# ሁሉን አቀፍ ግብረመልስ # አራስን ፈልጎ ማግኘት # 360 degree feedback# Dr. Adera Abdela

ሁሉን አቀፍ ግብረመልስ ወይም 360 degree feedback ማለት እራሳችንን ለማሳደግ፡ ያሉንን ጥንካሬዎች፣ ድክመቶች፣ ችሎታዎች እና አቅሞች ለማወቅ ሁሉን አቀፍ ግብረመልስ መሰብሰብ ማለት ነው፡፡ 360 ዲግሪ ማለት ከሁሉም አቅጣጫ ማለትም ከትዳር አገሮቻችን፣ ከልጆቻችን፣ ከቤተሰቦቻችን፣ ከጓደኞቻችን፣ ከአቻ የስራ ባልደረቦቻችን፣ ከአለቆቻችን እንዲሁም እኛ አለቃ ሆነን ከምንመራቸው ሰዎች ስለራሳችን ባህርይ፣ ብቃት፣ ድክመት እንዲሁም ጸጋዎች በመጠየቅ ስለእራሳችን መረጃ በመሰብሰብ ማንነታችንን የበለጠ ለመረዳት ያስችለናል፡፡ ከአንድ ወይም ከተወሰኑ አካላት ብቻ ግብረመልስ ከሰበሰብን የተሟላ መረጃ ሊኖረን አይችልም ስለዚህ ሁሉንም ያማከለ መረጃ ስናገኝ ግን ለእውነታ የቀረበ መረጃ እንድናገኝ ያስችለናል፡፡
ከሁሉም አቅጣጫ ግብረመልሱን ከተቀበልን በሗላ ጥንካሬዎቻችንን ለማጎልበት፣ ድክመቶቻችንን ለመጥፋት እንዲሁም ያሉንን አቅሞች አሟጠን ለመጠቀም የድርጊት መርሃግብር አውጥተን ተጠቃሚ ሊያደርገን ይችላል፡፡ ስለዚህ 360 ዲግሪ ግብረመልስን በመጠቀም ስለራሳችን ግብረመልስ በመሰብሰብ የተግባር መረጃ መሰብሰብ ይኖርብናል፡፡

Пікірлер: 2

  • @Teshome157
    @Teshome1572 ай бұрын

    Thank you

  • @hanaasged1421
    @hanaasged1421Ай бұрын

    ❤❤❤❤❤ ሠዎች ቢሠሙክ 🙏🙏🙏

Келесі