አገሩ የዘነጋችው የካራማራው ጀግና፤ አሊ በርኪ | Ali Berki | Karamara | Ethiopia

Ойын-сауық

የተከበራችሁ ተመልካቾቻችን ሻለቃ ዓሊ በርኬ ለአገራችን ያበረከቱትን ውለታ አስባችሁ አሁን የሚገኙበትን ወቅታዊ የኑሮ ሁኔታ ተመልክታችሁ የአቅማችሁን ድጋፍ ልታደርጉላቸው እንደምትፈልጉ ገልጻችሁልናል።
ለዚህ ኢትዮጵያዊ ክብር ወዳድነታችሁ ያለንን አክብሮት እየገለጽን አድራሻችሁን በገጻችን andafta ብታስቀምጡልን ከሻለቃ ዓሊ በርኬ ጋር ልናገናኛችሁ እንደምንችል እናሳውቃለን።
እናመሰግናለን!!
~~~~~~~~~~~~••••••••~~~~~~~~~~~~~~~
አገሩ የዘነጋችው የካራማራው ጀግና፤ አሊ በርኪ
ሰላም ጤና ይስጥልን ተመልካቾቻችን ተስፋፊው መሃመድ ዚያድ ባሬ የሚባሉት የሶማሊያ ፕሬዝዳንት በኢትዮጵያ ላይ ይፋዊ ወረራ የጀመሩት የዛሬ 42 ዓመት በሰኔ ወር 1969 ዓ.ም ነበር፡፡ በወቅቱ ከንጉሳዊ አስተዳደር ውድቀት በኋላ ገና የመንግስትነት ቁመና ላይ ያልደረሰው የደርግ መንግስት በሰሜን ከህወሓት እና ሻዕቢያ፣ በመሃል አገር ከኢህአፓ እንዲሁም በምዕራብ በኩል መጠኑ አነስተኛ ይሁን እንጂ ከኦነግ ጋር ፍልሚያ ላይ ነበር፡፡ በዚህ የተነሳ ብዙም ወታደራዊ አቅሙ ያልጎለበተው የደርግ መንግስት ከሰይድ ባሬ የገጠመውን ወረራ ተከትሎ በመላው አገሪቱ የእናት አገር ጥሪ መልዕክት አስተላለፈ፡፡
በወቅቱ ከ300 ሺህ በላይ ወጣቶች የመንግስትን ጥሪ ተቀብለው ለስልጠና በታጠቅ ጦር ሰፈር ከተሙ፡፡ የሶማሊያ ጦርነት ሲነሳ በብዙሃኑ ዘንድ ቀድሞ የሚታወሰው ደግሞ በእጅ ቦንብና በክላሽንኮቭ ጠብመንጃ ብቻ የጠላትን ጦር መሪዎች ከእነ ታንካቸው ዶግ አመድ ያደርጉ የነበሩት የያኔው 50 ዓለቃ፤ በኋላም የአገሪቱን ከፍተኛ ወታደራዊ ኒሻን ከኮሎኔል መንግስቱ እጅ የተሸለሙትና አሁን በቀን ስራ ህይወታቸውን የሚገፉት ሻለቃ ባሻ ዓሊ በርኬ ናቸው፡፡
ወታደራዊ መንግስት ስልጣኑን ለህወሓት ኢህአዴግ አስረክቦ ከወጣ በኋላ የመጀመሪያው ዙር ሚሊሻ ዘማቾች አባል የነበሩት ሻለቃ ባሻ ዓሊ በርኬም ለስደት ተዳርገው በኬንያ ስደተኞች ካምፕ ተጠልለው ቆይተዋል፡፡ ወደ ኬኒያ በሚሰደዱበት ወቅት ከኢትዮጵያ ድንበር ሲደርሱ አፈር ዘግነው በመሃረብ ቋጥረው ኬኒያ የገቡት ሻለቃ ዓሊ፤ በማያውቁት ምክንያት ለዘጠኝ ዓመታት በቃሊቲና ዓለም በቃኝ እስር ቤቶች ክስ ሳይመሰረትባቸው ማቀዋል፡፡ ከእስር ቤት ከተፈቱ በኋላ ኑሮን በጎዳናና በቀን ስራ የገፉት ሻለቃ ዓሊ በርኬ ‹‹የወቅቱ የአገራችን የቁርጥ ቀን ልጅ›› የሚሉትን ታማኝ በየነን ሲያደንቁት ቃላት ያጥራቸዋል ቢባል ይቀላል፡፡ ለአጼ ቴዎድሮስ፣ ለደጃዝማች በላይ ዘለቀና ለኮሎኔል አብዲሳ አጋ ያላቸው አክብሮት ከፍተኛ የሆነው ፤እኒሁ የጦር ሜዳ ጀግና፤ ኮሎኔል መንግስቱ ኃይለማሪያም አምባገነን ቢሆንም አገሩን የሚወድ ሰው ነበር ይላሉ፡፡
አቶ መለስና ፓርቲያቸው ህወሓት ደግሞ ‹‹የኢትዮጵያ አፍራሾች ናቸው›› ይላሉ፡፡ አሁን የተፈጠረው ለውጥ የህዝብ ድጋፍ ያስፈልገዋል የሚሉት ሻለቃ ዓሊ በርኬ፤ ትውልድና እድገታቸው ወለጋ ቢሆንም የኦነግን አክራሪ ፖለቲካ በጽኑ የሚያወግዙ ሲሆን፤ በቅርቡ ከኦነግ አመራሮች ጋር የተለዋወጧቸውን ጠንካራ ቃላትም በቃለ ምልልሳችን አንስተውልናል፡፡ የዚያድ ባሬን ወረራ 42ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ ባልደረባችን ይርጋ አበበ በሻለቃ ዓሊ በርኬ መኖሪያ ቤት ተገኝቶ ያደረገውን ሰፋ ያለ ቃለ ምልልስ የመጀመሪያ ክፍል ዛሬ እናቀርባለን፡፡

Пікірлер: 351

  • @Andafta
    @Andafta5 жыл бұрын

