የማይታመን ገጠመኝ🙃 ከደራሲው አንደበት | The Power Of Now እንዴት ተጻፈ |

Ойын-сауық

The Power Of Now እንዴት ተጻፈ የማይታመን ገጠመኝ፣ ከደራሲው አንደበት
ሙሉ መጽሃፉን ለማንበብ 👉 t.me/henokhirboro
▼ FOLLOW ME ▼
• Instagram : instagram.com/
• Facebook : / henokhirboro
• Telegram : t.me/henokhirboro
• TikTok : www.tiktok.com/henokhirboro
--------------------------------------------------------------------------------------------------------------
ለተወሰኑ አመታት ሰዎችን በማማከር ና በተለያዩ ትንንሽ ስብሰባዎች ላይ በመጋበዝ ንግግሮችን አደርግ ነበር። ከማደርጋቸው ንግግሮች አብዛኛው መንፈሳዊ ንግግሮች ነበሩ። እናም ንግግር ካደረግኩ በኋላ ወይም የምክር ክፍለ ጊዜ ከለቀ በኋላ፣ ብዙ ጊዜ ያደረኳቸውን ንግግሮችም ሆነ የሰጠሁትን ማንኛውንም ምክሮች ብዙም ሳልቆይ በማስታወሻ ደብተሬ ላይ የመጻፍ ልማድ ነበረኝ። በዚህም የተናገርኳቸውን ነገሮች እጽፍ ነበር። እናም የተናገርኳቸውን እነዚህ ሃሳቦችና ንግግሮች በምጽፍበት ጊዜ ከዚህ በፊት የማላውቀውን ብዙ ነገር ተናግሬ እንደነበር ወደ መረዳት መጣሁኝ።
በፊት የማላውቃቸውን ነገር ግን ንግግር በማደርግ ጊዜ የተናገርኳቸው እነዚያ ቃላት፣ ከውስጡ ማንነቴ የሚመነጩ ነበሩ። እነዚህም ነገሮች እናገረው የነበረው ከተሰበሰብ ሰው መሃል ለሚቀርብልኝ ጥያቄዎች ምላሽ በምሰጥበት ጊዜ ነበር።
አንድ ሰው ጥያቄን ሲጠይቅ ወይም ላለበት ችግር መፍትሄ ፍለጋ ሲጠይቀኝ ፣ እኔም ለዚያ ጥያቄ ወይም ችግር ምላሽ ና መፍትሄ ስሰጥ እነዚህን አዲስ ሃሳቦች ከውጥጣዊ ማንነቴ እየፈለቁ እንደነበር ገባኝ። በርግጥ እነዚህን ነገሮች ከዚህ በፊት ባላውቃቸውም ያደረኩትን ንግግሮችና ምክሮች በምጽፍበት ጊዜ እነዚህ ነገሮች አዲስና የተለዩ ሃሳቦች እንደሆኑ ወደ መረዳቱ መጣሁኝ።
ስጻፍቸው የነበረሩ እነዚህ ሁሉ ማስታወሻዎች ከአመታት በኋላ ፣ በመጨረሻ ወደ መጻፍነት ማደግ እንደሚችሉ ወደ መረዳቱ መጣሁኝ። ግን የጻፍኳቸው ማስታወሻዎቹ ብቻቸውን ገና መጽሐፉ እንዳልሆኑ አውቅ ነበር። ነገር ግን አንድ ወደዚህ አለም ሊወለድ ያለ መጽሃፍ በውስጣቸው አዝለው እንደነበር ግን ውስጥ ውስጡን የሚሰማኝ ስሜት ነበር። ይህ ስሜት ግን የማይቀረውን እነዚህ ማስታወሻዎች ወደ መጽሃፍ መለወጥ ወይም ደግሞ በጠራ መልኩ የሚጻፈው ጉዳይ ምን እንደሆነ በውል ማወቅ በሚሉ ሁለት ጉዳዮች ግማሽ መንገድ ላይ የተንጠለጠለ ነበር።
