የማቴዎስ ወንጌል ትምህርት 4 | ልጄን ከግብፅ ጠራሁት- በማሙሻ ፈንታ Matthew Teaching 4- I called my son...By Mamusha Fenta

Ойын-сауық

ይህ ትምህርት በኢትዮጵያ የሕይወት ብርሃን ቤተ ክርስቲያን፣ በአዲስ ክርስቲያን ላይፍ አሴምብሊይ አጥቢያ ዘወትር አርብ በማሙሻ ፈንታ እየተዘጋጀ የሚቀርብ ነው።
ትምህርቱን በቀጥታ ስርጭት መከታተል ለምትፈልጉ
ዓርብ ምሽት 11:30 - 1:30
Yoututube - Equip Media / @equipmedia2577
Facebook - Equip Media Mamusha Fenta
/ 312726798871156
አድራሻችን፡ ካዛንቺስ ከመለስ ዜናዊ ፋውንዴሽን ባሻገር 200 ሜትር ገባ ብሎ
ጉግል ማፕስ - google maps address
maps.app.goo.gl/q3YEWmN37C8ec...

Пікірлер: 74

  • @equipmedia2577
    @equipmedia2577 Жыл бұрын

    #እነሆ_ንጉሥሽ #የማቴዎስ_ወንጌል_ትምህርት #ልጄን_ከግብጽ_ጠራሁት 📖 ማቴ 2 : 13-15 (እስከ ቁ 23 የልጅነቱ ማጠቃለያ) ✔️ በዚህ ክፍል ስለ ኢየሱስ የሕፃንነቱ ወራት 3 የተመረጡ ማጠቃለያዎች አሉ። 1) ከቁ. 13-15 - ወደ ግብፅ የተደረገው ሽሽት 2) ከቁ.16-18 - የሕፃናቱ ጭፍጨፋ 3) ከቁ 19-23 - ወደ ናዝሬት መመለሱ ✔️ ልናልፋቸው የማንችላቸው ሶስት ምልከታዎች 1) የጻድቁ ዮሴፍ እምነትና መታዘዝ - ዮሴፍ እግዚአብሔር ይገለጥለታል፤ ይታዘዛል። ያለምንም ነገር እንዲሁ እግዚአብሔር ለሚናገረው ነገር ሁሉ ምላሽ ይሰጣል። - መታዙና እምነቱ ወንጌልን አመላካች ነው። ያምናል፤ ይታዘዛል። - አንዳንድ ሰዎች እግዚአብሔር እንዲናገራቸው ይፈልጋሉ፤ እቅዳቸውን ግን መቀየር አይፈልጉም። - እግዚአብሔር ሲናገር የሚሆነውን ስለሚያውቅ ነው። - የእኛ ዋስትና የህይወት መክበድ ወይም መቅለል አይደለም፤ እግዚአብሔር ባለን ቦታ መሆን እንጂ። - ዋስትናና ጥበቃ የሚገኘው በእግዚአብሔር ፈቃድ ውስጥ መሆን ነው። - በህይወት መክበድና መቅለል አትመሩ፤ በእግዚአብሔር ፈቃድ እንጂ። 2) የእግዚአብሔር ሀያልነት መንግስቱን በማስቀጠል - የእግዚአብሔር መንግሥት ምስኪን መሳይ ናት፤ ብትገፋም አትጠፋም። - የእግዚአብሔር መንግስት መገለጫ ኢየሱስ መጣ፤ ኢየሱስ ሲወለድ አለም ጸጥ አላለም፤ ነውጥ ነበረ። - የእግዚአብሔር መንግስት ልትገፋ ትችላለች እንጂ ማንም ሊያስቆማት አይችልም፤ አትጠፋም፤ ታድጋለች። - የማይናወጥ፣ አስተማማኝ ነገር በዚህ ምድር የለም። የማይናጠው የእግዚአብሔር መንግስት ብቻ ነው። 