5ኛ ወይ ፈተና ገጠመኝ ፦ ሙስሊሙ ወደኛ መጥቶ እንዳይድን እኛው ፈተና ስንሆንበት ይገርማል

Пікірлер: 384

  • @hanimadona2884
    @hanimadona28842 жыл бұрын

    የሚገርመዉ እኛ ጋ ያለዉ ዑራኤል ቤተክርስቲያን አጥር ጎን የሚኖሩ ሙስሊሞች ልጃቸዉ መናገር አይችልም ነበር እና እሁድ ቀን ሲጫወቱ ጠዋት ላይ የሰምበት ቂጣ ሲሰጥ ያዩ እና ሊቀበሉ ይሄዳሉ ልጆች እና ሙስሊሙ ልጂም አብሮ ሄዶ ይቀበላል ከዛን ቁጪ ብሎ ይበላል በልቶ ሲጨርስ አንደበቱ ተከፍቶ ማዉራት ጀመረ ቅዱስ ዑራኤል ያደረገዉ ታምር ይህ ነዉ

  • @-beteorthodoxchannel3244

    @-beteorthodoxchannel3244

    2 жыл бұрын

    በስመአም ደስ ሲል እኔም በ3 ወር ገና እንደተወለድኩ ጉበት በሽታ ይዞኝ መድሀኒት የለውም በዛ ሰአት ለ3ወር ህፃን ስለዚ ትሞታለች ተብሎ እየጠበቁ እናቴ ዑራኤል ቤተክርስቲያን ቁጭ ብላ አልቅሳ ወደ ቤት መጣች ልብሷን ስትቀይር አፈር ነገር ረገፈ ከነጠላዋ ዛፍ ተደግፋ እያለቀሰች ነበር ዑራኤል የለመነችው ከዛን ተገርማ እራሱ ነጠላዬ ተደግፎ ከመጣማ እምነት ነው ያድናል ብላ ከነጠላዋ የረገፈውን እምነት በውሀ በጥብጣ አጠጣችኝ ስንት ወራት የታመምኩት ልጅ ወዲያው ተሻለኝ አይኔ,ጥፍሬ ምናምን ሁሉ ቢጫ ነበር በአንድ ቀን normal ሆንኩ እና ጠባቂ መልአኬ ዑራኤል ያደረገልኝ ተአምር ይሄ ነው ክብር ምስጋና ይግባው🙏🙏🙏🙏

  • @selamkahsay2489

    @selamkahsay2489

    2 жыл бұрын

    እልልልልልልልልልልልልል👏👏👏👏✋

  • @selamkahsay2489

    @selamkahsay2489

    2 жыл бұрын

    እልልልልልልልልልልል👏👏👏👏👏እግዛብሔር ይመሰገን!!!

  • @yordanosmamo6642

    @yordanosmamo6642

    2 жыл бұрын

    @@-beteorthodoxchannel3244 እልልልልልልልልልልልልልልልልል አባቴ ቅዱስ ዑራኤል ክብር ምስጋና ይገባዉ ምልጃዉ አይለየን

