🙏 እንኳን ለእናታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም➕ በዓለ እግዚትነ ማርያም አደረሳቹ!🙏➕የተመረጡ የእመቤታችን መዝሙራትን ያድምጡ mariam mezmur

21: የቅድስት ድንግል ማርያም በዓል
እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ወራዊ ክብረ በዓል አደረሳችሁ፡፡
በዛሬው እለት ከማኅበራዊ ድረገጽ ያገኘሁትን ታቦተ ጽዮን ታላቅ ተአምራትን በዳጎን ላይ ማድረጓን የሚገልጸውን ሥዕል ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በፎቶ የተነሣ ሥዕል በማግኘቴ ላካፍላችሁ በማለት ይህችን ጽሑፍ ጽፌያለሁ፡፡
በቀጣይ ዕትም የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሥዕል በስፋት እና በጥልቀት መንፈሳዊ ትርጉምን ከብዙ ምሳሌ ሊሆኑ የሚችሉ ቅዱሳን ሥዕላት ጋር በማስተባበር እንመለከታለን፡፡
“እግዚአብሔር ጽዮንን መርጦአታልና፥ ማደሪያውም ትሆነው ዘንድ ወድዶአታልና፥ እንዲህ ብሎ።ይህች ለዘላለም ማረፊያዬ ናት መርጫታለሁና በዚህች አድራለሁ።አሮጊቶችዋን እጅግ እባርካለሁ፥ ድሆችዋንም እንጀራ አጠግባለሁ።ካህናቶችዋንም ደኅንነትን አለብሳቸዋለሁ፥ ቅዱሳኖችዋም እጅግ ደስ ይላቸዋል።” መዝ 131:13
“ጽዮን” ማለት “ጸወን - አምባ - መጠጊያ” ማለት ነው:: አንድም በምሥጢሩ “ማሕደረ አምላክ” ማለት ነው:: ጽዮን የሚለው ስም በቁሙ ለቅዱስ ዳዊት ተራራና ለኪዳኑ ጽላት ሲያገለግል በትንቢታዊ ምሥጢሩ ግን ለድንግል ማርያም: ለቤተ ክርስቲያንና ለዘለዓለማዊት ርስት ያገለግላል::
ኅዳር 21 ቀን የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ በዓል ነው ብለን በተለየ መልኩ የምናከብርበት ምክንያት፡-
በብሉይ ኪዳን ታቦተ ጽዮን የፈጸመችውን ልዩ ልዩ ገቢረ ተአምራትን ለማሰብ
ቀዳማዊ ምኒልክ ከዐሥራ ሁለቱ ነገደ እስራኤል የበኲር ልጆች ጋር ሊቀ ካህናቱን አዛርያስንና ታቦተ ጽዮንን ይዞ አክሱም የደረሰበት ዕለት በመሆኑ
በሦስት መቶ ሠላሳ ዓመተ ምሕረት በአብርሃ ወአጽብሃ ዘመነ መንግሥት ክርስትና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሃይማኖት ይሁን ተብሎ ዐዋጅ የታወጀበት
ዘካርያስ በተቅዋመ ወርቅ ምሳሌ ራእይ ያየበት
ነቢዩ ሕዝቅኤል በተቆለፈች ቤተ መቅደስ
ዕዝራ በቅድስት ሀገር ምሳሌ ራእይ ያየበት
አብርሃና አጽብሃ በወርቅና በዕንቁ ያሠሩት ባለ አሥራ ሁለት ክፍል ቤተመቅደስ ለመጀመሪያ ጊዜ ቅዳሴ ቤቱ የተከበረበት በዘጠነኛው መቶ ክፍለ ዘመን ዮዲት ጉዲት አብያተ ክርስቲያናትን ስታቃጥል ታቦተ ጸዮንን ይዘው ወደ ዝዋይ ሐይቅ ከተሰደዱ በኋላ ዘመነ ሰላም ሲጀመር አክሱም በነበሩ ካህናት አስታዋሽነት ከዝዋይ ወደ አክሱም የገባችበት ዕለት በመሆኑ በርእሰ አድባራት ወገዳማት አክሱም ጽዮን ከፍ ባለ መንፈሳዊ በዓል እናከብራለን፡፡
የወላዲተ አምላክ አማላጅነት የቅዱሳን ተራዳኢነት ከእኛ አይለየን፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር ፡፡
ወለወላዲቱ ድንግል፡፡
ወለመስቀሉ ክቡር፡፡
👉👉👉በሌሎች የማህበራዊ ድረ ገፆችም ያገኙናል 🙏🙏🙏
☑️Telegtam 👉t.me/Kidusmezmurerecords
☑️TikTok 👉 / kidus_mezmur_records
☑️Instagram👉 kidus_mezmure_r...
☑️Facebook👉 profile.php?...
☑️KZread 👉 / @kidusmezmurrecords

Пікірлер: 6

  • @kidusmezmurrecords
    @kidusmezmurrecordsАй бұрын

    👉👉👉በሌሎች የማህበራዊ ድረ ገፆችም ያገኙናል 🙏🙏🙏 ☑️Telegtam 👉t.me/Kidusmezmurerecords ☑️TikTok 👉 tiktok.com/@kidus_mezmur_records ☑️Instagram👉 instagram.com/kidus_mezmure_records?igshid=NTA5ZTk1NTc= ☑️Facebook👉 facebook.com/profile.php?id=61557385937834 ☑️KZread 👉 youtube.com/@kidusmezmurrecords

  • @Shaklama
    @ShaklamaАй бұрын

    እናቴ እመቤቴ 😢😢❤❤

  • @azebogbamichael6410
    @azebogbamichael6410Ай бұрын

    Amen Amen Amen ❤❤❤

  • @user-ug8dm2cw4i
    @user-ug8dm2cw4iАй бұрын

    ማርያም እናቴ አመቤቴ እመብርሀን❤️ 🙏😥💔🙏😥💔

  • @tsehyneshhaile8845
    @tsehyneshhaile8845Ай бұрын

    ❤❤❤❤❤🙏🙏🙏🙏🙏🙏

  • @muluneshtegena
    @muluneshtegenaАй бұрын

    እናቴ.እመቤቴ.ስደተኛ.ልጆችሽን.አስቢን.አገራችን.ሰላም.አድርጊልን.ከጐናችን.ሁኝ❤❤❤❤እመብረሀን❤❤❤❤🎉🎉🎉

Келесі