በውስጤ ሊጻፍ ያለ አንድ መጽሃፍ አለ። ነገር ግን መጽሃፉ በውል ምን እንደሆነና ምን ስያሜ እንደምሰጠው ገና አላወኩም ነበር። ይህ መጽሃፍ እውን መሆን ከቻለ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን ሕይወት የሚቀይር እና ንቃተ ህሊናን የሚፈጥር አንድ ድንቅ መጽሃፍ ወደ ምድራችን እያመጣሁኝ እንደሆነ እርግጠኛ ነበርኩኝ። በመጨረሻም ጽፍኩት! በምጽፍበት ወቅት ውስጤን ሲታገለኝ የነበረውን ሃይለኛ ስሜት በቃላት ለመግለፅ ይከብዳል።
በእርግጠኝነት የማውቀው ነገር ይህን መጽሃፍ በመጻፍ መካከል፣ ግማሽ መንገድ ላይ፣ የተወሰነ እውነታና አንድ ነገር ለመግለጥ በመፈለግ እራይ ውስጥ ነበርኩኝ። አንድን ነገር ለመግለጥ መፈለግና እንደተገለጠ አድርጎ ማየት ሁለት የተለያዩ ነገሮች ናቸው።
ለምሳሌ አንድን ነገር ለማየት ፈልጋችኋል ማለት ቀድሞኑ ያ ስሜት እናንተ ውስጥ አለ ማለት ነው። ይህንንም በሚታየው አካላዊ Universe ውስጥ ማየት አይቻልም። ስለዚህ ይህ መፅሃፍ አስቀድሞ በውስጤ እንዳለ አውቄ ነበር። አሁን አልቆ በእጃችሁ የገባውና ያነበባችሁት መጽሃፍ አስቀድሞ እንዳለ የማውቀው ሲሆን የእኔ ስራ የነበረው ከማይታየው አለም ቀድሞ የነበረን ነገር በዚህ ገሃዱ አለም እውን እንዲሆን ማንጸባረቅ ወይም መግለጥ ብቻ ነበር።
ይህም በወረቀት ላይ ትንሽ ክብ ሰራሁኝ፣. በሰራሁት ክብ መሃል መጽሐፉ አለ። በዚህ ወቅት ለመጽሃፉ ርእስ አልነበረውም ። እናም እንዲህ ብዬ በዙሪያው መስመሮችን ከክቡ ውስጥ እያወጣሁኝ መጻፍ ጀምርኩ። ይህ መጽሃፍ ታትሞ ይፋ ሲሆን በዓለም ዙሪያ ንግግሮችን እሰጣለሁ፣ በዚህም በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ይህን ንግግር ለማዳመጥ ይመጣሉ ይህን ከመሆኑ በፊት አውቄው ነበር።
በአጭሩ በሰአቱ አደርገው የነበረው የወደፊቱን ለመፍጠር ከመፈለግ ይልቅ የወደፊቱን ለመተንበይ እየሞከሩርኩኝ ነበር። በዚህ መሃል መፅሃፍ አለ፣ ንግግር ለማድረግ የማደርገው ጉዞ፣ ከዛ ደግሞ ሌላ የፃፍኩት የመሰለኝ መፅሃፍ ነበር ተጨማሪም የፃፍኳቸው የተለያዩ ነገሮች ነበሩ።
በሕይወቴ ውስጥ ባሉ ነገሮችም ሆነ ሁኔታዎች የበለጠ ደስተኛ እንደሆኑንኩና በቂ ገንዘብ እንዳለኝ ጻፍኩኝ። ስለ ገንዘብ በእውነቱ አልተጨነቅም ምክንያቱም ለብዙ አመታት ባለኝ ጥቂት ነገር የመኖርን ጥበብ ሰለተማኩኝ በዚህም በጣም ደስተኛ ነበርኩ።
ኑሮዬ ይበቃኛል ማለትን መማሬ በህይወቴ ውስጥ ብዙ ደስታና ተጨማሪ ሃብት እንዲኖረኝ አደረገ። ከዚህ መጽሃፍ መጽሃፍ በኋላ የሚኖረኝ በጣም አስደሳች የሆነ የኑሮ ሁኔታን በዚህ መልክ ጻፍኩ። ከማንነቴ ጋር የተገናኙ እንዲህ ያሉ ሌሎች ጥቂት ነገሮችም አክዬበት ዘውትር ላየው በምችልበት ቦታ ግርግዳ ላይ ለጠፍኩት።
