ያለ'ኔ ||አዲስ_ነሺዳ||የከውኑ_ሞገሥ_4||ምርኩዝ_22||MinberTV

Ойын-сауық

#ነሺዳ#ሚንበር_ቲቪ#Neshida# New_Neshida#Minber_TV
አዝማች
ልክ እንደ ጅረት ሳይታክት ሌት ተቀን የሚፈስ፣
አድማሱን ተሻግሮ በናፍቆት መዲና የሚደርስ፣
ይኸው ሰላምታዬ፣
ለውዱ ነቢዬ፣
አሰላም አለይከ
ሃቢብ ስጦታዬ፣
ሳይነግሩኝ የተዉት የለም ምን ቀርቶ ሃቢብ ካንቱማ፣
እኔው ነኝ የጎደለብኝ ውዴዋ አንቱን ሳልሰማ፣
መንገዱን ገር አድርጎልኝ ያሳየኝ ሁሉን አስፍቶ፣
ማን ሰጠኝ ሰይዲ ያላንቱ ወንድምን መውደድ አብዝቶ።
ስሜቴን ቅድሚያ ሰጥቼ አድሬ ፍፁም ላሳቤ፣
ስንቱን ካፋፍ ላይ ገፋሁት ሰፊውን መንገድ አጥብቤ፣
ማወቄ መስሎኝ ማሸነፍ ስፎክር ቆጨኝ መኖሬ፣
ከካዕባ የሚልቀውን ወንድሜን ቀልቡን ሰብሬ።
መንገድህ ባያሳምነኝ ባየሁት በኔ ዒልም አቅም፣
ጀርባህን ሰተኸኝ አትሂድ መጨከን ከቶ አያፀድቅም፣
ሃሳቤ ባይገጥም ካንተ ቢለያይ መልኩ ቢርቅም፣
ወንድምነቴ ይቀድማል ያለ'ኔ ጨርሶ አትደምቅም።
አዝማች
እንጉርገጉሮ
ሳናጣ መሄጃ መንገድ ሳያንሰን፣
እራቀ መድረሻው እንዳይሆን ቀርተን፣
ስንት ዘመን ሸኘን ቆመን ከጠባቡ፣
ተስኖን መላወስ አቅቶን መሳቡ።
ወይ አልተራመድን በጊዜ ነቅተን፣
ኡኹዋን የረሳን ኒዕማ ሆኖልን፣
ላመል በጠበበ በኩርማን ጉያችን፣
መች አስተቃቀፈን ኪታብ መያዛችን።
የበኒ ቁረይዛው የአሱር ሶላት፣
ሁሉም ቢከውነው በተረዳበት፣
መች በሽታ ሆኖ ኡኹዋ ፈረሰ፣
ማን ተመስግኖበት ማንስ ተወቀሰ?
ይህ ነው እስልምና ይህ ነው የእኛ ዲን፣
ወንድምን የሚያክም ቀልብን የሚያድን።
ያወቅኩት የገራው ለኔ ካራቀህ አንተን ከቅፅሩ፣
መምከን ነው ሂክማ ማጣቴ ካለአደብ ፊደል መቁጠሩ፣
ኢጅቲሃድ ያረከው ባይሰምር ላትሆን መቼም ባለዕዳ፣
ቁጭቱ በቁም ገደለኝ ለማይቀር ማግኘትህ ምንዳ።
ብገፋህ ሳላገናዝብ ዕይታ ንባቤ አንሶ፣
ምን ቢያምረኝ ውስጤ ቢጨክን ቂብላህን መቀየር ደርሶ፣
ተሳስሯል በዲን ልባችን ኡኹዋው መቼም ላይላላ፣
ድምቀት ነው ልዩነታችን ያቆመን በኢስላም ጥላ።
መቀበል ያቃተኝ ምነው ያቆምኩህ ደርሰህ ከበሬ፣
ያወቅኩት ላንተ እስኪገለጥ ኡዝር ያጣሁ ሰባ ቆጥሬ፣
የዘመን ሸክም ክምሩ በጀንበር ግዛት ባይለቅም፣
ከሥሩ ፀንተን እንገኝ ቅርንጫፍ ግንድ ሆኖ አያውቅም።
እንጉርጉሮ
ኪታቡ ሲሞጠል ከየምዕራፉ፣
ሲትሃፈዝ ቅርጧሱ ሳይቀር ሙኣሊፉ፣
ሲሸመደድ ሸርሁ ሳይዛነፍ ሃርፉ፣
ምነው በኡኹዋ በባቡ ማታልፉ፣
ስንት ዘመን ሸኘን ፈውሱን ስናርቀው፣
አብቃቅቶን ዟሂሩ ባጢኑን ሳናውቀው፣
የስንቱን ሩህ ቀማን ህመሙን ዘንግተን፣
በውሃ አስገድደን ተይሙምን ረስተን፣
በፈህም ነው እንጂ ቀሊሉ ሚሰፋ፣
በወንድም ነው እንጂ ተራራ ሚገፋ፣
አንሞላም ለብቻ ኡኹዋ ከጠፋ።
ምን ባይገጣጠም ያንተ ሃሳብ ከሃሳቤ፣
እኩል ባይመዘን ባልጠጋህ በንባቤ፣
ምናል ብታሳየኝ ምልከታህን በሂክማ፣
አመል ካልቸገረ መች ይጠባል ቤቱማ።
ስትከባበሩ ማየት እንጂ ሌላ አንሻም፣
ይህ ነው እስልምና ያላቹንን ቃል አንረሳም፣
መተባበር እንጂ ኃይል የሚያድስ ሚያበረታ፣
ወንድማማችነት የኛ ዓለም ነው ከፍታ!!!!