    የተከበራችሁ ተመልካቾቻችን ሻለቃ ዓሊ በርኬ ለአገራችን ያበረከቱትን ውለታ አስባችሁ አሁን የሚገኙበትን ወቅታዊ የኑሮ ሁኔታ ተመልክታችሁ የአቅማችሁን ድጋፍ ልታደርጉላቸው እንደምትፈልጉ ገልጻችሁልናል። ለዚህ ኢትዮጵያዊ ክብር ወዳድነታችሁ ያለንን አክብሮት እየገለጽን በግል የባንክ አካውንታቸው #ዓሊ_በርኬ 01320226970901 አዋሽ ባንክ 1000285707057 ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መርዳት ትችላላችሁ። ለተጨማሪ ጥያቄ እና አስተያየት በገጻችን facebook.com/andafta or andaftamedia@gmail.com ብታስቀምጡልን ከሻለቃ ዓሊ በርኬ ጋር ልናገናኛችሁ እንደምንችል እናሳውቃለን። እናመሰግናለን!!

  • @yy-ut3dh

    @yy-ut3dh

    5 жыл бұрын

    Andafta የባንክ አካውንት ቁጥር ካላቸው እባክህ እዚህ ላይ አስፍረው ውጭም ሀገርውስጥም ያለው ሀገር ወደድ ሊረዳቸው ይችላል እኔ በበኩሌ ዝግጁ ነኝ አመሰግናለሁ

  • @ethiopia9214

    @ethiopia9214

    5 жыл бұрын

    ረጅም እድሜ ከጤና ጋር ከልብ እየተመኘሁላቸው አድራሻቸውን ብታስቀምጡ የተሻለ ነው የአቅሜን በደስታ ለመርዳት ዝግጁ ነኝ

  • @Andafta

    @Andafta

    5 жыл бұрын

    @Dagmar andaftamedia@gmail.com

  • @ethiopiaethiopia2718

    @ethiopiaethiopia2718

    5 жыл бұрын

    Shaleka, thank you for serving your country so that our generation have a country now. I hope we will Cary our responsibility as you have!! Guys, thank you for posting his bank account which I just verified that it is in his name. I have put my share to his CBE account. It is a very small amount for what he did for his country but hopefully it will mean something if everyone pouts what they can. Let it be even 10 birr but to him you recondition mean something! Thank you Shaleka!!!

  • @yy-ut3dh

    @yy-ut3dh

    5 жыл бұрын

    እናመሰግናለን

  • @abbazegerdim7039
    @abbazegerdim70395 жыл бұрын

    ሻለቃ ባሻ አሊ በርኪ የኢትጲያ ምርጥ ልጅ! ጀግና! እንደአንተ ያለ ጀግና ያፈራች ወለጋ እንደነ ዳዉድ ኢብሳ ያሉ ፀረ ኢትዮጵያ የሆኑ ጭንቅላታቸው ያገር ፍቅር ሣይሆን ንፍጥና ጥላቻ የሞላው ጉዶችና ሌቦችንም አብቅላለች በጣም አድናቂህ ነኝ

  • @hey1232

    @hey1232

    5 жыл бұрын

    Abba Zegerdim= Eree Bakeshiee kkkkkk

  • @user-ve5oe4dt5b
    @user-ve5oe4dt5b5 жыл бұрын

    ኢትዯጰያ ካፈራቻቸው ጀግኖች እንድ ምርጥ ጀግና እሊበረኬ ነው ታሪክ የማይረሳው የእሁኑ ትውልድ ከዚህ ጀግና ብዙ ሊማር ይገባል 👍🏾👍🏾👍🏾👍🏾👍🏾👍🏾👍🏾

  • @shewaminilik1602
    @shewaminilik16025 жыл бұрын

    አይ ኢትዮጵያ እንደዚህ አይነት ጀግኖች እንዳላፈራሺ በተቃራኒዉ አሁን አገር ሻጭ ደንቆሮ ይቀልድብሻል። ባለዉለታሺ በየቦታዉ ወድቀዋል አሣዛኝ ነዉ በእዉነቱ።

  • @fithytaye2639
    @fithytaye26395 жыл бұрын

    ሻለቃ አሊ እግዚአብሔር ውለታዎን ከፋይ ያድርገኝ።

  • @yy-ut3dh

    @yy-ut3dh

    5 жыл бұрын

    Fithy Taye የሻለቃ ባሻንና የሻለቃን ልዩነት ታቃለህ?

