitayalgashaw7601
    @yitayalgashaw76012 жыл бұрын

    Henok super man

  • @henokhirboro

    @henokhirboro

    Жыл бұрын

    ይታይ ድንቅ ሰው፣ Sometimes the path is not clear to us, only the place we step on becomes light, but the closer we get, the darkness flees, we get closer to our goal.... There is always hope for those who hope. DO or DIE ብሮ፣ i am proud of you እኮራብሃለሁ ቀጥል፣

  • @jesuschristislord6940
    @jesuschristislord6940 Жыл бұрын

    I am reading this book now, I can't tell you how amazing it is!. Thank you for presenting its review, I liked 👍 it! Keep up the good work!

  • @henokhirboro

    @henokhirboro

    Жыл бұрын

    Thank You! JESUS IS LORD

  • @henockandualem5332

    @henockandualem5332

    Жыл бұрын

    How to download this book,plz

  • @yakobebogale4787
    @yakobebogale4787 Жыл бұрын

    ye migerme ergata bro

  • @michaelmulugeta3111
    @michaelmulugeta3111 Жыл бұрын

    the power of now ye Eckhart tolle ye megrme spirtual sew nw cheneketn le matefte or edanasebe wesagn መፅሐፍ nw present Moments wusti conscious honene endenerore yenegrnale yemir anebebute dmo A NEW EARTH Awakening to Your Life's Purpose lelagnwe germi መፅሐፍ nw Hena enamsegnalen selakerbkelen berta bro

  • @henokhirboro

    @henokhirboro

    Жыл бұрын

    ሚኮ ፣ ምርጥ ጥቆማ ነው፣ Thank you bro for your warm compliment

  • @user-ez2pn3xr2u
    @user-ez2pn3xr2u Жыл бұрын

    በጣም ምርጥ ነው ቀጥልበት

  • @henokhirboro

    @henokhirboro

    Жыл бұрын

    Thanks ፈትህ

  • @danielsolomon9952
    @danielsolomon9952 Жыл бұрын

    hiro hibro mirt akerare aterarekeh arif new

  • @henokhirboro

    @henokhirboro

    Жыл бұрын

    Thank you Danisha

  • @dn.ketemagofie
    @dn.ketemagofie9 ай бұрын

    10q bro

  • @yummybaraki
    @yummybaraki Жыл бұрын

    '12 Rules for life' Jordan B. Peterson

  • @henokhirboro

    @henokhirboro

    Жыл бұрын

    i will very Soooon

  • @senaityemane8946
    @senaityemane89462 жыл бұрын

    እንኩዋን ደና መጣህ

  • @henokhirboro

    @henokhirboro

    Жыл бұрын

    እንኳን ደህና ቆያችሁን lol Tnx seni

  • @user-wr3jj4lm1f
    @user-wr3jj4lm1f14 күн бұрын

    Eckhart Tolle bemayete desitegna negn

  • @henokhirboro

    @henokhirboro

    13 күн бұрын

    tnxs

  • @henockandualem5332
    @henockandualem5332 Жыл бұрын

    How to download this book

  • @nazrietkidane8909
    @nazrietkidane8909 Жыл бұрын

    Atomic habit please

  • @henokhirboro

    @henokhirboro

    Жыл бұрын

    kzread.info/dash/bejne/dH9hraVvesiwk84.html

  • @selameyeeliyas4344
    @selameyeeliyas4344 Жыл бұрын

    Brother is there Amharic translated version of this book pls?

