➕ የሰሞነ ሕማማት ዝማሬዎች ስብስብ ክፍል 2 🙏➕ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሰሞን ሕማማት መዝሙሮችን ያድምጡ 🙏 Orthodox Mezmur semune himamat

ሰሞነ ህማማት ከሰኞ እስከ ቅዳሜ
።።።።።።።።።።
1).ስግደት:-በሰሙነ ሕማማት 41 ጊዜ ኪርያላይሶን 12 ጊዜ አቡነ ዘበሰማያት እየተዜመ እጅግ አብዝቶ ይሰገዳል:: እንደ አቅም ጨምሮ መስገድ ይቻላል።
2) ጸሎት:- በሰሙነ ሕማማት ከ24 ሰዓት ውስጥ 10 የጸሎትና
የንባብ ሰዓታት ይገኛሉ እነዚህም ከጠዋቱ 1 ሰዓት; 3ሰዓት; 6ሰዓት; 9ሰዓት; 11ሰዓት እንዲሁም ከምሽቱ 1 ሰዓት; 3ሰዓት;6ሰዓት; 9ሰዓት; 11ሰዓት ናቸው:: በነዚህም ሰዓታት የጌታን ስቃይ ለማዘከር መዝሙረ ዳዊትና ግብረ ሕማማት ድርሳነ ማኅያዊ አብዝተው ይጸለያሉ::በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ተሰብስባችሁ መጻሕፍተ ኦሪትን እና መጻሕፍተ ነቢያትን፣ የዳዊትንም መዝሙር እያነበባችሁ በምስጋና በጸሎት ዶሮ እስከሚጮኽ ድረስ የሌሊቱን ሰዓት ጠብቁ፡፡
አንድ ምእመን የታመመ ቢሆን ወይም ክርስቲያን በሌለበት አገር
ሆኖ ሳያውቅ የሕማማት ሰሞን ቢያልፍበት ወይንም በደዌ ውስጥ
ሆኖ ቢቀርበት ከበዓለ ሃምሳ በኋላ ሰውነቱን በማድከምም ያካክስ። በእነዚህ ስድስት ቀናት ባለመፍራት እንዳይጠፋ
ውስጣዊ ሰውነቱን ይመርምር::
3) .ጾም:-በሰሙነ ሕማማት ብዙ አዝማደ መባልዕት /አዘውትረን የምንመገባቸው ምግቦች/አይበሉም:: በዚህም ሳምንት እስከ ምሽቱ አንድ ሰዓት እንድንጾም; ይኸውም ቆሎ;ዳቦ;ውኃና ጨው
ብቻ እንደታዘዙ በግብረ ሕማማት ላይ ተጽፎ ይገኛል::በሐዋርያት ቀኖና እንዲህ ይላል «ይልቁንም በእነዚህ በስድስቱ ቀኖች መጾም የሚችል ቢኖር ሁለት ሁለት ቀን ይጹም፡፡ የማይችል ግን አንድ አንድ ቀን ይጹም፡፡ ሌሎችን ቀኖች እስከ ዘጠኝ ሰዓት ይጹሙ። እችላለሁ የሚል ግን ፀሐይ እስኪገባ ድረስ ይጹም፡፡
4) .አለመሳሳም:-አይሁድ ጌታችንን ለመስቀል እየተንሾካሾኩ ስለተመካከሩና ይሁዳ ጌታችንን በመሳም አሳልፎ ስለሰጠው መሳሳም አይፈቀድም:: መስቀልም በዘመነ ኦሪት የወንጀለኛ መቅጫ የእርግማን ምልክት ስለ ነበር ጌታችን በክቡር ደሙ ቀድሶ የድል አርማ እስኪያደርግልን ድረስ አንሳለመውም ገላ. 3:13 ማቴ.10:38 ማቴ. 26:29ኘ
5.) አክፍሎት:-እመቤታችን; ያዕቆብና ዮሐንስ የጌታችን ትንሳኤ ሳናይ እህልና ውኃ አንቀምስም ብለው እስከ ትንሳኤው መቆየታቸውን በማሰብ የሚጾም ነው:: አርብ እራት ተበልቶ እስከ ሚፈሰክ ድረስ።
6.) ጉልባን:-ከባቄላ ከስንዴ ከገብስ የሚዘጋጅ በጸሎተ ሐሙስ ዕለት የሚበላ ንፍሮ ሲሆን ትውፊቱም የስቅለቱ ሐዘን መግለጫ ነው::
7) .ጥብጠባ:-ይህ ምዕመናን በሰሙነ ሕማማት የፈጸሟቸውን ኃጢአቶች ለካህን እየተናዘዙ በወይራ ቅጠል ቸብቸብ እየተደረጉ ስግደት የሚቀበሉበት ነው:: ይህም የጌታ ምሳሌ ነው::
8) .ቄጠማ:-ጌታችን ብርሃነ ትንሳኤዉን እንደገለጠልን የምናስብበት ሲሆን የእሾህ አክሊል በመድፋቱ ምሳሌም በራሳችን ላይ እናስረዋለን:: በጣት የሚጠለቀው ቃጤማ ክርስቶስ አዳምን ከኃጢአት መከራ እንደሚያወጣው የሰጠውን ቃልኪዳን ለመዘከር ነው።
።።።።።።።።።።
+ ኪርዬ ኤሌይሶን የግሪክ ቃል ሲሆን ኪርያ»
ማለት «እግዝእትነ» ማለት ሲሆን «ኪርዬ» ማለት ደግሞ
«እግዚኦ» ማለት ነው፡፡ "አቤቱ ማረን" ማለት ነው፡፡
«ኪርያላይሶን»
+ ናይናን
የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙ «መሐረነ፣ ማረን» ማለት ነው፡፡
+እብኖዲ
የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙ «አምላክ» ማለት ነው፡፡ «እብኖዲ
ናይናን» ሲልም «አምላክ ሆይ ማረን» ማለቱ ነው
+ታኦስ
የግሪክ ቃል ሲሆን ትርጉሙ «ጌታ፣ አምላክ» ማለት ነው፡፡ «ታኦስ
ናይናን» ማለትም «ጌታ ሆይ ማረን» ማለት ነው፡፡
+ ማስያስ
የዕብራይስጥ ቃል ሲሆነ ትርጉሙ «መሲሕ» ማለት ነው፡፡
«ማስያስ ናይናን» ሲልም «መሲሕ ሆይ ማረን» ማለት ነው
+ ትስቡጣ
«ዴስፓታ» ከሚለው የግሪክ ቃል የመጣ ሲሆን ትርጉሙም ደግ
ገዥ ማለት ነው
+ አምነስቲቲ ሙኪርያቱ አንቲ ፋሲልያሱ
የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙም
«ተዘከረነ እግዚኦ በውስተ
መንግሥትከ- አቤቱ በመንግሥትህ አስበኝ» ማለት ነው፡፡
+ አምንስቲቲ መዓግያ አንቲ ፋሲልያሱ
የቅብጥ ቃል ሲሆን «ተዘከረነ ኦ ቅዱስ በውስተ መንግሥትከ -
ቅዱስ ሆይ በመንግሥትህ አስበን» ማለት ነው
+አምንስቲቲ ሙዳሱጣ አንቲ ፋሲልያሱ
የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙም «ተዘከረነ እግዚአ ኩሉ በውስተ
መንግሥትከ- የሁሉ የበላይ የሆንክ ወይ በመንግሥትህ አስበን»
ማለት ነው፡፡
።።።።።።።።።።።
ገብረኪዳን ዘአቡነዮሴፍ

