ኢየሱስ ሊሞት የመጣባቸው አስር ምክንያቶች || Ten Reasons Jesus Came to Die || David Wood Amharic

I found this video useful, so I translated it to the best of my ability. Use this link to find the first video I translated from. I apologize for the minor mistakes I make.‌‌
• Ten Reasons Jesus Came...
መልካም ዜና
የምስራች፣ የምስራች፣ የምስራች! የምስራች ማለት መልካም ዜና ማለት ነው። የእግዚአብሔር ቃል ደጋግሞ የሚነግረን ይሄ መልካም ዜና ምንድነው? ዛሬ፣ በእግዚአብሔር ረዳትነት፣ በእግዚአብሔር ቃል ላይ ስለተጠቀሰው ስለዚህ መልካም ዜና እንነጋገራለን። ነገር ግን ስለ መልካሙ ዜና ከመነጋገራች በፊት ስለ መጥፎው ዜና ማስታወስ አለብን።
ምንድነው መጥፎው ዜና? በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን ከፈጠረ በኋላ አዳምንና ሔዋንን በምድራዊዋ ገነት ውስጥ እንዳስቀመጣቸው ታስታውሳላችሁ። እግዚአብሄር እንዲያውቁት፣ እንዲወዱት፣ እንዲታዘዙት እና ለዘላለም እንዲያከብሩት ፈጥሯቸዋል። ይሁን እንጂ እግዚአብሔር እነሱን ለመፈተን አዳምን እንዲህ አለው፡-
“በገነት ካለው ከዛፉ ፍሬ ብሉ፥ ነገር ግን እንዳትሞቱ በገነት መካከል ካለው ከዛፉ ፍሬ አትብሉ አትንኩትም።”
መጥፎው ዜና አዳምና ሔዋን እባቡን ማለትም ከተከለከለው ዛፍ ፍሬ እንዲበሉ የፈተናቸውን ዲያብሎስን ማዳመጣቸው ነው። የአዳምና የሔዋን ኃጢአት እነርሱንና ዘሮቻቸውን ሁሉ በመበከል በዓለም ላይ ችግርንና ሞትን አመጣ። ብዙ ጊዜ እንደምንሰማው፡ "ወረርሽኝ መነሻው ላይ ብቻ አይወሰንም!" የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል መጥፎ ዜና ይነግረናል፡-
“ለሰዎችም አንድ ጊዜ መሞት ከእርሱ በኋላም ፍርድ እንደ ተመደበባቸው፥...
እነሆ፥ ጌታ በሁሉ ላይ እንዲፈርድ፥ በኃጢአተኝነትም ስላደረጉት ስለ ኃጢአተኛ ሥራቸው ሁሉ ዓመፀኞችም ኃጢአተኞች በእርሱ ላይ ስለ ተናገሩ ስለ ጭከና ነገር ሁሉ ኃጢአተኞችን ሁሉ እንዲወቅስ ከአእላፋት ቅዱሳኑ ጋር መጥቶአል ብሎ ለእነዚህ ደግሞ ትንቢት ተናገረ።” (ዕብራውያን 9፥27 ይሁዳ 1፥15)
ስለዚህ፣ መጥፎው ዜና ሁላችንም ኃጢአተኞች ነን እናም የእግዚአብሔርን የጽድቅ ፍርድ መጋፈጥ አለብን! ይሁን እንጂ፣ መልካሙ ዜና (የምስራቹ) በዚያው በገነት ውስጥ፣ በምረቱ ባለጠጋ የሆነው እግዚአብሔር፣ አንድ ቀን ከድንግል የሚወለድን ኃጢአት የሌለበትን ሰው ወደ አለም እንደሚልክ ማስታወቁ ነው። ይህ ቅዱስ ሰው፣ ይህ ጻድቅ አዳኝ፣ ለአዳምና ለዘሮቹ ሁሉ ኃጢአት ለመክፈል ራሱን መስዋእት አድርጎ ይሞት ነበር። ለኛ የሚገባን የኃጢአት ቅጣት በዚህ ኃጢአት በሌለበት አዳኝ ላይ ይወድቃል። አዳምና ሔዋን ኃጢአት በሠሩበት ቀን እግዚአብሔር የሰበከው ወንጌል (የምስራች) ይህ ነው። እግዚአብሔር የዚህን አዳኝ መምጣት ለማወጅ ብዙ ሰዎችን ተጠቅሟል፣ እንዲሁም መሲህ ይባላል። እያንዳንዱ የእግዚአብሔር ነቢያት ስለ መሲሑ አንድ ነገር አውጀዋል፣ ስለዚህም እርሱ ሲመጣ እግዚአብሔር የሾመው እርሱ መሆኑን ሁሉም ይገነዘባል። ለምሳሌ ያህል፣ ከመሲሑ መምጣት ሰባት መቶ ዓመታት ቀደም ብሎ የነበረው ነቢዩ ኢሳይያስ፣ መሲሑ እንዴት እንደሚወለድ ተንብዮአል። "ድንግል ትፀንሳለች ወንድ ልጅም ትወልዳለች ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች ትርጓሜውም እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ማለት ነው።"( ማቴ. 1:23፤ ኢሳ. 7:14 ) ሚክያስ የተባለ ነቢይ ደግሞ መሲሁ ከሰማይ መጥቶ በቤተልሄም መንደር በምድር ላይ እንደሚወለድ ትንቢት ተናግሯል። በትክክል መሲሑ የተወለደበት ቦታ ይህ ነበር። ሆኖም ሚክያስ ይህን ትንቢት የተናገረው መሲሑ ከመወለዱ ከብዙ መቶ ዓመታት በፊት ነው። ነገር ግን ነቢያት የመሲሑን መወለድ ብቻ አላወጁም። በተጨማሪም መሲሁ በኃጢአተኞች ምትክ መከራ እንደሚደርስበትና እንደሚምት ትንቢት ተናግረዋል። ለምሳሌ ነቢዩ ዳዊት ሰዎች መሲሑን እንደሚንቁት፣ እንደሚያሰቃዩት፣ እጁንና እግሩን እንደሚወጉ እና እንደሚገድሉት ጽፏል። ዳዊት የመሲሑን ሞት ማወጅ ብቻ ሳይሆን፣ እግዚአብሔር መሲሁን ከሞት እንደሚያስነሳውም ተንብዮአል፤ ይህም እግዚአብሔር የአዳምን ልጆች ከኃጢአት ቅጣት ለማዳን የላከው አንድና ብቸኛ አዳኝ መሆኑን አረጋግጣል።
