⛪ ማየት ያለባችሁ የአገራችን ብርቅዬ ገዳም ⛪ ስለዚህ ቦታ ያልተሰሙ አስገራሚ እውነታወች ⛪ Ancient Ethiopia - ጥንታዊቷ ኢትዮጵያ

Saint George Monastery of Dima
ትንሽ ስለ አስደናቂው ዋሻ
የሰማዕቱ የቅዱስ ጊዮርጊስ ታቦተ ሕግ በዚያ አስፈሪና ግርማዊ በሆነ የተፈጥሮ ዋሻ ውስጥ ከመቼ አንስቶ መኖር እንደጀመረ ያስረዳኝ ባይኖርም ዋሻውን ከዲማ ጊዮርጊስ በስተግራ በኩል በግምት 1 ኪ.ሜ ከተጓዙ በኋላ ጸበሉ በአለበት የገደል አፋፍ ላይ ሆኖ ማየት ይቻላል፡፡
የቅዱስ ጊዮርጊስ ጽላተ ክብር የሚኖርበት ዋሻ በዲማና በግርኛ ማርያም ቤተክርስቲያናት መካከል በሁለተኛው የገደል እርከን ስር ይገኛል፡፡ ታቦቱ ከዋሻው ውስጥ ከመውጣቱ በፊት በእምብርክክ የሚያስኬደውን መንገድ ቁልቁል መውረድና ሽቅብ መውጣት ይጠይቃል። አባ ተከስተብርሃን የተባሉ አባት ታሪክም በገዳሙ ውስጥ በሰፊው ይተረካል። አባ ተከስተብርሃን በዲማ ጊዮርጊስ ገዳም የኖሩና የትሩፋት ሥራ ሰርተው ያለፉ የበቁ አባት ናቸው፡፡ እኒህ አባት በፆም በቀኖና በብህትውና በዋሻው ውስጥ ሲኖሩ ከትውልድ ቦታቸው አንዲት አህያ የሽንብራ ስንቃቸውን ጭና አድርሳላቸው ወደ አገሯ ትመለስ ነበር ይባላል፡፡ የትሩፋት ሥራ በመሥራት ላይ እንዳሉ ሥራቸውን ሳይጨርሱ፣ ፀሐይ ከምዕራብ የመግቢያ መስኮትዋ ላይ ደረሰች፡፡ በዚያ ወቅት “ሥራየን ሳልፈጽም አትጥለቂ” ብለው ሲገዝቷት ጨለማው ብርሃን በብርሃን ይሆናል፤ ከዚህም የተነሳ ነው ስማቸው አባ ተከስተ ብርሃን የተባለው፡፡
አባ ተከስተ በጾምና በቀኖና ላይ እንዳሉ በዋሻው ውስጥ ያርፋሉ፡፡ የዲማ ካህናትና መነኮሳትም ዋሻ ውስጥ በሕይወት ያሉ መስሎዋቸው ሲኖሩ በትራቸው ከዋሻ ተነሥታ ወደ ዲማ በመሄድ ሞታቸውን አስረድታለች፡፡ በትራቸውም በአሁኑ ሰዓት ዲማ ውስጥ አለች ይባላል፡፡
ዋሻው በእጅጉ የሚያስፈራ ሲሆን በዕለቱ በግርኛ ማርያምና በዲግ በኩል ባለው መግቢያ ሰው በገደሉ ላይ እየተንሸራተተ ወርዶ፣ ወደ ዋሻው አናት ላይ ሲወጣ ሲታይ በየገደሉ እየተንጠላጠለ ቅጠል የሚያሳድድ የፍየል መንጋ ይመስላል፡፡ ከዋሻው ጫፍ እስከ ጫፍ ለመድረስ ሁለት ጧፍ ይጨርሳል፡፡ ዋሻው ውስጥ ሲገባ ጧፍ እየተበራ ነው፡፡ ከዋሻ ውስጥ በጸበልነት የሚያገለግል ትልቅ ባሕር አለ፡፡ የጸበሉ መልክ ጥቁር ቡና ይመስላል፡፡
የጊዮርጊስ የንግሥ በዓል ሲቃረብ የበቁና ቅድስና ያላቸው አባቶች ወደ ዋሻ ውስጥ ይገቡና ለ7 ቀን እፍኝ ሽምብራ እየተመገቡ ሱባኤ ይገባሉ። ሲያስታኩቱና ቦታውንም ሲያጥኑ፣ ፈጣሪን ሲያመሰግኑ ይሰነብታሉ። የእግዚአብሔር ፈቃድ ሲሆን ታቦቱ ለንግሥ ይወጣና በመጀመሪያ ከገደሉ እርከን ሥር በተተከለለት ድንኳን ይገባል፡፡ ከዚያም ወደ ሜዳ ታጅቦ ከወጣ በኋላ በእልልታ፣ በሆታ፣ በጭብጨባ፣ በከበሮ ድምጽ እየታጀበ ሄዶ ዲማ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ይገባል፡፡ በራሱ ጊዜም ተመልሶ ወደ ዋሻው ይገባል፡፡
የፍጡነ ረድኤቱ የቅዱስ ጊዮርጊስ ታቦት ከመንበረ ክብሩ ሲወጣና ወደ መንበረ ክብሩ ሲመለስ በአውሎ ነፋስ ይታጀባል ይላሉ አባቶች። አንድ አባት እንዳወጉኝ፤ አንድ የበቁ ጻድቅ ታቦተ ሕጉን ከዋሻ ውስጥ ለማውጣት ጧፍ እያበሩ ወደ ዋሻው ሲገቡ፣ አንዲት የሌት ወፍ የሚበራውን ጧፍ በክንፍዋ መትታ ታጠፋባቸዋለች፡፡
ጻድቁ ተስፋ ሳይቆርጡ በዳበሳ ታቦተ ሕጉ ወደ አለበት ቦታ ደርሰው ታቦቱን በጨለማ ሲነኩት አምስቱም ጣቶቻቸው እንደጧፍ ያበራሉ፡፡ በዚህ ጊዜ ጽላቱ አንደበት አውጥቶ “አባ ተጠነቋቆልን” አላቸው ይባላል፡፡
