#ግብመተለም

ግብ ማለት ወደፊት በህይታችን ለማሳካት የምናልምው ቦታ ማለት ነው፡፡ግብ ከሌለን የዘፈቀደ ህይወት በመምራት በህይወታችን አቅጣዓዎች ላይ ትኩረት ለማድረግ አንችልም፣ ያለንን አቅም አሟጠን ለመጠቀም አንችልም አንዲሁም በኑሮአችን እርካታ ላንገኝ አንችላለን፡፡ ግብ ስንተልም የማያሻማ፣ የሚለካ፣ ሊደረስበት የሚችል፣ ተጨባጭ የሆነ እና የጊዜ ገደብ ያለው መሆን አለበት፡፡ ግባችን የሚከተሉትን ጥያቄዎች መመለስ አለበት ምን? ምንያህል? መቼ? ማን?አንዴት? በህይወታችን ላይ የተለያዩ ግቦች ሊኖሩን ይችላሉ ለምሳሌ የትምህርት፣ የቤተሰብ፣ የጤንነት፣ የማህበራዊ ሕይወት፣ የመንፈሳዊ ሕይወት አንዲሁም የኢኮኖሚ አቅም መዳረሻ ሊኖረን ይገባል፡፡
ግብ ከተዘጋጀ በኃል በድርጊት መታገዝ ይኖርበታል፡፡ ይህንን ሃሳብ ለማጠናከር ጃፓኖች “ግብ ያለ ድርጊት የለሊት ህልም ነው” የሚል አባባል አላቸው፡፡ በህይወታችን ላይ የምንኖርበትን አላማ እና ትልቁን ግብ ማስቀመጥ ይኖርብናል፡፡ ያለ ግብ የምንንቀሳቀስ ከሆነ እና የምንሄድነትን መንገድ ካላወቅን ማንኛውም መንገድ ይወስደናል ይባላል ይህም ጊዜን፣ ገንዘብን፣ ምቹ አጋጣሚዎችን ልናባክን አንችላለን፡፡
ወጤታማ ህይወት ለመምራት ግብባችንን በማዘጋጀት አላማ መር ህይወት መምራት አለብን፡፡

Пікірлер: 6

  • @kedir5245
    @kedir524526 күн бұрын

    great topic with wonderful speech !!

  • @BirukKelilew
    @BirukKelilew28 күн бұрын

    betam arief new Dr.adera,beketay sele(ANDE SEW PASSIONUN ,ENDET ENDEMIYAWEKE) betastemerene elalehu,amesegenalehu

  • @user-oy4nk1ek7v
    @user-oy4nk1ek7v28 күн бұрын

    ድንቅ ትምህርት የቂጣው ምሳሌ ...እምላክ ይርዳን ! , ተባረክ ዶ.ር ! አደራ.

  • @user-zg6bb1wl6f
    @user-zg6bb1wl6f26 күн бұрын

    Thank you so much Dr

  • @yonatangirma7219
    @yonatangirma721927 күн бұрын

    ሥልጠና አታዘጋጁም።

  • @SAK_Consultancy

    @SAK_Consultancy

    26 күн бұрын

    We are planning to start online call in September 2024.

Келесі