ስለ መሲሁ መወለድ ብዙም ክርክር የለም፣ ነገር ግን ብዙዎች በሞቱና በትንሳኤው ይሰናከላሉ። ሰዎች የላከውን መሲህ ሲያዋርዱት እግዚአብሔር እንዴት ሊቆም እና ሊመለከት እንደሚችል አይገባቸውም። ብዙ ሰዎች ሊረዱት ያልቻሉት ነገር መሲሑ ለኃጢአታችን እንዲህ አይነት መከራ እንዲደርስበት ያቀደው እኛን የሚወደን አምላክ መሆኑን ነው። ነገር ግን ነቢያቱ እንዲህ ሲሉ አውጀዋል፡- “እግዚአብሔርም በደዌ ያደቅቀው ዘንድ ፈቀደ፤ ነፍሱን ስለ ኃጢአት መሥዋዕት ካደረገ በኋላ ዘሩን ያያል፥ ዕድሜውም ይረዝማል፥ የእግዚአብሔርም ፈቃድ በእጁ ይከናወናል።”
- (ኢሳይያስ 53፥10)
ነቢያትን እናምናለን? አዎ እናምናቸዋለን እንላለን። ነቢያትን በእርግጥ የምናምን ከሆነ የጻፉትንም ማመን አለብን። ነብያት የራሳቸውን ሃሳብ እንዳልተናገሩ ማስታወስ አለብን። እግዚአብሔር የሚናገሩትን በመንፈሳቸው ውስጥ አኖረ። እንግዲያውስ እነዚያን ነቢያት ለማመን ብንቃወም፣ ማንን ነው ምንቃወመው? የምንቃወመው እግዚአብሔርን ነው። ምክንያቱም ነቢያት መሲሁ ኃጢአትን ለማስወገድ መስዋዕት ሆኖ እንደሚሞት ትንቢት እንዲተነብዩ ያነሳሳው እርሱ ነውና።
{የሚቀጥለው ማሊክ የሚባል ሰው የግል ምስክርነት ነው።} እዚህ ጋር ቆም ላድርገውና እንዴት በኢየሱስ ክርስቶስ አማኝ እንደሆንኩ ልንገራችሁ። በወጣትነቴ በቀን አምስት ጊዜ ለመጸለይ እና አመታዊ ጾምን ለመጾም ታማኝ ነበርኩ፣ ነገር ግን ከሞትኩ በኋላ ወዴት እንደምሄድ አላውቅም ነበር። ዙሪያዬ ያሉትን ሁሉ ጠየኩ፣ ሆኖም ግልጽ የሆነ መልስ አላገኘሁም። ወንጌልን (ኢንጂልን) ሳጠና ግን፣ ከሞቴ በኋላ ወዴት እንደምሄድ ማወቅ እንደምችል አወቅሁ፤ ምክንያቱም መሲሁ ኢየሱስ ራሱ በወንጌል እንዲህ ይላል፦ “እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ቃሌን የሚሰማ የላከኝንም የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፥ ከሞትም ወደ ሕይወት ተሻገረ እንጂ ወደ ፍርድ አይመጣም።” (ዮሐንስ 5፥24) እንዲሁም እንዲህ ብሏል፦ “ኢየሱስም፦ ትንሣኤና ሕይወት እኔ ነኝ፤ የሚያምንብኝ ቢሞት እንኳ ሕያው ይሆናል፤” (ዮሐንስ 11፥25) ስለዚ፣ ራሴን ለማዳን ከራሴ ጥረት ንስሃ ገብቼ ነቢያት ሁሉ “በእርሱ የሚያምን ሁሉ በስሙ የኃጢአቱን ስርየት ይቀበላል" ብለው ትንቢት በተናገሩለት መሲህ አመንኩኝ (ሐዋርያት 10፥43)። ተስፋዬን ሁሉ ወስጄ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ አስቀመጥኩት። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ እግዚአብሔር ለመንፈሴ ሰላም አምጥቶላታል። አሁን ህሊናዬ አይረበሽም። ኢየሱስ በመስቀል ላይ ከሰራው ሥራ የተነሳ የወደፊት እጣዬ በሚያስደንቅ ሁኔታ ብሩህ ነው። በሕይወቴ እንደ ክርስቶስ ደቀ መዝሙር፣ አንዳንድ ጊዜ ችግር እና መከራ ያጋጥመኛል ምክንያቱም እምነቴ ከዘመዶቼ እና ከጓደኞቼ አስተያየት ስለሚለያይ፤ ግን ሰላም አለኝ። የእግዚአብሔር ሰላም ልቤንና አእምሮዬን ሞልቶታል። ይህን የሰጠኝ ኢየሱስም እንዲህ ይላል፦ “ዓለም ቢጠላችሁ ከእናንተ በፊት እኔን እንደ ጠላኝ እወቁ።” (ዮሐንስ 15፥18) “ሰላምን እተውላችኋለሁ፥ ሰላሜን እሰጣችኋለሁ፤ እኔ የምሰጣችሁ ዓለም እንደሚሰጥ አይደለም። ልባችሁ አይታወክ አይፍራም።” (ዮሐንስ 14፥27) እና ወዳጆች ሆይ፣ ጌታ ለእኔ እና በእኔ ያደረገውን ለእያንዳንዳችሁ ሊያደርግ ይችላል። ካንተ ወይም ካንቺ አንድ ነገር ይጠይቃል፡-ሙሉ ልብህን እንድትሰጠው። ሙሉ ልብሽን እንድትሰጪው። የቀረውን እሱ ያደርገዋል። ጌታ ኢየሱስ ራሱ እንዲህ ብሏልና። "እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ። ቀንበሬን በላያችሁ ተሸከሙ ከእኔም ተማሩ፥ እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና፥ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ፤" (ማቴ. 11:28-29)
እግዚአብሔር ታላቁን ማዳኑን መቼም ቢሆን አይሸጥልህም ወይም አይሸጥልሽም። እንዲሁ ያለ ምንም ዋጋ (ከእናንተ ባልሆነ ዋጋ) በነጻ ሊሰጣችሁ ነው ሚፈልገው። መልካም ስራ፣ ፀሎት (ሶላት) እና ፆም በውስጣችሁ ጥሩ ስሜት ይሰጡ ይሆናል፣ ነገር ግን የእግዚአብሔርን ፅድቅ አያረኩም! ወደ እግዚአብሔር ገነት የምትገባበት/የምትገቢበት መንገድ አንድ ብቻ ነው።
1.) በመጀመሪያ ኃጢአተኛ እንደሆንክና አምላክን ለማስደሰት የሚያስችል ኃይል እንደሌለህ መገንዘብ ይኖርብሃል።
2.) ከዚያም ኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝ እንደሆነ፣ ኃጢአትህን ለማስወገድ እግዚአብሔር በመስቀል ላይ እንዲሞት እንደ ላከውና እግዚአብሔር የዘለአለም ሕይወትን ይሰጥህ ዘንድ እንዳስነሳው ማመን አለብህ።
የኦሮምኛውን ቻናሌን ለማግኘት ይህንን ተጫኑ👇
/ @dhugaanniboqachiisa
አስተያየታችሁን በውስጥ ማድረስ የምትፈልጉ ይህንን የቴሌግራም ሊንክ ተጠቀሙ👇
t.me/BibleAndMe
Additional: - ewnetyasarfal123@gmail.com