  • @yaredenayared8873
    @yaredenayared88735 жыл бұрын

    አንድ አፍታዎች እየሰራችሁ ያላችሁት በሙሉ ምርጥ ነው በርቱ ይህን አንበሳ ማቅረባችሁ ግን ከምንም በላይ አስደስቶኛልና ተባረኩ እባካችሁ የዚህን ብርቅዬ ጀግና አድራሻ ጻፉልን አደራ

  • @ethionile6096

    @ethionile6096

    5 жыл бұрын

    በፌስ ቡክ አድራሻችን አግኙንና የሻለቃን አድራሻ እንሰጠዎታለን። እናመሰግናለን

  • @meronberhan2395

    @meronberhan2395

    4 жыл бұрын

    Yirga Abebe be mariyam kuterachiwen seteg

  • @eyosiyasematiwos4884

    @eyosiyasematiwos4884

    4 жыл бұрын

    Please selekune bezekutere selekune lakelegne 0097470981281

  • @4mood
    @4mood5 жыл бұрын

    ውድ የኢትዮጵያ ልጅ።።።

  • @yy-ut3dh
    @yy-ut3dh5 жыл бұрын

    አሊ በርኬ ከዚህ በፊት በደራው ጨዋታ በ ደረጄ ፕሮግራም ላይ ሰምቻቸዋለሁ ላገራቸው ያላቸው ፍቅር ከሁላችንም ለየት ጠጠር ያለ ነው ግን ላበረከቱልን ታላቅ አስተዋፆ ውለታቸውን እልከፈልናቸውም:: የኢትዮጵያ አምላክ ይክፈላቸው እኛ እንደሆነ ከንፈር ከመምጠጥ ውጭ ምንም ማድረግ የማንችል ከንቱ ትውልድ ነን

  • @dilbegeta480
    @dilbegeta4805 жыл бұрын

    የእኔ ጌታ ስወድህ ጀግናው አሊ በርኪ አሳዛኝ ደግሞም አስደሳች

  • @nigatuteferi9347
    @nigatuteferi93475 жыл бұрын

    ጀግናዉን አሊ በርኬ አብሬዉ ከመታሰሬም በላይ ስለእርሱ "ትዉልድ ያናወጠዉ ጦርነት " በሚለዉ መጽሃፌ 'አል በርኬ የተረሳዉ ጀግና በሚል ረዕስ ጽፌአለሁ። አገራችን የጅግኖች ወዳጅ አይደለችም ።ይኸ ጀግና እንዲህ ተጎሳቅሎ መኖር አልነበረብትም። ዛሬም ቢሆን አልረፈደም መንግስት ተገቢዉን እንክብካቤ እንዲያደርግ ይኸንን የምታዩና የምታነቡ ሁሉ ተጽኖ ለማድረግ ጥረት እንድናደርግ እጠይቃችኃሁ። ባሻ አሊ በርኬ ""አማርኛ የጋራ ቋንቋችን ነዉ እንደተመቸኝ ብናገር ማንም አያገባዉም" በማለት በንግግሩ የሚቀልዱትን አስተማሪ የሆነ መልስ የሚሰጥ ጀግና ነበረ።

  • @solomonyeman3717

    @solomonyeman3717

    4 жыл бұрын

    አረባካችሁ እኝን ጃግና ሀውልት ይቁምላቸው ኩራታችን ናቸው

  • @addisaddis3562
    @addisaddis35625 жыл бұрын

    እድሜ ይስጥልን እንዲህ የሚወዷትን ኢትዮጵያ ሰላሟን ለማየት ያብቃዎ እግዚአብሔር ይስጥልን ይቺን ቀን በነጻነት እንድናይ ስላበቁን ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!! ስልካቸው ቢኖር የቻልነውን ብንረዳ ጥሩ ነበር ስንቶቹ መከራቸውን አይተው ለሀገራቸው በየጎዳና ወድቀው ቀርተዋል ፈጣሪ ልቦና ይስጠን።

  • @firstbornnet
    @firstbornnet5 жыл бұрын

    እኔ የዚህን ጀና ታሪክ በደንብ አውቃለሁ ምክንያቱም ወለጋ ደዴሳ ነበርኩ ብ/ውና በጣም ታዋቂ ጀግና ነው እነኚህ የታሪክ ማፈሪያወች ይህን ጀግና አስረው ማዋረዳቸው እንደ እግር እሳት አቃጠለኝ ስሜቴንም መቆጣጠር አቅቶኝ ለቅሶዬን ማቆም አቃተኝ በጣም የገርርመኝ በደረሰበት መከራ እስካሁን የአገር ክህድት የለበትም እናንተ ግን ይህን ጀግና በእስር ያዋራዳችሁ እግዚያብሄር የስራችሁን ይስጣችሁ አሊ በርኪ ድሮም አሁንም እስከዘላለም የኢትዮዺያ ጀግና ነው

  • @beewnetlenager2674
    @beewnetlenager26744 жыл бұрын

    ይህን በማቅረባችሁ እጅግ በጣም ደስ ብሎኛል፡፡ ይህን ሰው ከተደበቀበት ፈልጋችሁ በማቅረባችሁ የአገራችን ባለውለታ ናችሁ፡፡ የአገራችንም ታሪክ ተቀብሮ እንዳይቀር እድርጋችኋል፡፡ ምልበል ደስ አለኝ!