የጻፍኳቸውን እነዚህን ነገሮች ለምን ያህል ጊዜ በግርግዳው ላይ እንደቆዩ በውል ባላስታውስም፣ ምናልባትም ለብዙ ሳምንታት ዘውትር እያየኋቸው በዚህ መልክ ቶይተው ይሆናል። በእነዚህ ሳምንታት በእሱ ላይ አተኩሬ በየቀኑ ግድግዳዬ ላይ በጻፍኳቸው ነገሮች እራሴን ሆኜ አየዋለሁ። ይህንም ያለማቋረጥ አደርግ ነበር።
ነገር ግን ብዙ ጊዜ ከቦታ ቦታ ስለምንቀሳቀስ፣ ይህ ወረቀትና የጻፍኩት ሁሉ ተረሳ። ፣ ካሉኝ ወረቀቶች መሃል የሆነ ቦታ ገባና በዚህ መልክ ሁለት ወይም ሶስት ዓመታት አለፉ።ከእነጭራሹ ወረቀቱን እንደፃፍኩ ሙሉ በሙሉ ረሳሁት።
ከዚያም የተለያዩ ነገሮች ተከሰቱ፣ ወደ ዝርዝር ጉዳዮች ሳልገባ፣ ድንገት ይህ የኃይል ዥረቱ በውስጤ ገባና መጽሐፉ በድንገት በድጋሚ ከአመታት በኋላ መፃፍ ጀመርኩ። በፊት ከጻፍኳቸው ማስታወሻዎች ውስጥ በጥቂቱ ተጠቅሜያለሁ ግን እነሱ መጽሐፉ አይደሉም። መጽሐፉ ኃይል ያለው የኃይል ፍሰት ነበር።
ያ ወረቀት ና በዚያ ወረቀት ላይ የጻፍኩት አንዳንዶች ቪዥን ቦርድ ብለው ይጠሩታል, ይህን ከፍተኛ የሆነ የሃይል ፍሰት በውስጤ ከአመታት በኋላ ማለፍ ሲጀርምር የዚያ ውጤት እንደሆነ በጥቂቱም ቢሆን ተረድቼ ነበር። ግን ሙሉ በሙሉ ያየጻፍኩትና ያለመኩት ነገር እየሆነ አልነበረም በጣም ጥቂት በጥቂቱ ነበር ነገሮች እየሄዱ የነበሩት።
ንግግር አደርግም የነበረው በጣም ጥቂት ለሆኑ ሰዎች ነበር። ይህም የሚናቅ አልነበረም
ጥሩ ነው፣ ነገር ግን ብዙዎችን መርዳት እንደምችል አውቃለሁ።ታዲያ ያ ለምን አይሆንም? ነገሮች ለምን ባለምኳቸውና ባሰብኳቸው መጠን በሙላት አልሆኑም? ከዚያ በኋላ አንድ ተጨማሪ ጸሎት አደረግሁ፣
እንደማስታውሰው ከሆነ ለአንድ ጊዜ ወይም ሁለት ጊዜ ይሆናል ይህን ጸሉት ያቀረብኩት። በጊዜው በእንግሊዝ ውስጥ በምትገኝ ሱመርሴት በምትባል ትንሽ መንደር ውስጥ ነበር የምኖረው። በዚህች መንደር አንድ አነስተኛ ቤተክርስቲያን ውስጥ ገባሁ፤ ቤተ ክርስቲያኗ አነስተኛና ባዶ ነበረች። እዚያ ተቀምጬ ምልክቶቹን ተመለከትኩ እና ዝም ብዬ አንድ እንግዳ ነገር በጸሎት መልክ ጠየቅሁ ።
በመደበኛነት ነገሮችን የምጠይቅ ሰው አይደለሁም ፣ ነገር ግን የጠየቅኩት ነገሮች እንዲፈጡ ወይም በህይወቴ እየሆነው ያለው ነገር እንዲፈጥን ነበር። እንዲህም ብዬ በጸሎት ጠየኩ “መፋጠን እጠይቃለሁ” አልኩት። እንዳሰብኩትና እንደጻፍኩት እየሆነ እንደሆነ አውቃለሁ ነበር ግን ሂደቱ በጣም ቀርፋፋ ነበር። ስለዚህ መፍጠን የሚለውን ጠየኩ። ጸሎቴም እንደተሰማ ይሰማኝ ነበር። ምክንያቱም በሆነ መንገድ ቀድሞውኑ በራሴ ውስጥ የመፍጠን ፍላጎትና እውነታ እየተሰማኝ ነበር።