Пікірлер: 417

  • @mehdichala2074
    @mehdichala2074 Жыл бұрын

    መሀመድ ፈረጅ እራሱ አሁን ላይ ለእኛ ኢትዮጵያ ሙስሊሞች የተሰጠ ስጦታ ነው አላህ ይጠብቅህ

  • @abunilemedia9235
    @abunilemedia9235 Жыл бұрын

    ማሻ አላህ በጣም ደስ የሚል ነሽዳ ሸህ ገዛሊ ስለ ነሽዳ ምን ይላሉ አይን ጥሩ ነገር ማየት ትወዳለች አፍንጫም ጥሩ ሽታ ትወዳለች ጆሮም ጥዑም ዜማ ትወዳለች ይላሉ

  • @nurianuri5455
    @nurianuri5455 Жыл бұрын

    ያአላህ እንዴት ይነዝራል ማሻአላህ ግሩም መልክት !!!!!!

  • @dontjudgeme7968
    @dontjudgeme7968 Жыл бұрын

    Wow MashAllah betam des ylal yhaw selamtaye wdu Nebeye (S.A.W.)

  • @susutube360
    @susutube360 Жыл бұрын

    የግጥም መልእክት ረቂቅ ነው🎉🥰ማሜ እድሜና ጢና አብዝቶ ያድልልን😊

  • @nurbintebrahim1547
    @nurbintebrahim1547 Жыл бұрын

    ግጥም ማሜ አላህ ይጠብቅህ ቀለምህ ሁሌም ልብ ያቀልጣል💐💐💐

  • @fatiyanasir3956
    @fatiyanasir3956 Жыл бұрын

    ነሽዳዉ ልብ ይነካል ያስለቅሳል ያለንበትን ሁኔታ በደንብ ያስቀምጣል። ግን የሙዚቃ መሣሪያ ባይኖረወ የበለጠ በሙሉ ልብ ይደመጣል። ማሻ አላህ ምርጥ ድምፅ አላቸው የሙዚቃ መሣሪያ አያስፈልግም። በተረፈ ምርጥ ነው ። መሀመድ ፈረጅ ማሻ አላህ ያንተ ግጥም እንከን አይወጣዉም። ህጻናቱን በመጨመራችሁ በጣም ደስ ብሎኛል።

