በነብርና ዘንዶ የሚጠበቀው ምስካበ ቅዱሳን ዮርዳኖስ መድኃኔዓለም አንድነት ገዳም | ንስር አጽመ ቅዱሳንን የሚያሳርፍበት ስፍራ | orthodox tewahedo

ምስካበ ቅዱሳን መድኃኔ ዓለም አንድነት ገዳም
ምስካበ ቅዱሳን ዮርዳኖስ መድኃኔዓለም ገዳም በሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት በሞጃና ወደራ ወረዳ በፊላገነት ቀበሌ ገበሬ ማኅበር የሚገኝ ገዳም ነው፡፡
ምስካበ ቅዱሳን ዮርዳኖስ መድኃኔዓለም ገዳም ከአዲስ አበባ ከተማ በስተሰሜን አቅጣጫ በደሴ በር180 ኪ.ሜ. ከተጓዙ በኋላ ከጣርማ በር ከተማ ወደ ግራ የሚታጠፈውን ጠጠራማ መንገድ 17 ኪ.ሜ. እንደተጓዙ ሰላድንጋይ ከተማ ይደርሳሉ፡፡
ከሰላድንጋይ ከተማ በስተምዕራብ አቅጣጫ 4 ኪ.ሜ. ርቀት እንደተጓዙ በፊላገነት ቀበሌ ገበሬ ማኅበር ሁለት አነስተኛ ጉብታዎች መካከል ምስካበ ቅዱሳን ዮርዳኖስ መድኃኔዓለም ገዳምን ያገኛሉ፡፡
ገዳሙ ቀደሞ “አስከሬን ዋሻ” በመባል ይታወቅ ነበር፡፡ አስከሬን ዋሻ የተባለበትም በአካባቢው የነበሩ አባቶች ልዩ መዓዛ ያለው የዕጣን ሽታ ይሸታቸዋል፡፡ የከበሮ ድምጽ በተደጋጋሚ ይሰማሉ፡፡ ከዚህም ሌላ ነጭ አሞራ ትኩስ አስከሬን ይዞ በመምጣት med3 2007 2በቅድሚያ ከገዳሙ ፊት ለፊት ያለው “ጭንጫ ውድማ” ተብሎ የሚታወቀው ሜዳ ላይ ካሳረፈ በኋላ ቀጥታ ከወይራው አጠገብ ያለው ዋሻ ውስጥ አጽመ ቅዱሳንን በክብር ሲያስቀምጥ ይመለከታሉ፡፡
ወደ ስፍራው ሂደው በሚያዩበት ጊዜ በበፍታ፣ በቆዳ እና በሸራ የተገነዙ የቅዱሳን አባቶች አጽም ከመጻሕፍቶቻቸው እና መቁጠሪያቸው ጋራ ያገኙ ስለነበር “አስከሬን ዋሻ” እንደተባለ የገዳሙ አስተዳዳሪ መጋቢ ተክለ ጻዲቅ ሸዋረጋ ያስረዳሉ፡፡
ምስካበ ቅዱሳን መድኃኔዓለም ገዳም በማለት የሰየሙት ብፁዕ አቡነ ኤፍሬም የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ናቸው፡፡ ብፁዕ አቡነ ኤፍሬም ገዳሙን በባረኩበት ወቅት “ምስካበ ቅዱሳን መድኃኔዓለም አንድነት ገዳም” በማለት ሰይመውታል፡፡ምስካብ ማለት የግእዝ ቃል ሲሆን ትርጓሜውም ማረፊያ፣ ምርፋቅ ማለት ነው፡፡ ምርፋቅ የቅዱሳን ማረፊያና መሰብሰቢያ እነደሆነ ፡፡
አባ ተክለ ጻዲቅ ስለገዳሙ ጥንታዊነት ሲናገሩ“አባቶቻችን እንደነገሩን እኛም ደርሰን እንዳየነው በስተምሥራቅ ከወንዙ ማዶ በዘንዶ ሲጠበቅ በስተምዕራብ የቤተ ክርስቲያኑ ዋሻ አካባቢ በነብር ይጠበቅ ነበር፡፡ ቦታው ከሁሉም በላይ በቅዱሳን ጸሎት እና በእግዚአብሔር ቸርነት ከጥፋት ተሰውሮ ኖሮ እግዚአብሔር ፈቃዱ ሲሆን እና ጊዜ ሲደርስ በዘመናችን የቦታው ክብር እና የፈጣሪ ቸርነት ተገልጿል፡፡” በማለት አስረዱን፡፡
