ቃላት ባገኘሁና Kalat Bagegnehuna ለዓለም ጥላሁን LeAlem Tilahun

Музыка

Gospel song by Singer Dr. Lealem Tilahun. I wish I have words to explain what You have done for me Lord.
“ቃላት ባገኘሁና..”
በዘማሪ ዶ/ር ለዓለም ጥላሁን
እንታነጽበት ዘንድ አቅራቢ
ወንድም ሶካ
[እወድሃለሁ እጅግ አብዝቼ
ከልቤ ጋራ እጄን አንስቼ
በምን ቋንቋ ነው ከቶ የምገልጸው
የልቤ አምላክ ሆይ ፍቅርህ ብርቱ ነው]2
ቃላት ባገኘሁና
ባወራ የአንተን ምስጋና
የልቤ በደረሰልኝ
አምላኬ አንተ ከብረህልኝ
[የሚያስፈልገኝ አንድ ነገር
እርሱም አንተው ነህ ጌታ እግዚአብሔር
አንተን ካገኘሁ ጠግቤ አድራለሁ
ስለዚህ አምላኬ እወድሃለሁ]2
ቃላት ባገኘሁና …
[መላ እኔነቴ አንተን ይወዳል
በቀን በለሊት ልቤ ያስብሃል
ያላንተ መኖር አይሆንልኝም
ሕይወቴ አንተ ነህ ሌላም የለኝም]2
ቃላት ባገኘሁና …
[የእግዚአብሔር ልጅ መድህኔ
ሕይወቴ ነህ አንተ ለእኔ]2
ሕይወት ተገለጠ እኔም አይቻለሁ
ጌታ ቸር መሆኑን ቀምሼ አውቅያለሁ
እግዚአብሔር አምላክ ነው እኔም በርቶልኛል
ታዲያ ከእርሱ ፍቅር ማንስ ይለየኛል
የእግዚአብሔር ልጅ መድህኔ
ሕይወቴ ነህ አንተ ለእኔ
የእግዚአብሔር ልጅ መድህኔ
ሰላሜ ነህ አንተ ለእኔ
ሰው አንተን ካገኘ ምን ያስፈልገዋል
እፎይ ብሎ አርፎ ተደላድሎ ይኖራል
ፍቅርህ የሚያጠገብ ልብን የሚያረካ
የመኖር ትርጉሙ ጌታ አንተ ነህ ለካ
[የእግዚአብሔር ልጅ መድህኔ
ሕይወቴ ነህ አንተ ለእኔ]2
ዕረፍቴ ነህ አንተ ለእኔ
ሰላሜ ነህ አንተ ለእኔ

Пікірлер: 17

  • @TarikuGiovanni
    @TarikuGiovanni4 ай бұрын

    May the Lord Jesus forever be blessed. Amen “በእርሱ ሕይወት ነበረች፥ ሕይወትም የሰው ብርሃን ነበረች።” - ዮሐንስ 1፥4

  • @eyerusalemtagesse9475
    @eyerusalemtagesse9475 Жыл бұрын

    ልጅነቴን አስታወሰኝ sunday school

  • @etsegenetweldearegay6303
    @etsegenetweldearegay630310 ай бұрын

    ይህንን መዝሙር ጊዜ ወስደህ በፊደላት ስላስቀመጥክልን በጣም እናመሰግንሀለን!!!❤

  • @ErahelAbrham
    @ErahelAbrham2 ай бұрын

    😭😭😭🙏🙏🙏🙌🙌

  • @user-il8kp3lp1d
    @user-il8kp3lp1d5 ай бұрын

    Wow Dr Lali Tilahun the Lord Jesus christ bless you

  • @mekditube7296
    @mekditube72963 жыл бұрын

    በእውነት በጣም ተባረኩ የድሮ መርሙሮች ❤️❤️❤️❤️❤️💞💞💞💞💞💞💞💞💞

  • @user-il8kp3lp1d
    @user-il8kp3lp1d5 ай бұрын

    So Amazing song healing of our spirit

  • @kalgetachew2400
    @kalgetachew2400 Жыл бұрын

    ደስ ይላል መዝሙሩን

  • @user-go4xx8rl7v
    @user-go4xx8rl7v Жыл бұрын

    AMEN

  • @tewodrosgetachew4024
    @tewodrosgetachew4024 Жыл бұрын

    wedhalehu eske

  • @GeteneshGetachew-rh1ud
    @GeteneshGetachew-rh1ud Жыл бұрын

    Tebarek❤

  • @mishelwilliam931
    @mishelwilliam931 Жыл бұрын

    Wow lebe yemineka new

  • @abeba6818
    @abeba68183 жыл бұрын

    እግዚያብሄር ይባርክ

  • @redietemito2950
    @redietemito29503 жыл бұрын

    God bless you

  • @mesiayalew8634
    @mesiayalew86348 ай бұрын

    ❤❤❤

  • @jesusislord6649
    @jesusislord66493 жыл бұрын

    God bless you! Bro

  • @mathewosenku5942

    @mathewosenku5942

    3 жыл бұрын

    እኔም

Келесі