  • @funzone7275
    @funzone7275 Жыл бұрын

    በጣም የወደድኩት ስንኝ "ቅርንጫፍ ግንድ ሆኖ አያውቅም"😘

  • @ethiodire8953
    @ethiodire8953 Жыл бұрын

    ኢስላም የአባታችን አደም የእናታችን ሃዋ የተፈጥሮ እምነት ነው ነቢ ሙሀመድ የመጨረሻ ነብይ እና የዚህ ዘመን ትውልድ መልክተኛ ናቸው የመጨረሻውን ህግ ቁዱስ ቁረአንም ከአላህ ተወረደላቸው ፈጣሪያችን አላህ የማይቀየር ጥንታዊ የማይሞት የማያንቀላፋ ህያው ዘላለማዊ ሃያል ነው ክብር እና ምስጋን ይድረሰው

  • @mudinabdella2861

    @mudinabdella2861

    Жыл бұрын

    Asalamualikum..warh..wab, Mohmmed Faraj we love Minber Tv . But there is the comment also i like to mention. How woman's are not covered & Screaming & making big noise like big Music programs.

  • @NoMore0768
    @NoMore0768 Жыл бұрын

    ሱብሃን አላህ ድንቅ ነሺዳ ድንቅ መልክት ነውም በርቱ አልልም ምክሩ ለኛው ነውና ሚተርፈው ወንድማማቺነት ያረቢ አንተው አስተካክለው።

  • @Shaika-ft6rk
    @Shaika-ft6rk Жыл бұрын

    Masha Allah libe yinakale maliktuuu

  • @khadiatoudiarra6420
    @khadiatoudiarra6420Ай бұрын

    machalaho tabkalaho😍🤲🤝

  • @hamdiyahamdiyaa966
    @hamdiyahamdiyaa966 Жыл бұрын

    MASHALLAH ☝☝☝

  • @musilmaasharfuu1847
    @musilmaasharfuu1847 Жыл бұрын

    Mashaa Allah Mashaa Allah Mashaa Allah 💯💯💯💯💯💯💯💯💯💯💯💯💯💯💯👌👌👌👌💯💯💯💯💯

  • @amanyasin8651
    @amanyasin8651 Жыл бұрын

    ረሱል ሀቢቡና መሃባ የሚጨምር በጣም ምርጥ ነሽዳ ነው ሙስሊም ሙስሊማት ላይክ ግጩ አለሀምዱልላሂ❤❤❤

  • @everythingtube1915
    @everythingtube1915 Жыл бұрын

    Welahi mert neshida nw👍👍

  • @nejatahmed2904
    @nejatahmed2904 Жыл бұрын

    Wendmachen mamy allah kef yadergh

  • @nnur9988
    @nnur9988 Жыл бұрын

    የልብ አድርስኮ ነዉ ምርኩዝ ኘሮግራም። እዉነትም ምርኩዝ። ዘመን ተሻጋሪ እይታ በዚ ስራ ዉስጥ አስተዉያለሁ። እባካችሁ ሚንበሮች ከከፍታችሁ እንዳቶርዱ አደራ።👏👏👏👏👏👏

  • @kamilaymiftawa5546
    @kamilaymiftawa5546 Жыл бұрын

    ማሜ ምርጥ ጋዜጠኛ ምርጥ ገጣሚ አንደበተ ርቱ ብቻ ለኢስላም የምታደርገው ነገር ሁሉ ጀዛከላሁ ኸይር ከነመላው ቤተሰብህ ረቢ ይጠብቅህ

  • @mardiafa7926
    @mardiafa7926 Жыл бұрын

    Masha Allah baxam xiru new

  • @AliAminOfficial
    @AliAminOfficial Жыл бұрын

    ስሜቴን ቅድሚያ ሰጥቼ አድሬ ፍፁም ላሳቤ፣ ስንቱን ካፋፍ ላይ ገፋሁት ሰፊውን መንገድ አጥብቤ፣ ማወቄ መስሎኝ ማሸነፍ ስፎክር ቆጨኝ መኖሬ፣ ከካዕባ የሚልቀውን ወንድሜን ቀልቡን ሰብሬ።

