ትምህርተ ሰዓታት ክፍል - ፩ | seatat zema part 1

ትምህርተ ሰዓታት ከአብ ወወልድ እስከ ግነዩ
በመልአከ ኀይል ቆሞስ አባ ዘድንግል
💒💒💒
የመጽሐፍ ሰዓታት ጸሐፊ ቅዱስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ ከ፲፫፻፶፯ - ፲፬፻፲፯ ዓ.ም ድረስ የነበረ ታላቅ ሊቅ ሲኾን ካለው ከፍተኛ መንፈሳዊ ዕውቀት የተነሣ "ዐምደ ሃይማኖት፣ ኢትዮጵያዊ ቄርሎስ" የሚል ሥያሜ ሲሰጠው ከ፳፩ በላይ መንፈሳውያት መጻሕፍትን የጻፈ አባት ነው።
ሰዓታት ማለት የበርካታ ሰዓቶች ስብስብ ሲኾን በነጠላ ሰዓት ሊባል ይችላል።
የተፈጠሩ ፳፪ቱ ፍጥረታት ኹሉ መነሻ ጊዜ (ሰዓት) ያላቸው ሲኾኑ፤ በተለይ ሰውና መላእክት በየሰዓቱ በየጊዜያቱ የእግዚአብሔርን ስሙን አመስግነው ክብሩን ሊያወርሳቸው ፈጥሯቸዋል።
ቅዱስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫም ይኽነን መጽሐፉን "መጽሐፍ ሰዓታት ዘሌሊት እና መጽሐፍ ሰዓታት ዘመዓልት ብሎ በዚኽ ስም ሊሠይምበት የቻለበት ምክንያት፦
፩, በመዓልትም በሌሊትም በሰዓቱ ኹሉ በአንድነቱ ምንታዌ(ኹለትነት) በሦስትነቱ ርባዔ (አራትነት) የሌለበት ልዑል እግዚአብሔር ምስጉን ስለኾነ ሲኾን
፪, ካህናት፣ ዲያቆናት፣ ምእመናን በደመ ወልደ እግዚአብሔር በተመሠረተችው የልዑል ማደሪያ በኾነችው በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ተሰብስበው በእነዚህ የሌሊትና የመዓልት የሰዓት ጊዜያት ልዑል እግዚአብሔርን የሚያመሰግኑበት ታላቅ የምስጋና መጽሐፍ ስለኾነ ነው።
💒 ይዘቱም
• ምስጢረ ሥላሴ
• ስለልዑል እግዚአብሔር ቸርነት
• ስለ እግዚአብሔር ወልድ ኢየሱስ ክርስቶስ
• ሰለ ነገረ ማርያም
• ሰለ ነገረ መላእክት
• ስለ መስቀልና ስለ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ስለ ሰንበተ ክርስቲያን ክብር
• ስለ ቀደምት አርዕስተ አበው እና ነቢያት ክብርና አማላጅነት
• ስለ፬ቱ ወንጌላውያን ምሳሌ
• ሰለ ሰማዕታት ተጋድሎና አማላጅነት
• ሰለ ጻድቃን ስለ መነኮሳት ሰለ ደናግል ሕይወትና ቅድስናዊ ኑሮ
• ስለ ሥዩማነ ቤተ ክርስቲያን
• ስለ ሥነ ዘፍጥረት። በጥልቀት ተብራርቶበታል።
💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒
"የእግዚአብሔርን ቃል የተናገሩአችሁን ዋኖቻችሁን አስቡ፥ የኑሮአቸውንም ፍሬ እየተመለከታችሁ በእምነታቸው ምሰሉአቸው"።
Subscribe for more...
/ @ztw
Follow us on Instagram...
/ zenawe_tefsehet_wehaset
Follow us on Telegram...
t.me/lediyakonat

Пікірлер: 16

  • @wubiyutezera2549
    @wubiyutezera25492 жыл бұрын

    እጅግ በጣም አስተማሪ ነው ዜማው ለመያዝ አያስቸግርም ቃለ ህይወት ያሰማልን። እስከ መጨረሻው ይለቀቅልን!!! እየተማርንበት ነው።

  • @melatsemunigus6195
    @melatsemunigus61952 ай бұрын

    እግዚአብሔር ያክብርልን እውነት በጣም ትልቅ ስራ ነው እንዲህ አስተምሩን🙏

  • @pawlosberhane9396
    @pawlosberhane9396 Жыл бұрын

    እኔ ኤርትራ ነይ የተማሃርኩ ነዉ ምርጥ ትምህት ጥእና ይስጥልን መምህሬ

  • @gebrehiwotsime-tn4yc
    @gebrehiwotsime-tn4yc3 ай бұрын

    ቃለ ህወት ያሰማልን

  • @endriaswsilassie2727
    @endriaswsilassie27273 ай бұрын

    እግዚአብሄር ይባርክህ

  • @sebed1085
    @sebed1085 Жыл бұрын

    እግዝአብሔር ዝማሬ መላእክት ያሰማልን

  • @alemarage1056
    @alemarage1056 Жыл бұрын

    ቃለ ህይወት ያሰማልን 🙏

  • @tebletfekadu7079
    @tebletfekadu7079 Жыл бұрын

    🙏🙏❤️

  • @elsabetbogale7227
    @elsabetbogale72272 жыл бұрын

    Kale hiywet yasemalin 🌹🌹🌹❤🙏

  • @birhanutube3919
    @birhanutube3919 Жыл бұрын

    እግዚአብሔር ያክብርልን ብዙ ግዜ ስፈልገዉ የነበረ ትምህርት

  • @-yeabsiratube980
    @-yeabsiratube9802 жыл бұрын

    Wowww arif nw.......bertu part 2...3...4......tolo tolo lekekulen

  • @ztw

    @ztw

    2 жыл бұрын

    በየሳምንቱ ይጠብቁን።

  • @YariedSAmera
    @YariedSAmera2 жыл бұрын

    ቃለ ሕይወት ያሰማልን፤ መንግስተ ሰማያትን ያውርስልን ያድልልን፤ የአገልግሎት ዘመንዎን ያርዝምልን። 🙏🙏🙏🙏

  • @tekaeyasu8119
    @tekaeyasu8119 Жыл бұрын

    እግዚአብሔር ይባርካችሁ። ቀጣይ ክፍሎችም ይለቀቁ

  • @andromedacassiopiea
    @andromedacassiopiea Жыл бұрын

    በርቱ።! የሰዓታት ት/ት በደንብ መጤን አለበት።!

  • @user-zs9nc9mf8w
    @user-zs9nc9mf8w3 ай бұрын

    የት ነው የሚያስተምሩት

Келесі