3) የእግዚአብሔር ሉአላዊነት /ገዢነት/ - በህይወት ደስ የሚያሰኝ ነገር ይሆናል፤ ደስ የማያሰኝም ነገር ይሆናል (በወደቀ አለም ውስጥ እስከኖርን ድረስ)። - የወደድናቸው ነገሮች ይኖራሉ፤ ያልወደድናቸውም ነገሮች ይኖራሉ። ደግ ደጉ ላይ እግዚአብሔር አለ፤ ክፉው ክፉው ላይ እግዚአብሔር የለም ግን አይባልም። - እግዚአብሔር ደግ የምንለው ነገር ብቻ ተቆጣጣሪ አይደለም። የአለማት ተቆጣጣሪ ጌታ እንዴት ክፉ የምንለውን ነገር መቆጣጠር ያቅተዋል? እግዚአብሔር ከክፉው ያድናል፤ ያተርፋል። - ደስ የሚያሰኙን፣ የሚያስከፉን፣ ማብራሪያ የማናገኝላቸው ነገሮች በግራና በቀኝ ሲሆኑ እግዚአብሔር ተቆጣጣሪ ነው። - እግዚአብሔር በህይወታችን ያለውን ይፈጽማል። - እግዚአብሔር እኛ ሳስቀመጥንለት ሳጥን ውስጥ ብቻ ገብቶ የሚሰራ አምላክ አይደለም። - ከእግዚአብሔር ቁጥጥር ውጪ የሚሆን ነገር የለም፤ ሉአላዊ ነው እሱ። - በህይወታችን ላልተብራራልንም ነገር ተቆጣጣሪው አምላክ አይሳሳትም። - ክፉ በሚመስሉንም፤ ደግ በሚመስሉንም ነገሮች አልፎ እግዚአብሔር ያለው ይሆናል፣ ፈቃዱን ይፈጽማል። - እግዚአብሔር ፍትህ የሚያጓድሉትን፣ ሀይል አለን የሚሉትን ይቀጣቸዋል፣ ዳኝነት ይሰጣል። - ጌታን ለሚወዱ በህይወታቸው ደግ ደግ ብቻ ነው የሚሆነው ያለው ማነው? የማይመች ነገር አለ። ነገር ግን እግዚአብሔር ደስ የሚለውንም የማይለውንም ነገር ወስዶ ሀሳቡን ይፈጽማል። 📖 ሮሜ 8: 28 - ሁሉን ወስዶ ለመልካም ያደርገዋል። - እኛ የምንተማመነው በመንገዱ ላይ ሳይሆን የህይወታችን መሪና ሹፌር እርሱ ሁሉን ተቆጣጣሪ አምላክ ሁሉን አሳልፎ በጎ ነገር ላይ ስለሚያደርሰን ነው። - በህይወታችን ውስጥ የሚያልፉት ነገሮች ሁሉ ከቁጥጥሩ ውጪ ሊሆኑ አይችሉም። 📖 ሆሴ 11:1-2 (ከላይ የሆነው ሁሉ በዚህ ክፍል እንደተጻፈው የተባለው ይፈጸም ዘንድ ነው) - ወኪላችን ነው ኢየሱስ፤ አሸንፎ የወጣ፣ ሁሉን ስለሕዝቡ ለመፈጸም የመጣ አዳኝ፣ ሁለተኛው አዳም፣ በነገር ሁሉ እኛን ሆኖ ያሸነፈልን፣ ሊቀ ካህናችን ነው ኢየሱስ። - ወኪል እንደሌለን፤ አዳኝ እንደሌለን ዝም ብለን በኃጢአት እየተቀጠቀጥን መኖር የለብንም፤ ሊያድነን መጥቷል እርሱን እንመንና እንያዝ።

  • @desalegnworku2048

    @desalegnworku2048

    Жыл бұрын

    8

  • @Jesusislove-gf3ox6wo8m

    @Jesusislove-gf3ox6wo8m

    Жыл бұрын

    thank you D.R ❤

  • @biruktawitalemayehu2912

    @biruktawitalemayehu2912

    Жыл бұрын

    Yetebarekachu nachu

  • @zinashmamo9676
    @zinashmamo9676 Жыл бұрын

    ምናለ ሁሉም ሰው ጥርግ ብሎ ይሄንን ቢሰማ ምነው ጴንጤ እዳለ ቢስማ ምነው ይሄ እድል ቢድርስው እኔ እድለኛ ነኝ ከዚህ ገበታ መብላቴ ዶር ጌታ ይባርክህ