  • @fatumaendris9159

    @fatumaendris9159

    Жыл бұрын

    Mashiala

  • @hawamohammed6419
    @hawamohammed6419 Жыл бұрын

    Mashaa Allh mashaa mashaa Taabaaraaka Allh ❤❤❤❤💯💯💯💯💯

  • @salahadinsultan4914
    @salahadinsultan4914 Жыл бұрын

    ማሜ ግጥሞችህ ልብ ያርዳሉ ቃላቶች ይታዙሀል አላህ ይጨምርልህ።

  • @user-ri2yk7zw4s
    @user-ri2yk7zw4s10 ай бұрын

    As wr wb rabin ol ta'e milka'inara isin ha ansu galatomaa

  • @user-ri2yk7zw4s
    @user-ri2yk7zw4s10 ай бұрын

    As wr wb mashalah mashalah mashalah mashalah mashalah ❤❤❤❤❤❤

  • @aliyimumme4630
    @aliyimumme4630 Жыл бұрын

    wow wow wow wow jazakallahu kheyran

  • @muhabahabib243
    @muhabahabib243 Жыл бұрын

    ማሻ አላህ ወንድሞቼ አሪፍ ምክር ነው

  • @sadiaabduseid8825
    @sadiaabduseid8825 Жыл бұрын

    ማሻአላህ አላህ ይጨምርላችሁ ለኛም አላህ ልቦና ይሰጠን

  • @jamalmala1317
    @jamalmala1317 Жыл бұрын

    ማሸአላህተባረክላህ።የኔጩጩወች።አናተ።ተተምጦደምቀ።አላህለቆምነገረያብቃችሆ የኡመትኢስላምልጆች።አላህይጠብቃችሆ አገራችአላህምያረገልን

  • @nefisaseid5982
    @nefisaseid5982 Жыл бұрын

    ሚንበሮች የኔ አንደኞች❤

  • @seidmussa4573
    @seidmussa4573 Жыл бұрын

    Mashallah mabrook . It was amazing 👏 😍 🙌

  • @Its_Me_Ebra
    @Its_Me_Ebra Жыл бұрын

    መሀመድ ፈረጅ በቃ ብዕሩ አንተው ፃፈው የምርኩዝ የጀርባ አጥንት ኢማን ትግል ፅናት ✌️✌️

  • @emanjimma730
    @emanjimma730 Жыл бұрын

    Masha Allah gurum nashida new Allah yaganagnen yegna wudu nabiy صلي الله عليه وسالم🥰❤👌

  • @anufriki5030
    @anufriki5030 Жыл бұрын

    ወንድም ሙሃመድ ፈረጅ አንተ ድንቅ የጥበብ ሰው አላህ ይጠብቅህ ትልቅ ሃብታችን ነህ ወላሂ

  • @nejunejuti7233

    @nejunejuti7233

    Жыл бұрын

    Mn muzika newa ?

  • @zebibaumerft

    @zebibaumerft

    10 ай бұрын

    Mohammed ferej is antiyouth as 1 muslim we have to fear allah using music instrument is heram therefore he has to protest such action for the people those take poim from him. Because

  • @yasinabdul3828
    @yasinabdul3828 Жыл бұрын

    Meshallah Allah mindachun yikfelachu

  • @hikmaareb4020
    @hikmaareb4020 Жыл бұрын

    መሀመድ ግጥሞችን እደሰማው ነው ያንተ መሆኑን የማውቀው በጣም ነው የምወድህ ኑርልን

  • @ahamidakmel9094
    @ahamidakmel9094 Жыл бұрын

    አላህዬ በዲንም በድንያም በዘር ከመከፋፈል አንተው ነጃ በለን ልክ እኮ ነው ያላቹት ኪታቡ ሲሞጠል ከየምዕራፍ ሲተሀፈዝ ቅርጧሱ ሳይቀር ሙአሊፉ ሲሸመደድ ሸርሁ ሳይዛለፍ ሀርፍ ምነው በኡኹዋ በባቡ ማታልፉ