Пікірлер: 78

  • @zerihunnega7809
    @zerihunnega78093 ай бұрын

    እሱ ሞታችን ሞተ የዘላለም ህወሃት ሰጠን ተባረክ ጌታ እየሱስ ❤❤❤❤❤❤❤

  • @user-sn9ru3hk5i
    @user-sn9ru3hk5i2 ай бұрын

    Tebarek wondime እግዚአብሔር ከዚህ በላይ ትጋትን ይጨምርልህ ... ጸጋውንም ይጨምርልህ ....❤❤❤🎉🎉🎉🎉🎉🎉

  • @reyanabera9856
    @reyanabera98562 ай бұрын

    በጣም ብዙ ማወቅ ያለብኝን ነገር እያወኩ ነው thank you bro

  • @Lisalove.-yz9xl
    @Lisalove.-yz9xl2 ай бұрын

    መሃመድ እምነቱን ለመመስረት የብዙ ንፁሃንን ሰዎችን ደም አፈሰሰ የምስኪኗ ህፃን የአይሻን ደም ሳይቀር ። ኢየሱስ ክርስቶስ ግን እኛን ለማዳን በመስቀል ላይ ደሙን አፈሰሰ ለኛ ሲል ሞተ ተቀበረ ሞትንም ድል ነስቶ ከሞት ተነሳ ለኛም የዘላለምን ህይወት አደለን ስሙ ይባረረክ ። ኢየሱስ ይለያል ይበልጣል ያድናል !!!!!!!!!!!!!!!!!!

