ተአምረኛው ማለዳ:The Miracle Morning by Hal Elrod: Amharic Summary

amazon
amzn.to/3CpMK0L
ይህ መጽሐፍ ለግል ህይወት እድገት እና ለስኬታማ ህይወት በየጥዋቱ ልንሰራቸው የምንችላቸውን ስድስት ልምምዶች የሚዘረዝር እና የሚያብራራ መፀሐፍ ነው።
ዛሬ በመጽሐፍ ቅምሻችን ከዚህ መጸሐፍ ሊገኙ የሚችሉ ቁምነገሮችን አጠር አርገን ይዘን መጥተናል።
በነገራችን ላይ በመጸሐፍ ቅምሻችን የሚቀርቡ የመጸሐፍቶች ከሚሊዮን በላይ ቅጂ የተሸጡ እና ለአንባብያን ደግሞ በምእራቡ አለም አሉ በሚባሉ ጋዜጦች እና ሌሎች ሚዲያዎች የተገመገሙ ናቸው።
ወደ መጸሐፉ ስንመለስ ሃል ኤልራድ በመጸሐፉ አስረግጦ የሚናገረው በሕይወታችሁ ውሰጥ እናንተን የሚመለከቱ ነገሮች ላይ ሙሉ በሙሉ ሀላፊነታችሁን ከወሰዳችሁ ወዲያው ድንቅ ወደሚባል የለውጥ ጎዳና ልትገቡ ትችላላችሁ።
ሃል ኤልራድ በአንድ ወቅት በደረሰበት የመኪና አደጋ ሆስፒታል ገብቶ ለስድስት ደቂቃ ሞቱዋል ከተባለ በሁዋላ ሕይወት ዘርቶ እራሱን ሊያውቅ ችሉዋል።
በሆስፒታል ቆይታው ሀኪሞቹ ድጋሚ ቆሞ መሄድ እንደማይችል ቢነግሩትም
በተአምራዊ ሁኔታ ከህመሙ አገግሞ እንደቀድሞ መቆም ችሉዋል።
የሚከተሉት ሀሳቦች ከመጸሐፉ የተጨመቁ ናቸው ።
አንድ
በህይወትህ የሚከሰቱ ነገሮችን ከአንተነትህ ነጥለህ አትይ
እያንዳንዱ ከአንተ ጋር የተገናኙ ነገሮች የሚከሰቱት ትልቁን የሕይወትህን አካል የሚገነቡ ስለሆኑ ቸል አትበላቸው።
dansilvestre.com/
www.pixbay.com
www.fourminutesbookreview.com

Пікірлер: 5

  • @jemalkederseid8005
    @jemalkederseid8005 Жыл бұрын

    አመሰግናለው ጣፋጭ አንደበት

  • @addishiwottaklu6841
    @addishiwottaklu6841 Жыл бұрын

    እናመሰግናለን በጣም ጠቃሚ ሀሳብ ነው

  • @Azzistyle
    @Azzistyle Жыл бұрын

    ሰላም ብያለው ቆንጆ አቀራረብ ነው ይሄን መፀሀፈ ቡዙ ሰው ሄወቴን ቀይሮታ ሲሉ እየሰማው ነው በጣም ነው ያጎጎኝ ለማንበብ እውነት እናመሰግናለን

  • @tekatame3472
    @tekatame34727 ай бұрын

    Pedf magnyet inchilalen

  • @Dagnachewshitaw2
    @Dagnachewshitaw2 Жыл бұрын

    በጣም ጥሩ አቀራረብ ነው ፤ the automatic millionaire. David Bach. the richest man in Babylon. think and grow rich . rich dad poor dad robert kiyosaki. unlimited power tony robins ተርጉሚልን።

Келесі