  • @yordanosmamo6642

    @yordanosmamo6642

    2 жыл бұрын

    አሜን አሜን አሜን አለ እልል እልል እልል እልል እልል እልል እልል

  • @woldesenbet
    @woldesenbet2 жыл бұрын

    ✝ በስግደት የጸሎትን መንገድ መክፈት ✝ ✝ በስግደት የጠላትን መንገድ መዝጋት ✝ ሰብአ ሰገል ሰማያዊ ኮከባቸውን የብርሃን ምሪት አድርገው ወደ ክርስቶስ መንገድ ድርሰው 'ወድቀው ከሰገዱ' በኋላ፤ ወደ አጥፊው ንጉሥ እንዳይመለሱ ሌላ የእግዚአብሔርን መንገድ አግኘተው ወደ አገራቸው ተመለሱ፡፡ እንዲሁ በአምልኮት ልምምድ ውስጥ ወደ እግዚአብሔር መንገድ በመንፈስ ቅዱስ ምሪት እየተመራን ስንጓዝ፤ የጸሎት ኃይላችን መለኮታዊ አቅም እንዲኖረው፣ የውስጥ እምነታችን እንዲጨምርና ሰማያዊ ጉልበታችን እንዲበረታ የዕለቱን የሰዓት ጸሎት ከመጀመራችን በፊት ቀድመን የቃለ-ኪዳን ጸሎት አድርሰን መስገድ የጸሎታችን መንገድ ይከፈትልን ዘንድ መልካም ያደርግልናል፡፡ እንዲህ ስንል የቃለ-ኪዳን ጸሎት ማድረስ እንችላለን፡፡ "አባት የሆንከን እግዚአብሔር አምላካችን ሆይ፥ ጸሎተ ጊዜያችንን በመስቀለ ብርሃንህ ቀድስልን፡፡ አቤቱ የቸርነትህ ፍቅር በባሕሪያችን፣ በጠባያችን፣ በአሳባችን፣ በእቅዳችን፣ በመሻታችን፣ በምግባራችን ውስጥ ተቀርጾ ይታተም ዘንድ እንለምንሃለን፡፡ ቅዱስ አምላካችን ሆይ፥ የጸሎት ጊዜያችን መንገዱ ላይ ቀኝህን ትሰደድልን ዘንድ፤ መለኮታዊ ምሪትህ አስቀድሞ እያለፈ ይመራን ዘንድ፥ የመንፈስ ቅዱስ ኃይል እየተከተለ ያበረታን ዘንድ በስምህ ስለስምህ እንሰግዳለን" ✝ የጸሎት መንገድ መክፈቻ የአምልኮት ስግደት ✝ ለአብ እሰግዳለሁ ለወልድ እሰግዳለሁ ለመንፈስ ቅዱስ እሰግዳለሁ ምስጋና ይሁን ለአብ ምስጋና ይሁን ለወልድ ምስጋና ይሁን ለመንፈስ ቅዱስ ሃሌሉያ ለአብ ሃሌሉያ ለወልድ ሃሌሉያ ለመንፈስ ቅዱስ በረከቱን ለሰጠን ኃይሉን ላበዛልን በዚህ ሰዓት ላቆመን በቸርነቱ መንገድ ለመራን በዚህ ሰዓት በጸጋው ለጠበቀን በብርሃኑ መንገድ ለመራን ቅዱስ እግዚአብሔር ቅዱስ ኃያል ቅዱስ ሕያው ቅዱስ ኤልሻዳይ ቅዱስ አዶናይ ቅዱስ ያሕዌ ቅዱስ ጸባዖት ቅዱስ ኢየሱስ ቅዱስ ክርስቶስ ቅዱስ አማኑኤል የድንግል ማርያም ልጅ ክብር ምስጋና ይግባው ለዘለዓለሙ አሜን፡፡ እንደዚህ ሰግደን፤ እንደ ሰብአ ሰገል የጸሎት ጉዞአችንን ከመጀመራችን በፊት የነፍስ ኮከባችንን ካበራን በኋላ፤ የዕለቱን ምስጋና፣ የሰዓቱን የምንባብ ጸሎት፣ እና የግል የቃል ጸሎት ከጨረስን በኋላ ደግሞ፤ በመቁጠሪያ ጠላትን ቀጥቅጠን፤ መዝጊያ ስግደት እንሰግዳለን፡፡ ይሄ ስግደት ከመጀመሪያው የጸሎት መክፈቻ ስግደት የሚለየው፤ አንደኛ ያመሰገንነው ምስጋና ላይ፣ የምንባብ ጸሎት ላይ እና የግል መጠይቅ ጸሎታችን ላይ የማሰረገጫ ማኅተም መትቶ በአምልኮት ለማስጸደቅ ሲሆን፤ ሁለተኛው በጸሎት ያቃጠልነውን ጠላት የጥፋት መንገዱን ለመዝጋት፣ ከውስጣችን ተቀምጦ ጠቡን፣ አለመከናወኑን፣ እርግማኑን፣ ግራ ዘመሙን፣ ጤና፥ ሰላምና በረከት ማሳጣቱን እንዳይመራ የክፋት ግብር መንገዱን ለመዝጋት እንድንችል ነው፡፡ በመሆኑም "በሥላሴ ስም፣ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ በድንግል ማርያም ስም፣ በቅዱስ ሚካኤል ስም፣ በቅዱስ ገብርኤል ስም ወዘተ.. በጸሎት የተቃጠልክ አጥፊ መንፈስ እስከ ሠራዊትህ ግንባር ላይ ታስረህ፤ በአብ፥ በወልድ፥ በመንፈስ ቅዱር ኃይለ ሥልጣን አብረህ ስገድ" ብሎ በማዘዝ ግንባርን የጸለይንበት የጸሎት መጽሐፍን እያስነካን የጠላትን መንገድ ለመዝጋትና እንዲዳከም ደግሞ ሁለተኛውን የአምልኮት ስግደት እንሰግዳለን፡፡ ✝ የጠላት መንገድ መዝጊያ የአምልኮት ስግደት ✝ እሰግድ ለአብ እሰግድ ለወልድ እሰግድ ለመንፈስ ቅዱስ እሰግድ ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ 3X ቅዱሰ እግዚአብሔር ኃይል ሁነኝ ቅዱስ ኃያል ሥልጣን ሁነኝ ቅዱስ ሕያው ብርታት ሁነኝ ቅዱስ አዶናይ ጉልበት ሆነኝ ቅዱስ ኤልሻዳይ ግርማ ሁነኝ ቅዱስ ያሕዌ ጽናት ሁነኝ ቅዱስ ጸባዖት ምርኩዝ ሁነኝ ቅዱስ ማስያስ በረከት ሁነኝ ቅዱስ ትስቡጣ ጸጋና ሞገስ ሁነኝ ቅዱስ ኢየሱስ ቅዱስ ክርስቶስ ቅዱስ አማኑኤል አሜን፡፡ ለሚያስደነግጥ መለኮታዊ መብረቅ እሰግዳለሁ ለተንቦገቦገ መለኮታዊ ፍሕም እሰግዳለሁ ለተወርዋሪ መለኮታዊ ቀስት እሰግዳለሁ ለሚያቃጥል መለኮታዊ እሳት እሰግዳለሁ ለሚያበራ መለኮታዊ ፋና እሰግዳለሁ ለአንጸባራቂ መለኮታዊ ፀሐይ እሰግዳለሁ ክቡድ ለሆነ ዕብነ መለኮት እሰግዳለሁ ለሚያንቀጠቅጥ መለኮታዊ ግርማ እሰግዳለሁ ለሚንቦገቦግ መለኮታዊ ነበልባል እሰግዳለሁ ላማረ መለኮታዊ ጋሻ እሰግዳለሁ ለስኩረ ኃይል መለኮታዊ ጦር እሰግዳለሁ ለሚያቃጥል መለኮታዊ ግለት እሰግዳለሁ ለአሸናፊ መለኮታዊ እዘዝ እሰግዳለሁ ለረቀቀ መለኮታዊ ሥልጣን እሰግዳለሁ ለብርሃናዊ መለኮታዊ ጸዳል እሰግዳለሁ ለተሳለ መለኮታዊ ሰይፍ እሰግዳለሁ ለሚያስፈራ መለኮታዊ ቃል እሰግዳለሁ ለአስደናቂ መለኮታዊ ነበልባል እሰግዳለሁ ለሚቆራርጥ መለኮታዊ ገጀሞ እሰግዳለሁ ለንጹሕ መለኮታዊ ባሕርይ እሰግዳለሁ ለጽኑ መለኮታዊ ምሣር እሰግዳለሁ ለምጡቅ መለኮታዊ ተራራ እሰግዳለሁ ለተነጣጠረ መለኮታዊ ቀስት እሰግዳለሁ ለትኩስ መለኮታዊ ሙቀት እሰግዳለሁ ነበልባሉን ላስረዘመ መለኮታዊ እሳት እሰግዳለሁ ለአሸናፊ መለኮታዊ ኃይል እሰግዳለሁ ገዥነት ላለው መለኮታዊ ገናንነት እሰግዳለሁ የአድማስ ስፋት ላለው መለኮታዊ ብርሃን እሰግዳለሁ በእሳት ለተከበበ መለኮታዊ ዙፋን እሰግዳለሁ እውነት በእውነት ለዘላለሙ አሜን፡፡ የጸሎታችን መነሻ መንገድ ላይ የአምልኮት ስግደት በመስገድ ብርሃን አብርተን፤ ጸሎቱን ስንጨርስ ደግሞ ሄሮድስ ያበራነውን መንገዳችንን አይቶ እንዳይከተል ኃይሉ ከድቶት ከኋላችን እንዲቀር በመቁጠሪያ ቀጥቅጠን አቅሙን ካወረድነው በኋላ እንዳይንቀሳቀስ በማሰር፤ የማጥፋት ጎዳናው እንዲዘጋና መዳከሙ እንዲጨምር፤ ሁለተኛውን ሰግደት እንሰግዳለን፡፡ ማስታወሻ፦ ከላይ በተጠቀሱት ስግደቶች ፈንታ እንደ አቅማችን፣ እንደ ፍቅር መጠናችንና ጠላትን ለማድከም እንደመፈለግ መጠናችን ሌሎቹን ረዘም ረዘም ያሉትን የአምልኮት ስግደቶች መተካት እንችላለን፡፡ የሚተካ ሳይሆን በተጨማሪ የንስሐና የቅዱሳንን ስግደትን መጨመር መንፈሳዊ የነፍስ አቅምን ይጨምራል፡፡ የጸሎት ቅደም ተከተል መርሃ ግብርን ለማታውቁ ወገኖቻችን፥ ከበታች ያለውን ንባበ ጥራዝ መመልከት ትችላለችሁ፡፡ #በርቱ @bemaleda_neku

  • @marytsebel8504

    @marytsebel8504

    2 жыл бұрын

    Tebarek wendimachin woldesenbey

  • @user-go2gx4it3w

    @user-go2gx4it3w

    2 жыл бұрын

    እናመሰግናለን ወንድማችን

  • @user-ky8zr8rm6m

    @user-ky8zr8rm6m

    2 жыл бұрын

    በግል ላክልኝ ወልደ ሰንበት

  • @almaaztamire4890

    @almaaztamire4890

    2 жыл бұрын

    Ameen Ameen Ameen Kale Hiyoten Yasemln

  • @rubyruby1458

    @rubyruby1458

    2 жыл бұрын

    እናመስግናለን ወንድማችን

  • @user-dl6tp2qf4w
    @user-dl6tp2qf4w2 жыл бұрын

    የዛሬው ገጠመኝ ለኔ በጣም የማይጠገብ እና ብዙ አስተምሮ ያለው ቢደገም የማይሰለች ነው መምህርራችን በጤና ኑርልን ወንድማችን እግዚአብሔር በቤቱ ያፅናህ