  • @user-zq4jl1gb1e

    @user-zq4jl1gb1e

    Жыл бұрын

    ይሄው እኔም ሰማው እድለኛ ነኝ

  • @frehiwotkelelaw5401
    @frehiwotkelelaw5401 Жыл бұрын

    የእግዚአብሔር ፀጋ በኔ ዘመን በምድር ላይ በእናንተ ላይ ስለተገለጠ አምላኬን አመስግናለሁ።

  • @genetmoges3206
    @genetmoges3206 Жыл бұрын

    የዘመኑ ቅሬታ ዶ/ር ማሙሻ ጌታ ይባርክህ

  • @salameskyes7240
    @salameskyes7240 Жыл бұрын

    አሜንንንንን መቶ ግዜ ቢደገም የማይጠገቡ ምግብ የቃሉ ባለቤት ጌታ ይከበር🙏

  • @gechya2490
    @gechya2490 Жыл бұрын

    እግዚአብሔር እናንተን ለዚህ ትውልድ ስለሰጠን ስሙ ይባረክ!

  • @Nuhamin.953
    @Nuhamin.953 Жыл бұрын

    ፀጋና ህይወት ይብዛልህ ማሙሻ 😍🙏

  • @tensumamush9918
    @tensumamush9918 Жыл бұрын

    Amennnnnn geta,yibarek silezih agelglot egziyabherin ameseginewalehu aba keff bel🙏🙏🙏 dr mamusha,tebarek

  • @eliasgelan5735
    @eliasgelan5735 Жыл бұрын

    እናንተ በብዙ ስማችን በጠፋበት በዚህ ወቅት ምሳሌ ስለዎናቹ ያለምንም መሰልቸት ደግሞ እውነተኛውን ወንጌል እያስተማራቹን ስለሆነም እግዚአብሔር አምላክ አሁንም ይባርካቹ። በምሳሌም ያቆያቹ። #Equip-media dr mamusha dr abrham በተለያየ መንገድ የምታገለግሉ 🙏❤

  • @biretube1046
    @biretube1046 Жыл бұрын

    Doctor Mamusha, thank you so much and God bless you!! I am alone in the USA, your Mathew teaching is for me from God. I am always waiting this day eagerly. For your surprise I am listening it again and again.

