ተዓምራዊ የሆነዉን ቅዱስ ሥፍራ ለማክበር እና ለመጎብኘት ከነሐሴ 20-27 ድረስ በየዓመቱ ከ35,000-50,000 ሺህ ምዕምናን ወደ ሥፍራዉ ይጎርፋሉ፡፡

ግንዳንሳዉ መድሃኒዓለም
ይህ ቤተክርስቲያን የሚገኘዉ በዑባ ደብረፀሓይ ወረዳ ዉስጥ የሚገኝ ሲሆን ከዞኑ ዋና ከተማም በተለያዩ አቅጣቻዎች የሚያስኬድ በመሆኑ ርቀቱ እንደየ ጉዞዉ መስመር የሚለያይ ቢሆንም፤ በወረዳዋ ዋና ከተማ ከበቶ 34 ከ.ሜ ርቀት ላይ የሚገኝ ሲሆን፤ ቦታዉም እጅግ በጣም ቀዝቃዛ እና ተራራማ በሆነ ሥፍራ ላይ የሚገኝ ቤተክርስቲያን ነዉ፡፡ ቤተክርስቲያኑም ብዙ ተዓምራቶች የሚታዩበት ሥፍራ ሲሆን ተዓምራቱም መታየት የተጀመረዉ በአንድ አርሶአደር ላይ እና በማሣዉ ላይ እንደነበር ይነገራል ፡፡ አርሶአደሩም እርሻዉን በሚያርስበት ጊዜ በአንደኛዉ የበሬዉ ሻኛ ላይ ቀንድ እንደበቀለበት፤ ለአርሶአደሩ ምልክት ታየዉ፡፡ ይህ ቦታም ከብዙ ተዓምራቶች በኋላ ሥሙ እንደተቀየረ ሲነገር፤ የቀድሞ ስሙም ሐራ ተብሎ እንደሚጠራ የእድሜ ባለፀጎች ይናገራሉ፡፡
በ1905 ዓ.ም አንድ ታላቅ ተዓምር በዚህ አከባቢ እንደተከሰተ ይነገራል የክስተቱም ዓይነት፤- በዚሁ ቦታ አንድ ትልቅ ዛፍ በራሱ ጊዜ ወድቆ ለረዥም ጊዜ የቆየ ዘፍ እንደነበር ከዕለታት በአንድ ቀንም አንዲት እንስት ሴት ከልጇ ጋር በመሆን የወደቀዉን ግንዱን እጃቸዉ እስከሚዝል ድረስ በተለያዩ አቅጣጫዎች በምሳር ደጋግመዉ ለመፍለጥ ቢሞክሩት ራሱን ለምሳሩ ባለማመቻቸት አሰቸጋሪ በማድረግ ሴቲቱን አሽቀንጥሮ በመወርወር ነሓሴ/27/1905 ዓ.ም ለሦስት ጊዜያት አከባቢዉን በሚያናዉፅ ድምፅ በመጮህ ከገተጋደመበት/ከወደቀበት ቦታ በመነሳት የቆመ እና የለመለሙ ቅጠሎችን ያወጣ በመሆኑ ይህ በከባቢዉ ኖሩዉ በዓይናቸዉ ለሚመለከቱት እንዲሁም በሩቅ በመሆን ይህንን ለሰሙ ሰዎች ሁሉ ይህንን ተዓምራቱን ለማመን የሚከብድ በመሆኑ እስከአሁንም ድረስ ይህ ተዓምር ወደተፈፀመበት ቦታ በርካታ ሰዎች መጉረፋቸዉን አላቆሙም፡፡ ግንዱም በተነሳ በነጋታዉ ነሓሴ 28/1905 ዓ.ም በወቅቱ የገለብ ሐመር ባኮ እና የቡልቂ አስተዳዳሪ ለሆኑት ለደጅአዝማች መርዕድ ኃይለማሪም ከአከባቢዉ ነዋሪዎች ይህንን ተዓምር የሚያስረዳ መልዕክተኛ የተላከላቸዉ በመሆኑ እሳቸዉም እስከ ቦታዉ ድረስ በመምጣት ይህንን ተዓምር በመመልከት ለዳግማዊ አፄ ሚኒሊክ በቴሌፎን የደወሉላቸዉ ሲሆን ዳግማዊ አፄ ሚኒሊክም ለዚህ ተዓምራዊ ደብር ፅላት እንዲላክ ትዕዛዛቸዉን ሠጡ፡፡