  • @user-qv7ni5uq6u
    @user-qv7ni5uq6u2 жыл бұрын

    ወይ ፈተና ሰለሁሉ ነገር እግዚአብሔር ይመስገን ወንድማችን እንኳን ከጨለማው ሕይወትህ ወደብርሀኑ ሕይወትህ መጣህ ታድለህ ግን መመረጥ መታደል ነው ቅዱስ ዑራኤል አክሎ ጥላከለላ ይሁንህ አሜን የጠየከውን ሁሉ ይመልስልህ አሜን ክርስቲያና ፈተና ናት ናትግን ጠክር ዋናው ነፍስህን. ማዳንህ ነው በተሰብህንም እግዚአብሔር ባድ ይሰብስብ እልህ እውነተኛውን መንግድ ይምራቸው ላተየደረሰ አምላክ ለነሱም ይድረስላቸው አሜን ተይዘው ነው ፍርዳቸው ነው አልፈርድም ታአምሩን ለሁለተኛ ዙር እምንሰማ ያድርግልን አሜን ። ልጂቱንም ልቦና ይስጣት ይገርማል እኮ በስመ አብ

  • @sara.a3214
    @sara.a32142 жыл бұрын

    አሜን አሜን አሜን ቃለ ህይወት ያሠማልን መምህር ግሩም ወይ ፈተና /ገጠመኝ *እፁብ ድንቅ ነው በእውነት* እኔማ ቅዱሳን ተገለፁልን ሲሉ በጣም እደለኞች ናቸው በእውንት

  • @roychehwan1959
    @roychehwan19592 жыл бұрын

    እግዚአብሔር ይመስገን እንኳን ደና መጣህልን ቃል ህይወት ያሰማል የተዋህዶ ልጆች እንንቃ እናስተዋል 🙏🙏🙏🙏

  • @saniatube2360
    @saniatube23602 жыл бұрын

    እልልልልልልልልልልል የግዚአብሔር ሰም የተመሠገነ ይሁን ወድማችን ወዶ ፈቅዶ ሰለመጣ እግዚአብሔር ይመሥገን አሜን@ መምህርዬ ጥቅሰ ላይ እኔም ሰነፍ ነኝ ቅዱስ ዑራኤል የኔንም ይክፈትልኝ በእውነት ድንቅ ነው እውነትም ወይ ፈተና

  • @user-et6wr8og6m
    @user-et6wr8og6m2 жыл бұрын

    ቃለ ህይወትን ያሰማልን መምህር በጣም ደስ ይላል አዎ ቁርአንን ጨርሶ ያነበበ ሙስሊም መፀሀፍ ቅዱስን ሲያነብ እውነቱ ይገባዋል ግን አብዛኛው ሙስሊም ክርክርን እንጂ እውነትን ማወቅ አይፈልጉም ጀማሪያችን ምንም ይሁን የሉላችንንም ፍፃሜ ያሳምርልን 👏🏻👏🏻👏🏻🌹⚘🌾🌾🕊🕊

  • @yordanosmamo6642

    @yordanosmamo6642

    2 жыл бұрын

    ትክክል እነሱ እዉነት ለማወቅ አይታገሉም እኛ ትክክል ነ ን ነዉ ብለዉ ነፍሳቸዉ መሀመድ ን ብቻ የሚያመልከዉ

  • @bere2532
    @bere25322 жыл бұрын

    በስመ አብ ወወልድ ወመንፋስ ቅዱስ አሀዱ አማላክ አሜን እንኳን ደህና መጡ መምህራችን በፀሎት አስቡና አባቶች ወንድሞች እህቶች ወለተ ሩፋኤል፣ወለተ እግዚአብሔር፣ሀብተማርያም፣ብርሃነ መስቀል፣ወለተ ስላሴ፣ወለተ እግዚአብሔር፣ወልደ ሚካኤል፣ማህደረ ማርያም፣ወለተ ማርያም፣ወልደ ገብርኤል፣ወለተ የውሀንሰ፣ፍቅረ ማርያም፣ወለተ ሚካኤል፣ወለተ ፃዲቅ፣ገብረ ስላሴ፣ሀብተሚካኤል፣ወለተ ሚካኤል፣ፍቅርተ ማርያም፣ ሰይፈ ኡራኤል እንዲሁም በፀሎት እስቡኝ ያሉትን አሳስቡልኝ

  • @user-is6oe6wv4v
    @user-is6oe6wv4v2 жыл бұрын

    እኛ ታኝታን ሰሌ ከኛ ወገን ያሎነ እናት ቤተክርስቲያንን ታቀለቀሉ አንድዬ ያንቀን🙏🙏🙏

  • @user-dn7ru2zn1y
    @user-dn7ru2zn1y2 жыл бұрын

    ወንድማችን ወልደ ሚካኤል እኳን ደህና መጣህ ወደ ክርስትና እምነት እልልልልልልልል ብለን ተቀብለናል ለኛም አስተምረህና እግዚአብሔር ይስጥልን እልልልልልልልልልልልልልልልልል መምህራችን ዝማሬ መላእክት ያሰማልን

  • @millonphoto811
    @millonphoto8112 жыл бұрын

    አሜን አሜን አሜን መምህር ቃለህይወት ያስማልን የተዋህዶ እምነት እማ ገና ገና እንደፀሀይ ያበራል እድሜና ጤና ይስጠን ብቻ ወንድማችን እንኩዋን በደህና መጣህ የክርስቲያኖች አምላክ በቤቱ ያጽናህ ለማለት እወዳለሁኝ ሀገራችንን ስላም ያድርግልን!!!

  • @sofiagetachew3079
    @sofiagetachew30792 жыл бұрын

    ሰላመ እግዚአብሔር ይብዛልህ መምህር እናመሰግናለን 👏 ወንድማችን እንኳን ወደ #ንፅህይ_ቅድስት_ኦርቶዶክስ_ተዋህዶ ቤተክርስቲያናችን በሰላም መጣህ✝️👏👏👏በቤቷ ያፅናህ ✝️👏✝️👏✝️

  • @hiwotfekadufekadu4724
    @hiwotfekadufekadu47242 жыл бұрын

    ስለ ማይነገር ስጦታው እግዚአብሔር ይመስገን ቅዱስ ዑራኤል ለእኛም ጠላት ዲያብሎስ የዘጋውን አእምሮአችንን እንዲከፍትልን ቅዱስ ፍቃዱ ይሁንልንልን መምህር እግዚአብሔር ይባርክህ የዚህ ልጅ መለወጥ ያንታም አስተዋፆ ስላለበት ቃለሂወትን ያሰማልን።

  • @user-wy7zg8ff7r

    @user-wy7zg8ff7r

    2 жыл бұрын

    አሜን አሜን አሜን

  • @malemale8487

    @malemale8487

    2 жыл бұрын

    Amen

  • @yordanosmamo6642

    @yordanosmamo6642

    2 жыл бұрын

    አሜን አሜን አሜን

  • @askaledechasa501

    @askaledechasa501

    2 жыл бұрын

    ✍️

  • @askaledechasa501

    @askaledechasa501

    2 жыл бұрын

    🙄

  • @user-dt4ii9wp8q
    @user-dt4ii9wp8q2 жыл бұрын

    🌿መምህር የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ክፍል ፭ ልቀቅልን ፊተኞች ኋለኞች ይሁናሉ ኋለኞች ፊተኞች ይሆናሉ የሚለው ቃል ተፈፀመ በቤቱ ያፅናህ ወልደ ሚካኤል አሜን ፫ 🌿ቅዱስ ዑራኤል የእኔንም አእምሮ ክፈትልኝ 🌿የሊቀ ሰማዕታት ቅዱስ ጊዮርጊስ በረከቱ ይደርብን🌿 አሜን 💚💛❤👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏 ዝማሬ መላእክትን ያሰማልን!