  • @basamatbasamat6026
    @basamatbasamat6026 Жыл бұрын

    ሀቢቢ ሰለላዋለይ ወሰለም ማሻ አላህ አላህ ይጨምርላችሁ

  • @agf2247
    @agf2247 Жыл бұрын

    አላሁመ ሶሊ ወሰለም አላ ሀቢቡና ሙሀመድ በጣም ውብ ነው ተጠቃሚ ያርገን አሁንም መልክቱን መረዳቱ ላይ ልብ እንበል ማስተዋልን ማገናዘብን ይስጠን አሁንም ኮመንትች ዘፈን ነው ተው የምትሉ እህት ወንድሞች ዋናውን ግንዱን ትታችሁ በቅርጫፍ ነውና ቁምነገሩ ላይ እናተኩር መልክቱን ጀዛኩሙላህ ኸይረን ግጥሙን አቅራቢ ማሜ ያችን አላህ ሚዛን ሀሰናትህን ከፍ ያርግልህ ዱንያ ወል አኼራያረብ

  • @mariammariam3750
    @mariammariam3750 Жыл бұрын

    اللهم صلى 🍀 وسلم🌺 وبارك☘️ علي سيدنا💚 وحبيبنا💚 محمد عدد ما ذكره الذاكرون🌹 وغفل عن ذكره الغافلون🍀 عدد ما كان🌺 وعدد ما يكون 💚وعدد الحركات والسكون☘️ صلاة تنحل بها العقد🍀 وتنفرج بها الكرب🍀 وتقضى بها الحوائج☘️ وتنال بها الرغائب 🌙 صلى الله عليك يا خير الورى 🌺قد صار حبك في🌙 شراييني دما💚وعلى آله وصحبه الطيبين الطاهرين أجمعين🌙 يارب العالمين💚💚 اللهم أمين 🍀🌙☘️

  • @shmsbnetnuritube502
    @shmsbnetnuritube502 Жыл бұрын

    በርቱ ጥሩ መልእክት ነው

  • @temimasaed4718
    @temimasaed4718 Жыл бұрын

    ማሻ አላህ ደስ የሚል ልብ ያም ናከ፣አላህ አገራችን ሰላም፣ አድርልን🇰🇼☝🇪🇹

  • @fatumamohammed1689
    @fatumamohammed1689 Жыл бұрын

    ማሻአላህ ውድ የሚንበር ቲቪ አዘጋጆች እንዲሁም ሚንበሮች አላህ ይጨምርላችሁ

  • @Rabia-lm7dq
    @Rabia-lm7dq Жыл бұрын

    ምርጥ ነሺዳ ነው ማሜ ሁለየ ነሺዳወቺህ አንጀቴ ይባላሉ ይህን እስልምና ይህነው የኛ ዲን

  • @wusmanmohammed6847
    @wusmanmohammed6847 Жыл бұрын

    ማሻ አላህ ልዩ እኮ ናችሁ

  • @user-ke1ip8bc7q
    @user-ke1ip8bc7qАй бұрын

    Maashaa Allaah 🥀🥀🥀🥀🥀🥀🌟🌟🥀🌟

  • @mouloukomed6502
    @mouloukomed6502 Жыл бұрын

    Machallah machallah machallah Allah youbarak

  • @intalaaarsiishkiraa9784
    @intalaaarsiishkiraa9784 Жыл бұрын

    Sallallahu Aleyhii wasallam ❤️ Mashaa Allah TabarakAllah ❤️

  • @rashadloba8383
    @rashadloba8383 Жыл бұрын

    መሃመድ ፈረጃ ከምንም በላይ እይታክ በጣም ነው ምወድል ሁልግዜም ግዜውን ጠብቀ ምጣመታቸው አሳቡች ደስ ይላሉ አላሃ ይጠብቅ እውነትም አተ የአገር አብት ነህ