  • @selamleethiopia5675
    @selamleethiopia56754 жыл бұрын

    ኡኡኡኡኡኡ እንዲህ አይነት ክብር ነው ለኢትዮጵያ እናመሰግናለን ስላስተዋወቃችሁን

  • @amourgagnetoujours
    @amourgagnetoujours5 жыл бұрын

    ሻለቃ ባሻ አሊ በርኬን ጠብቆ ላኖረው እግዚአብሔር ክብር ይሁን። ፈልገው አፈላልገው ላገኙት 2 ጋዜጠኞች ደረጀ እና አዜብም እግዚአብሔርም ይባርካችሁ ማለት እወዳለሁ። አንዳፍታ ደግማችሁ ስላመጣችሁት ተባረኩ። ጀግናችን ረጅም እድሜና ጤና ይስጥዎ።

  • @zobleselam5695
    @zobleselam56955 жыл бұрын

    ጋዜጠኞች እኚህን ጀግና ስላቀረባችሁልን እናመሰግናለን።ግን በዚያውም አካውንት ተከፍቶላቸው ለምን ህዝቡ እንዲረዳቸው አታደርጉም።

  • @mussahussen2719
    @mussahussen27195 жыл бұрын

    ሻለቃ አሊ በርኬ እድሜ እና ጤና ይስጥህ በኛ ሀገር የሰረቀ እንጅ ጥሩ የሰራ አይኖርም

  • @MMMoneyMae4sure
    @MMMoneyMae4sure5 жыл бұрын

    ጀግናዬ ነዎት በእውነት አባቴ ይኑሩልኝ በዚህ ዘመን እንደሰዎ አይነት ጀግና ክብር ይገባዎታል::

  • @gebtezera5822
    @gebtezera58225 жыл бұрын

    He's is national hero forever! God bless you Ali Barkey!

  • @malmal5918
    @malmal59185 жыл бұрын

    ፊልም ነው የሚመስለው እንዲህ ነበሩ አባቶቻችን አሁን ግን የኛ ጀግንነት ወንድምን መግደል ነው

  • @michaelcorleone1861

    @michaelcorleone1861

    3 жыл бұрын

    እድሜ ለሰይጣን መለስ ዜናዊ አገር ከፋፍሎ ለዛሬ የተረገመ ጊዜ ደረስን

  • @gontelbelay8516
    @gontelbelay85165 жыл бұрын

    በጣም ይገርማል አሊ በርኬን የረሳች አገር እና የረሳ ህዝብ ለወደፊት ምን አይነት ጀግና ይወጣባታል ?ጎበዝ አስቡ እስኪ በዚህ 27 ዓመት ውስጥ የፈጀናቸውን ጀግኖች።

  • @solodamedia1029
    @solodamedia10295 жыл бұрын

    በዘርና በጎሳ ሳይለያይ ከዚያድባሬ ከገንጣይ አስገንጣዬች ጋር እየተፋለመ አገር የጠበቀ ሆኖም በአገራችን ጠላቶች ደባ ታሪክ የዘለለው የኢትዮጵያ የቀድሞው ሰራዊት አባል ሻለቃ ባሻ አሊ በርኬ ብሔራዊ ጀግናችን ነው።

  • @firehiwotseblegiorgis301
    @firehiwotseblegiorgis3015 жыл бұрын

    አከበርኮት ለርሶ ሳይሆን ለራሴ አለቀስኩ የኛ የኢትዮጵያ ባለውለታ እ/ር ያክብሮት እድሜ ከጤና ያድሎት ይኸው ዛሬ እንዲ ውጥንቅጣችን ወቶ በእውነት ያማል ይህንን የመሰለ መስዋእት የተከፈለላት ሀገር በገዛ ጡት ነካሽ ልጆችዋ እንዲህ ምስቅልቅል አሳሯን ያሳዩናል ምድረ ባንዳ

  • @honnatamiru5413

    @honnatamiru5413

    5 жыл бұрын

    👍👍👍👍❤️❤️❤️❤️💋💋❤️❤️

  • @posthue
    @posthue5 жыл бұрын

    Very interesting! Thank you! Ali Berki is a national hero!

  • @stongetower2337
    @stongetower23374 жыл бұрын

    This man is a hero. What an example for all Ethiopians and Africans!! This is how we are suppose to love our country!! Much love for Ali Berki.

  • @walleaddis807
    @walleaddis8075 жыл бұрын

    ሻለቃ ባሻ አሊ በርኪ ሌላው አብቹ ነው ! ጀግኖቻንን አናክብር !

  • @samuelkassa192
    @samuelkassa1925 жыл бұрын

    God bless you and your family Alliy Brikee. Thank you so much!!!