  • @samsungsam4681

    @samsungsam4681

    2 жыл бұрын

    አሜን 🤲🤲🤲

  • @user-zl6iu3fd8x
    @user-zl6iu3fd8x2 жыл бұрын

    *ስለ ሁሉም ነገር ተቀዳሚ ተከታይ የለለው ልኡል እግዚአብሔር ይክበር ይመስገን እንካን ወደ እውነተኛው ሃይማኖት በሰላም መጣህ ወንድማችን እመብርሃን ጥላ ከለላ ትሁንህ

  • @selam801
    @selam8012 жыл бұрын

    እግዚአብሄር ይመሰገን እንኳን በሰላም መጣህ ውድ መምህራችን በእውነት እኛ አንድ አንድ ግዜ ደካሞች ነን ብቻ እግዚአብሄር ይርዳን እና የሚገርም ገጠመኝ ነው ወንድማችን እንኳን በሰላም መጣህ ወደ ኦርቶዶክሰ ተዋህዶ ቀጥተኛዋ እምነት እግዚአብሄር እሰከ መጨረሻ በቤቱ ያጽናህ ኑኑኑ አብረን እንማር የተዋህዶ ልጆች

  • @azebshefirawo1050

    @azebshefirawo1050

    2 жыл бұрын

    ⛪️💕💞💚💛❤️

  • @user-kd2te7hr5c
    @user-kd2te7hr5c2 жыл бұрын

    መምህር እግዚአብሔር ጸጋውን ያብዛልህ በርታ እግዚአብሔር ይርዳህ። ጥሩ ትምህርት ነው እኛም ድካማችንን ስንፍናችንን ችግራችንን የምናይበት መድረክ ነው እግዚአብሔር ማስተዋል እንድናገኝ ይርዳን።

  • @dmulugeta
    @dmulugeta2 жыл бұрын

    አይቶ መርምሮ፣ በክፍት ልብ እውነትን በመሻት እንዴት እግዚአብሔር እንደሚገኝ ያሳየናል። እግዚአብሔር በአንድም በሌላም ይጠራል፣ ስንጠራ ለመስማት ያብቃን። እንኳን ደህና መጣህ ወንድማችን! ዘመዶችህንም እኛንም መልካም ምሳሌ ሆነነሃል። በተዋህዶ እምነት ያጽናህ መድኃኒዓለም!

  • @ruhama824
    @ruhama8242 жыл бұрын

    እዉነትም ወይ ፈተና በጣም ይገርማል መምህር ቃል ሕይወት ያሰማልን ወንድማችን እንኳን ደህና መጣህ በቤቱ ያፅናህ

  • @user-xf2rx3ex9y
    @user-xf2rx3ex9y2 жыл бұрын

    እግዚአብሔር ይመስገን ስለሁሉም ነገር በእውነት በጣም ትልቅ ትምህርት ነው የወንድማችን ሒወቱ ያስተምራል:: መምህር ቃል ሕይወትን ያሰማልን

  • @justdoit1446
    @justdoit14462 жыл бұрын

    ሰላም መምህር ቃለ ህይወት ያሰማልን እህት ወንድሞቼ በፀሎታችሁ አስቡኝ እግዚአብሔር ይስጥልኝ ።

  • @burteemyselfwithmywork5912
    @burteemyselfwithmywork59122 жыл бұрын

    አሜንመምራችንን ኑሪልንንንንንንንን ለዛለም🌿🌿🌿👏👏👏👏🌿🌿🌿🌿🌿❤❤❤❤💚💚❤❤🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏

  • @user-tz1hf4dl4j
    @user-tz1hf4dl4j2 жыл бұрын

    እግዚአብሔር ይመስገን መምህር የምንሰማውን ለፍሬ ለበረከት ያድርግልን አሜን አሜን በእውነት እጅግ ደስ የሚል ድንቅ ነው እግዚአብሔር ሲጠራን እንዲህ ነው "ሳትምረኝ አለቅህም " እንዳለው ብላቴና እሱ ፍቅሩ ሳይገባን አይለቀንም አብዱልሰመል (ወልደ ሚካኤል )እንኩዋን ወደ ቅድስት ተዋህዶ በሰላም መጣህ በበቤቱ ያፅናህ አሜን 👏

  • @shopiahhailu7659
    @shopiahhailu76592 жыл бұрын

    መምህሬ ሰላምህ ይብዛልኝ ስለ ሁሉም ነገር እግዚአብሔር ይመሥገን የድንግል ማርያም ልጅ እየሡሥ ክርስቶስ ወንድማችን እንኳን ደና መጣህ ወደ ቀጥተኛዋ ሀይማኖታችን እልልልልልልልልልልልልልልል በቤቱ ያፅናህ መምህራችን ዝማሬ መላእክት ያሠማልን አሜን፫

  • @user-bj7xq6ln3j
    @user-bj7xq6ln3j2 жыл бұрын

    ክብር ለልዑል ይሁን፡ የሚገርም ታሪክ ነው፡ የልጁ ፅናትና ትዕግስት ልዩ ነው፡ መምህር ፀጋውን ያብዛልህ፡

  • @user-pg3cm3wu8e
    @user-pg3cm3wu8e2 жыл бұрын

    ወይ ፈተና መምህራችን ቃለ ህይወት ያሰማልን እግዚአብሕር ይመስገን ወድማችን እንኳን ደህና መጣህ በጣም ደስ የሚል ነው 💚💚💛💛❤❤👏👏👏👏👏 እግዚአብሕሀ

  • @user-xw9nw2vj1d
    @user-xw9nw2vj1d2 жыл бұрын

    ሰላም መምህር ቃለ ህይወት ያሰማልን እህት ወንድሞቼ በፀሎታችሁ አስቡኝ እህተ ገብርኤል እና ቤተሰቦቿ ብላችሁ እግዚአብሔር ይስጥልኝ ።

  • @tajtaj9676
    @tajtaj96762 жыл бұрын

    በእውነት ቃለ ህይወት ያሰማልን መምህራችን ወድማችን እንኳን ደስ አለክ ተዋህዶ ለዘላለም ትኑር

  • @artflow216
    @artflow2162 жыл бұрын

    በእወነት በጣም ደሰሰ ይምል ትምህረት ነው ተመሰገን አምላከ ቃል ህይወት ያሰማልን መምህረ ተሰፋየ እግዜአብሔር አምላከ ዕድመና ጤና ይሰጠልን እንም ደሰሰሰ ቡልኛል እና ሰም እግዜአብሔር ይመሰገን ወንድሜች እንኳን በሰላም መጣህ ❤💕💕💕💕

  • @amalaldrawsheh4606

    @amalaldrawsheh4606

    Жыл бұрын

    በእው ነት በጣም ደስስ ይምል ትምህረት ነው ተመሰገንፈጣሪ ህይወት ያሰማልን ምህረተሰፈየ እግዚአብሔር ዕድመና ጤና ይሰጠልንእንም

  • @selamchala8687
    @selamchala86872 жыл бұрын

    መምህር በእውነት ቃለ-ህይወትን ያሰማልን፣ወንድማችን እንኳን ንፅይት፡ቅድስት፣ወደሆነች ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት መጣህልን፣በቤቱ ያፅናህ።

