ለአደጋ የማይበገሩ ቤተሰቦች ዶክመታሪ | L4R project Docmentary

የተጠቃሚዎችን ህይዎት የቀየረው ለአደጋ የማይበገር የኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት
Livelihoods for Resilience Activity project achievements which brought significant livelihood changes to beneficiaries!
-----------------------------------
በአመልድ ኢትዮጵያ ለአደጋ የማይበገር የኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት በአማራ ክልል 7 ወረዳዎች (ወልድያ ክላስተር 3 ወረዳዎች - ራያ ቆቦ፣ ሃብሩ እና ጉባ ላፍቶ)፣ መቄት ክላስተር 2 ወረዳዎች (መቄት እና ዋድላ) እና መሃል ሜዳ ክላስተር 2 ወረዳዎች (መንዝ ማማ ምድር እና መንዝ ጌራ ምድር) 36,000 ቤተሰቦችን በምግብ ዋስትና እራሳቸውን እንዲችሉ በማድረግ ከተረጅነት እንዲወጡ እየሰራ ይገኛል። ፕሮጀክቱ ከአሜሪካ መንግስት እና ህዝብ በኬር ኢትዮጵያ በኩል በተገኘ $9.92 ሚሊዮን የገንዘብ ድጋፍ እ.ኤ.አ ከታህሳስ 2016 - ሰኔ 2023 እየተተገበረ ይገኛል።
ላለፉት 6 ዐመታት በፕሮጀክቱ አማካኝነት 36,186 (ሴት፡ 11,119) ቤተሰቦች በመንደር ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ቁጠባ በመደራጀት $1.22 ሚሊዮን ቆጥበዋል። እንዲሁም 27,544 (ሴት፡ 10,530) ቤተሰቦች በተመረጡ እሴት ሰንሰለቶች ተሳትፈዋል፤ 33,452 ቤተሰቦች (ሴት፡ 15,153) በተጓዳኝ ስራዎች በመሰማራት ተጨማሪ የገቢ ምንጭ አግኝተዋል።
በወጣቶች የስራ እድል ፈጠራን በተመለከተ ለ 649 ወጣቶች (ሴት፡ 205) የራሳቸውን ስራ እንዲፈጥሩ አድርጓል፤ 373 ወጣቶች የስራ እድል ተመቻችቶላቸዋል። በተጨማሪም 20,482 ቤተሰቦች ከማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት እና ከገጠር ብድርና ቁጠባ ተቋማት ጋር በማስተሳሰር $8.4 ሚሊዮን ብድር እንዲያገኙ አድርጓል። በሌላ በኩል ለፕሮጀክቱ ተጠቃሚዎች የገበያ ትሥር ለመፍጠር 23 የግብርና ግባት አቅራቢዎች፣ 11 የዶሮ ጫጩት አሳዳጊዎች እና 3 የመኖ አከፋፋዮች ወደ ስራ ገብተው ለተጠቃሚዎች ምርት እያቅረቡ ነው።
ORDA Ethiopia’s livelihoods for Resilience project (L4R) has been working in Amhara region 7 woredas (Woldia cluster (Raya Kobo, Habru & Guba Lafto); 2 woredas of Meket cluster (Meket and Wadla woreads ); and 2 woredas of Mehalmeda cluster (Menze Mama Midir & Menze Gera Midir) to benefit 36,000 rural households (HHs) and to graduate with resilience from the productive safety net program. It is funded $9.92 from USAID through CARE Ethiopia and is being implemented from December 2016 to June 2023.
For the past 6 years, through the project, 36,186 (11,119 female) households are organized in village economic and social associations (VESAs) and mobilized USD 1.22 million. Also, 27,544 (10,530 female) HHs are engaged in selected value chain commodities, and 33,452 (15,153 female) HHs are engaged in at least one off-farm livelihood for diversifying their income sources.
With the support of the project, 649 (205 female) youths were self-employed and 373 (145 female) youths got wage. In addition, the project created an enabling environment for 20,482 HHs (44% female) to access nearly USD 8.4 million in loans from microfinance institutions (MFIs) and RuSaCCOs (rural saving cooperatives).furthermore to create market linkage for input and output suppliers of the project clients, 23 Agro-dealers are operating and supplying inputs to project clients; 8 pullet growers started supplying pullets and 3 feed franchisees are delivering products to project clients.
ለተጨማሪ መረጃ/ Social media platforms
ፌስቡክ/ Facebook: / orda-ethiopia
ቴሌግራም/ Telegram፡ t.me/ordaethiopia
ዌብሳይት/ Website: www.ordaethiopia.org
ትዊተር/ Twitter፡ / officialorda
ዩቱዩብ/ KZread: www.youtube.com/ ORDA Ethiopia

Пікірлер

    Келесі