ከዋሻው አቅጣጫ ከሜዳው ላይ ከገደሉ አፋፍ ደግሞ ሌላ ትንግርት አለ፡፡ አንድ ወቅት በዚያ አለታማ መንገድ አንዲት መነኩሴ ስትሄድ አንድ የጠገበ ጐረምሳ ክንዷን ይዞ ሊጥላት ሲል፤ “አቤት አቤት ፍጡነ ረድኤቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ድረስልኝ” ብላ ትጮሃለች፡፡ ወዲያው ፍጡነ ረድኤቱ ያንን አለት ሰንጥቆ ይደርስላትና ያንን ባለጌ ወጣት ቀሰፈው ይባላል፡፡ እናም አሁን ድረስ የፈረሱ ኮቴ፣ ጦሩ ያረፈበት ድንጋይ ይታያል፡፡ በደማሚት የማይፈርሰው ጥቁር አለትም እስከ ታች ድረስ ክፍት ሆኖ ሰው ይሾልክበታል፡፡
#ethiopianorthodoxmonastry #ገዳም #የኢትዮጵያኦርቶዶክስተዋህዶቤተክርስቲያን
AncientEthiopiaጥንታዊቷኢትዮጵያ | Ancient Ethiopia - ጥንታዊቷ ኢትዮጵያ | ጥንታዊቷ ኢትዮጵያ | Ancient Ethiopia | ancientethiopia | AncientEthiopia - ጥንታዊቷኢትዮጵያ | ancient ethiopia - ጥንታዊቷ ኢትዮጵያ |
axumtube , day 7 tube , axum tube,ahaz tube,Abel Birhanu የወይኗ ልጅ 2 , Rodas Tadese , አቢይ ይልማ,አሃዝ ቲዩብ , አክሱም ቲዩብ , ኢትዮጵያ , Ancient Ethiopia , ancient ethiopia , አስገራሚ , አስደናቂ , ለማመን የሚከብድ , የማይታመን , orthodox , Ethiopia , ethiopian , ጊዜ ቲዩብ , አንድሮመዳ , ሚስጢራዊ , ሣልሳዊ ቴዎድሮስ , ቶ መስቀል , ንጉሥ ቴዎድሮስ ትንቢቶች , ቶ , የኢትዮጵያ ትንሳኤ , ራፋቶኤል ወርቁ , ራፋቶኤል ምእላድ , አንድሮሜዳ Andromeda,Axum Tube / አክሱም ቲዩብ,Mahibere Kidusan,ኢትዮጵ ቲዩብ,ራእየ ሳቤላ,ራእየ ሲኖዳ,ፍካሬ ኢየሱስ,ዶ/ር ሮዳስ ታደሰ,ትንቢት | መምህር ዘበነ ለማ |
ሮዳስ ታደሰ | መምህር | መንፈሳዊ | memihir tesfaye abera | ማኅበረ ቅዱሳን | ኢኦተቤ | ኢትዮጵያ | Ancient Ethiopia | ancient ethiopia | መምህር ምህረተአብ አሰፋ | Feta Daily News | axum tube , ahaz tube , Abel Birhanu የወይኗ ልጅ 2 , Abel birhanu yeweynua lij , lij bini , ethio beteseb , feta daily , Feta Daily , Yeneta Tube , asgerami , Lucy tips , Lucy Tips , Rodas Tadese , memher abiy yilma , Abiy Yilma , አቢይ ይልማ , አሃዝ ቲዩብ , አክሱም ቲዩብ , ኢትዮጵያ , Ancient Ethiopia , ancient ethiopia ,
| ለማመንየሚከብድ | ethiopianorthodox
| ኢትዮጵያ | ኦርቶዶክስ ተዋህዶ | ethiopianorthodox
| የኢትዮጵያኦርቶዶክስ | የኢትዮጵያኦርቶዶክስተዋህዶ | የኢትዮጵያኦርቶዶክስተዋህዶቤተክርስቲያን
| ethiopianorthodoxmezmur | ethiopianorthodoxtewahedomezmur | ethiopianorthodoxsibket
| ethiopianorthodoxtewahido | EthiopianOrthodox | ethiopianorthodoxtewahdochurch | EthiopianOrthodoxTewahedoChurch | ETHIOPIANORTHODOX | ማህበረቅዱሳን

Пікірлер: 3

  • @senaitgebremedhin7460
    @senaitgebremedhin7460 Жыл бұрын

    🌹እግዚአብሔር ይመስገን 🌹 አሜን (3) ቃለ ሂወት ያሰማልን . የቅዱስ አባታችን አቡነ ተከሰተ ብርሃን በረከታቸው ይደርብን 🙏🌹🙏🌻🙏

  • @backgroundmusictubechannel195
    @backgroundmusictubechannel195 Жыл бұрын

    አባቴ እናመሰግናለን

  • @ymiskelsirsetoty
    @ymiskelsirsetoty Жыл бұрын

    በረከታቸው ይደርብን

Келесі