ETHIOPIA ብሄረ ብፁአን - ቅዱስ ዞሲማስ ገዳማዊ

#ETHIOPIA † በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን †
ብሔረ ብጹዐን
† ሚያዝያ 9 ስንክሳር †
+"+ ብጹዐን ጻድቃን +"+
=በዚህ ቀን ብሔረ ብጹዐን ውስጥ የሚኖሩ ጻድቃን ይታሠባሉ::
በሃይማኖት ትምሕርት 5 ዓለማተ መሬት አሉ:: እነሱም አቀማመጣቸው ቢለያይም ከላይ ወደ ታች:-
1.ገነት
2.ብሔረ ሕያዋን
3.ብሔረ ብጹዐን - ብሔረ አዛፍ/እረፍት
4.የእኛዋ ምድር እና
5.ሲዖል ናቸው::
+ከእነዚሕ ዓለማት ባንዱ የሚኖሩ የብሔረ ብጹዐን ጻድቃን:-
*ኃጢአትን የማይሠሩ
*ለ1,000 ዓመታት የሚኖሩ
*ሐዘን የሌለባቸው
*በዘመናቸው 3 ልጆችን ወልደው - 2 ወንድና አንድ ሴት - 2ቱ ለጋብቻ: አንዱን ለቤተ እግዚአብሔር አግልግሎት የሚያውሉ ሰዎች ናቸው::
+ቅዱሳኑ ወደዚሕ ቦታ የገቡት በነቢዩ ኤርምያስ እና በቅዱስ እዝራ ዘመን ሲሆን አንዴ የተወሰኑት በዘመነ ሰማዕታት ወጥተው በዚሕ ቀን ተሰይፈዋል::
+በመጨረሻ ግን በሐሳዌ መሲሕ ዘመን ወጥተው ሰማዕትነትን ይቀበላሉ::
=የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ምሕረቱና ይቅርታው ለምናምን ሁሉ ይደረግልን:: ከደግነታቸውም በረከትን አይንሳን::
† ቅዱስ ዘሲማስ ገዳማዊ †
በዚች ቀን የከበረ ቀሲስ ዘሲማስ አረፈ። ይህም ፃድቅ ከፍልስጥኤም ሰዎች ወገን ነው። ወላጆቹም ደጋጎች ክርስቲያኖች ናቸው ይህንን ፃድቅ በወለዱት ጊዜ አምስት አመት አሳደጉት። ከዚያም የቤተክርስቲያን ትምህርትን የሀይማኖትንም ምስጢር ህግና ስርአትንም እያስተማረ እንዲያሳድገው ለአንድ ሽማግሌ መምህር ሰጡት።
ያ ሽማግሌም ተቀበሎ ልጁ አደረገው ትምህርቱንም ሁሉ አምላካዊ ጥበብ ሀይማኖትንም አስተምሮ አመነኰሰው ዲቁናም አሾመው በበጎ ስራም አደገ ትሩፋት መስራትንም አበዛ እግዚአብሄርንም ሁልጊዜ ያመሰግነዋል በቀንና በሌሊትም መፃህፍትን ያነባል።
ስራ ሲሰራ ሲበላም ቢሆን ሁል ጊዜ ከአፉ ምስጋናዎችን አያቋርጥም።በዚያ ገዳም አርባ አምስት አመት በተፈፀመለት ጊዜ ቅስና ተሾመ ተጋድሎውንም ጨመረ።
ከዚህ በኃላም እየተጋደለና አገልግሎት በመጨመር በቅስና ሹመት አስራ ሶስት አመት ሲሆነው በዘመኑ ካሉ ተጋዳዮች ሁሉ እርሱ በገድሉ ከፍ ከፍ እንዳለ ተቃራኒ ጠላት ዲያብሎስ በልቡ ክፉ ሀሳብ አሳደረበት በልቡም ከበጎ ስራ እኔ ያልሰራሁት የቀረኝ አለን ይል ጀመር።
ነገር ግን የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አልተወውም መልአኩን ልኮ በዮርዳኖስ ወንዝ አቅራቢያ ወደ አለ ገዳም ይሄድ ዘንድ እንጂ። ያን ጊዜም ተነስቶ ሄዶ ወደዚያ ገዳም ደረሰ በገድላቸው ፍፁማን የሆኑ እውነተኞች አገራውያንን አገኘ እርሱ ከእርሳቸው እንደሚያንስ አወቀ እርሱ በአለም ውስጥ ነው የኖረውና ስለዚህ ከእርሱ ይሻላሉ።
በዚያ ገዳም ከሳቸው ጋር ኖረ ብዙ ዘመናትም አብሮአቸው ሲጋደል ኖረ። ለዚያ ገዳም መነኰሳትም ልማድ አላቸው ታላቁ ፆም በደረሰ ጊዜ የመጀመሪያውን አንድ ሱባኤ በአንድነት ይፆማሉ በቅድስት እሑድ ስጋውንና ደሙን ይቀበላሉ በማግስቱም ሰኞ ጥዋት ሀያ ስድስተኛ መዝሙር እግዚአብሄር ብርሀነ ረድኤቱን ሰጥቶ ያድነኛል የሚያስፈራኝ ምንድነው የሚለውን እሰከ መጨረሻው እየዘመሩ ይወጣሉ በሚወጡም ጊዜ ወደ በሩ ተሰብስበው በአንድነት ፀልየው እርስ በርሳቸው ሰላምታ ይሰጣጣሉ የገደሙ አበ ምኔትም ይባርካቸዋል።
