መዝሙር ይትፌሣሕ ጸናጽል

Ойын-сауық

(በ፩/ዩ) ይትፌሣሕ ሰማይ ወትትሐሠይ ምድር ወይንፍሑ ቀርነ መሠረታተ ሕምዝ ወይወውዑ አድባር ወአውግር ወኵሉ ዕፀወ ገዳም ወዮምሰ ዓባይ ፍሥሐ በሰማያት ወምድርኒ ትገብር ፋሲካ ተሐጺባ በደመ ክርስቶስ።
ትርጕም፦
ሰማይ ደስ ይለዋል ምድርም ደስ ይላታል የምድር መሠረቶች መለከትን ይነፋሉ ተራራዎቹ ኮርብታዎቹ የምድረ በዳ እንጨቶች ሁሉ ይጮሃሉ ዛሬ በሰማያት ታላቅ ደስታ ነው ምድርም በክርስቶስ ደም ታጥባ ፋሲካን ታደርጋለች።

Пікірлер

    Келесі