"የጊዜ ሚዛን" - ቅፅ ሁለት - ዋሲሁን አራጌ| "Yegizye Mizan" Vol. Two - Wasihun Aragie |

በገብያ ላይ "የጊዜ ሚዛን" ረዥም ኢ-ልብወለድ መፅሐፍ በ372 ገፆች የተቀነበበ ሲሆን፣ መሸጫ ዋጋውም ሀገር ውስጥ 250 ብር ባህር ማዶ ደግሞ $20 USD ነው፡
የታሪኩ መቸት በሀገራችን ደቡብ ምዕራብ ክፍል ሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ በተለይ ቴፒ ካምፓስ ከ2003 እስከ 2008 ዓ.ም ድረስ በነበርኩባቸው ዓመታት ባካባቢው ይስተዋሉ የነበሩ የተለያዩ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ፓለቲካዊ እንዲሁም ሀገር በቀል እውቀቶች በጥቅሉ አስደሳችና አሳዛኝ ኩነቶችን በተጨማሪም የዩኒቨርስቲ ህይዎትን በስፋት ያስቃኛል። ይህንን መጽሐፍ ወደእናንተ ለንባብ ሳደርስ ድርጊቱ ሲፈጠር
በአካባቢው ለነበሩና ሁኔታውን ላስተዋሉ መማሪያና ማስታወሻ፣ ላላዩና ላልሰሙት ደግሞ መዳረሻ እንዲሆን በማሰብ ነው፡፡
ዋሲሁን አራጌ የጥቁር ዕንቁ የግጥም መድብልና አጫጭር ወጎች ስብስብ ደራሲ እና በአሐዱ ሬዲዮ 94.3 የተረክ የራዲዮ ፕሮግራም አዘጋጅና አቅራቢ ነው።
ለገሀር በጀፈር መፅሐፍት መደብር ያገኙታል። 2014 ዓ.ም

Пікірлер

    Келесі