  • @fairoozfairooz3607
    @fairoozfairooz36072 жыл бұрын

    ተስፋ ስላሴ እመብርሃን ጎዳናው ሁሉ ታስተካክልልህ ምን ቃላት ይኖረኛል እግዚአብሔር ይጠብቅልን ወድማችን ሁሉን ነገር እግዚአብሔር ስለገለፀልህ በጣም ደስ ብሎኛል ጎዶልያስ በረከትህ ይደርብን አሜን ፫

  • @bahrnshwolde2894

    @bahrnshwolde2894

    Жыл бұрын

    AMEN AMEN AMEN 🤲🤲🤲

  • @saraT22
    @saraT22 Жыл бұрын

    ቃለ ህይወትን ያሰማልን ያገልግሎት ዘመንህን ይባርክልን እኛንም የረድኤት በረከቱ ተካፋይ ያድርገን... ከኔ የበረታቹ ፍቅርተ ሚካኤል ብላቹ የተጣመመው መንገዴን የድንግል ማሪያም ልጅ እንዲያቃናልኝ በፀሎታቹ አስቡኝ 🙏🙏🙏

  • @user-vm9zm3br4l
    @user-vm9zm3br4l2 жыл бұрын

    ውይይይ ደስ ሲል በጣም ምርጥ ገጠመኝ ነው በጣም አስተማሪ እግዚአብሔር ይባርክህ መምህር ወንድማችንም ፍፃሜህን ያሳምርልህ ።

  • @mmm-wi3pe
    @mmm-wi3pe2 жыл бұрын

    እግዚአብሔር ይመስገን መምህር ቃለ ህይውት ያሰማልን መምህር ወንድማችን እንካን ደናመጣክልን ዝማሬ መላእክት ያሰማልን መምህር አንተ አማልደን ሚካኤል እልልልልልልልልልልልል እልልልልልልልልልልልል አንተ አግዘን ሚካኤል ♥♥♥

  • @betigebeyehu2171
    @betigebeyehu21712 жыл бұрын

    እግዚአብሔር ይመስገን ቃለህይወት ያሰማልን እንዴት ደስ ይላል የእግዚአብሔር ድንቅ ስራ 💞🤲💐

  • @user-hh9df8cf4r
    @user-hh9df8cf4r2 жыл бұрын

    ስለ ሁሉም ነገር እግዚአብሔር ይመስገን መምህር ወንድማችንን አይነ ልቦናውን የመለሰ አምላክ እኛንምልቦናችንን ይመልስልን ወንድማችን በቤቱ ያፅናህ ቅዱስ ሚካኤል ጥላ ከላለ ይሁንህ መምህር ቃለ ህይወት ያሰማልን

  • @bezachanel2516
    @bezachanel25162 жыл бұрын

    መምህራችን በእድሜ በጤና ከነቤተሰብህ እግዚሐብሔር ይጠብቅህ እኛም አስተዋይ ልቦና ይስጠን መጨርሻዉ በጣም ደስ ይላል እመብርሃን አድንድ ታርጋቸዉ አሜን

  • @asefashyimam4102
    @asefashyimam41022 жыл бұрын

    ቃለ ህይወት ያሰማልን መመምህራችን ወንድማችነን ቅዱስ ዑራኤል መርቶህ እንኳን ወደ ትክክለኛዋ የኦርቶዶክስ እምነት አመጣው። እኛም የድንግል ማሪያም ልጆች እንበርታ እንፀልይ ንስሐ እንግባ እግዚአብሔር አምላክ አገራችነን ሰላም አንዲያደርግልን ሁሉን ማድረግ ይችላል!!! መጣህ

  • @user-ke5nx6sq7n
    @user-ke5nx6sq7n2 жыл бұрын

    እግዚአብሔር ይመስገን መምህራችን ደስ የሚል ነው ወንድሜችን እንኳን መጣህልን እግዚአብሔር አምላክ በቤቱ ያፅናህ በስደት ያለነውን በፀሎትህ አስበን ወንድማችን መምህራችን ስለምትመግበን የነፍስ ምግብ ሁሉ እግዚአብሔር አምላክ ይስጥልን ፀጋና ሞገስን ያላብስህ መምህርራችን የመምህር ፍሬዎች ሰማእቱ ቅዱስ እሲጢፍኖስ ከሁላችን ጋር ይሁን🙏❤

  • @yeqidusemikayeleliji5545
    @yeqidusemikayeleliji55452 жыл бұрын

    እግዚአብሔር ይክበር ይመስገን ውንድማችን እንኳን ወደ እውነተኛዋ ቅድስት ቤተክርስቲያን በሰላም መጣህ እውነቱን የገለፀልህ መድኅኔአለም ይክበር ይመስገን እግዚአብሔር የልብህን መሻት ይፈፅምልህ በቤቱ ያፅናህ ውድ መምህሬ ቃለለሕይወት ያሰማልን አባቴ ቅዱስ ሚካኤል ከክፉ ነገር ሁሉ ይጠብቅህ ከነቤተሰቦችህ

  • @yordanosmamo6642

    @yordanosmamo6642

    2 жыл бұрын

    አሜን አሜን አሜን

  • @merymain5649
    @merymain56492 жыл бұрын

    ውድ መምህራችን በእውነት ቃለ ህይወት ያሰማልን ፀጋውን ያብዛልህ ወንድማችን እንኳን መጣህልን በቤቱ እስከመጨረሻው ያፅናህ

  • @mebratsntayehu8843
    @mebratsntayehu88432 жыл бұрын

    እግዚአብሔር ይመስገን ውድ ወንድሜ መምህራችን ተስፍሽየ እንካንም በስላም መጣህልን አሜን አሜን አሜን ቃል ህይወት ያስማልን ለሁላችን እግዚአብሔር ያግልግሎት ዘመንህን ይባርክልህ እግዚአብሔር ሀይልና ብርታቱ ይስጥልን ውድ ወንድሜ መምህራችን ተስፍሽየ

  • @selamkahsay2489
    @selamkahsay24892 жыл бұрын

    ወይኔ! እግዛብሔር ልጆቹን የሚጠራበት መንገድ እንዴት ድንቅ ነው? አምላካችን ሆይ ሰምህ ለዘላለም ይክበር ይመሰገን! አሜን! ውንድማችን ክርሰቶሰ በፍቅሩ በሚገርም አጠራሩ ሰለጠራክ እንኳን ደሰሰሰ አለክ እልልልልልልልልልልልልል በጣም ነው ደሰ ያለኝ

  • @debritutulu5126
    @debritutulu51262 жыл бұрын

    የእግዚአብሔር ሰም የተመሰገን ይሁን ወንድማችን በቤቱ ያፅናክ እጅግ በጣም ደሰ ይላል መምህር ቃልህወት ያሰማልን እሬጅም እድሜ እና ጤና ይሰጥልን

  • @user-px4hk8wl8v
    @user-px4hk8wl8v2 жыл бұрын

    አሜን መምህሬ ቃለ ህይወት ያሰማልን ወንድማችን ወደ ኦርቶዶክስ እምነት እንኳን በሰላም መጣህ

  • @fuff9372
    @fuff93722 жыл бұрын

    በእውነት መምህር ቃለ ሂወትን ያሰማልን ፀጋውን ያብዛልህ የሰማአቱ ቅዱስ ጊወርግስ ስራው ድንቅ ነው ወድማችን እንኳንም ወደ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ መጣህልን እግዚአብሔር መጨረሻህን ያሳምርልህ እድህ ነው መመረጥ እኛ እውስጥ ሆነን እያቀላፍን ነው