ይህ ከሆነ ብዙም ሳይቆይ ሁሉም ነገር በሕይወቴ ውስጥ መለወጥ ጀመረ። ነገሮች በፍጥነት መቀያየር ጀምሩ። ከምኖርበት አካባቢ ርቄ መሄድ እንዳለብኝ ውስጣዊ ግፊቱ ከፍተኛ ነበር። በዚህም ያለኝን ሁሉንም ነገር ሽጬ ወደ ሰሜን አሜሪካ ምዕራባዊ የባህር ዳርቻ አዲስ ኑሮዬን ሃብዬ ጀመርኩ። እዚያም እያለሁ ብዙም ሳልቆይ በድንገት መጽሐፉ ወጣ። ነገሮች በዚህ መልክ በፍጥነት መለዋወጥ ጀመሩ።
The Power of Now መጽሃፌ ታትሞ ለገበያ ሲቀርብ። በአጭር ጊዜ ውስጥ በሚሊዮን የሚቆጠሩ አንባቢዎች እጅ ለመድረስ በቃ። እኔም በእነዚህ መጽሃፍ ላይ የክብር ፊርማዬን እንዳሳርፍ በሚወተውቱኝ አድናቂዎቼ ተከበብኩ። መጽሃፍ አሁን ላይ ወደ ምን ያህል ቋንቋዎች ተተርጉሞ ለንባብ እንደበቃ አላስታውስም።
#henokhirboro #abelbirhanu #tadel #ethiopia #inspireethiopia #habesha #manyazewaleshetu #dawitdreams
#tedeltube

Пікірлер: 8

  • @kifleabebew9568
    @kifleabebew9568 Жыл бұрын

    ሄኖኬ እባክህ የዚህን ሰው መጵሀፎች በጣም እፈልጋለሁ እኛ አካባቢ አጠሁት ብታግዘኝ?

  • @temesgensebro7011
    @temesgensebro70116 ай бұрын

    Heni, you are blessed! Please, try to translate and work on summary of "Emotional Intelligence" book by Daniel Goleman

  • @alemhishe6794
    @alemhishe6794 Жыл бұрын

    Thank you Bro🙏 🙏 🙏

  • @esubrass97
    @esubrass97 Жыл бұрын

    ❤❤ thanks

  • @hopeeleverlast3092
    @hopeeleverlast3092 Жыл бұрын

    Man this was really very help full, talented and professional !!! Strengthen Your muscle, You have many legacies to do.......GOD Bless You more.....!

  • @saralec1311
    @saralec1311 Жыл бұрын

    Good job 👏

  • @danielsolomon9952
    @danielsolomon9952 Жыл бұрын

    ድንቅ አተራረክ

  • @staylumer4049
    @staylumer4049 Жыл бұрын

    🙏🙏🙏💞

Келесі