  • @user-wv9yy1gu2b
    @user-wv9yy1gu2b2 ай бұрын

    አሜን❤❤❤❤❤❤❤❤ኢየሱስ ለዘላለም ጌታ ነው

  • @aishamohammid5487
    @aishamohammid5487Ай бұрын

    እግዚአብሔር ይመስገን አሜን አሜን እግዚአብሔር ይመስገን

  • @noorwaga4502
    @noorwaga45023 ай бұрын

    የእግዚአብሔር ፍቅር የተለየ ነው ።ብዙዎች እየነቁ ስለሆነ በርታ ተባረክ ❤❤❤

  • @user-dc5dr9cw2e

    @user-dc5dr9cw2e

    2 ай бұрын

    አዎ እየነቁነው ኢየሱስ ፈጣሪ አለመሆኑንና መልእክተኛ ነቢይ ብቻ መሆኑን እየተረዱ መጥተዋል፡፡ ወንድሜ ብዙ ሰዎች እኮ በወከባ፡በድራማ፡በጩኸትና የሌላውን እምነት በሀሰት በማጥላላት ሳይሆን ባይብሉን ብቻበጥልቀት በመመርመር እየሰለሙ መሆኑን መረጃው ከሌለህ ጎግል ላይ ሰርች አድርገህ ድረስበት፡

  • @ewnetyasarfal

    @ewnetyasarfal

    2 ай бұрын

    @user-dc5dr9cw2e 😁😁😂😂

  • @mintesnot6857
    @mintesnot68573 ай бұрын

    ተባረክ ወንድሜ በርታ😇

  • @haseerahmad2421
    @haseerahmad24212 ай бұрын

    ቃለህይወትያሰማልን

  • @FevenZerihun-ld8dd
    @FevenZerihun-ld8dd3 ай бұрын

    እግዚአብሔር ይባርክህ በፀጋውን ያብዛልህ

  • @SurafelFekadu-zl9mc
    @SurafelFekadu-zl9mcАй бұрын

    በጣም እየተማርንበት ነው በርታልን

  • @user-rj1go6zw6e
    @user-rj1go6zw6e3 ай бұрын

    ተባረክ❤❤❤faithful servant's of kingdom ❤❤❤

  • @mintesnot6857
    @mintesnot68573 ай бұрын

    ኢሳይያስ 53 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹ የሰማነውን ነገር ማን አምኖአል? የእግዚአብሔርስ ክንድ ለማን ተገልጦአል? ² በፊቱ እንደ ቡቃያ ከደረቅም መሬት እንደ ሥር አድጎአል፤ መልክና ውበት የለውም፥ ባየነውም ጊዜ እንወድደው ዘንድ ደም ግባት የለውም። ³ የተናቀ ከሰውም የተጠላ፥ የሕማም ሰው ደዌንም የሚያውቅ ነው፤ ሰውም ፊቱን እንደሚሰውርበት የተናቀ ነው፥ እኛም አላከበርነውም። ⁴ በእውነት ደዌያችንን ተቀበለ ሕመማችንንም ተሸክሞአል፤ እኛ ግን እንደ ተመታ በእግዚአብሔርም እንደ ተቀሠፈ እንደ ተቸገረም ቈጠርነው። ⁵ እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቈሰለ፥ ስለ በደላችንም ደቀቀ፤ የደኅንነታችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ፥ በእርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን። ⁶ እኛ ሁላችን እንደ በጎች ተቅበዝብዘን ጠፋን፤ ከእኛ እያንዳንዱ ወደ ገዛ መንገዱ አዘነበለ፤ እግዚአብሔርም የሁላችንን በደል በእርሱ ላይ አኖረ። ⁷ ተጨነቀ ተሣቀየም አፉንም አልከፈተም፤ ለመታረድ እንደሚነዳ ጠቦት፥ በሸላቶቹም ፊት ዝም እንደሚል በግ፥ እንዲሁ አፉን አልከፈተም። ⁸ በማስጨነቅና በፍርድ ተወሰደ፤ ስለ ሕዝቤ ኃጢአት ተመትቶ ከሕያዋን ምድር እንደ ተወገደ ከትውልዱ ማን አስተዋለ? ⁹ ከክፉዎችም ጋር መቃብሩን አደረጉ፥ ከባለጠጎችም ጋር በሞቱ፤ ሆኖም ግፍን አላደረገም ነበር፥ በአፉም ተንኮል አልተገኘበትም ነበር። ¹⁰ እግዚአብሔርም በደዌ ያደቅቀው ዘንድ ፈቀደ፤ ነፍሱን ስለ ኃጢአት መሥዋዕት ካደረገ በኋላ ዘሩን ያያል፥ ዕድሜውም ይረዝማል፥ የእግዚአብሔርም ፈቃድ በእጁ ይከናወናል። ¹¹ ከነፍሱ ድካም ብርሃን ያያል ደስም ይለዋል፤ ጻድቅ ባሪያዬም በእውቀቱ ብዙ ሰዎችን ያጸድቃል፥ ኃጢአታቸውን ይሸከማል። ¹² ስለዚህም እርሱ ብዙዎችን ይወርሳል፥ ከኃያላንም ጋር ምርኮን ይከፋፈላል፤ ነፍሱን ለሞት አሳልፎ ሰጥቶአልና፥ ከዓመፀኞችም ጋር ተቈጥሮአልና እርሱ ግን የብዙ ሰዎችን ኃጢአት ተሸከመ፥ ስለ ዓመፀኞችም ማለደ።