  • @ayantutesfaye595
    @ayantutesfaye59511 ай бұрын

    አሜን የምልህ ነገር የለኘም ጌታ እየሱስ ከሰማይ ይባርክ።

  • @habatamhabatam8769
    @habatamhabatam8769 Жыл бұрын

    ዼንጤ እንዳ እንዲህ የሚል ክፉ ነገር ሲነገር በመልካም ከሚታወሱኝ አብያተክርስቲያናት የመጀመሪያዋ ይች ቤተክርስቲያን ናት ።

  • @user-nx2lo8fy8v
    @user-nx2lo8fy8vАй бұрын

    ዶ/ር ተባረክ

  • @zeritumengistuzd8703
    @zeritumengistuzd8703 Жыл бұрын

    አግዚአብሔር ይባረክ አግዚአብሔር አድሜ ይጨምርል እንዳንተን አይነቱ ይብዛልን 🙏🙏🙏

  • @ruthkebede755
    @ruthkebede755 Жыл бұрын

    ወይኔ ስሰማው ነፍስም አይቀርልኝ ምን እላለሁ ከክፉ ሁሉ እግዚአብሔር ይጠብቅህ

  • @rodasgetachew9347
    @rodasgetachew9347 Жыл бұрын

    አሜን እውነት ነው ብዙ ማብራራት የማንችላቸው ነገሮች ቢኖሩም ሁሉ ባይገባንም...የነገሮች መክበድም መቅለለም ሳይሆን ትልቁ ዋስትናችን በእግዚአብሔር ፈቃድና ሃሳብ ውስጥ መሆናችን ነው ፈቃዱ ደግ ደጉ ውስጥ ብቻ አይደለም ባይመስለንም ቢያመንም መልካም በማይመስለንም ነገር ውስጥ የእግዚአብሔር ፈቃድ አለበት....(እንደ ጻድቁ ዮሴፍ የእግዚአብሔርን ፈቃድ አምነን ሰምተን መታዘዝ ይሁንልን 🙏 ... የሄሮድስ ጭካኔ ኢየሱስን አላገኘውም ያለ እግዚአብሔር ፈቃድ ያለ እገዚአብሔር ጊዜ አንዳች አልሆነም እንደተጻፈው ሆነ እንጂ ...!! በወደቀ ዓለም ስንኖር ደስ የሚሉም ደስ የማይሉም ነገሮች ቢኖሩ የማይናወጥ መንግስት ስለምንቀበል ሊቀካህናችን የቀደመልን ያሸነፈልን ስላለ በእርሱ እርፍ ብለናል !! ያሳረፈን በሚናወጥ ዓለም እንዳንናወጥ ሁሉን የተቆጣጠረ ሉዐላዊ አምላክ ስሙ ለዘላለም የተመሰገነ ይሁን❤️ !! በጣም ልባችን አየተነካ ነው መልክቱን የምንሰማው ለመኖርም ለመታዘዝም እንዲያስጨክነን በመማጸን ...ጌታ ኢየሱስ አንተንና የአንተ የሆነውን ሁሉ ይባርክ ይጠብቅ ብዙ ጸጋ ይብዛልህ በጣም እንወድሃለን ወንድማችን ዶ/ር ማሙሻ !! አብረውህ የሚያገለግሉትን ሁሉ ጌታ ይባርክ !!የተወደዳችሁ🙏❤️

  • @tarikuademise7689
    @tarikuademise7689 Жыл бұрын

    ጌታ አብዝቶ ይባርክህ ፀጋውን ያብዛልክ

  • @biruktawitalemayehu2912
    @biruktawitalemayehu2912 Жыл бұрын

    ድንቅ ነው በርቱ እንበርታ

  • @desta5885
    @desta5885 Жыл бұрын

    እግዚአብሔር ይባርክህ ተባረክ። ሁላችሁም ተባረኩ።

  • @selamtewolde8044
    @selamtewolde8044 Жыл бұрын

    My God bless you more and more 🙏. Ke Geta honelin be felegnew gize seat mobilachin keften mesimat sile honelin. Kibr hulu le geta yhun. Dr. Mamush Briiiikkkkk belilin.

  • @user-vz3fh5xq9v
    @user-vz3fh5xq9v7 ай бұрын

    ጌታ ኢየሱስ ይባርክ🙏🙏🙏

  • @menahussen9333
    @menahussen9333 Жыл бұрын

    በትክክል ካዘንኩ አዛንኩ ነው እግዚአብሔር ፊት እውነተኛ እንሁን። ማሙሻ እግዚአብሔር ይባርክህ

  • @nitreworkmulat9461
    @nitreworkmulat94615 ай бұрын

    ዘርህ ይባረክ ወንድሜ

  • @Nunu-hq5vf
    @Nunu-hq5vf Жыл бұрын

    ጌታ ይመስገን በብዙ ተባረክ

  • @Rosei870
    @Rosei870 Жыл бұрын

    እግዚአብሔር ይባርካቹ

  • @trhaskafel6109
    @trhaskafel6109 Жыл бұрын

    Amenn le twuld neh ena haylh huluye end Nsr ....... Esayas 40. 30..31

  • @fifififi1119
    @fifififi1119 Жыл бұрын

    ውድ ወንድሜ ዘመንህን ሁሉ እንደተቀጣጠልክ እንደነደድክ በፍቅሩ ትኖር ዘንድ የጌታ ምሕረት እና ቸርነት ይደግፍህ። ሁሌም 'አሁን' ይሁንልህ።' ነበር' እና 'ግን' ሳያገኝህ ዘመንህ በእርሱ ይጠቅለል። በጣም እወድሃለሁ አንተ የጌታ ባሪያ