  • @kalidawel6266
    @kalidawel6266 Жыл бұрын

    ማሻ አላህ ምርጥ ነሺዳ።ምርጥ ስንኞች፥ ትልቅ መልዕክት ያለው ግጥም ከቆንጆ አቀራረብ ጋር ።አላህ እናንተን ይጠብቅልን ።

  • @user-xf5ct5cg3c

    @user-xf5ct5cg3c

    Жыл бұрын

    ኧረሚንበሮች አላህን ፍሩ ሴትእናወንድ አንድላይ መቀመጣቸው ሳያንስ ነሽዳው ግጥሙአሪፍ ክላሲካሉ ምንያደርጋ እያወቅን ባናጠፍ ጥሩነው ።ብዙሰውች እነበድሩሁሴንአሉ ችግርባይኖረውነው ይላሉ እንዳለው ያውቃሉግን ምንምአላሉም ለምን? ቁርአን ላይየለም ሀድስምላይየለም አላህንልንፈራይገባል

  • @faezabekri7999
    @faezabekri7999 Жыл бұрын

    Masha Allah

  • @teyibapellereau477
    @teyibapellereau477 Жыл бұрын

    Yarebi yallah 😭😭😭😭😭🙏🙏🙏❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️

  • @emuzuzutube
    @emuzuzutube Жыл бұрын

    ማሻላህ ነሽዳቹ ልቤ ይነካል ፊዳካ አብ ዋኡመ የረሱለአለህ ሰለአለሁአለህወሰላም

  • @rabitube7432
    @rabitube7432 Жыл бұрын

    ደስ የሚል ማሻ አላህየነሽዳ ጣዕም ያለው

  • @mariamali6961
    @mariamali6961 Жыл бұрын

    🥰🥰🥰 waaaaw is a beautiful nashida Mohamed Ahmed and all brothers Macha'Allah

  • @shemsubaissa8061
    @shemsubaissa8061 Жыл бұрын

    Masha Allah! Wisdom!

  • @abdulhamidmohammed1857
    @abdulhamidmohammed1857 Жыл бұрын

    Wow Masha allah das sil wow 1gn

  • @BrightIT14
    @BrightIT14 Жыл бұрын

    ማሻዓሏህ ወላሂ ውስጥን የሚነዝር ነሺዳ

  • @zenabaali536
    @zenabaali536 Жыл бұрын

    Masha Allah ❤❤❤❤

  • @Nasir-rd1ky
    @Nasir-rd1ky Жыл бұрын

    መሸአለህ አለህ ይጠብቃቹሁ

  • @monahamida7201
    @monahamida72013 ай бұрын

    Mashalaha Mashalaha ❤❤

  • @nursuleman2978
    @nursuleman2978 Жыл бұрын

    Mashallah Mashallah

  • @madinaaahemad6954
    @madinaaahemad6954 Жыл бұрын

    Masha aallahaa masha aallahaa masha aallahaa masha aallahaa masha aallahaa masha aallahaa masha aallahaa masha aallahaa ❤❤❤❤💔💔🙏

  • @munaali2129
    @munaali2129 Жыл бұрын

    MashaAllah TabrkAllah 🎉🎉

  • @jameelajemila5472
    @jameelajemila5472 Жыл бұрын

    ማሻአላህ ማሻአላህ ማሜ ብዕርህ አይንጠፍ ምርኩዝ ላይ የሚቀርቡ ነሺዳዎች ታሪክ ማይረሳቸው ምርጥ ግጥም በምርጥ ቅንብር በምርጥ መድረክ

  • @youssoufaissa508
    @youssoufaissa508 Жыл бұрын

    Fantastic qu'Allah vous récompense ❤️❤️

  • @sofiamahmoud7088
    @sofiamahmoud7088 Жыл бұрын

    No body perfect except Allah.....

  • @sadnursidsid9445
    @sadnursidsid9445 Жыл бұрын

    ዉብ ነሺዳ ዝም ብሎ የሚንቆረቆር ማሻአሏህ

  • @zubydaethiopia4204
    @zubydaethiopia4204 Жыл бұрын

    ሰለላ አለይሂ ወሰለም❤

  • @feysellmohammed6581
    @feysellmohammed6581 Жыл бұрын

    ደስ ነሚል ትላንታችንና ዛሬያችንን በደምብ የሚገልፅ ነሺዳ

  • @mekonnenteferi5198

    @mekonnenteferi5198

    Жыл бұрын

    ሰላም ለእናንተ ይሁን !! እንዴት ግሩም የሆነ መዝሙር ነው:: እያለቀስኩ ነው የሰማሁት: ቃላት የለኝም.. ..ድምቀት ነው ልዩነታችን...