ገዳሙ የተመሠረተበት ዓመት በትክክል አይታወቅም፡፡ ይሁን እንጂ በአህመድ ግራኝ ወረራ ወቅት ከጎንደር ሸሽተው በመጡ ቅዱሳን አባቶች መመስረቱን በአካባቢው የነበሩ አባቶች ያስረዳሉ፡፡
የገዳሙ አስተዳዳሪ መጋቢ ተክለ ጻዲቅም ይህንን ሀሳብ እንዲህ በማለት ያጠናክራሉ፡፡
“በግራኝ አሕመድ ወረራ ወቅት አባ ብሩ መስቀል፣ አባ ብሶይ እና አባ ወርቅ አገኘሁ የሚባሉ ሦስት ቅዱሳን አባቶች ውኃ ማውጫ ከሚባል አካባቢ ጽላቶችንና ንዋየ ቅዱሳትን አሽሽተው በገዳሙ አካባቢ በማሳረፍ ብዙ ተጋድሎ ፈጽመዋል፡፡ ከእነዚህ ሦስት ቅዱሳን አባቶች መካከል አባ ብሩ መስቀል የተባሉት ከበረት ላም ስለጠፋባቸው ከመጨነቃቸው የተነሳ ሱባኤ ገብተው ምስጢሩን ፈጣሪያቸው እንዲገልጽላቸው በጸሎት ይጠይቃሉ፡፡
የለመኑትን የማይነሳ እግዚአብሔር አምላክም ልመናቸውን ተቀብሎ ላሚቱ በጠፋች በስድስት ወሯ በአጽመ ቅዱሳኑ ዋሻ ሥር እንደሚያገኟት በራእይ ይገለጽላቸዋል፡፡ በራእይ እንደተመለከቱትም ላሚቱን ነጭ ጥጃ ይዛ ከአጽመ ቅዱሳን በር ላይ ያገኟታል፡፡ በዚሁ ጊዜ የመንፈስ ቅዱስ ምሪት ነው ብለው በማመን ከጎንደር አሽሽተው ያመጧቸውን ጽላቶች እና ንዋየ ቅዱሳት ከዝርፊያና ቃጠሎ ለመታደግ በዋሻው ውስጥ እንደ ሰወሩት እና በዚህም የገዳሙ መሠረት ተጣለ ”በማለት ያስረዳሉ፡፡
አባቶች ሸሽገው በስውር ያስቀመጡት ጽላት እና ንዋያተ ቅዱሳት አባቶች ትንቢት በተናገሩት መሠረት ሊገለጽ ዘመኑ መቃረቡን ታላላቅ አባቶች ያስረዱ ነበር፡፡ከዚህ ጋር በተያያዘም ዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ ከሳቸው ንግስና ዘመን በኋላ በሀገር፣በቤተ ክርስቲያንና በንዋየ ቅዱሳቱ ላይ ሊደርስ ያለውን አደጋ እግዚአብሔር አምላክ ገልጾላቸው ጽላትን እና ንዋያተ ቅዱሳትን እንዲሸሽጉ በታዘዙት መሠረት ለንዋየ ቅዱሳቱ ማረፊያ የሚሆነውን ቦታ ሲያስሱ በአካባቢው በስፋት ተዘዋውረዋል፡፡
በአንድ ወቅት ዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ ወደ ደብረ ምጥማቅ እየተጓዙ ሳለ በዚሁ አካባቢ እንዳረፉና ጸሎት ሲያደርሱ የቦታውን ክብር መንፈስ ቅዱስ ገልጾላቸው “ቦታውን አጥብቃችሁ ጠብቁ፣ ሚስጥሩን መንፈስ ቅዱስ ኋላ ላይ ይገልጽላችኋል” በማለት መናገራቸውን አባቶች ያስረዳሉ፡፡