  • @yordanosmamo6642
    @yordanosmamo66422 жыл бұрын

    አሜን አሜን አሜን ቃለ ሕይወት ያሰማልን መ ምህር ተመስገን ልብ ይስጣቸዉ እኔም አረቡ መፅሐፍ ቅዱስ ን ጨርሷል ከእኔ እኔ እንኳን ልጨርስ አላነበ ብኩም ወንጌልን ቤተክርስቲያን አዳምጣለሁ እና ሚስጥረ ስላሴ በጭራሽ አልገባ አለዉ ኢየሱስ ክርስቶስ እንዴት አምላክ ሰዉ ይሆናል አላምንም አለኝ እግዚአብሔር ሁሉን ማድረግ ይችላል እኮ እና በጣም ጥያቄ የሆነባቸዉ እሱ ነዉ ።እግዚአብሔር በፈለገዉ ይገለጣል

  • @tesgeredawolde4522
    @tesgeredawolde45222 жыл бұрын

    🎚 እግዚአብሔር ይመስገን🤲 መምህር ተስፋ ሥላሴ ! ይህ ድንቅ ተዓምር ነው እንጂ ገጠመኝ ( ወይ ፈተና ) ብቻ ተብሎ የሚታለፍ አይደለም 🎚

  • @_patience1001
    @_patience10012 жыл бұрын

    መምህራችን አንተን የሚቀየምህ ጠላታችን ዲያቢሎስ ነው። ባንተ ትምህርት የሚማረክ እንጂ የሚቀየም ከልቡ ያልሆነ ሰው ነው። ፈጣሪ ከክፉ ይጠብቅህ እመብርሃን ጥላ ከለላ ትሁንህ❤❤❤

  • @user-qt1gk3fz1w
    @user-qt1gk3fz1w2 жыл бұрын

    እግዚአብሔር ይመስገን በእውነት መምህራችን ቃል ህይወት ያስማልን ፀጋዉን ያብዛልህ ዕድሜና ጤና ይስጥልኝ አሜን አሜን አሜን

  • @selamdangewy8765
    @selamdangewy87652 жыл бұрын

    የአምላካችን ስሙ የተመሰገነ ይሆን ወድማች እዉነቱን አዉቀህ እንኳን ወደ ተዋህዶ መጣህ

  • @user-up2xr1mv9p
    @user-up2xr1mv9p2 жыл бұрын

    🤲🤲🤲🤲🤲🤲 አሜን ፫ እግዚአብሔር ይመስገን አሜን የተመሰገነ ይሁን አሜን ፫ መምህር ቃለ ህይወት ያሰማልን አሜን ፫ 🙏🙏💒ወይ ፈተና የሚገርምና በጣም አስተማሪ ገጠመኝ ነው ስለ ማይነገር ስጦታው እግዚአብሔር ይመስገን ወንድማችን በቤቱ ያፅናህ የአምላካችን ስም የተመሰገነ ይሁን አሜን🙏💓አሜን🕊💒አሜን💓🌹መምህራችን ዝማሬ መላእክት ያሰማልን ፀጋዉን ያብዛልህ 🙏🕊💒አተን የሰጠን ልዉል እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን አሜን ፫👏👏👏👏🙏🕊💒💓❤💐💐💐💐💐💐🕊🕊🕊🕊

  • @user-yl1oi2wk7p
    @user-yl1oi2wk7p2 жыл бұрын

    እግዚአብሔር ይመስገን እሄን ላደረገ ወንድማችን እንኳን ተመለስክልን መምህረ ፀጋውን ናብዛልህ🥰👏

  • @user-ji5rd2fb2h
    @user-ji5rd2fb2h2 жыл бұрын

    እግዚአብሔር ኣምላክ ይመስገን ሰላምህ ይብዛ ውድ መምህሬ እንኳዕ ብሰላም መጣህልን እሰይ ተመስገን ወንድማችን እንኳን ወደ ቀጥተኛዋ እምነት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ በሰላም መጣህ በቤቱ ያፅናህ ውድ መምህራችን የአገልግሎት ዘመንህ የድንግል ማርያም ልጅ ይባርክ እመ ብርሃን ትጠብቅህ

  • @user-kp5kq8ed1z
    @user-kp5kq8ed1z2 жыл бұрын

    እንኳን ብሰላም መጣህ እንቁ መምህራችን ብፅሎቶች ኣሰብኝ ወግናቼ ፍቅርተ ማርያም ብላቹሁ

  • @ghhghy3086
    @ghhghy30862 жыл бұрын

    እልልልልልልልልልልልልልልልልልልል እግዚአብሔር ይመስገን ወንድማችን እንኳን ወደ ቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሀይማኖት መጣህ በቤቱ ያፅናህ ፈተናን ያርቅልህ ቅዱስ ኡራኤል ይጠብቅህ መምህራን ቃለ ሕይወት ያሰማልን ጠላቶችሆን ያስታግስልን በጣም ብዙ ናቸዉ እድትሳሳት የሚፈልጉ እግዚአብሔር ይመስገን ምንም ስህተት እስካሁን አላገኙም በጭፍን ነዉ ጥላቻቸዉ ቅድስት ድንግል ማርያም ግርማ ሞገስ ትሁን በሔድክበት ሁሉ ትቅደምልክ አ ወይ ፈተና

  • @user-dc8kx6bv4l
    @user-dc8kx6bv4l2 жыл бұрын

    በጣም እሚገርምና ደስ የሚል ታርክ ነው እግዚአብሔር ይመስገን እንኳን ደህና መጣህልን ወድማችን በቤቱ ያፅናህ መመረጥ እደዚህ ነው 🙏❤️😍😍ቃል ሕይወት ያሰማልን መምህራችን እናመሰግናለን 😊❤️❤️❤️

  • @user-gf5pr7mx4k
    @user-gf5pr7mx4k2 жыл бұрын

    እግዚአብሔር አምላክ ይመስገን መምህር ቀዳሚ ሰማአት ቅዱስ እስጢፋኖስ የኛንም የተዘጋ አይምሮአችን ይክፈትልን አሜን

  • @user-do2ke2ll2g
    @user-do2ke2ll2g2 жыл бұрын

    እግዚአብሔር ይመስገን ሰላምህ ይብዛ መምህር ወንድማችን እንኳን ደህና መጣህልን ቃለ ህይወት ቃለ በረከት ያሰማልን ጸጋውን ያብዛልህ መምህር

  • @chfucuuccyyc2338
    @chfucuuccyyc23382 жыл бұрын

    ግሩም ነው የእግዚአብሔር ስራ ክብር ምስጋ ለሱ ይሁን አሜን ወድማችን እኳን ደና መጣህ እና ላተም መምህራችን ቃለ ህይወትን ያስማልን የኛ እቁ ፀጋውን ያብዛልህ ዘርህ ይባረክ አሜን

  • @aishyoman7316
    @aishyoman73162 жыл бұрын

    ክብርምስጋናይግባልን፣ለአምላከችን ማምራችን፣እግዚአብሔር፣ይጣብቅልን እልልልልልልልልልልልልልልልልል እልልልልልልልልልልልልልልልልልል እልልልልልልልልልልልልልልልልልልል 👏👏👏🕯🕊🤲🕯🕊🤲✝️🤲✝️✝️💐✝️🤲🕊💠🌾💐💐🌾🌾💠💠🌾🌾🌾💐👆