  • @lidacall4552
    @lidacall45525 жыл бұрын

    ጀግና ሀገር ወዳድ ብርቅዬ የኢትዮጵያ ልጅ እረጅም እድሜ እና ጤና ይስጥልን❤

  • @achamyelehabebe879
    @achamyelehabebe8795 жыл бұрын

    አይ አንቺ ሀገር የሞተልሽ ቀርቶ የገደለሽ በላ ጋዜጠኛው ተባረክ

  • @user-qb6kz5xw4e
    @user-qb6kz5xw4e5 жыл бұрын

    የኢትዮጵያ ምርጥ ጀግና !! የወያኔ ስራ በየቦታው የኢትዮጵያ ምርጥ ጀግኖችን ሳሰቃይ ሲበድል ነው የከረመው! ጀግና መቼም አይሞትም ስሙ!

  • @yeshifananegash2793
    @yeshifananegash27935 жыл бұрын

    ጀግናው አሊ በርኬ በጣም ደስ ይላል በሕይወት መኖሩ::

  • @biniboss7533
    @biniboss75335 жыл бұрын

    ተባረኩ ይህን ጀግና ስላቀረባቹሁልን እናመሰግናለን አሊ በርኬ ውለታህ አለብን

  • @haileworku6507
    @haileworku65075 жыл бұрын

    ድሮም ጀግና አገሩና ህዝቡን ይወዳል ፣ጤናና እድሜ ተመኘሁልህ፣

  • @eskinderteshome9681
    @eskinderteshome96815 жыл бұрын

    How can we pay you for your service

  • @aregagashaw836
    @aregagashaw8365 жыл бұрын

    ኢትዮጵያየ አለሽ እኮ ጀግና ጀግናው አሊ በርጌ እድሜና ጤና ተመኘሁ ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር

  • @sabatiruneh5280
    @sabatiruneh52805 жыл бұрын

    እንዲያው ወያኔ ምን ቢቀምሳቸው እንዴት አድርገው ቢጠመዞቸው ነው ወጣቱን የኦሮሞ ትውልድ ከኢትዮጲያ ጋር ያጣሉት እንደነኝህ አይነት የኦሮሞ ጀግና ለኢትዮጵያ ያላቸውን ፍቅር ስናይ ይገርማል

  • @amourgagnetoujours

    @amourgagnetoujours

    5 жыл бұрын

    Saba Tiruneh hulum banda alew eko. Bandawochu oromowochem eko gebtew haymanot qeyerew ke Somale gar liweru eza neberu. Enesunem techawetubachew camp ketew zegubachewenji.

  • @user-fe4pw1ww7m
    @user-fe4pw1ww7m5 жыл бұрын

    የጋዜጤኛውም የአርበኛውም አማርኛ ደስ ይላል።ኢትዮጵያዊነት ደግሞ ይበልጥ ደስ ይላል።

  • @truthmes5360
    @truthmes53605 жыл бұрын

    አንዳፍታዎች እባካችሁ ይህንን ጀግና ሰው አገናኙኝ። ለእኔ ሰላም ለእኔ ህልውና እኔ ትምህርቴን በሰላም እንድማር ሳያውቀኝ የተዋጋልኝን ህይወቱን ያጋፈጠልኝን ጀግና ሰው ወሮታ ላድርግለት። ከጎኑ እንደሆንኩ የአቅሜን ላበርክትለት። አድራሻዬ። mesfinkassa@yahoo.com ነው። ስልካቸውን ብትልኩልኝ ምስጋናዬ የላቀ ነው።

  • @Andafta

    @Andafta

    5 жыл бұрын

    የተከበራችሁ ተመልካቾቻችን ሻለቃ ዓሊ በርኬ ለአገራችን ያበረከቱትን ውለታ አስባችሁ አሁን የሚገኙበትን ወቅታዊ የኑሮ ሁኔታ ተመልክታችሁ የአቅማችሁን ድጋፍ ልታደርጉላቸው እንደምትፈልጉ ገልጻችሁልናል። ለዚህ ኢትዮጵያዊ ክብር ወዳድነታችሁ ያለንን አክብሮት እየገለጽን አድራሻችሁን በገጻችን facebook.com/andafta ብታስቀምጡልን ከሻለቃ ዓሊ በርኬ ጋር ልናገናኛችሁ እንደምንችል እናሳውቃለን። እናመሰግናለን!!

  • @selamawitghebre6143
    @selamawitghebre61435 жыл бұрын

    የቀድሞው ሰራዊት ጀግኖች ናቸው ለእናት አገራችን ዋጋ የከፈሉ አሊ በርኬ በጣም እንወዶታለን አሁንም እናንተን የመሳሰሉ ኢትዮጵያን አድኑ ህዝቡን ቀስቅሱ😍💕💞

  • @sabatiruneh5280
    @sabatiruneh52805 жыл бұрын

    በእውነት ዶክተር ዓብይ የኢዩያዊነትስሚት እንዲመጣ ከፍለጉ እንደነኝህ አይነቶች በመቶሽወች የሚቆጠሩ የቀድሞወ ስራዊት አሉ እነሱን ማስገባት አለበት

  • @binyamm8209

    @binyamm8209

    5 жыл бұрын

    ጀግናቻችንን የማናከብር ጉዶች ተንከባክበን ልኒዛቸው የሚገባን እንቁ የሆኑ ጀግና ነሆት

  • @ahmedjemal6362
    @ahmedjemal63625 жыл бұрын

    Thank you for your service for mama Ethiopian!. 👏👏👏

  • @bisratasrat5694
    @bisratasrat56945 жыл бұрын

    በጣም ልጆች ሆነን ስለእኚህ ጀግና ሲወራ በጣም እሰማ ነበር። እንኳን በህይወት ኖሩልን።ህዝብና መንግስት ተባብሮ በቀሪው ዘመናቸው እንኳ ደስተኛ ሆነው እንዲያሳልፉ እንደረግ ቢሆን ለህሊናችንም ጥሩ ነበር።

  • @user-zs4yr3mj2j
    @user-zs4yr3mj2j5 жыл бұрын

    ዋወ ጅግና አባት ኑት እግዚአብሔር እድሜ ከጤናጋር ይስጡት ቱሉ ብላችሁ ቁጥር ሁለትን ልቀቁልን!!