ከዚህም በኃላ እየአንዳንዱ ወደ በረሀ ይበተናሉ አንዱም አንዱ ባልንጀራውን ያየ እንደሆነ እንዳያየው ወደ ሌላ ቦታ ይሄዳል። ቅዱስ ዘሲማስም በየአመቱ ከሳቸው ጋራ ወጥቶ በበረሀው ውስጥ ይዘዋወራል የሚፅናናበትንም ይገልጥለት ዘንድ እግዚአብሄርን ይለምነው ነበር።
ሲዘዋወርም በበረሀ የምትኖር ግብፃዊት ማርያምን አገኘ ከእርሷም በልጅነቷ ወራት በእርሷ ላይ እንዴት እንደሆነና በበረሀም የሆነውን ኑሮዋን ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ ተረዳ።
ከዚህ በኃላም በሁለተኛው አመት ስጋውንና ደሙን ያመጣላት ዘንድ ፈለገች እንዳለችውም አደረገላት። ለዚህም ፃድቅ ብሄረ ብፁአን ይገባ ዘንድ ተገባው እርሱም ገድላቸውን ፃፈ ስራቸውንና ፅድቃቸውን ገለጠ። ዘጠና ሶስት የሚሆን መላ እድሜው በተፈፀመለት ጊዜ በሰላም አረፈ።
† አባ ስንትዩ †
በዚችም ቀን በእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት በአባ ስንትዩ እጅ ታላቅ ምልክት ታየ።ይኸውም የከበረች የጌታን ፆም ከመነኰሳት ጋራ ይፆም ዘንድ ወደ አስቄጥስ ወደ አባ መቃርስ ገዳም ወጣ ።
ሰሙነ ህማማትም በሆነ ጊዜ ገዳማቱንና አድባራቱን ሊዘርፉና ሊማርኩ የአረብ እስላሞች ተሰበሰቡ። በቤተ ክርስቲያኒቱ በስተምስራቅ ሰዎችንም ይገድሉ ዘንድ ሰይፎቻቸውን መዝዘው በእጆቻቸውም ይዘው በአለት ላይ ቆሙ።
ኤጲስቆጶሳትና መነኰሳትም ወደ አባ ስንትዩ ተሰብስበው ከአረብ እስላሞች እንዴት እንደሆነ ነግረው ከዚያ ገለል እንዲል ለመኑት። የከበረ አባ ስንትዩም ጌታችን የደቀ መዛሙርቱን እግራቸውን አጥቦ አዲስ ስርአት የሰራበት የፋሲካ ፍስህ በአል ሳይፈፀም እኔ ከዚህ አልለይም አላቸው።
እነዚህ እስላሞችም እየደነፉ ጩኸታቸው ተጨመረ። አባ ስንትዩም የወገኖቹን ድንጋፄ በአየ ጊዜ በላዩ የመስቀል ምልክት ያለበት በትሩን ይዞ ከእግዚአብሄር ወገኖች ጋራ ብሞት ይሻለኛል እያለ ወደ እነርሱ ሊወጣ ተነሳ ።
ኤጲስቆጶሳቱም እንዳይወጣ ያዙት። እርሱ ግን ልባቸውን በማፅናናት አረጋጋቸውና ወደ አረብ እስላሞች ወጣ። እስላሞችም መስቀል ያለበትን በትር በእጁ ይዞ በአዩት ጊዜ ብዙ ሰራዊት እንዳሳደዳቸው ሆነው ወደ ኃላቸው ተመልሰው ሸሹ። ከዚያችም እለት ወዲህ ወደ ቅዱሳት መካናት እስላሞች አልተመለሱም።
=ሚያዝያ 9 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱሳን የብሔረ ብጹዐን ጻድቃን
2.አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ ጻድቅ - ኢትዮዽያዊ
3.ቅዱስ ዞሲማስ ገዳማዊ - ብሔረ ብጹዐንን ያየ እና ዜናቸውን የጻፈ አባት
4.ቅዱስ ኤስድሮስ ሕጻን ሰማዕት - ገና በ10 ወር ዕድሜው ሰማዕት የሆነ
5.አባ ሱንቱዩ ሊቀ ዻዻሳት
=ወርሐዊ በዓላት
1.አባ በርሱማ ሶርያዊ - ለሶርያ መነኮሳት ኁሉ አባት
2."318ቱ" ቅዱሳን ሊቃውንት - ርቱዐነ ሃይማኖት ዘኒቅያ
3.አባ መልከ ጼዴቅ ዘሚዳ - ኢትዮዽያዊ
=+"+ ስለዚህ የልቡናችሁን ወገብ ታጥቃችሁና በመጠን ኑራችሁ: ኢየሱስ ክርስቶስ ሲገለጥ የምታገኙትን ጸጋ ፈጽማችሁ ተስፋ አድርጉ:: እንደሚታዘዙ ልጆች ባለ ማወቃችሁ አስቀድሞ የኖራችሁበትን ምኞት አትከተሉ:: ዳሩ ግን 'እኔ ቅዱስ ነኝና ቅዱሳን ሁኑ' ተብሎ ስለ ተጻፈ የጠራችሁ ቅዱስ እንደ ሆነ እናንተ ደግሞ በኑሯችሁ ሁሉ ቅዱሳን ሁኑ:: +"+ 1ዼጥ. 1:13
ወስብሀት ለእግዚአብሄር
ወለወላዲቱ ድንግል