  • @AnwarTriche-ep5hi

    @AnwarTriche-ep5hi

    3 ай бұрын

    ምንቴ በምታቀርባቸው መዝሙሮች እተባረክን ነው

  • @melkamuyosef9509
    @melkamuyosef95093 ай бұрын

    ትልቅ አደረ ነው በርታ ወንድሜ

  • @melkamusonko
    @melkamusonko3 ай бұрын

    እውነት ያሳርፋል ስለ አንተ እግዚአብሔር ይመስገን እንደ ቅጠል ለምረግፍ ፍጥረት እኒድረስ 😢😢 ቅዱሳን ሼር እናደርግ አብሬን ወንጌል እኒስራ ኤሄን የመሰለ ትምህርተ ወንጌል ካላረገን ምን እናደርግ ? የሀሰተኛ ነብያት ስብከት መክና ቤት ቁሳቁስ ከማለት መሠረታዊ ክርስትና ትምህርት እንኳን በደንብ የማያስተምሩ ናቸው ትሄዳለ ትገባለ ከማለት ውጭ

  • @eexx5392
    @eexx53923 ай бұрын

    እግዚአብሔር ይባርክህ ወንድሜ ፀጋውን ያብዛልህ የእግዚአብሔር ፍቅር ምንኛ የበዛ ነው

  • @MesayAdmasu-oe7ci
    @MesayAdmasu-oe7ci3 ай бұрын

    ተባረክ እየተጠቀመን ነዉ

  • @hassanuddan8788
    @hassanuddan87882 ай бұрын

    Amen tebarek❤❤❤❤❤

  • @berhanualemu4689
    @berhanualemu46893 ай бұрын

    ተባረኩ!!

  • @AnwarTriche-ep5hi
    @AnwarTriche-ep5hi3 ай бұрын

    እኔ በጣም ይገርመኛል ምን ያክል ጌታ ኢየሱስ ቢወደን ነው እላለሁ

  • @asagdachmahammda9283
    @asagdachmahammda9283Ай бұрын

    ❤❤❤❤❤❤❤እግዚአብሔር ያብዛልህ

  • @bettybreaep
    @bettybreaep3 ай бұрын

    ዋዋዋዋውውውውው❤❤❤

  • @IsraelTesfalem
    @IsraelTesfalem3 ай бұрын

    bertaln wedme 💛💛💛💛💛💛💛💛💛💛💛💛💛💛💛💛

  • @user-qv4zq6mc9c
    @user-qv4zq6mc9c3 ай бұрын

    ተባረኩ

  • @user-rp8bk8cr6p
    @user-rp8bk8cr6p2 ай бұрын

    Yene geta ❤️

  • @amlisium6189
    @amlisium61893 ай бұрын

    Kbr le Geta Jesus Krstos yhun, 🙏✝️🙏

  • @BekiAshagre
    @BekiAshagre2 ай бұрын

    ❤❤bewunet wendimachin tsegawun yabizalh

  • @aziebsolomon7360
    @aziebsolomon73603 ай бұрын

    🙏🙏🙏

  • @masara7252
    @masara72523 ай бұрын

    Egezehabeher yabarekachu ❤❤

  • @degefuililogifatodegefuili8823
    @degefuililogifatodegefuili88233 ай бұрын

    ተባረክ በርታ ❤❤❤

  • @noahpaul8390
    @noahpaul83903 ай бұрын

    ፀጋው ይብዛልህ በርታልን ወንድሜ

  • @user-hh2zm8tm1y
    @user-hh2zm8tm1y2 ай бұрын

    I appreciate the Love of God

  • @motumaasefa1822
    @motumaasefa18222 ай бұрын

    wooow

  • @FikaduAyita-nq3ro
    @FikaduAyita-nq3ro3 ай бұрын

    Wendema tebarik

  • @teshomebekele3479
    @teshomebekele34793 ай бұрын

    God bless you. Keep go on

  • @asratfeyisa9377
    @asratfeyisa93772 ай бұрын

    Bonjour la traduction en français je voudrais bien l'explication en français merci

  • @bonakena4902
    @bonakena49023 ай бұрын

    Geta yebarkh bzuwoch eyamallaxu nw❤❤

  • @TwmTemesgen
    @TwmTemesgen3 ай бұрын

    Amen amen amen

  • @HanaAdem-nl5rn
    @HanaAdem-nl5rn3 ай бұрын

    God belss you

  • @misganabere6115
    @misganabere61152 ай бұрын

    ኢየሱስ ክርስቶስ እውነተኛ አምላክና የዘላለም ህይወት ነው።ሮሜ 9:5 ኢየሱስ ፍቅሩ ይለያል ሰው በጎቹን ቢጠብቅ አርዶ ሊበላቸው ነው ኢየሱስ ግን ስለበጎቹ ራሱን አሳልፎ ሰጠ።ኢየሱስ ሆይ ሁሉም በፍቅርህ እንኖር ዘንድ እርዳን።የጌታችን ጸጋና ሰላም በአንተ ላይ ይሁን ወንድሜ።

  • @user-hb1fb1jd7w

    @user-hb1fb1jd7w

    2 ай бұрын

    እያሱስ ሰው ነው በፍፁም አምላክ ሊሆን አይቻልም ሁላችሁም ይን እውነት ታቃላችሁ መዳን እየሱስን በፈጠረው ብቻ ነው እሱ ጥበበኛ ሁሉን ችይ በመጀመሪያም በመጨረሻም አሽናፊ አንድ አላህ ብቻ ነው

  • @misganabere6115

    @misganabere6115

    2 ай бұрын

    @@user-hb1fb1jd7w Allah yemibal toat enji amlak yelem eyesus amlak new mnm tirtir yelewum

  • @ganethailu7156
    @ganethailu71563 ай бұрын

    ❤❤

  • @ruhamafati4217
    @ruhamafati42173 ай бұрын

    ❤❤❤

  • @user-dc5dr9cw2e
    @user-dc5dr9cw2e3 ай бұрын

    ማሻ አላህ❤❤

  • @AdmasuAdmasu-ww1xc
    @AdmasuAdmasu-ww1xc2 ай бұрын

    ተጠናክሮ መቀጠል ያለበት አገልግሎት ነው !!!