  • @gedionmelese1081
    @gedionmelese10815 жыл бұрын

    ጀግና!!!💚💛❤

  • @abduebrahim4909
    @abduebrahim49095 жыл бұрын

    እውነት እላችሁለሁ ዛሬ ላስደመጣቺሁኝ ዝግጅታችሁ ከፍ ያለ ምስጋና ይድረሳችሁ፡፡ ከዚህ ቀደም የደራው ጫወታ በሚል ፕሮግራም ስለ ሻለቃ አሊ በርኬ ታላቅ ጀግነት ሰምቼ ተከታታይ ሁለት ክፍል ፕሮግራም በጣም ተመስጨ ነበር፡፡ ስለ ሻለቃ አሊ በርኬ በናንተ ፕሮግራም ፎቶቸውን ሳይ ደግሞ ድርብ ደስታ ተሰማኝ፡፡ እንህን ጀግና እድሜ ይስጥልን፡፡

  • @Huda19998
    @Huda199985 жыл бұрын

    Mashallah May Allah give you long life.

  • @ephihara6345
    @ephihara63455 жыл бұрын

    ክብር ለአባቶቻችን ይሁን::

  • @endalksisay6918
    @endalksisay69185 жыл бұрын

    ሻለቃ ዓሊ በርኬ ስለ አገልግሎትህ እናመሰግናለን። የጀግና ስም ዘላለም ይነግሳል።

  • @zelalemabebe3375
    @zelalemabebe33755 жыл бұрын

    Mr Ali Berke you are our Hero. Thank you. Geletoma

  • @berrez4985
    @berrez49853 жыл бұрын

    Ali Berki, you are a good lesson for most people who don't bother for their mother land but only their stomach.

  • @yenazretlij3321
    @yenazretlij33215 жыл бұрын

    Thanks you for your service

  • @rayarayuma658
    @rayarayuma6585 жыл бұрын

    የአላህ እድ ያሉትን ጀግኖቻችን አላህያብዛልን

  • @gebrehannabalcha2331
    @gebrehannabalcha23315 жыл бұрын

    እግዚአብሔር ይባርክ እኔም ለሀገሬ ደምቼ ቆስያለሁ ምንም ያደርጋል አሁንም ሀገሬ !

  • @azizaomar2001

    @azizaomar2001

    5 жыл бұрын

    እድሜጤናተመኘሁለወት

  • @user-mf7zh9zj9b
    @user-mf7zh9zj9b4 жыл бұрын

    አሊ በርኬ የዳዊት ልጅ የይሁዳ ልጅ የጌድዮን ልጅ እግዚአብሔር ይባርክህ ይጠብቅህ ጠላቶችህን ከእግርህ በታች አምላክ ይጣልልህ።አሜን።

  • @yomamo7781
    @yomamo77813 жыл бұрын

    የጀግና የጀግና

  • @asfawgetachew713
    @asfawgetachew7134 жыл бұрын

    Thanks to Andafta midea you interview our hero Ali Berke . I appreciate Ali berk for his committed love to his country Ethiopia and aknolagdement to President Mengistu Hailmariam / Menge .

  • @nimonanuti8569
    @nimonanuti85695 жыл бұрын

    Wow thanks andafta i know this respected man in Nekemte City during dergue regim ...he was a respected man .

  • @temesgentsegaye2048
    @temesgentsegaye20485 жыл бұрын

    ምንአለበት:ለዚህ:ጀግና:በጎፈንድሚ:ወይ:በሆነ:መንገድ:ትንሽ፣ትንሽ፣አዋጥተን:ብንረዳው?አይ:ኢትዮጵያ:የሞተልሽን:የማትጠቅሚ:አገር፣የስንት:ጀግኖች:ግፍ:በላያችን:አለ?