Пікірлер: 37

  • @kiflubeyenegebremariam3792
    @kiflubeyenegebremariam37924 жыл бұрын

    ከአምስቱ ብሄረ አለማት አንዱ የሆነውን ብሔረ ብፁሃንን በአይነ ህሊና ስላስጎበኛችሁን እናመስግናችዋለን የሰው ልጆች ሁሉ እኩል ይሆናሉ የሚለው አስተሳሰብ ብቅ ያለው ከዚህ ትረካ ተነስቶ ይሆን የማርክስ ፍልስፍና በኋላም የኮሚኒዝም ፅንሰ ሐሳብ የፈለቀው ይህን መፀሐፍ አንብበው ይመስላል ደንቅ መንፈሳዊ ዓለም ነው በተለይ ስርአት ያለው አለም ባዮሎጂካል ሂድትን ተከተሎ የሚከሰተው የስውልጅ የአኗኗር ሁኔታ ገራሚና አስጎምጂ ነው በውነት ሰባ አለም በዚህ ያኗኗ ር ይኖር ይሆን ገራሚ ነው ገራሚ ስርሃት ነው ፀሎትና በረከታቸው ይደርብን ላንቺም ለተራኪዋ ቃለ ሕይወት ያሰማልን ድነቅ ገድል አንተን ነገድህን ወገኖችህን ያድናቸው ብሎ መላኩ እነደባረከው እኛንም ኢትዮጵያንን ወገኖቻችንን ሐይማኖታችንን እግዚሃብሔር ይባርከን አሜን

  • @addisetube
    @addisetube6 ай бұрын

    እግዚአብር ይመስገን ቃለሒወት ያሰማል ያባትቻች በረከት ይደረብን አሜን አሜን አሜን🙏🙏🙏

  • @senayamelake7483
    @senayamelake74834 жыл бұрын

    ቃል ሕይወትን ያሰማልን ተስፋ መንግሰተ ሰማያትን ያውርስል። አሜን

  • @getanehwodajo7511
    @getanehwodajo75114 жыл бұрын

    እግዚአብሔር አብዝቶ ይባርካችሁ

  • @user-wt5gh5ub2l
    @user-wt5gh5ub2lАй бұрын

    ቃለሂወት ያሰማልን

  • @wudetesfa8583
    @wudetesfa85834 жыл бұрын

    Egzabher yimsgen slam lhulachew yihuen

  • @turmi7408
    @turmi74084 жыл бұрын

    ስላካፈላችሁን እናመሰግናለን

  • @user-us9zg7nz5r
    @user-us9zg7nz5r2 жыл бұрын

    አቤቱ ንፁ ልብን ፍጠርልኝ 🙏

  • @poop6034
    @poop6034 Жыл бұрын

    ቃለ ህይወት ያሰማልን ፀጋዉን ያብዛልሽ እህቴ ደስ የሚል ምንባብ ስርአት የተሞላበትም አነባበብ ኡፉፉፉፉ ደስስስስ ሲል የቅዱሳን ፀሎታቸዉ አይለየን😍😍😘😘😘😘