  • @medhanitnegussie3682
    @medhanitnegussie36823 ай бұрын

    ❤❤❤❤❤❤❤

  • @user-st7es7ij1g
    @user-st7es7ij1g3 ай бұрын

    Waqaayyoo Sina ebisuu

  • @teklittewelde1487
    @teklittewelde14872 ай бұрын

    Translation to Tigrinya will be more useful. Do it also in Tigrinya

  • @AkaluGebere-z8d
    @AkaluGebere-z8d29 күн бұрын

    Hi

  • @TadelaTsagaye-re7se
    @TadelaTsagaye-re7se25 күн бұрын

    ❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤🎉🎉🎉🎉🎉

  • @kumelgeremew9335
    @kumelgeremew93353 ай бұрын

    ❤❤❤❤❤❤......

  • @user-mo6vs4sk3v
    @user-mo6vs4sk3v3 ай бұрын

    ❤❤❤❤❤❤❤❤❤🎉🎉🎉🎉🎉

  • @ahmubinali6838
    @ahmubinali68383 ай бұрын

    Chirstianu eyesusin geta bloo ketekebele .geta endet yimotal

  • @Hopeofsammy

    @Hopeofsammy

    3 ай бұрын

    meche aygebachume 😂

  • @masartmissoo1160

    @masartmissoo1160

    3 ай бұрын

    Awo unat now wondim amilak silamayimot now qali siga hona kaza iyesus siga labiso basiga ignani masilo siga labiso mamot chala iyesus kehatiyat baqar hulumi nagaru yesu lik inde igna now inde igna hatiyat bicha now yalisarwu

  • @masartmissoo1160

    @masartmissoo1160

    3 ай бұрын

    Qoyi lamin inde migarmachu gira yigabagali sasibo miknyatum samayinina midirn baqal bicha yefatar fatar indet irasun basiga magilat yikabdal bilachu tasibalachu fatar ayiwolidm ayiwoladim gin isu basiga yematawu kalamanori wode manor satihon kemanori wode matayet now yematwu gabachu sitasibu isk fatar irsaun basiga magilat yaqitowal yefalagawun nagar madirag ayichlm isu min yaqitowal

  • @Teyboawlou
    @Teyboawlou3 ай бұрын

    አልተሰቀለም አልተገደለም ስቃይና መከራ ሲበዛበት ኢሎሄ ኢሎሄያ (ጌታዬ ጌታዬ ሆይ) ሳማ ሰበቅተኒ ብሎ ፀልያል ጌታዬ ጌታዬ ሆይ ለማን ትተወኛለህ ብሎ አምላኩን ተማፅኗል መከራ ሲያበዙበት አምላክም ከመሃላቸው አነሳው ለኛ ብሎ መከራን ተቀበለ ትላላችሁ ስቃይ አልቻለም ሲበረታበት ሰው ነውና አልቻለም ጌታውን ተማፀነ መጵሃፍ ቅዱስን በደንብ ተረዳ

  • @ewnetyasarfal

    @ewnetyasarfal

    3 ай бұрын

    ለማንኛውም እስኪ ይህንን ሊንክ ነክተህ ስማው። ለጥያቄህ መልስ የሚሆን ይመስለኛል። kzread.info/dash/bejne/aYRt27t7ccbOk6w.htmlsi=um8PJ_C2GmW6vicI

  • @AY-me3rw

    @AY-me3rw

    3 ай бұрын

    ትንቢት ምን እንደሆነ ምታቅ ከሆነ እስቲ "መዝሙረ ዳዊት 22" አንብበው

  • @selambirhane1173
    @selambirhane11733 ай бұрын

    Please for this change tag aerglen

  • @ewnetyasarfal

    @ewnetyasarfal

    3 ай бұрын

    ይቅርታ አልገባኝም

  • @user-dc5dr9cw2e
    @user-dc5dr9cw2e3 ай бұрын

    ቃልም በእግዚአብር ዘንድ ነበረ ፡ቃልም እዚአብሄር ነበረ ከተባለ፡፡፡እግዚአብሄር በእግዚአብሄር ዘንድ ነበረ ማለት ነው፡፡ ይሄ ምን አይነት እርስ በርሱ የተጠላለፈ ጥቅስ ነው