ምስካበ ቅዱሳን መድኃኔ ዓለም ገዳም ቅዱሳን አባቶች የእግዚአብሔርን መንግሥት ናፍቀው ከዘመድ ከወገን ርቀው፣ ዳዋ ጥሰው ድንጋይ ተንተርሰው፣ ድምጸ አራዊትን ጸብአ አጋንንትን፣ የቀን ሀሩሩን የሌሊት ቁሩን ታግሰው መላ ዘመናቸውን ፈጣሪያቸውን ሲያገለግሉ የኖሩ ቅዱሳን አባቶች ጊዜ እረፍታቸው ሲደርስ እግዚአብሔር አምላክ ነፍሳቸውን በክብር ሲያሳርግ ሥጋቸውን ደግሞ እርሱ በመረጠው እና ባከበረው ሥፍራ በክብር እንዲያርፍ ያደርጋል፡፡ ለከበረው የቅዱሳን አጽም ማረፊያ እግዚአብሔር ከመረጣቸው እና ካከበራቸው ቦታዎች አንዱ ነው፡፡
ምስካበ ቅዱሳን መድኃኔ ዓለም ገዳም በቅዱሳን ጸሎት በእግዚአብሔር ቸርነት ለበርካታ ዓመታት ተሰውሮ ከኖረ በኋላ ለሁሉም ጊዜ አለው እንዳለው ንጉስ ሰሎሞን በእኛ ዘመን እግዚአብሔር በፈቀደ በሚያስደንቅ ሁኔታ በአዲስ መልክ ገዳሙ ተመሥርቷል፡፡
ለገዳሙ በአዲስ መልክ መመስረት ምክንያት የሆኑት መጋቢ ተክለ ጻዲቅ ሸዋረጋ ናቸው፡፡ መጋቢ አባ ተክለ ጻዲቅ ሸዋረጋ ስለተነገራቸው መልእክት ሲናገሩ “በጻድቃኔ ማርያም መካነ ቅዱሳን አንድነት ገዳም የተለመደ ጸሎቴን እያደረሱኩ ሳለ አሁን ምስካበ ቅዱሳን መድኃኔ ዓለም ገዳም በተገደመበት አካባቢ የነጭ አውራ ዶሮ አምሳል ከሰማይ ሲወርድ በራእይ ተመለከትኩ ወደዚህ ቦታ እንድሔድም ታዘዝኩ፡፡
ስለተገለጸልኝ መልእክት ለታላላቅ አባቶች በጸሎታቸው እንዲረዱኝ አሳሰብኩ ሱባኤ ይዘው ፈቃደ እግዚአብሔር መሆኑንም ተረዳ ለኔም አስረዱኝ፡፡
ይህንን መሠረት አድርገን በመጀመሪያ የአካባቢውን ሽማግሌዎች በመሰብሰብ ተወያየን ፈቃደ እግዚአብሔር በመሆኑ የአካባቢው ሽማግሌዎች ተስማሙ፡፡ ከዚያም አስፈላጊውን በሟሟላት ቦታውን ተረከብን፡፡” በማለት አስረዱን፡፡
መጋቢት 20 ቀን 1998 ዓ.ም. የምስካበ ቅዱሳን መድኃኔ ዓለም ገዳም ዋሻ ቤተክርስቲያን ሥራ ተጀምሮ በዓመቱ መጨረሻ ወደ ዋናው ዋሻ መግቢያ ያለው የቤተ ክርስቲያኑ አካል ሥራ ተጠናቀቀ፡፡ በጥቅምት ወር 1999 ዓም ዋሻውን የመፈልፈል ሥራ ተጀመረ፡፡
ጻድቃኔ ማርያም መካነ ቅዱሳን ገዳም ለጸሎትና ለፈውስ የሚመጡ ምእመናንን በማስተባበር ገንዘብ ያለው በገንዘቡ፣ ገንዘብ የሌለው በጉልበቱ በመተባበር ሥራው ላይ መረባረብ ያዘ፡፡ይህንን ታሪክ በመስማት ዕለት ዕለት እየተመላለሱ ቁፋሮውን አፋጠኑት፡፡ ከቅርብም ከሩቅም ያሉ ሕዝበ ክርስቲያኖች ለመድኃኔዓለም ገዳም አቅማቸው የፈቀደውን ሁሉ አደረጉ፡፡