  • @mousman22
    @mousman22 Жыл бұрын

    ወንድምነቴ ይቀድማል ያለኔ ጨርሶ አትደምቅም"""👌

  • @sabontuujimma3911
    @sabontuujimma3911 Жыл бұрын

    Mashaa Allah mashaa Allah mashaa Allah mashaa Allah mashaa Allah mashaa Allah mashaa Allah mashaa Allah mashaa Allah mashaa Allah

  • @mom946
    @mom946 Жыл бұрын

    ልክ እንደ ጅረት ሳይታክት ልክ ከ የሚፈስ አድማሱን ተሻግሮ በላኩት መድና የሚድርስ ይሄው ስጦታየ ውዱ ነብየ አ ሰላም አለይከ ሃቢቢ ስጦታየ🙏🙏🙏 ማሻላ ሁሌም ተደማጭ

  • @sman1324
    @sman1324 Жыл бұрын

    ነሽዳዎቻችን የሚያስተላልፉት መልእክት በጣም ጥሩ ሆኖ ሳለ ግን ለምንድን ነው የሙዚቃ መሳሪያ የምታስገቡበት ? አሏህን ልንፈራ ይገባል

  • @agf2247

    @agf2247

    Жыл бұрын

    በፁሁፍ ቢያቀርቡት ይሻል ነበር ወይ?

  • @user-ou1xv6ei6s

    @user-ou1xv6ei6s

    Жыл бұрын

    ሣሕ

  • @hussenyimer3756

    @hussenyimer3756

    Жыл бұрын

    የነሺዳውን ግሩም መልእክት ከልብ እንድናደምጠው ያደረገን ሙዚቃው ሥላለበት ነው ።እንደኔ እንደኔ የመሳሪያው ድምፅ ሊያነጋግረን አይችልም ሙንሺዶቹ ያወጡትን ድምፅ መሳሪያውም እንደዛ ነው ሜሎዲውን የሚለው እና ሁለቱም መልካም ነገሮች ማሥነገሪያ ነውና የሚል ሐሳቤን አሥቀመጥኩ ካጠፋሁ አፉ በለኝ

  • @user-ty5zc4fd3u

    @user-ty5zc4fd3u

    Жыл бұрын

    @@hussenyimer3756 ትክክል

  • @ferdwsmuktar1689

    @ferdwsmuktar1689

    Жыл бұрын

    Hak nw wellahi

  • @jemuyeamumisit759
    @jemuyeamumisit759 Жыл бұрын

    Wallahi Alaqesiku ihe new Eslimina

  • @emann7734
    @emann77342 ай бұрын

    اللهم صل وسلم وبارك على نبينا محمد

  • @selmanareba8874
    @selmanareba8874 Жыл бұрын

    Wellahi betam masha allaha alu enji eneza ya huwahuwa huwa dedebochu keep it enanta wudoch Allah balachu lay yicemerelachu

  • @rahmetmohammed8365
    @rahmetmohammed8365 Жыл бұрын

    ❤❤❤❤አሪፍ ስራ ነው

  • @user-ne5xw5mi4h
    @user-ne5xw5mi4h Жыл бұрын

    አላሁመ ሰልይ ወሰለም አላነብይናሙሀመድ

  • @ahamidakmel9094
    @ahamidakmel9094 Жыл бұрын

    ስንት ዘመን ሸኘንፈውሱን ስናርቀው አብቃቅቶን ዟሂሩ ባጢኑን ሳናውቀው የስንቱን ቀማን ህመሙን ዘንግተን 😭 በውሃ አስገድደን ተይሙምን ረስተን በፈህም ነው እንጂ ቀሊሉ ሚሰፋ በወንድም ነው እንጂ ተራራም ሚገፋ💪💪 አንምላም ለብቻ ከኸቁ ከጠፋ