  • @negashdesta7200

    @negashdesta7200

    5 жыл бұрын

    ያሰብኩትን ነው የፃፍከው! አመሰግንሀለሁ ተመስገን

  • @ibrahimjemal9185

    @ibrahimjemal9185

    5 жыл бұрын

    Thankyou brother good ieda place start we supprt this guy

  • @abedi76
    @abedi763 жыл бұрын

    እድለኛ ነህ በሄወት መኖርህ ጀግና ነህ

  • @selinaandu2585
    @selinaandu25854 жыл бұрын

    ውድ ኢትዮጵያዊ።

  • @esayasbelay2451
    @esayasbelay24515 жыл бұрын

    Ale berka yanten history i heard from my daddy ur my 1 hero 🇪🇹

  • @mollahoresa9435
    @mollahoresa94354 жыл бұрын

    Ali i can't stop lesson your interesting interview I tell you this you are our national hero of all time against backward Somalia invaders. Thanks for your great sacrifice and service🙏🙏🙏💚💛❤.

  • @user-db5ib6zd8z
    @user-db5ib6zd8z4 жыл бұрын

    እግዚአብሔር ይባርኮዎት መልካም ሰው አይጥፋ የማንም ልቅምቅም የሰው ልክ አያቅም አሉ እስኪ ይንገራዋቸው ኢትዮጵያን ብትንትን እናረጋታለን ለሚሉውት የአስተሳሰብ ጭቃዎች 💚💛❤️👏👏👏

  • @gtgt842
    @gtgt8425 жыл бұрын

    ኣይ ኢትዮጵያ አንዲህ ኣይነት ጀግና መደገፍና መሽለም ሲገባው አስር ቤት

  • @sabatiruneh5280
    @sabatiruneh52805 жыл бұрын

    አሁን ምናለበት የሁኖቹ ቄሮወች ከነኝህ ጀግኖች ቢማሩ

  • @semiem8141
    @semiem81415 жыл бұрын

    Thanks Ali Berkie I love you so much

  • @mesfinkebedegonfa580
    @mesfinkebedegonfa5805 жыл бұрын

    We have to organize go fund me program for this wonderful person. My Ethiopians God let you long live

  • @Ethiopiahagere7057
    @Ethiopiahagere70575 жыл бұрын

    እንዲህ አይነት ሰዎችን ሳይ ልቤ ሀሴት ታደርጋለች miss part 2 please!!

  • @user-wv8vz1fl5s
    @user-wv8vz1fl5s Жыл бұрын

    ማርያምን እውነተኛ ኢትዮጵያዊ ሰው ጀግንነት እውነትነቱ ጀግናው እሳቱ አሊ በርኪ አይ አንቺ ኢትዮጵያ የጀግና እናት።

  • @peaceandlove6678
    @peaceandlove66785 жыл бұрын

    እባካችሁ አቅም የፈቀደ ለመርዳት ስልካቸውን አድራሻቸውን ልቀቁልን ይጀግና ዛሬም ወኔው አለ አይዛህ ልንለው ከጎኑ ልንቆም ይገባል

  • @Josefe4950
    @Josefe49505 жыл бұрын

    ምርጥ የሀገራችን የቁርጥ ቀን ልጅ

  • @ethiomalcomx7416
    @ethiomalcomx74165 жыл бұрын

    ስንት ጀግኖች ወድቀው ቀርተዋል We Love You Ali Berke

  • @tujubaethiopia5464
    @tujubaethiopia54645 жыл бұрын

    የዚህን ጀግና ታሪክ ሸገር ላይ አምና ሲተረክ በጣም ገርሞኝ ነበር፡፡ አሁንም እንዳዲስ እያዳመጥኩ ነዉ፡፡ አርበኞችን እያሰብኩ ዉስጤ ደማ!

  • @yeduteshome2748
    @yeduteshome27485 жыл бұрын

    በጣም ጀግናኖት ክብር ይገባዎታል አባቴ

  • @manhope5961
    @manhope59615 жыл бұрын

    እናት ሀገር ኢትዮጵያ ያላንቺ ማን አለኝ.....!!!!??? የነኩሽ የደፈሩሽ የሞከሩሽ ይመስክሩ። አሁን ግን በልጃችሽ በአብራክሽ ክፋይ በፅንፈኞች በጎጠኞች እየተደፈርሽ ነው ያሳዝናል። ሞት ለዘረኞች ና ለፅንፈኞች...🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹ረዥም እድሜ ለምየ ኢትዮጵያ 🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

  • @asterassefa7005
    @asterassefa70055 жыл бұрын

    JEGNAW SHALEKA ALI BERKI you make me cry you are our HERO . .take my love from Gonder.✌✌✌✌✌✌✌✌✌✌✌

  • @user-hv1sk2zx6u
    @user-hv1sk2zx6u5 жыл бұрын

    ኢትዬዸያ ሲል ብልጭ አለብኝ ሲሉ ሰውነቴን ወረረኝ አንቺ እናት አገሬ ደማችን ውስጥ ነሽ ያለሽው። ሰላምሽ ይብዛ!! አባታችን ሰላሞት ይብዛ!!

  • @selamleethiopia5675
    @selamleethiopia56754 жыл бұрын

    I love this Hero wow I can’t stop watch this great hero wow he is so open and very clean person

  • @awekesidlel2176
    @awekesidlel21765 жыл бұрын

    ኧረ በናትህ አንተ ጋዜጠኛ የዚህን ጀግና ስልክ ቍጥር ጻፍልን።

  • @kingaklilu9665
    @kingaklilu96655 жыл бұрын

    በታሪክ ብቻ የማውቆት የኢትዮጵያ ጀግና አቶ አሊ በርኬ ረጅም ዕድሜና ጤና ይስጥዎት

  • @berisharjo7903
    @berisharjo79035 жыл бұрын

    I LIKE YOU MORE THAN I CAN SAY. SUCH A NATURAL WARRIOR!!

