ሜዳ ትረካ፡- "የወገን ጦር" መጽሀፍ ትረካ|"ወታደሮች ነበርን ለኢትዮጵያ" |ክፍል 16|የደራሲውና የጓዶቻቸው ፈተና በጠላት ወረዳ|ጸሀፊ፡- ሻለቃ ማሞ ለማ

Ойын-сауық

የጸሀፊው መልእክት!
በ"የወገን ጦር" መጽሀፍ ክፍል 5 "ከጠላት ጀርባ" በሚለው ንኡስ ርእስ ስር ወይም በኢትዮ ሜዳ ትረካ ከክፍል 16 እስከ 18 በውጊያ ውስጥ ከወገን ተነጥለው ከጠላት ጀርባ ተቆርጠው ቀርተው ከነበሩት ሦስት መኮንኖች ውስጥ መቶ አለቃ በቀለ (ብራቮ) በማለት የተጠቀሰው መኮንን እውነተኛ ስሙ አይደለም፡፡ ይህም የሆነበት ምክንያት ጸሐፊው መጽሐፉን በሚጽፉበት ወቅት መኮንኑ በህይወት ይኑር ይሙት፤ ስለማያውቁና በተለይ ደግሞ በህይወት ካለ እውነተኛ ስሙን ጠቅሰው ታሪኩን ሲጽፉ በግሉ ምን ሊሰማው እንደሚችል ስለማያውቁና ከዚህ ሁሉ በላይ ግን ምናልባት የተጻፈው ታሪክ በሱ ህይወት ላይ አደጋ ሊያመጣበት ቢችልስ የሚለውን በማገናዘብ ነበር፡፡
ከጊዜ በኋላ ግን በመጽሐፉ አማካኝነትና በዘመኑ ማህበራዊ ሚድያ ድጋፍ ፀሐፊውና ባለታሪኩ የጦር ጓዳቸው በህይወት ሊገናኙ ችለው ባለታሪኩም በመጽሐፉ ላይ ያለው ታሪኩ በስሙ ቢጠቀስ ያኮራው ካልሆነ በስተቀር ቅር እንደማያሰኘውና እንደማያሰጋው ስላረጋገጠላቸው እነሆ መቶ አለቃ በቀለ (ብራቮ) የተባለው እውነተኛ ስሙ ሻለቃ ንጉሤ ለማ መሆኑን ለማሳወቅ ይወዳሉ፡፡
ይህ የሆነበት ምክያትም በታሪኩ ላይ እንደተመለከተው የአሁኑ ሻለቃ የዛን ጊዜው መቶ አለቃ ንጉሤ (ብራቮ) በአልጌና ውጊያ ኪራይ በተባለው አካባቢ ከፀሐፊው ጎን ሆኖ ሲዋጋና ሲያዋጋ ሽንጡ ላይ በጥይት ቆስሎ ፀሐፊው እታንክ ቱሬት ጀርባ ላይ ተሳፍሮ ወደ ኋላ ወረዳ እንዲገለል አድርገውት ነበር፡፡ መኮንኑም ሕክምና ያለበት ደርሶ ከዛም ወደ ሆስፒታል ተጓጉዞ ታክሞ ከዳነ በኋላ ወደ ስራው ተመልሶ አገልግሎቱን በመቀጠል ከፀሀፊው ጋር ሳይገናኙ እስከ በ1983 ዓ/ም የሻለቃነት ማዕረግ ድረስ ደርሶ አሁን ድረስ በህይወት የሚገኝ በመሆኑ ነው፡፡
ሻለቃ ማሞ ለማ
"የወገን ጦር" መጽሀፍን ከአማዞን ላይ በተከታዩ ሊንክ መሰረት ማግኘት የምትችሉ መሆኑን ለማሳወቅ እንወዳለን፡፡
www.amazon.co.uk/Yewegen-Tor-...

Пікірлер: 10

  • @teddysiyoum5612
    @teddysiyoum5612 Жыл бұрын

    Thanks 🙏🏾

  • @banchibelayneh5759
    @banchibelayneh5759 Жыл бұрын

    ❤❤👍👍👍

  • @ephremtamirat6280
    @ephremtamirat6280 Жыл бұрын

    👍👍👍

  • @fekadugebreyohannes3672
    @fekadugebreyohannes3672 Жыл бұрын

    Thanks my hero. Keep it up ur good job!

  • @senda9782
    @senda9782 Жыл бұрын

    ይህን ቻናል በቀን ሁለት ጊዜ የግድ እሰማለሁ። አንደኛ ታሪኩን ለመከታተል ሁለተኛው ማታ እንቅልፍ እንዲወስደኝ

  • @araedombahram4150
    @araedombahram4150 Жыл бұрын

    ምን ኣይነት ውሸት ነው ብናትህ ይሄ ልብ ወለድ ነው

  • @bruka3513

    @bruka3513

    Жыл бұрын

    ቦታው ላይ ነበርክ ግልፀ ሂሰ ሰጥ

  • @faamasha2900

    @faamasha2900

    Жыл бұрын

    ደደብ ሰው ማንን ይመስላል? ልክ አንተን ቁጭ፤

Келесі