ግንቦት 16 ቀን በ1906 ዓ.ም በቦታዉ ቤተክርስትያን ተሠርቶ ጽላቱ እንድገባ ተደረገ ፡፡ የዚያን ዕለትም ከምሽቱ 3 ሠዓት እስከ 6 ሠዓት ድረስ በቦታዉ አድማስ ላይ ቀስተደመና በመዘርጋት በአከባቢዉ ፀሐይ እንደወጣና አከባቢዉ ከተፈጥሮ ሕግ እና ሥርዓት ዉጪ ምሽቱ/ጨለማዉ ያለ ጊዜዉ ወደ ቀንነት/ብርሃን በመቀየሩ በታየዉ ሌላ ታላቅ ተዓምር ታዬ፤ በዚህም ተዓምር ምክንያት የቀድሞዉ የቦታዉ መጠሪያ የነበረዉ ሥም ሐራ የሚባለዉ በአከባቢዉ በታየዉ ታላቅ ተዓምር ምክኒያት አዲስ ስያሜን አግኝቶ ደብረ ፀሐይ/ የፀሐይ ደብር ተብሎ መጠራት እንደተጀመረ እና እሰከአሁንም ድረስ በዚሁ ስያሜዉ ፀንቶ ቆይቷል ፡፡
በዚህ ተዓምራዊ ቦታ የተለያዩ ተዓምራት በተለያዩ ጊዜያት እየተከናወኑ እንደቆዩም የሚታወቅ ሲሆን ይህም ደብር ልክ እንደ እናት ሀገሩ ኢትዬጵያ ሀገሩን ሊደፍር ለመጣ ጠላት ክብሩን አሳልፎ የማይሰጥ መሆኑን በአንድ አጋጣሚም አሳይቷል፡፡ ነገሩ እንዲህ ነዉ በ1928 ዓ.ም ወራሪዉ የጣሊያን ጦር በአዉሮፕላን በመምጣት ሦስት ቦንቦችን በቤተክርስቲያኑ ላይ ቢጥሉም ቦምቦቹ ሳይፈነዱ ጭስ ብቻ በማሳየት ከሽፈዉ እንደቀሩ በህይወት የሚገኙ እድሜ ጠገብ እማኞች ያስረዳሉ፡፡ በዚህም የተበሳጩት ጣሊያናዊያን ታቦቱን ለመዝረፍ በ1933 ዓ.ም በድጋሚ የመጡ ቢሆንም በአባቶች ብርታት እንዳልተደፈረ እስከ አሁን ድረስ በሕይወት የሚገኙ አባቶች ለወረዳዉ ባሕል ቱሪዝም እና ስፖርት ጽ/ቤት አስረድተዋል፡፡
በመቀጠልም በ1961 ዓ.ም በተጨማሪም ሌሎች የዉጪ ሀገር ሚሶኒያዊያን ወደ ቤተክርሰቲያኑ ዉስጥ ከቤተክርስቲያኑ ህገ ሥረዓት ዉጪ በሆነ መንገድ በድፍረት ጫማቸዉን ሳያወልቁ ለመግባት ከወቅቱ የደብሩ አለቃ የሆኑትን አባ ወልደ ሥላሤን በኃይል ጥሰዉ ወደ ዉስጥ ለመግባት ቢታገሉዋቸዉም በአባ ወልደ ሥላሤ ላይ ያደረባቸዉን መንፈሳዊ ኃይል ታግለዉ ማሸነፍ ባለመቻላቸዉ፤ በንዴት ጦፈዉ የመጡባትን ሂሊኮፍተር አስነስተዉ ሊሔዱ ሲሞክሩ ሂሊኮፍተርዋ ሦስት ጊዜ ተሸከርክራ አሁን በደብሩ ከሚገኘዉ ከመዳሕኒዓለም ፀበል በላይ በኩል ካለዉ ከኮሶ ዛፍ ጋር ተጋጭተዉ መከስከሳቸዉን የዕድሜ ጠገብ አባቶች ያስረዳሉ፤ ለእማኝነትም እስከ አሁን ድረስ የሂሊኮፍተሯም ስብርባሪ ከፀበሉ ባሻገር በሚገኘዉ ሸለቆ ዉስጥ የሚገኝ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል፡፡
በደብረፀሐይ ግንድአንሳዉ መዳሕኒዓለም ቤተክርስቲያን ዉስጥ የሚገኙ ጥንታዊ ቅርሶችንም በተመለከተ በርካታ የወርቅ እና የነሐስ መስቀሎች እና ሌሎች በምስጢር የተጠበቁ ኃይማኖታዊ ቅርሶች ይገኙበታል፡፡ ከዚህ ባሻገር ቤተክርስቲያኑን በተለያዩ ጊዜያቶች ሊያጠቁት ከመጡ ኃይሎችም ጋር ቤተክርስቲያኑን ከዉድመት እና ከጥቃት ለመከላከል ሲታገሉ የወደቁ የደጋግ እና የጀግኖች አባቶቻችንም አፅም በክብር አርፎ ይገኛል፡፡
በየዓመቱ ወደዚህ ሥፍራ ከተለያዩ አከባቢዉች ይህንን ታሪካዊ እና ተዓምራዊ የሆነዉን ቅዱስ ሥፍራ ለማክበር እና ለመጎብኘት ከነሐሴ 20-27 ድረስ በየዓመቱ በትንሹ ከ35,000-50,000 ሺህ ምዕምናን ወደ ሥፍራዉ ይጎርፋሉ፡፡ ነገር ግን ወደዚህ ሥፍራ የሚጎርፈዉን ሕዝብ ቁጥሩ እስከ አሁን ድረስ በተደራጀ መረጃ ቢያዝ ኖሮ፤ ከፍተኛ ትኩረትን በማግኘት የቦታዉ እዉቅና ከአከባቢያዊነት ወጥቶ ሀገራዊ ብሎም የዓለም ዓቀፋዊነት ዝናን በማትረፍ በዩኔስኮ ከመመዝገብ የሚያግደዉ ምንም ነገር እንደሌለ መመስከር ይቻላል፡፡ በመሆኑም የመንደገድ መሠረተ ልማትን በተሸለ መንገድ በማልማት ፡፡ ኢትዮጵያዊያን በጥንት ጊዜም ረዥም እና አደገኛ የአምልኮ ጉዞ Pilligramage በማድረግ የግብፅን እና የሴይናይን በረሃዎች በማቋረጥ ለአምልኮ እስራኤል ድረስ ይጓዙ እንደነበር የተረዳዉ ንጉስ ላሊበላ ቤተክርስቲያኖችን ከአንድ ዉቅር አለት ፈልፍሎ በመስራት ይህንን አደገኛ ጉዞ እንዳስቀረዉ እና የእስራኤልን የአምልኮ ቦታዎች ግልባጭ በኢትዮጵያ እንደሠራ ሁሉ አኛም አዲስ ባንሠራም እንኳን የተለያዩ ጠንካራ ሥራዎችን (የመንገድ እና የሆቱል) አገልግሎቶች ላይ አተኩረን በመሠራት ቦታዉን የቱሪስት መዳረሻ ማድረግ ስለሚቻል፤ በቀጣዩ በሚመለከተዉ አካል በስፋት መታሰብ ይኖርበታል እንላለን
(ምንጭ፤- የኡባ ደብረፀሓይ ወረዳ ባ/ቱ/ስ/ጽ/ቤት)

Пікірлер

    Келесі