✞ የዐብይ ጾም የበገና መዝሙሮች ስብስብ ክፍል 5|✞Orthodox Nesha/Tsom/Begena Mezmur Collection part 5|✞

ዐቢይ ጾም ( ሊቀ ጉባኤ ቀለመወርቅ ውብነህ)
ዐቢይ ጾም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶሰ ከተጠመቀ በኋላ ዐርባ ቀን የጾመው፤ እኛም እንድንጾማቸው በቤተ ክርስቲያናችን ከታዘዝናቸው ሰባቱ የአዋጅ አጽዋማት አንዱ ነው፡፡ ምእመናን ጌታችን ያደረገውን ምሳሌ ተከትለን ጾሙን በየዓመቱ እንጾመዋለን፡፡ ዐቢይ ጾም ስምንት ሳምንታት (፶፭ ቀኖች) አሉት፡፡ በውስጡ ስምንት ቅዳሜዎች፣ ሰባት እሑዶች ይገኛሉ፡፡ ይኸውም ዐሥራ አምስት ቀን ማለት ነው፡፡ እነዚህ ቀናት ከጥሉላት እንጂ ከእህል ውኃ ስለማይጦሙ የጦሙ ወራት ዐርባ ቀን ብቻ ይሆናል፡፡ ጾሙ በተለያዩ ስሞች ይጠራል፤ አንደኛ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከተጠመቀ በኋላ የጾመው በመሆኑ፣ እንደዚሁም ‹‹ዐቢይ እግዚአብሔር ወዐቢይ ኀይሉ ዐቢይ እግዚአብሔር ወብዙኅ አኰቴቱ›› /መዝ.፵፯፥፩፤ መዝ.፻፵፮፥፭/ የተባለ ጌታችን የጾመው ጾም ስለሆነ ‹‹ዐቢይ ጾም›› ይባላል፡፡ ሁለተኛ ‹‹ሁዳዴ ጾም›› ይባላል፡፡ ይህም የመንግሥት እርሻ ወይም ማንኛውም የሕዝብ ብዛት ያለበት ሥራ ሁዳድ ስለሚባል ሲሆን፣ ዐቢይ ጾምም ከአጽዋማት ሁሉ ብዙ ቀናት ስለሚጾምና ኃያሉ አምላካችን ስለጾመው ነው /አሞ.፯፥፩/፡፡ ሦስተኛ ‹‹በአተ ጾም›› ይባላል፡፡ የጾም መግቢያ፣ መባቻ ማለት ነው፡፡ አራተኛ ‹‹ጾመ ዐርባ›› ይባላል፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የጾመው ፵ ቀን ስለሆነ /ማቴ.፬፥፩/፡፡ አምስተኛ ‹‹ጾመ ኢየሱስ›› ይባላል፡፡ ጌታችን እርሱ ጾሞ፣ ጹሙ ብሎ ስላዘዘን፡፡ ስድስተኛ ‹‹ጾመ ሙሴ›› ይባላል፡፡ ቅዱስ ያሬድ በዘወረደ ጾመ ድጓው ‹‹ከመዝ ይቤ ሙሴ እስመ ለዓለም ሙሴኒ ይቤ በውስተ ኦሪት›› እያለ ስለዘመረ /የሰኞ ዕዝል/፡፡

Пікірлер: 2

  • @user-sn9er3in3x
    @user-sn9er3in3xАй бұрын

    Amen Amen Amen Zemari Melaket yesemaln❤❤❤❤❤

  • @tsehyneshhaile8845
    @tsehyneshhaile8845Ай бұрын

    🙏🙏🙏🙏🙏❤❤❤❤❤

Келесі