  • @rahelaz1917
    @rahelaz19175 жыл бұрын

    ጀግና ሰዉ አሁን እኛም ሀገር እኖዳለን እንላለን

  • @Et-cb7gx
    @Et-cb7gx3 жыл бұрын

    ምርጥ ጀግና ኢትዮጵያዊ!!!❤

  • @tadeledadie2698
    @tadeledadie26983 жыл бұрын

    THE MOST IMPRESSIVE, HONEST AND BRAVE MAN THIS HERO IS!!!

  • @abrahamt2356
    @abrahamt23565 жыл бұрын

    እባካችሁ የሚቀጥለወን ክፍል በፍጥነት ላኩልን

  • @ayanabushan9814

    @ayanabushan9814

    5 жыл бұрын

    please come with the 2nd part

  • @TsegayeRegassa-cc4if
    @TsegayeRegassa-cc4if5 ай бұрын

    ጀግና

  • @yesokay3047
    @yesokay30475 жыл бұрын

    yes.this is my father History 2 ,, Thank you,Ye 1000 saw Alke Ali Berkey , for the survice for your Home land Ethioopia!! we ethiopia will never forget !!! Ethiopia Tekdem!!!!

  • @queencrown1674
    @queencrown16745 жыл бұрын

    Let's do gofundme for him

  • @ibrahimjemal9185

    @ibrahimjemal9185

    5 жыл бұрын

    Thankyou this is good idea

  • @amourgagnetoujours

    @amourgagnetoujours

    5 жыл бұрын

    good idea

  • @abrahamt2356

    @abrahamt2356

    5 жыл бұрын

    I think It is much better if Tamagin beyene Advocate him

  • @ermiasbeyene1559
    @ermiasbeyene15595 жыл бұрын

    ኢትዮጵያ ሀገሬ ሞኝነሽ ተላላ የሞተልሽ ቀርቶ የገደለሽ በላ የኢትዮጵያ ጀግኖች የትም ወድቀው የባንዳ ልጆች የነገሱበት ዘመን ያሳዝናል

  • @gebrehannabalcha2331
    @gebrehannabalcha23315 жыл бұрын

    ጋዜጠኛ ይርጋ አበበ በጣም እወድሃለሁ

  • @dichagena3726
    @dichagena37265 жыл бұрын

    አሊ በርኬ የኢትዬጵያዊነት ፅኑ ተምሳሌት ነው።እስኪ እያንዳንዱ ሀገሩን የሚወድ ኢትዮጵያዊ ሁሉ ያለንን አሰባስበን እናንግሰው።የእሱ አይነት ሰው ማግኘት ይከብዳል።ሀገሩ የሽለመችው ኒሻን የሚያስገኝለትን ጥቅም ጥቅም ያገኝ ዘንድ የምንችለውን ሁሉ እናድርግ።አሊ በቅን ልብ ሀገሩን የሚወድ ንፁህ ኢትዬጵያዊ ነው።

  • @abrahamt2356
    @abrahamt23565 жыл бұрын

    Really i was eager to see his interview. Thanks to your service. Sir. We love you. Deeply sir. You did a very good job for your country

  • @ethioethio1748
    @ethioethio17485 жыл бұрын

    ጀግና ጀግና ጀግና ሀገሬ ኢትዮጲያ ሞኝ ነሽ ተላላ የሞተለሽ ሳለ…………… ለዚህች ሀገር ብዙ ተከፍሏል ሲባል ተረተረት ለሚመስላቸው ሰዎች ቋሚ ምስክር እረጅም እድሜ ከጤና ጋር ተመኘው ለጀግናችን!! ድሮም ጀግና አያካብድም ቀለል

  • @leya8572
    @leya85725 жыл бұрын

    great man

  • @MikeMike-bc7jg
    @MikeMike-bc7jg5 жыл бұрын

    In the past Ethiopian won every war, because they were one. No ethic division. Unity is power. Thank you sir, Ali Burki.

  • @user-vw9ot7re2z
    @user-vw9ot7re2z5 жыл бұрын

    😍😍😍 ኢትዮጲያ

  • @bogaleabose277
    @bogaleabose2775 жыл бұрын

    When I was child My Father told me about this Hero soldier and I really able see him in my imagination how he was super

  • @gebrehannabalcha2331
    @gebrehannabalcha23315 жыл бұрын

    አቤት እግዞኦ ወገኔን አገኘሁኝ እባካችሁ ይህን ሰው በምንም መንገድ ላግኘው ?

  • @mansoursunusy1421
    @mansoursunusy14215 жыл бұрын

    ፍቅርና ክብር !

  • @wudegudu6430
    @wudegudu64305 жыл бұрын

    he is really hero .the respect he had was not unfogetable at that time.he is john McCain of ethiopia

Келесі