መምህር ገብረ መድህን እንየው ስብከት / የወላጅ ሃጢአት ለልጅ ለምን ይተላለፋል?

መምህር ገብረ መድህን እንየው ስብከት memhir gebremedhin enyew sibket የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ስብከት
ብዙዎቻችን ወንድሞቻችንን ለማማት የፈጠንን ነን። የራሳችንን ግንድ ትተን የሰዉን ጉድፍ ለማውጣት የምንቻኮል ነን። በወንድሞቻችን ላይ ለመፍረድ እህቶቻችንን ለመኮነን የምንጣደፍ ነን። ወዳጄ ሆይ መፍረድ የእግዚአብሔር እንጂ ያንተ ስልጣን አይደለምና ተጠንቀቅ። እህቴ ሆይ በአምላክ ዙፋን ላይ ለመቀመጥ አታስቢ።
ወዳጄ ሆይ! መፍረድ አማረህን? እንኪያስ ምንም ወቀሳ የሌለበት፤ ይልቁንም ብዙ ጥቅምን የሚያስገኝ የፍርድ ችሎት አለልህ፤ በራስህ ላይ መፍረድ ትችላለህና ተቀመጥ። ከሁሉም አስቀድመህ የበደልህን መዝገብ በፊትህ አኑረው። ነፍስህ የሰራችወንም ወንጀል በሙሉ በጥንቃቄ መርምር፤ ከዚያም "ነፍሴ ሆይ! ይህንና ያንን በደል የፈጸምሽው ስለምንድነው?" በላት። የበደለችበትን ምክንያት ትታ በሌሎች ላይ ለማሳበብና በሌሎች ላይ ለመፍረድ ከጀመረችም "የተከሰስሽው በራስሽ ወንጀል እንጂ በሌላ ሰው ወንጀል አይደለም። ፍርድ ቤት የመጣሽው ስለነዚያ ሰዎች ለመመስከር አይደለም። ስለዚህ ንገሪኝ! ይህን ያህል በደል የፈጸምሽው፤ ይህንና ያንን ሁሉ ጥፋት ያጠፋሽው ስለ ምንድነው?" በላት። ዘወትር ይህን የመሰለ አስጨናቂ ጥያቄ ጠይቃት። አፍራ የምትመልሰው ከሌላትም አስፈላጊውን ፍርድ ወይም ቀኖና ወስንባት። ይህን ልዩ ፍርድ ቤት ዘወትር የምትቀመጥ ከሆነ ያንን የእሳት ባህር፤ ያ እሳቱ የማይጠፋው ትሉ የማያንቀላፋው ስቃይ በልቡናህ ይቀረጻል።
"ወደ እኔ መጥቶ ነው፤ እርሱ አታሎኝ ነው፤ እርሱ ፈትኖኝ ነው" እያለች በዲያብሎስ እንድታመካኝም አትፍቀድላት። ይልቁንም "አንቺ ባትፈቅጂ ነው እንጂ እነዚህ ሁሉ ባአንቺ ላይ ስልጣን የላቸውም" ብለህ ንገራት። "እኔ እኮ ስጋ ለባሽ ነኝ፤ የምኖረዉም በዚህ ኃጢአት በሞላበት ዓለም ነው" ካለችህም "ይህ ሁሉ ሰበብ እና ምክንያት ነው። ብዙዎች አንቺ የለበሽውን ስጋ ለብሰው በዚህ ዓለም ኖረው ፃድቃንና ሰማዕታት ሆነዋል። አንቺ ራስሽ አንዳንድ ጊዜ መልካም ምግባራትን ስታደርጊ ይህ አሁን የምታሳብቢበትን ሥጋ ለብሰሽ ነው" በላት። ይህን ስትላት ቢያማትም እጅህን አታንሳባት። ምክንያቱም ቀኖናው ከሞት የሚታደጋት መንፈሳዊ ልምምድ እንጂ የሚገድላት ቅጣት አይደለምና። ስለዚህ ምክንያት የምታበዛብህ ከሆነ "እባብ አሳተኝ ብላ" ከተጠያቂነት ያላመለጠቺውን ሄዋንን አስታዉሳት።
ይህን ሁሉ ስታደርግም ከአጠገብህ ማንም አይኑር። የሚረብሽህ ሰው ከአጠገብህ አይገኝ። ይልቁንም ዳኛ በፍርድ ወንበር ላይ እንደሚቀመጥ አንተም በፍርድ ወንበር ፈንታ በምቹ ጊዜና ቦታ በጽሞና ተቀመጥ። ነቢዩ "በመኝታችሁ ሳላችሁ በልባችሁ የምታስቡት ይታወቃችሁ" እንዳለው /መዝ. 4:4/ ይህ ቦታና ጊዜ ከሁሉም ይልቅ ተስማሚ ነዉና እራትህን ከበላህ በኋላ ዘወትር ይህን የፍርድ ወንበር ወደ መኝታ ክፍልህ ይዘኸው ሂድ። ዕለት ዕለት ይህን የምታደርግ ከሆነ ሓዋርያው "እኛ በራሳችን ብንፈርድ ኖሮ ባልተፈረደብን ነበር" እንዲል በዚያ አስፈሪው የፍርድ ወንበር ፊት ያለፍርሓት ትቆማለህ /1ኛ ቆሮ. 11፡31/።
'"ሰማዕትነት አያምልጣችሁ እና ሌሎች" በቅዱስ ዮሓንስ አፈወርቅ፤ ትርጉም በገብረእግዚአብሔር ኪዶ'
• orthodox sibket
• orthodox mezmur
/ @ethiopianorthodoxteac...
#suryal1219 #Yemankiya_Dewel #Memihir_Mehreteab_Asefa

Пікірлер: 3

  • @hbi980
    @hbi980 Жыл бұрын

    ቃለ ህይወት ያሰማልን

  • @brhanie6823
    @brhanie6823 Жыл бұрын

    ቃለ ህይወት ያሰማልን መምህራችን

Келесі