Пікірлер: 14

  • @BirtukanMeleka
    @BirtukanMelekaАй бұрын

    ዝማሬ መላእክት ያሰማልን አሜን አሜን አሜን አሜን ❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤

  • @user-zm7ci8mi7s
    @user-zm7ci8mi7sАй бұрын

    አሜን አሜን አሜን

  • @AsdAsd-od7ql
    @AsdAsd-od7qlАй бұрын

    አሜን(3)ነብስን የሚያስደስት ዝማሬ😢❤

  • @user-kj5bv2ox7g
    @user-kj5bv2ox7gАй бұрын

    አሜን ማሀረነ ክርስቶስ

  • @BbbbBbbb-ol2vv
    @BbbbBbbb-ol2vvАй бұрын

    አሜን አሜን አሜን❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤

  • @user-ez8xb4cr8x
    @user-ez8xb4cr8xАй бұрын

    ❤❤Amen amen amen ❤

  • @tsehyneshhaile8845
    @tsehyneshhaile8845Ай бұрын

    ❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤

  • @selamselam3465
    @selamselam3465Ай бұрын

    ❤❤❤❤❤Thanks!

  • @SamSam-hv7yj
    @SamSam-hv7yjАй бұрын

    ❤❤❤❤❤🎉❤❤❤😢😢

  • @asnetulu6216
    @asnetulu6216Ай бұрын

    😢😢😢❤❤❤❤

  • @gggh8877
    @gggh8877Ай бұрын

    ❤❤❤❤😢😢😢😢😢😢😢😢😢😢😢😢😢😢😢😢😢😢😢😢😢😢😢

  • @SamSam-hv7yj
    @SamSam-hv7yjАй бұрын

    አሜን አሜን አሜን ዝማሬ መላእትን ያሰማልን❤❤❤🎉❤

  • @selamtesfaye8422
    @selamtesfaye8422Ай бұрын

    አሜን አሜን አሜን

  • @user-zm7ci8mi7s
    @user-zm7ci8mi7sАй бұрын

    ❤😍❤😍❤😍😘

Келесі