  • @ewnetyasarfal

    @ewnetyasarfal

    3 ай бұрын

    ወሬ ምታቀብልለት አባትህ አህመዲን እንደሚከትለው ጠይቆ መልስ ተሰቶት ነበር። አንብበው፡ 1. ዮሐንስ 1፡1 የኢየሱስን “አምላክነት” ይገልፃል ብለው ያምናሉን?“በመጀመሪያ ቃል ነበር፡፡ ቃልም እግዚያብሔር ዘንድ ነበር፡፡ ቃልም እግዚያብሔር ነበር” ይላል፡፡ “እርሱም በመጀመሪያ ከእግዚአብሔር ጋር ነበር፡፡” (ዮሐንስ 1:2) ሀ) “በመጀመሪያ” ሲባል የምን መጀመሪያ? ለመሆኑ አምላክ መጀመሪያ አለውን? እንዴት “በመጀመሪያ” ይባላል? ዘለዓለማዊ አይደለምን? ጠያቂው ጥቅሶችን በትክክል ያለማንበብ ችግር በእጅጉ ይስተዋልባቸዋል፡፡ በመጀመርያ፣ ማለትም መጀመርያ የተባለው ቅፅበት ሲፈጠር ቃል ነበረ፡፡ ቃል በመጀመርያ ወደ መኖር የመጣ ሳይሆን በመጀመርያ የነበረ ነው፡፡ ይህ ቃል ጊዜና ቦታን (Time and Space) ጨምሮ የሁሉ ፈጣሪ በመሆኑ (ቁ.3) ለመኖር ጊዜና ቦታ አያስፈልገውም፡፡ ይህ ባሕርይ ደግሞ የአምላክ እንጂ የሌላ ሊሆን አይችልም፡፡ ለ) “የአምላክ ቃል” የሚባለው ኢየሱስ ክርስቲያኖች እንደ ሚሉት “ዘለዓለማዊ ነው” ከተባለ እንዴት “መጀመሪያ” ይኖረዋል? በዚህ ቦታ ኢየሱስ በመጀመርያ እንደነበረ እንጂ መጀመርያ እንደነበረው አልተጻፈም፡፡ ጠያቂው አንብቦ የመረዳት ችሎታቸው ደካማ ነው፡፡ ሐ) በዮሐንስ 1:1 በሦስተኛው ዐረፍተ ነገር ቃልና እግዚአብሔር አንድ መሆናቸውን ተነግሮናል፤ ቃል በሚለው ምትክ “እግዚአብሔር”ን ብንተካ “በመጀመሪያ” እግዚአብሔር ነበር፤ እግዚአብሔርም እግዚአብሔር ዘንድ ነበር፤ እግዚአብሔርም እግዚአብሔር ነበር” ይሆናል፡፡ የትኛው እግዚአብሔር ነው እግዚአብሔር ዘንድ የነበረው? አእምሮ መጠቀም አይሻልምን? ኧረ እባካችሁ እናስብ!! አሕመዲን ኧረ ባክዎትን ከሐዋርያት፣ ከቅዱሳን አባቶች፣ በየዘመናቱ ከኖሩት ክርስቲያን ሊቃውንት እና ከመላው ሕዝበ ክርስቲያን ይልቅ እርስዎ የተሻለ የማሰብ ችሎታ እንዳሎት በማስመሰል አይንጠባረሩ! ያልገባዎትንና ልክ ያልመሰልዎትን ነገር በትህትና ከመጠየቅ ይልቅ ራስዎን ብቻ አሳቢ ሌላውን ማሰብ የተሳነው ማስመሰሉ ለምን አስፈለገ? የዚህች የተለመደች የአላዋቂዎች ስላቅ ምንጭ እንኳ እርስዎ እንዳልሆኑ ጠንቅቀን እናውቃለን፡፡ ሐዋርያው እየተናገረ ያለው ከሥላሴ አካላት መካከል ስለ ሁለቱ ሲሆን ሁለቱንም “እግዚአብሔር ብሎ መጥራቱ የሚያመለክተው አብ እና ወልድ በመለኮት አንድ በአካል ግን ልዩ መሆናቸውን ነው፡፡ ጥቅሱ እየተናገረ ያለው እግዚአብሔር ወልድ ከእግዚአብሔር አብ ጋር ስለመኖሩ ነው፡፡ ከአሕመዲን በስተቀር ይህንን ሐቅ ሊስት የሚችል አሳቢ አዕምሮ ያለው ሰው ሊኖር አይችልም፡፡

  • @abebayehuyigzaw
    @abebayehuyigzaw3 ай бұрын

    ፀድቄአለሁ ብለህ ተኛ የጴንጤ ስብከት

  • @noahpaul8390

    @noahpaul8390

    3 ай бұрын

    መጽሐፉን ብታነብ አይሻልም

  • @ZewduRegassa

    @ZewduRegassa

    3 ай бұрын

    በሥራ እፀድቃለሁ ብለህ ልፋ ኦርቶዶክስ ።ስራ የኢየሱስን ደም ለማራከስ የሚደረግ .....ሮሜ ምዕራ 3 ን አንብብ።

  • @bewketgelaw7415

    @bewketgelaw7415

    2 ай бұрын

    wondme yeyakob meliktn anbib emnet yale sira kentu new yilal

  • @user-dc5dr9cw2e
    @user-dc5dr9cw2e3 ай бұрын

    እስቲ ልጠይቃችሁ ኤሎሄ ማለት ምን ማለት ነው?