  • @jesuschrist15111
    @jesuschrist15111 Жыл бұрын

    ✞ክብር ለእግዚአብሔር አብ ክብር ለእግዚአብሔር ወልድ ክብር ለእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ አንድ አምላክ ይሁን አሜን።✟❤ “ሁሉም ከእርሱ፣ በእርሱ፣ ለእርሱ ነውና፤ ለእርሱ ለዘላለም ክብር ይሁን፤ አሜን።” - ሮሜ 11፥36 (አዲሱ መ.ት)

  • @yakoball5672
    @yakoball5672 Жыл бұрын

    God 🙏 bless you all members of this Church!!

  • @abiaaa2210
    @abiaaa2210 Жыл бұрын

    ተባረክ 🙏🙏

  • @abebayehuamanuel3768
    @abebayehuamanuel3768 Жыл бұрын

    Geta Eyesus yebarkh dr mamusha

  • @almey.7770
    @almey.7770 Жыл бұрын

    God bless you

  • @betty9705
    @betty9705 Жыл бұрын

    ጌታ ይባርካችሁ

  • @Jesusislove-gf3ox6wo8m
    @Jesusislove-gf3ox6wo8m Жыл бұрын

    እግዚአብሔር ስለ አንተ ይመስገን ጸጋ ይብዛልህ❤🤲 በጣም ነዉ ዉስጥን የሚነካዉ!!🥺

  • @tsigetekalegne771
    @tsigetekalegne771 Жыл бұрын

    Amen tebarek

  • @helenawonde9771
    @helenawonde9771 Жыл бұрын

    መታዘዝ ይሁንልኝ

  • @mesfinwolde5999
    @mesfinwolde5999 Жыл бұрын

    Bro, we appreciate you .

  • @user-mq1cm2sk6f
    @user-mq1cm2sk6f11 ай бұрын

    ameen

  • @bethelnigussie8196
    @bethelnigussie819610 ай бұрын

    Amen

  • @user-mq1cm2sk6f
    @user-mq1cm2sk6f11 ай бұрын

    ameeen

  • @hiwigelaye6509
    @hiwigelaye6509 Жыл бұрын

    ኢየሱስ ሞዴላችን 😍😍😍😍😍😍😍

  • @mossesg
    @mossesg Жыл бұрын

    ጌታ እየሱስ ዘመንህን ይባርክ ዶክተር ማሙሻ፡ የትውልድ በረከት ነህ ጌታ ከክፉ ይጠብቅህ ተባረክልን።

  • @lemlemghebremedhinweldeghi5205
    @lemlemghebremedhinweldeghi5205 Жыл бұрын

    ዋው!! እንዴት የሰባ ጮማ ነው እባካቹ፡ ኢየሱስን የወለደልኝ እህት ወንድሞቼ እየተመገብን ያለነው፡ እዛ ከእናንተ ተገኝቼ ብማር ደስ ባለኝ ነበር ነገር ግን ክብር ለእግዚአብሄር ይሁን ።በሩቅም ቢሆን መንፈሱ እየነካኝ ነው፡ ታድለናል ከቃሉ ስር ቁጭ ብለን ለመማር። በብዙ ተባረኩ የequip media ቤተሰብ ። በእናንተ ጸጋ እየተገለገልኩ ነው። ወንድም ማሙሻ፡ ከዚህ በላይ ገደብ በሌለው ፀጋው ይሙላህ፡ አትርፍያለሁ፡ ተባረኩ አሜን አሜን !!