  • @user-jd2mc7kp2x
    @user-jd2mc7kp2x4 жыл бұрын

    እህቴ እናመሰግናለን።

  • @abebechdemse5884
    @abebechdemse5884 Жыл бұрын

    ቃለ ሂወት ያሰማልን

  • @gattusojgtpw1899
    @gattusojgtpw18992 жыл бұрын

    ቃለህይወትያሰማልን

  • @esayasabebe6085
    @esayasabebe60852 жыл бұрын

    በጣም ጥሩ ትምህርት ነው

  • @fisehafisho
    @fisehafisho4 жыл бұрын

    እሙዬ! ...ፍፁም ከልቤ ነው ምልሽ...እግዚአብሔር ህይወትሽን ይባርክ ፣ የተመኘሽውን ይስጥሽ ፣ ሃሴት እንዲሰማን ያደረገ ንባብ እንዳነበብሽልን ፣ ላንቺም ሰማያዊ ሃሴትን ያሰማሽ...በቃ! እመቤቴ ትጠብቅሽ ... 'subscribe' ከማድረግ ውጪ ሌላ የሚደረግ ነገር ኖሮ ፣ ለዚህ ' channel ' ባደርግ ደስ ባለኝ ነበር !!!

  • @lydiaseifu6688

    @lydiaseifu6688

    4 жыл бұрын

    እውነት ነው፡፡

  • @terumenfes5553

    @terumenfes5553

    3 жыл бұрын

    @@lydiaseifu6688 @'ll

  • @giontube5332
    @giontube53324 жыл бұрын

    እባክሽ ተመሳሳይ ቪዲዮ ስሪልን እናመሰግናለን

  • @mekdesgufar8387
    @mekdesgufar8387 Жыл бұрын

    Kal hiwet yasemaln ehetachen bezaw degmo sel beher bezuhan betenegrin

  • @bereketfesseha3559
    @bereketfesseha35593 жыл бұрын

    እህታችን ቃለህይወት ያሰማልን መልካም ጥሩ ትምህርት ነዉ።

  • @eheteabebe9059
    @eheteabebe90594 жыл бұрын

    ቃለህይወት ያሰማልን ፀጋ መንገሰተ ሰማያትን ያውርስልን።

  • @kudustesfay2652
    @kudustesfay26524 жыл бұрын

    ኣሜን ኣሜን ኣሜን ቃለ ሂወት ያሰማልን ጸጋው ያብዛላቹ እመብርሃን ኣትለያቹ የኣባቶቻችን በረከት ረድኤት ያካፍተለን የእግዚኣብሔር ሰላም ከሁላችን ጋ ይሁን ኣሜን

  • @user-us9zg7nz5r
    @user-us9zg7nz5r2 жыл бұрын

    ቃለህይወት ያሰማልን ፀጋውን ያብዛልሽ እህት የአባ ዞሲማስ በረከት ይድረሰን

  • @tklekachaw9957
    @tklekachaw9957 Жыл бұрын

    Betam Teru Nawo

  • @kumarkumarkumar1718
    @kumarkumarkumar17183 жыл бұрын

    እህቴ ቃላ ህይወት ያሰማልን ደከማ ጎናችንን እሱ ያበርታልን ማንገዱን ይምራን አሜን(3)

  • @ghkvkhvhdu5774
    @ghkvkhvhdu57744 жыл бұрын

    አሜን ቃል ህይወት ያስማልን እህታችን ፀጋውን ያብዛልሺ

  • @zewdekebede9145
    @zewdekebede91453 жыл бұрын

    AMILAK hoy sile bihere Bitsuan lijochik bilek maren Le programu Aqirabiwochum Qale Hiwot Yasemalin.

  • @geeztube7Tube
    @geeztube7Tube4 жыл бұрын

    የሰው ልጅ የሚኖረው ምድር ላይ ፣ ብሔረ ብጹዐን እና ብሔረ ህያዋን ላይ ነው፡፡

  • @kisisebsibe9408

    @kisisebsibe9408

    Жыл бұрын

    በሲኦልም በገነትም በነፍስ ይኖር የለ ወዳጄ።

  • @danielhagos5513
    @danielhagos55134 жыл бұрын

    Amen Amen Amen

  • @senaitmulugeta9356
    @senaitmulugeta93564 жыл бұрын

    እግዚአብሔር ይስጥልን

  • @shewayedebessa9642
    @shewayedebessa96424 жыл бұрын

    አሜን አሜን

  • @raheladdis7820
    @raheladdis78204 жыл бұрын

    ❤️❤️❤️😇➕➕➕

  • @tizitaadmasu7067
    @tizitaadmasu70674 жыл бұрын

    አሜን

  • @aisamanin3279
    @aisamanin327911 ай бұрын

    ከየትኛው መፅሀፍ የተወሰደ ነው

  • @user-jt9zr2hs4e
    @user-jt9zr2hs4e4 жыл бұрын

    Des endasegnachugn des yebelachu

  • @redeityilma6635
    @redeityilma66353 жыл бұрын

    Egzabeare _estachu

  • @seritu9867
    @seritu98674 жыл бұрын

    አሜን ቃለህይወት ያሰማልን

Келесі