  • @zewdusima8049

    @zewdusima8049

    3 ай бұрын

    “በዘጠኝ ሰዓትም ኢየሱስ፦ ኤሎሄ ኤሎሄ ላማ ሰበቅታኒ? ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኸ። ይህም፦ አምላኬ አምላኬ፥ ስለ ምን ተውኸኝ? ማለት ነው።” - ማቴዎስ 27፥46

  • @user-dc5dr9cw2e
    @user-dc5dr9cw2e3 ай бұрын

    የሚሞት ፡የሚበላ፡ የሚጠጣ አምላክ😂😂

  • @user-jl9ty6gs4b

    @user-jl9ty6gs4b

    3 ай бұрын

    😂😂😂😂😂 መሀመድ የሽፍቶች አለቃ የቁረይሾችን ቅፍለት በመዝረፍ ውንብድና ጀመሬ😂😂😂 ከድጃን ተጠጋት ሀብት አፈራ በ 10 ዓመታት 83 ጦርነት ተዋጋ በመርዝ ገደሉት ሳሀቦቹ እርስ በርስ ተጨፋጭፈው አለቁ 😂😂

  • @Alemtsehay777

    @Alemtsehay777

    3 ай бұрын

    ኢየሱስ ጌታ ነዉ። በሱ ብታምን የዘላለም ህይወትን ታገኛለህ።

  • @ZennaalemayehuEshete

    @ZennaalemayehuEshete

    3 ай бұрын

    ለነገሩ የመሐመድ አይብስ ብለሽ ነው ? የሥድስት አመትዋን ዐይሻን አቅፎ የሚተኛ ነብይ😅😅 ጨካኝ፣ ቁላውሥ እንዴት ይቆምለታል ? ደግሞስ፣ ከጉዱ ሑሉ የሚገርመው፣ መሐመድ የፈለጋትን ሴት መውሰድ ይችላል፣ ባለትዳርም ብትሆን ትዳሩዋን ትታ መሔድ ዐለባት፣ ከዐላሕ የተሠጠው ሥልጣን😅😅 ይሔው ጥቁሩን ዲንጋይ ዐቁሞ፣ለጣዖት ሥታፈነድዱ እንትኖሩ ያደረገ የቆሬሽ ዐራዳ😅😂። ምላሥሽን ከዘረጋሽ፣ ሥለዚሑ ሌባ ነብይሽ፣ ከቁርዐኑ፣ ሐዲሡ የተፃፈውን ሑሉ ዐሣፋሪ ሥራው ይላክልሐል። ሠላሙዐሌኩም፣ ወራክማቱላ፣ወባረካቱ። ዐላሕ ይክረቤተክዒንሻዐላህ😁😁😁😁👌

  • @user-jl9ty6gs4b

    @user-jl9ty6gs4b

    3 ай бұрын

    @@ZennaalemayehuEshete ክርስቲያን መሆን እኮ መታደል ከሁሉ ደስ የምለኝ የክርስቶስ ተከታዩች የተማሩ ሁሉን ነገር ጠንቅቀው የምያውቁ ጌታቸውን በተገቢ ቦታ ተገቢ ጥያቄ የምጠይቁ ክብር ለክርስቶስ ይሁን kkkkkkkk ሙስሊሞች የምገርሙኝ ጭራሽ ተራ ገበሬን የማይወዳደረውን መሀመድን ከክርስቶስ ጋር ስያወዳድሩት ያስቀኛል kkkkkkkkkkkkkkkkkkkk የሀገሬ ሚስኪን ገበሬ ለመስራት ሂሊናው የከበደውን እምቢ ያለውን መሀመድ አድርጎት ፈፂሞት አልፈዋል መሀመድ እኮ ታርኩ እጅግ ያስደነግጣል ያሳፍራል ያሸማቅቃል አረ ሙስሊሞች pls ታርካችሁን አንብቡ ተረዱ ወይ መረዳት ካቃታችሁ ዝም በሉ እየሱስ ይበላል ይጠጣል አይሁድ ሰቀለው የምበላ የምጠጣ ሰው ታመልካላችሁ ለእናንተ ሀይማኖታችሁ ላይ መዘዝ እያመጣችሁበት ነው አትመኑበት እሥልም እንተርኔት አፈር ከድሜ እያስጋጠው ባላወቃችሁበት መንገድ እስልምና እየተለወጠ ነው ህዝቡ እስልምና እየተወ ነው 100% መሀመድን ማን ገደለው? የመሀመድ 72 የልጅ ልጆቹ ጭምር ለምን በሙስሊሞች ተጨፍጭፈው ተገደሉ? አራቱ የመሀመድ ኻሊፋዎች ለምን በመርዝ በገዛ አሳዳሪያቸው ባሪያ በሙስሊሞች በአሰቃቂ ሁኔታ ተገደሉ የውሼት የቁራዔን ሱራ 17 ቁጥር 111 ለምን ተፃፈ? አላቅሳን የእየሩሳለም መስክድ ያሰራው ሽፍታው የኡመያዶች ከሊፋ አብዱል አሊ ማልክ ለምን ዋሸ? መሀመድ በህይወት እያለ ጨርሶ መስክዲ አልተገነባም በየትኛው በር መሀመድ ገብት አልቃሳ ሰገደ ??? እስላም ውርጦች መልስ አምጡ አምቢ ካላችሁ አሰቃቂው የመሀመድ ቤተሰቦች ላይ ሙስሊሞች በሙስሊም ነብያቸው ላይ ያደረሱት ጭፍጨፋ ታርክ ይቀጥላል kkkkkkkkkkk ሹክራን ላክ ሁቤል ጣኦት አላህ kkkkkkkkkkk

Келесі