  • @bereketgebregziabher444
    @bereketgebregziabher444 Жыл бұрын

    stay blessed

  • @tenagnemedhanit7052
    @tenagnemedhanit7052 Жыл бұрын

    ዶ/ር የረዳህን መንፈስ ቅዱስን እባርከዋለሁ ብዙ ያልገባኝን ተረዳሁ ጌታ ኢየሱስ ይባርክህ

  • @habatamhabatam8769
    @habatamhabatam8769 Жыл бұрын

    ዶክተር ጸጋ ይብዛልህ እዛ ቁጭ ብለው የሚማሩት እንደት እድለኞች እንደሆኑ ምን ያክል እግዚአብሔር እንደባረካቸው ያስተውሉት ይሆን ?

  • @feaaef5243
    @feaaef5243 Жыл бұрын

    አሜን አምላኬ በብዙ ይባርክህ ዶክተር ማሙሻ እንወድሀለን

  • @ethiopiaethio1579
    @ethiopiaethio1579 Жыл бұрын

    Egziabhear Yibarkachu

  • @almazwoldemichael7915
    @almazwoldemichael7915 Жыл бұрын

    God bless you all

  • @edensuliito7057
    @edensuliito7057 Жыл бұрын

    Dr ማሙሽ ፀጋ ይጫማርልህ ምናኛ ግሩም ትምህርት ነው እናደተ የወንጌል እውነት የሚያስተምሩትን እግዚአብሔር ያብዛልን 🙏❤️‍🔥❤️‍🔥

  • @Mercy-sw1zi
    @Mercy-sw1zi Жыл бұрын

    May God bless you dear Dr Mamusha and equip media for opening the door to equip and edify us to grow into maturity in knowing our Lord. This has never been something that ever take so lightly. I praise the Lord for His inexpressible gift, and I am also grateful for your obedience to be used of Him as such vessels. What can I say, this weekend’s message in Matthew has been such a blessing that I even shared your emotional presentation (in tears), and I am getting ready to listen to it agin. The Lord spoke to me (once before at a crucial time in my life) thru that blessed brother saint Joseph’s righteous life in his decision to listen to and obey His Lord and none else. Yet it has never failed to speak to me every time his story is presented. I prayed tearfully to have such a life of hearing and obeying the Lord. Most importantly, the parallelism you drew between the life of Mosses, the Israelites and our Lord Jesus was great. With your conclusion being so crucial for us to REST in our God who’s got things, events, timelines set up and purposed from the get go. What more do we need than Him being in control of all the ups,downs and the destiny of our lives? Not only does He know the end from the beginning, but He also knows the process that gets us there too. We are utterly dependent on Him, and He never disappoints! Amen. “The Lord is in his holy temple; let all the earth be silent before him.” ‭‭Habakkuk‬ ‭2‬:‭20‬ ‭NIV‬‬ bible.com/bible/111/hab.2.20.NIV

  • @merhawitgebremeskel
    @merhawitgebremeskel Жыл бұрын

    አሜን ክብር ሁሉ ለእግዚአብሔር. ይሁን ተባረኩ ፀጋ ይብዛላችሁ ሁላችሁ የዚህ ፕሮግራም አዘጋጆች ።

  • @wendesenhaile2321
    @wendesenhaile2321 Жыл бұрын

    ትምህርቱ ግሩም ነው የጌታ ፀጋ ይብዛላችሁ። "ያን ጊዜ በነቢዩ በኤርምያስ፥ ድምፅ በራማ ተሰማ፥ ልቅሶና ብዙ ዋይታ፤ ራሔል ስለ ልጆችዋ አለቀሰች፥ መጽናናትም አልወደደችም፥ የሉምና የተባለው ተፈጸመ። ያልገባኝ ጥያቄ ? /1 ጻድቅና ሩሕሩህ ሃያል አምላክ ሄሮድስ እነዚያን ምስኪን ህፃናት ሲፈጅ እንዴት ዝም አለ ? ወይንም ፈቀደ? ምን አልባት ቀጥሎ ባለዉ ቃል መሠረት ያ ትዉልድ ሊከፍለው የነበረ ደም ስለነበረ ይሆን? "ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ የፈሰሰው የነቢያት ሁሉ ደም፥ ከአቤል ደም ጀምሮ በመሠዊያውና በቤተ መቅደስ መካከል እስከ ጠፋው እስከ ዘካርያስ ደም ድረስ፥ ከዚህ ትውልድ እንዲፈለግ አዎን እላችኋለሁ፥ ከዚህ ትውልድ ይፈለጋል። (ሉቃ 11: 50-51) ጥያቄ ? /2 " በነቢያት፦ ናዝራዊ ይባላል የተባለው ይፈጸም ዘንድ፥ ናዝሬት ወደምትባል ከተማ መጥቶ ኖረ" (ማቴ 2:23) ይህንን ትንቢት ማቴዎስ ከየትኛዉ የቅዱስ መጽሐፍ ምንጭ አገኘዉ ወይንም ወሰደው ?

