እመቤታችን እና አቡነ መልከ ጼዴቅ ኢትዮጵያዊቷን ነፍስ ለመውሰድ ተካሰው ፍርድ ፊት ቀረቡ | ኢትዮጵያ የድንግል ማርያም የአሥራት አገር | የቅዱሳን ታሪክ

ታላቁ ጻድቅ አባታችን አቡነ መልከ ጼዴቅ አቤል የሚባል መንፈሳዊ ወንድም ነበራቸው፡፡ የእግዚአብሔርም ቃል ወደሳቸው መጥቶ “ወንድምህ አቤል በንጉሱ አዳራሽ ሞተ” አላቸው፡፡ አባታችን ያን ጊዜ ወደ ገዳም ሄደው ‹‹አቤል ወንድሜን ነፍሱን ያኖርህበትን አሳየ›› እያሉ ወደ እግዚአብሔር ጸለዩ፡፡ ጌታችንም ወደ ጻድቁ መጣና ‹‹በአስቀመጥሁት በሲኦል ውስጥ ንስሐውን ይፈጽም ዘንድ ተወኝ›› አላችው፡፡ ጌታችንም ይህንን ብሎ ተሰወራቸው፡፡ ወዳጆቼ ንስሐ ከሞት በኋላ ኖሮ ሳይሆን ለአቡነ መልከ ጼዴቅ እንዲፈጽምላቸው ነገራቸው እንጂ፡፡
ከዚህ በኋላ አባታችን አቡነ መልከ ጼዴቅ ወደ ጌታችን ስለ አቤል ነፍስ ይለምኑለት ጀመሩ፡፡ ደማቸውም እንደ ውሃ በምድር ላይ እስኪፈስ፣ ቁጥር በሌለው ግርፋት ሥጋቸው እስኪፈርስ፣ ናላቸው ተበጥብጦ በአፍንጫቸው እስኪወርድ ድረስ፣በጌታችን ፊት ብዙ ስግደት ሰገዱ፡፡ ደም ከተቀላቀለው ዕንባ ጋር እያነቡም መራራ ለቅሶን አለቀሱ፡፡ የዓይናቸው ብሌን ተለቅጦ /ተገልብጦ/ የውስጡ ወደ ውጭ ወጣ፡፡
ከዚህ በኋላ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ አባታችን መጥቶ ‹‹ስለ ድካምህ ምሬልሃለሁ ግርፋትህ በጲላጦስ እጅ እንደተገረፍኩት ይሁን፣ ስግደትህም አይሁድ በሚይዙኝ ጊዜ በእለተ ሐሙስ በአባቴ ፊት እንደሰገድኩት ስግደቴ ይሁን፣ ችንካርህም በዕፀ መስቀል ላይ አይሁድ እንደቸነከሩኝ ችንካሬ ይሁን፣ መታሰርህና የደምህ መፍሰስም ስለ ፈሰሰው ደሜ ይሁንልህ፡፡ ነፍስህን መስጠትህም ስለ ነፍሴ መውጣት ይሁን፡፡ ዛሬም ና የወንድምህ የአቤል ነፍስ ያለችበትን ላሳይህ›› አለው፡፡ ያንጊዜም የመንፈስቅዱስ ክንፍ ተሰጠው /ወጣለት/፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እየመራው እየበረረ ሄደና ከሲኦል በር አደረሰው፡፡ እንዲህም አለው ‹‹እኔ ወደ ሲኦል ወርጄ የጻድቃንን ነፍሳት እንደ አወጣሁ አንተም ወደ ሲኦል ውረድና ወንድምህን አቤልን አውጣው›› አለው፡፡
አባታችን አቡነ መልከ ጼዴቅም መልሶ ‹‹እኔ መሬታዊ ሰው ስሆን ወደ ሲኦል መውረድ እንዴት እችላለሁ፡፡ አንተስ ኃይልህ የበረታ ስለሆነ ከውስጧ ወርደህ የብረት በሮቿንና መወርመሪያዎቿን ቀጥቅጠህ ትሰባብራለህ›› አለው፡፡ ጌታችንም በእኔ የሚያምን እኔ የምሠራውን ይሠራልና እምቢ አትበለኝ ሂድ ውረድ›› አለው፡፡ አባታችንም ያን ጊዜ መርከብ ወደ ጥልቅ ባህር እንደሚወርድ ወደ ሲኦል ወረደ፡፡
ሲኦልም ደነገጠችና ‹‹የተሰጡኝ ነፍሳት ይቀማኝ ዘንድ ፈጣሪዬ ዳግመኛ ወረደን?›› አለች፡፡ እንዲህ እያለች ሳለ አባታችን አቡነ መልከ ጼዴቅ ያን ጊዜ ወንድማቸውን አቤልን ያዙትና ከሲኦል አወጡት፡፡ ከእሱ ጋርም ብዙዎች የኃጥአን ነፍሳትን አወጣ፡፡ በእሱ ላይም የነበረው የእሳት ሽታ ምንም አልነበረም፡፡ አባታችን አቡነ መልከ ጼዴቅ አቤልን ‹‹ሲኦል እንደዚህ ቀዝቃዛ ናትን?›› አሉ፡፡ አቤልን ከሲኦል እንዳወጡት እንደ እንጨት ግንድ ከሰል መስሎ አዩት፡፡ ከሱ ጋር የወጡት ነፍሳትም እንደእሱ ጠቁረው ነበር፡፡ አባታችንም ጌታችንን ‹‹ወንድሜ እንዲህ ጠቁሮ አየሁት ምኑን ማርክልኝ እነዚህንም ነፍሳት እንደዚሁ›› አሉት፡፡ ጌታችንም መላእክቱን አዘዛቸውና መርተው ወስደው የገነትን ውሃ አሳዩት፡፡ አባታችንም አቤልንና ከእሱ ጋር የወጡትን ነፍሳትን አጠመቋቸው ያን ጊዜ ፊቱ ከፀሐይ ሰባት እጅ አበራ፡፡
