ጌታ ሆይ ጨርቅህን ይዤ እማፀናለሁ Dr, Dereje Kebede

ጌታ ሆይ ጨርቅህን ይዤ እማፀናለሁ
ከአንተ ወዴት ከቶ እሄዳለሁ
ደጃፍህ ብኖር ተጥዬ
ክብሬ ነው ለእኔ ተስፋዬ /2X/
ድካሜን አውቃለሁ ኃጢያት ሲያሸንፈኝ
ያም ቢሆን ጨርቅህን ማንም አያስጥለኝ
ማንም አያስጥለኝ
የአመፃዬ ክምር ቢያስቆጣህም በጣም
አንተው እስክትምረኝ ከቤትህ አልወጣም
ከቤትህ አልወጣም
አዝ
ጌታ ሆይ ጨርቅህን ይዤ እማፀናለሁ
ከአንተ ወዴት ከቶ እሄዳለሁ ደጃፍህ
ብኖር ተጥዬ
ክብሬ ነው ለእኔ ተስፋዬ /2X/
ፍሬ አልባ ንሰሃ ነጋ ጠባ ማረኝ
በፊትህ እንዳልቆይ እጅግ አሳፈረኝ
እጅግ አሳፈረኝ
አመጻዬ በዝቶ ጭቃ ባላቁጥም
ደጅህ እሞታለሁ ተስፋዬን አልቆርጥም
ተስፋዬን አልቆርጥም
አዝ
ጌታ ሆይ ጨርቅህን ይዤ እማፀናለሁ
ከአንተ ወዴት ከቶ እሄዳለሁ
ደጃፍህ ብኖር ተጥዬ
ክብሬ ነው ለእኔ ተስፋዬ /2X/
የነፍሴን ውሳኔ አንተው ታውቀዋለህ
እንደምወድህም ውስጤን ታየዋለህ
ውስጤን ታየዋለህ
ከልጅነት ወራት ጀምሮ አውቅሃለሁ
እንዳንተ ቸር ወዳጅ ወዴት አገኛለሁ
ወዴት አገኛለሁ
አዝ ጌታ ሆይ ጨርቅህን ይዤ እማፀናለሁ
ከአንተ ወዴት ከቶ እሄዳለሁ
ደጃፍህ ብኖር ተጥዬ
ክብሬ ነው ለእኔ ተስፋዬ /2X/
ለህይወቴ ሰላም ለልቤ ፀጥታ
ዘለአለም ገዥዬ አንተ ብቻ ጌታ
አንተ ብቻ ጌታ
ግራ ቀኝም አልል ነፍሴንም አልሸጣት
ከአንተ ተለይታ አወይ ትርጉም የላት
አወይ ትርጉም የላት
ጌታ ሆይ ጨርቅህን ይዤ እማፀናለሁ
ከአንተ ወዴት ከቶ እሄዳለሁ
ደጃፍህ ብኖር ተጥዬ
ክብሬ ነው ለእኔ ተስፋዬ /2X/

Пікірлер

    Келесі