ሰብአ ሰገል || የጥበብ ሰዎች እነማን ናቸው ?

በየዓመቱ የጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ልደት በዓል በመጣ ቁጥር ከሚነሡ ሰዎች መካከል ናቸው፤ ሰብአ ሰገል፡፡ ማናቸው? ከየት መጡ? ሀገራቸው የት ነው? ስንት ናቸው? ለምን ዕጣን፣ ከርቤ እና ወርቅ አመጡ? የሚሉት ጉዳዮችም አብረው ይነሣሉ፡፡
ስለ «ሰብአ ሰገል» የመጀመርያውን መረጃ የሰጠን ወንጌላዊው ቅዱስ ማቴዎስ ነው፡፡ ማቴዎስ በወንጌሉ በምዕራፍ ሁለት ላይ የጥበብ ሰዎች መሆናቸውን፣ የመጡት ከምሥራቅ መሆኑን፣ የተመሩት በኮከብ መሆኑን፣ የመጡበት ዘመን ንጉሥ ሄሮድስ ይሁዳን ሲገዛ መሆኑን፣ ሕፃኑ በተወለደ ጊዜ መድረሳቸውን፣ ዕጣን፣ ከርቤ እና ወርቅ በእጅ መንሻነት መስጠታቸውን፣ በኋላም ደስ ብሏቸው በሌላ መንገድ ወደመጡበት መመለሳቸውን ይነግረናል፡፡
መጀመርያ የሚነሣው ጥያቄ እነዚህ «ሰብአ ሰገል» እነማን ናቸው? የሚለው ነው፡፡ «ሰብአ ሰገል» ማለት በግእዙ «የጥበብ ሰዎች» ማለት ሲሆን በእንግሊዝኛው ሐዲስ ኪዳን magi ይላቸዋል፡፡ አንድም ጥበብ ያላቸው የስነ-ከዋክብት ተመራማሪዎች ማለት ነው። ይኸስ እንደምነው ቢሉ የሥነ ከዋክብት ተመራማሪዎቹ ከፍ ያለ ዕውቀት እንዳላቸው ስለሚገመት ይህንን ዕውቀት የያዙ አንዳንዶች በከዋክብት ምሕዋር ተጠቅመው የወደፊቱን እንደሚተነብዩ ስለሚታመን ነው፡፡ በየሚዲያው ታላላቅ የሚባሉት የሥነ ጽሑፍ ሰዎች ሳይቀሩ ሰብአ ሰገል የሚለውን «ሰባዎቹ ሰገሎች» እያሉ የገለጡልንን በአፈ መላእክት ያርምልን በማለት ስለ ሰብአ ሰገል ማንነት ለማወቅ ሙሉ ቪዲዮውን ተመልከቱት እንላለን ።
ምንጭ ፦ መራሪስ አማን በላይ “የጥንቷ የኢትዮጵያ ትንሣኤ ታሪክ” ፣ የዲያቆን ዳንኤል ክብር እይታዎች “ሰብዓ ሰገል”
#ሰብአ_ሰገል
Subscribe 👇 Our KZread Channel
ዩቲዩብ=www.youtube.com/@TobiyaMedia
እምነት፣ እውነት፣ እውቀት፣ ጥበብ፣ ፍቅር ሰውን ነጻ ያወጣሉ !
#ጦቢያሚዲያ #TobiyaMedia
© ጦቢያ ሚዲያ

Пікірлер