ሰይድ እንድሪስ (ዶ/ር) በሀብሩ ወረዳ የግብርና ግብዓት አቅራቢ I Dr. Syed Endris

ጥራት ያለው የግብርና ግባት ለአርሶ አደሮች በማቅረብ ለውጥ ያምጡት- ዶ/ር ሰይድ እንድሪስ
Dr. Syed Endris, who brought change by providing quality agricultural inputs to farmers,
_______________________
ሰይድ እንድሪስ (ዶ/ር) በሀብሩ ወረዳ መርሳ ከተማ ነዋሪ ናቸው፡፡ ባለትዳር እና የአንድ ወንድ ልጅ አባት ሲሆኑ ኑሯቸውን በግል ስራ ተሰማርተው ይመራሉ፡፡
ዶ/ር ሰይድ በእንስሳት ህክምና የዶክትሬት ዲግሪ አላቸው፡፡ ከዓመታት በፊት በመንግስት ስራ ተቀጥረው ሲሰሩ ነበር፡፡ ነገር ግን አርሶ አደሮችን ለማገልገል እና የተሻለ ገቢ ለማግኘት ከ2009 ዓ.ም ጀምሮ የተወሰኑ የግብርና ግባቶችን ለአርሶ አደሮች ያቀርቡ ነበር፡፡
በአመልድ ኢትዮጵያ ለአደጋ የማይበገር የኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት በአማራ ክልል 7 ወረዳዎች (ወልድያ ክላስተር 3 ወረዳዎች - ራያ ቆቦ፣ ሃብሩ እና ጉባ ላፍቶ)፣ መቄት ክላስተር 2 ወረዳዎች (መቄት እና ዋድላ) እና መሃል ሜዳ ክላስተር 2 ወረዳዎች (መንዝ ማማ ምድር እና መንዝ ጌራ ምድር) 36,000 ቤተሰቦችን በምግብ ዋስትና እራሳቸውን እንዲችሉ በማድረግ ከተረጅነት እንዲወጡ እየሰራ ይገኛል። ፕሮጀክቱ ከአሜሪካ መንግስት እና ህዝብ በኬር ኢትዮጵያ በኩል በተገኘ $9.92 ሚሊዮን የገንዘብ ድጋፍ እ.ኤ.አ ከታህሳስ 2016 - ሰኔ 2023 እየተተገበረ ይገኛል። ከፕሮጀክቱ ዓላማዎች መካከል አርሶ አደሮች በተለያዩ የእሴት ሰንሰለቶች ማለትም በእንስሳት ማድለብ፣ በጓሮ አትክልት ልማት፣ በዶሮ እርባታ እና በበግ እርባታ ተሰማርተው ኑሯቸውን እንዲሻሻል የገበያ ትስስር እንዲፈጠር ያደርጋል፡፡ በፕሮጀክቱ አማካኝነት ሙያዊ ስልጠና እና የቁሳቁስ ድጋፍ ተደርጎላቸው ለአርሶ አደሮች አጠቃላይ የግብርና ግባቶችን እያቀረቡ ያሉት ዶ/ር ሰይድ እንድሪስ አንዱ ናቸው፡፡
"በፕሮጀክቱ ሙያዊ ስልጠና እና የቁሳቁስ ድጋፍ ካገኘሁ በኋላ ለአርሶ አደሮች የእንስሳት ምጥን መኖ፣ የግብርና ኬሚካል፣ የ45 ቀን ጫጩት እና የአትክልት ዘር እያቀረብሁ ነው፡፡ በተለይም የአንድ ቀን ጫጩቶችን ከኢትዮቺክን በማምጣት እና እስከ 45 ቀን ድረስ በጥሩ ሁኔታ በመመገብ እና አስፈላጊውን ክትባት ሰጥተን አሳድገን ዶሮ ለሚያረቡ አርሶ አደሮች እያቀረብን ነው፡፡ እነዚህን ግባቶችን ለአርሶ አደሮች ስንሸጥላቸው አጠቃቀማቸውን በማስረዳት እና ከሌሎች ሙያዊ ምክሮች ጋር ነው" ብለዋል፡፡
ዶ/ር ሰይድ የአርሶ አደሮችን የግብርና ምርታማነት የሚያሳድጉ ጥራት ያላቸውን የግብርና ግባቶችን በማቀርባቸው ደስተኛ ናቸው፡፡ ጠንክረው በመስራታቸውን እና የገበያ ትስስራቸውን በማስፋት በንግዳቸው ላይ ለውጥ አሳይተዋል፡፡ የመስሪያ ካፒታላቸውም ከ50,000 ብር ወደ 3ሚሊዮን ብር እንዳደገ ተናግረዋል፡፡ የግብርና ግባት መሸጫ ተጨማሪ ሱቆችን በወልዲያ ከተማ እና በመርሳ ከተማ ከፍተው ለአርሶ አደሮች አገልግሎት እየሰጡ ነው፡፡ ከዚህ በኋላ ከአርሶ አደሮች ጋር የገበያ ትስስር ስለተፈጠረ የሚፈልጉትን የግብርና ግባት ከሙያዊ ምክር ጋር ማግኘት ይችላሉ ብለዋል፡፡
Dr. Syed Endris, who brought change by providing quality agricultural inputs to farmers -
Syed Endris (Dr.) is a resident of Mersa town in Habru woreda. He is married and the father of one son and leads his life by being engaged in self-employment.
Dr. Syed holds a doctorate in veterinary medicine. Years ago, he was employed by the government. But in order to serve the farmers and get better income, he enjoyed in private business by providing some agricultural inputs to the farmers since 2009.
ORDA Ethiopia’s livelihoods for Resilience project (L4R) has been working in Amhara region 7 woredas (Woldia cluster (Raya Kobo, Habru & Guba Lafto); 2 woredas of Meket cluster (Meket and Wadla woreads ); and 2 woredas of Mehalmeda cluster (Menze Mama Midir & Menze Gera Midir) to benefit 36,000 rural households (HHs) and to graduate with resilience from the productive safety net program. It is funded $9.92 from USAID through CARE Ethiopia and is being implemented from December 2016 to June 2023. Dr. Syed Endris is one of them who has been provided with professional training and material support through the project, and he is providing general agricultural inputs to the farmers.
"After receiving professional training and material support from the project, I am providing the farmers with animal feed, agricultural chemicals, 45-day-old chicks and vegetable seeds. Especially by bringing one-day-old chicks from Ethio-chick and feeding them well up to 45 days and after giving them the necessary vaccinations, we offers them to farmers. We are selling all agricultural inputs to farmers by explaining their use and other professional advice," he said.
Dr. Syed is happy to provide quality agricultural inputs that increase the agricultural productivity of farmers. He has made a difference in his business by working hard and expanding his market linkage. He said that his working capital has increased from 50,000 birr to 3 million birr. He opened more agricultural input shops in Woldia city and Mersa town and are providing services to farmers. He said that after this, market linkages are established with the farmers, so they can get the agricultural inputs they need along with professional advice.
ለተጨማሪ መረጃ/ Social media platforms
ፌስቡክ/ Facebook: / orda-ethiopia
ቴሌግራም/ Telegram፡ t.me/ordaethiopia
ዌብሳይት/ Website: www.ordaethiopia.org
ትዊተር/ Twitter፡ / officialorda
ዩቱዩብ/ KZread: www.youtube.com/ ORDA Ethiopia

Пікірлер

    Келесі