የዋሻ ፍልፈላ ሥራው በተጀመረ በአንድ ዓመት ከስምንት ወር ጊዜ ውስጥ ተጠናቅቆ ግንቦት 27 ቀን 2002 ዓ.ም. በሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ በብፁዕ አቡነ ኤፍሬም መልካም ፈቃድ የአፋር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በብፁዕ አቡነ ዮናስ ተባርኮ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል፡፡
ፍልፍል ዋሻው 4.000/አራት ሺህ/ ካ.ሜ. የሚደርስ ስፋት እንዳለው የሚገመት ሲሆን በውስጡ ሦስት ፍልፍል ቤተ መቅደሶችን የያዘ ነው፡፡
እነርሱም፡-
1. የመድኃኔዓለም ቤተ መቅደስ፣
2. የመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ቤተ መቅደስ፣
3. የቅድስት አርሴማ ቤተ መቅደስ ናቸው፡፡
በምስካበ ቅዱሳን መድኃኔዓለም ገዳም የሚከበሩ በዓላት
ሀ/ መድኃኔዓለም፡-
ጥቅምት 27፣መጋቢት 27 ና ግንቦት 27 ናቸው፡፡
ለ/ መጥምቀ መለኮት የቅዱስ ዮሐንስ፡-
መስከረም 1፣2ና ሚያዚያ 15 ቀን በቅዳሴ፡፡ ሰኔ 30 ቀን ታቦተ ህጉ ወጥቶ በንግሥ ይከበራል፡፡
ሐ/ የቅድስት አርሴማ፡-
መስከረም 29፣ ታኅሣሥ 6 ና ጥር 6 ቀን ይከበራል፡፡
በምስካበ ቅዱሳን ዮርዳኖስ መድኃኔዓለም ገዳም ያሉ ጸበሎች፡-
የመድኃኔዓለም ጸበል ፣ የመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ጸበል፣ የቅዱስ ጊዮርጊስ ጸበል ናቸው፡፡
#ethiopianorthodoxmonastry #ቅዱሳንመካናት #ethiopianorthodox የኢትዮጵያኦርቶዶክስተዋህዶቤተክርስቲያን
| ኢትዮጵያ | ኦርቶዶክስተዋህዶ | ethiopianorthodox | RodasTadese
| የኢትዮጵያኦርቶዶክስ | የኢትዮጵያኦርቶዶክስተዋህዶ
| ethiopianorthodoxtewahdo | EthiopianOrthodox | ethiopianorthodoxtewahdochurch | ETHIOPIANORTHODOX | ማህበረቅዱሳን | AncientEthiopiaጥንታዊቷኢትዮጵያ | Ancient Ethiopia - ጥንታዊቷ ኢትዮጵያ | ጥንታዊቷ ኢትዮጵያ | Ancient Ethiopia | ancientethiopia | AncientEthiopia - ጥንታዊቷኢትዮጵያ | ancient ethiopia - ጥንታዊቷ ኢትዮጵያ

Пікірлер: 1

  • @senaitgebremedhin7460
    @senaitgebremedhin7460 Жыл бұрын

    ❤እግዚአብሔር ይመስገን ❤ አሜን (3) ቃለ ሂወት ያሰማልን 🙏 በረከቱ ይድረሰን 🙏🙏🙏

Келесі