አምላክን የወለደች ወለላይቱ እመቤታችን ማርያምም መጣችና አባታችን አቡነ መልከ ጼዴቅን ‹‹ወንድምህን አቤልን ስጠኝ ወደ ርስቴ ልውሰደው እሱ እድል ፈንታዬ /የእኔ ድርሻ ነውና/›› አለቻቸው፡፡ አባታችንም ወለላይቱ እመቤትን ‹‹የእኔ ድርሻ ነው፡፡ ልጅሽም የደምህ ዋጋ ይሁን ብሎኛል›› አሏት፡፡ እመቤታችም አባታችንን ‹‹ና ወደ ልጄ እንሒድ›› አለቻቸውና ሁለቱም ሄደው ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ ደረሱ፡፡ እመቤታችንም ‹‹ይህ ኢትዮጵያዊ የሰጠኸኝ የእኔ ድርሻ ነው›› አለችው፡፡ አባታችን አቡነ መልከ ጼዴቅም ‹‹ለእኔም የደምህ ዋጋ ይሁንልህ ብለኸኛል›› አሉ፡፡
ጌታችንም ‹‹አንተም ኢትዮጵያዊ እሱም ኢትዮጵያዊ የኢትዮጵያን ሰዎች ሁሉ የእሷ ድርሻ ይሆኑ ዘንድ ሰጥቻለሁና›› አላቸው፡፡ ያን ጊዜም እመቤታችን በፊቱ ተደስታ ‹‹የከበረ የተቀደሰ ስሙ ይመስገን›› ብላ አቤልን ወሰደችውና የብርሃን ልብስ አልብሳ ወደ ገነት በደስታ አስገባችው፡፡ ‹‹ከአቤል ጋር የወጡት ነፍሳትም ከፀሐይ ሰባት እጅ አብርተው አባታችን መልከ ጼዴቅ ወሰዳቸውና ወደ ዘለአለም ርስቱ አስገባቸው›› ይለናል የአቡነ መልከ ጼዴቅ አስደናቂ ገድላቸው፡፡
ውድ የእመብርሃን ልጆች እመቤታችን የወደደቻት ነፍስ በምን ዓይነት ክብር እና ፍቅር የርስቷ ተካፋይ እንደምትሆን፤ እንኳን ከሰይጣን እጅ ከቅዱሳኑ እጅ ተወስዳ፣ ለእሷ ክብር በተሰናዳ፣ ዘላለማዊ ሰማያዊ ቦታ በእፎይታ እንደምትኖር አስተዋላችሁ? ወለላይቱ እመቤት የወደደቻት ነፍስ መቼም ቢሆን ከእሷ እቅፍ አትወጣም ለሌላም አትሰጥም፡፡ ሁላችንም የእርሷ ድርሻ ነንና!
እመቤታችንን በመለኮት ፀጋ ላስጌጠ፣ ለእኛም እናት ትሆነን ዘንድ ለሰጠ፣ ተወዳጅ ልጇ በመላእክቱ ቃና፣ ይድረሰው ምስጋና!!!
#ethiopianorthodox #ገድል #ስንክሳር
#AncientEthiopiaጥንታዊቷኢትዮጵያ | Ancient Ethiopia - ጥንታዊቷ ኢትዮጵያ | ጥንታዊቷ ኢትዮጵያ | Ancient Ethiopia | ancientethiopia | AncientEthiopia - ጥንታዊቷኢትዮጵያ | ancient ethiopia - ጥንታዊቷ ኢትዮጵያ
ኢትዮጵያ | ኦርቶዶክስ ተዋህዶ | ethiopianorthodox
| የኢትዮጵያኦርቶዶክስ | የኢትዮጵያኦርቶዶክስተዋህዶ | የኢትዮጵያኦርቶዶክስተዋህዶቤተክርስቲያን
| ethiopianorthodoxmezmur | ethiopianorthodoxtewahedomezmur | ethiopianorthodoxsibket
| ethiopianorthodoxtewahido | EthiopianOrthodox | ethiopianorthodoxtewahdochurch | EthiopianOrthodoxTewahedoChurch | ETHIOPIANORTHODOX | ማህበረቅዱሳን

Пікірлер: 2

  • @user-hw9dq9gv9e
    @user-hw9dq9gv9e3 ай бұрын

    አሜን አሜን አሜን ቃለ ሂወት ያሰማልን የአብነ መልከ ፃዲቅ በረከት ይደርብን ❤❤❤

  • @senaitgebremedhin7460
    @senaitgebremedhin74604 ай бұрын

    ❤️🕯እግዚአብሔር ይመስገን 🕯❤️ አሜን (3) ቃለ ሂወት ያሰማልን .የቅዱስ አባታችን አቡነ መልከ ጼዴቅ በረከታቸው ይደርብን .በሎታቸው ይማረን 🌾🌼💐🌿🙏🌿💐🌼🌾🙏🌾🌼💐🌿🙏

Келесі