  • @uaeuar8642
    @uaeuar86422 жыл бұрын

    አሜን ቃለ ህይወት ያሰማልን ወንድማችን እንኳን ደና መጣህልን የድንግል ማርያም ልጅ እየሱስ ክርስቶስ ይክበር ይመስገን በቤቱም ያፅናህ

  • @user-lw5vi7kl9u
    @user-lw5vi7kl9u2 жыл бұрын

    በእዉነት የወንድማችን ጥንካሬ የሚደነቅ ነዉ ይህን ያደረገ አምላክ እግዚአብሔር ይመሥገን በቤቱ ያፅናልን

  • @banchiamlakkassahun3215
    @banchiamlakkassahun32152 жыл бұрын

    መምህር እንኳን ለመስቀለ ክርስቶስ ወርሃዊ በአል አደረሳችሁ ገጠመኙ በጣም ደስ የሚል ነው ወንድማችን እንኳን ወደ እናታችን ቅድስት ኦርቶዶክስ ሃይማኖት በደህና መጣህ በቤቱ ያጽናህ

  • @user-gm3sm6eq4l
    @user-gm3sm6eq4l2 жыл бұрын

    እግዚአብሔር ይመስገን አሜን እኳንም ወደእውነተኛው እምነት መጣህልን ፍፃሜህን ያሳምርልህ ወድማችን በውነት ፀጋውን ያብዛለት ከዚህም በላይ ለእህታችንም ልቦናዋን ከሱጋር አንቅቷት ተጋብተው ወልደው ለመሳም ያብቃቸው መምህር ፀጋውን ያብዛልህ

  • @asternegeash1312
    @asternegeash13122 жыл бұрын

    መምህራችን ቃለ ህይወትን ያሰማልን ወንድማችን እንኳን ደህና መጣልን

  • @lidyalidya7062
    @lidyalidya70622 жыл бұрын

    መምህሬ እንኳንጰደህና መጡ 💐❤ እውነትም ወይ ፈተና ይገረማን

  • @asichalkonjo3811
    @asichalkonjo38112 жыл бұрын

    ያሰተማረን የመከረን እግዚአብሔር ይመሰገን በውነት ይሄን ያደረገ እግዚአብሔር ይመሰገን ቃለህወትን ያሰማልን መምህራችን

  • @user-lw5vi7kl9u
    @user-lw5vi7kl9u2 жыл бұрын

    እግዚአብሔር ስራዉ ድንቅ ነዉ።ስለሥጦታዉ ምንይከፈላል ምሥጋና ይድረሰዉ።መምህር እንኳን ደህና መጣህልን የነብስን ምግብ መገብከን፣እኔ በአንተ ትምህርትና በስደት ሂወት ድሮ ከነበረ መጥፎ ማንነቴ በእግዚአብሔር ቸርነት ዛሬ አዲስ ሰዉሆኛለሁ ለወዳጅ ዘመድ እስቀሚደንቃቸዉ ድረስ በእንባ ይታጠባሉ።ሁለተኛ ተወልደሽ መሆን አለበት ይሉኛል።ብቻ በዚች ኮሜንት ተዘርዝሮ አያልቅም የተደረገልኝ ተአምር የድንግል ማርያም ልጅ አምላካችን መድኃኒአለም የተመሰገነ ይሁን።በፀሎታችሁ አስቡኝ፡ወለተ ዜና ማርቆስ ነኝ ቃለ ህይወት ያሰማልን እረጅም እድሜ ከጤና ያድልልን

  • @selamgebre6344
    @selamgebre63442 жыл бұрын

    በረከትህ ይደርብን ውድ መምህራችን 🙏🙏🙏 ቃለ ህይወት ያሰማልን 💚💚💚💚

  • @birutawtteshometeshome3234
    @birutawtteshometeshome32342 жыл бұрын

    በእውነት የሚገርም ታሪክ ነው እኔ እራሱ መምህር ሳልጠግበው ነው ያለቀው ገራሚ ነው ታድሎ ሙስሊሙ ፅናቱ ገራማ ነው መምህር በደንብ አርገህ ነው ያቀረብከው መጨረሻውን ያሳምርልህ የሰማዕቱ ነገርም ድንቅ ድንቅ ነው የሰማዕቱ አምላክ እግዚአብሔር ይመስገን

  • @geedadkalisam3037
    @geedadkalisam30372 жыл бұрын

    አሜን አሜን አሜን ቃለህይወት ያሰማልን መምህራችን

  • @helina123
    @helina1239 ай бұрын

    እግዝአብሔር ይባርክ መምህር እንደ አዲስ ጀምሪ 5ኛ ላይ ደርሻለው በጣም ብዙ እውቀት አግኝቼበታለሁ ። መምህር የእኔም ታሪክ ተመሳሳይ ነው የዛሬ 12 አመት በፌት ነው ከእስልምና ወደ ኦርቶዳክስ እምነት የተመረጥኩት በጣም ተፈትኜበታለሁ አሁን ደግሞ ቀድሞ በቤተሰቤ ውስጥ በለው የዛር መንፈስ እየተፈተንኩ እገኛለሁ እግዚብሔር ይህንንም አልፌ እግዚአብሔር ለእኔ ያደረገውን ሀያል ነገር እመሰክራለሁ እስከዝያው ግን በፀሎትህ አስበኝ መምህር ሂሩተ ስላሴ ነኝ።

  • @abrahamberhe2015EOTC
    @abrahamberhe2015EOTC2 жыл бұрын

    ሠላም ለኣንተ ይሁን መምህር እንዲሁም ወንድማችን እንኳን ወደ ጥንታዊት ቀጥተኛዋ ኦርቶዶክስ ክርሥትያን ተዋህዶ ሐይማኖት በሠላም መጣህ : ቅዱሥ እግዚአብሔር / የቅድስት ድንግል ማርያም ልጅ ቅዱሥ ኣማኑኤል በቤቱ ያፅናህ::

  • @user-nd1kj4vz4r
    @user-nd1kj4vz4r2 жыл бұрын

    እግዚአብሔር ይመስገን መምህራችን ሰላምህ ይብዛ መምህራችን በጣም ደስ ይላል እግዚያብሄር በአንድም በሌላም መንገድ ያስተምራል በጣም ሰነፎች ነን እኛ

  • @user-zy3dc5wg1z
    @user-zy3dc5wg1z2 жыл бұрын

    ሰማአቱ ቅዱስ ጊወርጊስ ፈጥኖ ደራሹ ለኔም በጣም ብዙ ነገር ያደረገልኝ ስሙን ጠርቸው አፍሬ አላውቅም ፈጥኖ ደራሹ ታምረኛው ሰማአት ክብር ምስጋና ይግባው

  • @user-on1fk7wx2o
    @user-on1fk7wx2o2 жыл бұрын

    እግዚአብሔር ይመስገን በጣም ደስ ይላል ወንድማችን እንኳን በሰላም ተቀላቀልከን የኛ ውድ መምህር ረጅም እድሜ ያኑርህ መድሀንያአለም የሰማነው በልቦናችን ይፃፍልን ቅዱስ ዑራኤል አባቴ የተዘጋው አይምሮአችን ያብራልን አሜን አሜን አሜን የቅዱስ ሚካኤል ሚልጃ አይለየን አሜን አሜን አሜን ዝማሬመላእክት ያሰማልን ፀጋውናበረከቱ ያብዛልህ