  • @henokhirboro

    @henokhirboro

    Жыл бұрын

    t.me/henokhirboro/654

  • @kasahunniguse2061
    @kasahunniguse2061 Жыл бұрын

    በጣም አመሰግናለሁ ወንድሜ ግን ወደ አማረኛ ተትርጉም የለሺም? ካለ እባክህ።

  • @kalbakilo3673
    @kalbakilo3673 Жыл бұрын

    Brother pls መፃሀፍቶችን መግዛት እፈልጋለሁ የት አካባቢ ነው የማገኘው

  • @henokhirboro

    @henokhirboro

    Жыл бұрын

    አዲስ አበባ ውስጥ ያሉ ድንቅ መጽሃፍት መደብሮች ከብዙዎቹ በጥቂቱ፣ ጃፋር(ለገሃር እንዲሁም ሜክሲኮ ድብረወርቅ ህንጻ አካባቢ)፣ Book wold(መስቀል አደባባይ ቀይ ሽብር ሰማእታት ጎን)፣ Book Site(ቦሌ ብራስ ፊት ለፊት ) በክልል ከተሞች ሃዋሳ( ሲሚር መጽሃፍ፣ ከሳውዝ ስታር ሆቴል ወደ ገብርኤል በሚወስደው መንገድ በስተ ቀኝ በኩል) እንዲሁም ነጻ E-book ለማግኘት z-lib.org/ ይህን ሊንክ መጠቀም ትችላለህ

  • @haymanotgizachew
    @haymanotgizachew Жыл бұрын

    in amharic tatimoal

  • @henokhirboro

    @henokhirboro

    Жыл бұрын

    you can get from my telegram channel

  • @adu4451
    @adu4451 Жыл бұрын

    Please be Amharic audio yelem

  • @henokhirboro

    @henokhirboro

    Жыл бұрын

    በ አማርኛ audio search አረኩኝ ላገኝ አልቻልኩም፣ መጽሃፉ በ አማርኛ ሳይተረጎም አይቀርም እርግጠኛ አይደለሁም You can check this link in English በ አማርኛ audio search አረኩኝ ላገኝ አልቻልኩም፣ መጽሃፉ በ አማርኛ ሳይተረጎም አይቀርም እርግጠኛ አይደለሁም You can check this link in English kzread.info/dash/bejne/l4VnxpmNlMrHZ5s.html

  • @ashenafiregassayeamarechle5497
    @ashenafiregassayeamarechle5497 Жыл бұрын

    Yet new megezat yemechelw pls

  • @henokhirboro

    @henokhirboro

    Жыл бұрын

    Bole or Stadium Jafar BOOK Store

  • @kifleabebew9568
    @kifleabebew9568 Жыл бұрын

    ሰላም ውድ ሄኖክ እንዴት ነህ የኢካርት ቶሌ መጽሀፍትን በአካባቢየ አጠሁ ብትልክኝ እባክህ ስልክህን ባገኝ ወንድሜ?

  • @henokhirboro

    @henokhirboro

    Жыл бұрын

    0943803489

  • @slmonselmo1067
    @slmonselmo1067 Жыл бұрын

    Wow

  • @kasahunniguse2061
    @kasahunniguse2061 Жыл бұрын

    በጣም አመሰግናለሁ ወንድሜ ግን ወደ አማረኛ ተትርጉም የለሺም? ካለ እባክህ።

  • @henokhirboro

    @henokhirboro

    Жыл бұрын

    አሁን ላይ የለኝም ግን ካገኘው አሳውቅሃለሁ።

  • @biltek2030

    @biltek2030

    Жыл бұрын

    kzread.info/dash/bejne/o4l1j9qHZ7ucqrg.html ON TEDEL TUBE ( THE POWER OF NOW Amharic Audio)

  • @kasahunniguse2061
    @kasahunniguse2061 Жыл бұрын

    በጣም አመሰግናለሁ ወንድሜ ግን ወደ አማረኛ ተትርጉም የለሺም? ካለ እባክህ።

  • @mulkaahmed8725

    @mulkaahmed8725

    Жыл бұрын

    Ale

  • @etumeskinigusse4822

    @etumeskinigusse4822

    Жыл бұрын

    Yemsethafun teregum /beamarignaw/ yet enagegnew

  • @jemaljemalmohamed3207

    @jemaljemalmohamed3207

    Жыл бұрын

    አለ በድምፅ የአሁኑ ሀይል ይላል

Келесі