  • @user-xu8gu1cj7k
    @user-xu8gu1cj7k Жыл бұрын

    መሀመድ አህመድ ተሾመ አቤት ድምፅ ማሻ አላህ

  • @elhammohammed4831
    @elhammohammed4831 Жыл бұрын

    ማሻአላህ ከዚህ ውጪ ቃል የለኝም

  • @user-xq6tc9nd7e
    @user-xq6tc9nd7e Жыл бұрын

    ይህ ነው እስልምና ማሻአላህ አላህ ይጨምርላችሁ

  • @hussenyimer3756
    @hussenyimer3756 Жыл бұрын

    ሚንበር የሚለቃቸውን ነሺዳዎች በጉጉት ከሚጠብቁት አንዱ እኔነኝ ።ለምን ቢባል የሚያነሡዋቸው ነጥቦች ተነበው ለመያዝ የሚከብዱንን በዜማ እንዲገባን አድርገው መሴጅ ያደርሱናል ።ለዚህም ነው ህፃናት ባንድ ግዜ ሠምተው ቃል በቃል የሚሉት እናማሽአላህ ሸጋ ነው ማለፊያ ነው

  • @dhbdnxbxn5809
    @dhbdnxbxn5809 Жыл бұрын

    💚👏ድንቅ💕 ነሺዳ 👌💗💖

  • @munaademmunaadem703
    @munaademmunaadem703 Жыл бұрын

    masha Allah

  • @xayyibajimma3188
    @xayyibajimma3188 Жыл бұрын

    🌷فداك ابي وامي يا رسول الله 🌷 صلى الله عليه وسلم ❤❤❤

  • @xayyibajimma3188
    @xayyibajimma3188 Жыл бұрын

    ماشاء الله تبارك الله يفيظاكم الله ❤❤❤❤❤ ምርጥ ስራ ነው መሜ ወንድሜ ማሻ አላህ 🙏❤

  • @semuetube5094
    @semuetube5094 Жыл бұрын

    ኧረ ምርጉዝን ሁሉንም ልቀቁልን በአላህ አሪፍ ፕሮግራም እንደሆነ ስምቻለሁ 🥺💚 ነሽዳው ማሻ አላህ በርቱ አሪፍ ጥምረት 👑

  • @ethiodire8953
    @ethiodire8953 Жыл бұрын

    ماشاءالله mashallah ☪️✌️🕌🕌🕌🕌🕌🕌

  • @newalfaruk4571
    @newalfaruk4571 Жыл бұрын

    ብርቱ አሪፍ ሰራ ነው💗💗💗

  • @behappy8341
    @behappy8341 Жыл бұрын

    Betam stebkew nbr wlhi..

  • @mukeremshemsu9505
    @mukeremshemsu9505 Жыл бұрын

    Mashallah በጣም ድንቅ ነሺዳ ነው። ከድምፅ • ከመልዕክት • ከዜማ! ዋው ወላሒ። በተለይ ልጆቹ

  • @neser9447
    @neser9447 Жыл бұрын

    በጣም ያምራል ድንቅ ስራ

  • @user-cf2zl5wy9c
    @user-cf2zl5wy9cАй бұрын

    ማሻአላ በጣምደሰይላል❤❤❤❤❤❤❤

  • @khayriasoror4787
    @khayriasoror4787 Жыл бұрын

    አደኛነሻዳ ትምረትአዘለን ከድቤነጻ ማሻአላህ

  • @awztube.100kviews2
    @awztube.100kviews2 Жыл бұрын

    Alahamdulilah I am proud for being muslim and I love you all my sister , brother accross the world.

  • @aishahamza4111

    @aishahamza4111

    Жыл бұрын

    Aysha from Nigeria

  • @jojobeder7598
    @jojobeder7598 Жыл бұрын

    ماشاء الله الكاتب محمد فرج انت تختلف ربنا يحفظك اخي الغالى. منشدين، والحان، والرسالة النشيدة كله جميل. مخرجين منبر الله يجملكم في الدنيا والآخرة!❤

  • @momin8886
    @momin8886 Жыл бұрын

    ሠለላሁ አለይሂ ወሰለም

  • @fatimanega3683
    @fatimanega3683 Жыл бұрын

    harife neshida dess yemile

Келесі