የንጉሥ ሰለሞን ፍርድ || ድንቅ መንፈሳዊ ጥበብ

የንጉስ የሰሎሞን ፍርድ !
በአንድ ወቅት ሦስት ነጋዴዎች ድንገት አንድ ቀን በንጉሥ ሰሎሞን የዘውድ ችሎት ተገኙ፡፡ ሦስቱም ለብዙ ዘመን አብረው ለመነገድ ተማምለው፣ ግመል ጭነው፣ ገንዘብ ቋጥረው፣ ስንቅ አንጠልጥለው፣ ሀገር ጥለው የሄዱ ናቸው፡፡ ‹ንጉሥ ሆይ› አለ አንዱ በዙፋኑ ፊት እጅ ነሥቶ፡፡ ‹እኛ አብረን ለመነገድ ተስማምተን መንገድ የጀመርን ጓደኛሞች ነን› አለ፡፡
ሁለተኛውም ነጋዴ ተቀብሎ ‹ቃላችንንም አክብረን ለንግድ ሩቅ ሀገር ስንጓዝ ድንገት የሰንበት በዓል ደረሰብን› ሲል ቀጠለ፡፡ ሦስተኛውም ነጋዴ ‹ሰንበትን አክብረን ለመዋል ስለፈለግንም ድንኳን ከተከልንበት ቦታ ራቅ አድርገን ጉድጓድ ቆፍረን ገንዘባችንን በከረጢት ቀበርነው፡፡ ከመካከላችን ማናችንም ገንዘቡን ተደብቀን ላንወስድ መሐላ ፈጽመን ነበር፡፡ በማግሥቱ ግን ወደ ጉደጓዱ ሄደን ስንቆፍረው ገንዘባችንን አጣነው› አለና አስረዳ፡፡
የመጀመሪያው ነጋዴም አንገቱን ከነቀነቀ በኋላ ‹ንጉሥ ሆይ ጉድጓዱን ስንቆፍርም ሆነ ገንዘቡን ስንደብቅ ሌላ ሰው ያየን የለም፡፡ ከሰረቅነው እኛው ነን፡፡ ነገር ግን ማናችን እንደሰረቅን ልንተማመን አልቻልንም› አለ፡፡ ንጉሥ ሰሎሞን በልቡ ‹መስረቅ የቻለ ሰው መዋሸትና መሐላን ማፍረስ አያቅተውም› ብሎ አሰበና ነገሩን ቀለል አድርጎ ‹ነገ ተመልሳችሁ ስትመጡ ማን እንደሰቀረው እነግራችኋለሁ› ሲል አሰናበታቸው፡፡
በማግሥቱ ሦስቱ ጓደኛሞች መጡ፡፡ ችሎቱም ተጀመረ፡፡ ንጉሥ ሰሎሞን ‹የእናንተን ጉዳይ ከመመልከቴ በፊት ሦስታችሁም ጠቢባን መሆናችሁን ማወቅ እፈልጋለሁ፡፡ በመሆኑም በሚከተለው ታሪክ ላይ ያላችሁን አስተያየት እንድትሰጡ እፈልጋለሁ፡፡
ነገሩ እንዲህ ነው ፦ አንዲት ሴትና አንድ ወንድ ከልጅነታቸው ጀምሮ አብረው እየተማሩና እየተጫወቱ አደጉ፡፡ ወደፊት ትልቅ ሰው ሲሆኑ ተጋብተው አብረው ለመኖር ቃል ተግባቡ.............።
እያሉ ይቀጥላሉ ......... ሙሉውን በቪዲዮው ስሙት።
‹አንድ ታሪክ ልንገራችሁ› አላቸው ጠቢቡ ሰሎሞን፡፡ እንዲቀመጡ ተፈቀደላቸው፡፡ ሁሉም ሌባውን ያወቀበት መንገድ አስደንቋቸዋልና ምንጣፍ ላይ ቁጭ አሉ፡፡ አንድ ቀን አንድ ልጅ እኔ ዘንድ ለፍርድ ቀረበ......፡፡
እንዲህ እያሉ ለፍርዳቸው አንድ ወግ አጫወቷቸው .......... ሙሉውን ስሙት ።
ሰውዬውም በነገሩ ተገርሞ ገንዘቡን መለሰ ይለናል ሚድራሽ የተባለው የአይሁድ የትውፊት መጽሐፍ፡፡
" ኵሉ ጽድቅ ወኵሉ ጥበብ እምኀበ
እግዚአብሔር ውእቱ ። "
#ንጉሥሰለሞን #መንፈሳዊጥበብ
Subscribe 👇 Our KZread Channel
ዩቲዩብ= / @tobiyamedia
እምነት፣ እውነት፣ እውቀት፣ ጥበብ፣ ፍቅር ሰውን ነጻ ያወጣሉ !
#ጦቢያሚዲያ #TobiyaMedia
© ጦቢያ ሚዲያ

Пікірлер: 5

  • @tigistlegesse8443
    @tigistlegesse84432 жыл бұрын

    በጣም ደስ ይላል

  • @woynishetyemr5523
    @woynishetyemr5523 Жыл бұрын

    በጣም የዉነት ቃል ጠቢቡ ሰለሞን

  • @user-gi5wh1jb1z
    @user-gi5wh1jb1z3 ай бұрын

    ድንቅ ትምህርት በተለይ የመጨረሻው ልጆችን እንዴት ማሳደግ እንዳለብን የሚያስተምር እናመሰግናለን 🙏🙏🙏

  • @MelkamuLawOffice
    @MelkamuLawOffice2 ай бұрын

    waw

  • @user-ng6tu5pi8u
    @user-ng6tu5pi8u9 ай бұрын

    ❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤😢😢😢

Келесі