  • @kali2839
    @kali2839 Жыл бұрын

    ኡኡኡኡ ጌታ ዘመንህን ትዉልድህን ይባርክ

  • @mulukenmihretu8711
    @mulukenmihretu8711 Жыл бұрын

    እግዚአብሔር አምላክ አብዝቶ ይባርካችሁ ❤️❤️❤️❤️🙏🙏🙏🙏

  • @selamusorssa3970
    @selamusorssa3970 Жыл бұрын

    God bless you Mamusha,

  • @enarekassaofficial4420
    @enarekassaofficial4420 Жыл бұрын

    What a wonderful teaching 👏👏You’re blessed DR it’s big privilege to learn from you😇may God give you more grace up on you keep shining my beloved teacher I love you so much from Seattle wa

  • @genetkalata9710
    @genetkalata9710 Жыл бұрын

    Geta eyesus tsegaw yechmrleh

  • @amanuelkibret9327
    @amanuelkibret9327 Жыл бұрын

    በውነትም Equip! እግዘብሔርን ስለ አገልግሎታችሁ ሁሌም አመሠግነዋለሁ።

  • @medhanitmaja7856
    @medhanitmaja7856 Жыл бұрын

    ተባረኩ በርቱልን

  • @selamugenetu9253
    @selamugenetu9253 Жыл бұрын

    የተባለው ይፈጸም ዘንድ ኢየሱስ ሆነልን

  • @bogaleagga9026
    @bogaleagga9026 Жыл бұрын

    Amen🙏🏾

  • @tesfaaman5291
    @tesfaaman5291 Жыл бұрын

    ቅዱሳን ይህንን ሚድያ ብዙ ሰዎች ይድኑበታል እኛም እንታነጽበታለ ላይክ ሰብስክራይብ አድርጉ በጌታ ፍቅር ኮሜንት ጻፉ ብሩካን ናችሁ

  • @elenimuluneh3838
    @elenimuluneh3838 Жыл бұрын

    የድሃ አደጎች አባት የመበለቶች ዳኛ አለ በዙፋኑ

  • @sineduayele6519
    @sineduayele6519 Жыл бұрын

    ዶክተር አንጀቴን አራስከው።ይበልጡን ደግሞ ለካ መነጫነጭ ይቻላል ? ካዘንኩበት ነገር በላይ መነጫነጭ እየፈለግኩ ለመነጫነጭ መፍራቴ ነገሩን ያከብድብኝ ነበር። ለካስ ልጁ ነኝ።አመሠግንሃለሁ አከብርሃለሁ ተባረክ!!!!!!!!!

  • @oyniop9291
    @oyniop9291 Жыл бұрын

    What’s the church’s name? Where can we find it? When do you have programs?

  • @equipmedia2577

    @equipmedia2577

    Жыл бұрын

    Yehiwot Berhan Chuch Addis Christian Life Assembly Church. Here is the map. maps.app.goo.gl/7ffKT71PQgMrwA4X9 and we have programs on Friday evening & Sunday morning

  • @oyniop9291

    @oyniop9291

    Жыл бұрын

    @@equipmedia2577 thank you🙏🏽🙏🏽🙏🏽

  • @BirtukanKebededemise
    @BirtukanKebededemise Жыл бұрын

  • @genetkalata9710
    @genetkalata9710 Жыл бұрын

    Amen

Келесі