  • @batyweda8690
    @batyweda86902 жыл бұрын

    ውንድማችን እንኳን ደና መጣህ ቃለ ህይወት ያስማልን

  • @user-wj3sc6wy7o
    @user-wj3sc6wy7o2 жыл бұрын

    እግዚአብሔር ይመስገን በጣም ደስ የሚል ድንቅ ገጠመኝ ነው እንካን እግዚአብሔር ወደ ቤቱ አመጣህ ወንድሜ በጣም ቡዙ ትምህርት አግኝቼበታለው እግዚአብሔር አምላክ ፀጋውን ያብዛልህ ኑርልን መምህራችን 💞💞💞

  • @user-dr5xe1il2o
    @user-dr5xe1il2o2 жыл бұрын

    እግዚአብሔር ይመስገን መምህር በእውነት ያስደንቃል እግዚአብሔር አምላክ እንኮን ወደእራሱ አመጣህ ሌሎችንም በቸርነቱ ያምጣልን እስከመጨረሻው በቤቱ ያኑርህ ወንድማችን❤❤❤አቤቱ እኛንም ደካማወችን አሚሮአችንን ክፈትልን✝️

  • @efrataefrata6448
    @efrataefrata64482 жыл бұрын

    እግዚአብሔር ይመስገን እኳን ሰላም መጣህ ወንድማችን ወደ ወደ ኦርቶዶክስ እምነት ወደ ጠባቧ መንገድ

  • @user-ef6he7kg2o
    @user-ef6he7kg2o2 жыл бұрын

    እግዚአብሔር ይመስገን በጣም ደስ ይላል እኳን በሰላም ወደ ቀጥተኛዋ እምነት ኦክቶዶክስ ተዋህዶ ክርስትያን መጣህልን ወድማችን እማ ፍቅር ድግል ማሪያም ምግዜም ከጎንህ ትሁን አሜን

  • @helenkeflekefle9766
    @helenkeflekefle97662 жыл бұрын

    የእግዚአብሔር ስራ ግሩም ድንቅ ነው። መምህር ይህንን ታሪክ ስሰማ ራሴን እየመረመርኩ ነበር ለስም ክርስትያን ውስጤ ባዶ ያለእውቀት ክርስትናን እየኖርኩ እንደሆነ ገባኝ ።ብርሃነማርያም ብላቹ በፆሎት አስቡኝ እህትና ወንድሞቼ

  • @birhanulambebo7094
    @birhanulambebo70942 жыл бұрын

    ቅድስት ድንግል ማርያም ሩቱህ አንጀበት ሰተሀለች ትባርክሀ

  • @teduadaayal2841
    @teduadaayal28412 жыл бұрын

    እንኳን ደህና መጡ መምህር እንዴት አደሩ እኛ ደህናነን እግዚአብሔር ይመስገን አሜን አሜን አሜን

  • @user-fl8mb1if3x
    @user-fl8mb1if3x2 жыл бұрын

    እግዚአብሄር ይመስገን መምህር እንኳን ሰላም መጣህልን 😍😍😍😍😍

  • @user-bv6iw1ot4j
    @user-bv6iw1ot4j2 жыл бұрын

    እግዚአብሔር በድሜ በጤና ይጠብቅልን

  • @annatadbeer4172
    @annatadbeer41722 жыл бұрын

    ሰላም የእግዛብሄር ልጆች ሰላም መምህራችን እውነት ነው ሙስሊሞች የኡራኤልን ጠበል ይጠመቃሉ ይጠጣሉ እኔም የ ማቃት ጎረቤታችን ለቡዙ አመታት ልጅ መውለድ እምቢ ብሏት ነበር የኡራኤልን ጠበል ተጠምቃ ግን ወልዳለች

  • @rfes9321
    @rfes9321 Жыл бұрын

    እግዚአብሔር ይመስገን በወንድማችን ደስ ብሎኛል፣ክርስቶስ እየሱስ የእኛ አስተማሪ ያድርግህ።

  • @binubelatenaw8353
    @binubelatenaw83532 жыл бұрын

    አሜን አሜን አሜን እድሜ ይስጥልን መምህር ኢሞን እየዉ መምህር የዉስጥ ግሩፕ አለዉ የዉኑ እፕላይ ብዙ ልጆች እየጠፉ ነዉ እዳለ ክርስቲያን ይበዛሉ የትዳር ግሩፕ የብልግና ግሩፖችም አሉ ጎብኛቸዉ ማለትም ትናንሽ ምንም የማያቁ ልጆች ስልክ ስይዙ ገብተዉ ያዳምጣሉና ወላጆች ተጠንቀቁ መምህር ይችን እያት እኛ በዚኛዉ ስንሮጥ በሌ ያለዉ ችግር እኛም ብንርዳህ ብየነዉ

  • @user-tx9ej2rm4q
    @user-tx9ej2rm4q2 жыл бұрын

    እንኳን ሰላም መጣክ መምሕራችን ሰላምለ ናተይሁን እድ የትዋሕዶልጆች እህት ወድማቼ በያለንበት ፈጣሪ ይጠብቀን ሀገራችን ይጠብቅልን🙏🙏🙏

  • @bezachanel2516
    @bezachanel25162 жыл бұрын

    እግዚሐብሔር ሆይ እሄ ትምህርት እድንሰማ ስለፈቀድክልን እናመሠግንሀለን ሰምተን ቢቻ ሳይሆን በተግባር እድናዉሎ እንተ ፍቀድልን የዛሬ ልዩ ነዉ ገጠመኙ አይጠገብም እግዚሐብሔር ፀጋዉ ያብዛልህ ዉድ መምህራችን 🥰🥰🥰🥰

  • @user-xv5kw8or2c
    @user-xv5kw8or2c2 жыл бұрын

    እግዚአብሔር ይመስገን መምህርእየ የኛ እቁ እንኳን ደና መጣህልን እማ ፍቅር ትጠብቅልን ወድማችን እንኳን ደና መጣህ ስለ ማይነገር ስጦታው እግዚአብሔር ይመስገን

  • @procell803
    @procell8032 жыл бұрын

    እንኳን ደህና መጣህ መምህር እውነት ሰላምህ ይብዛልህ ሃይማኖታችንን እንድናዉቅ ነው ያስተማርሀን እና ማስተዋሉን አብዝቶ ይስጠን መዋደዱን አብዝቶ ይስጠን አገራችንን ሰላም ያድርግልን ለንስሀ ሞት ያብቃን አሜን አሜን አሜን

  • @user-qe9vc8rs5g
    @user-qe9vc8rs5g2 жыл бұрын

    እግዚአብሔር ይመስገን እንኳን ደና መጣህልን ቃል ህይወት ያሰማል የተዋህዶ

  • @binubelatenaw8353
    @binubelatenaw83532 жыл бұрын

    እድሜ ይስጥልን መምህር እደበትህ ሲጣፍጥ እልልልልል ደስ ሲል አስለቀሰኝ የቅዱስ ጊወርጊስራ በደስታ ስውድድድድ! !!!!!

  • @medina2419
    @medina24192 жыл бұрын

    ያስተማረን ቅዱስ እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን ለሱ የደረሰ ቅዱስ ኡራኤል ለኛም ለተቸገርን ወይ አንሔድ ወይ አንቆይ ግራ ለገባን እሱ ያስተምረን ወንድማችን በቤቱ ያፅናህ መምህር ስላንተ ምን እንደምል አላቅም በርታ ስላሴ እድሜና ጤና ይስጥ

  • @abenetyilma2486
    @abenetyilma24862 жыл бұрын

    አንተ በርታ ወንድም አለም እግዚአብሔር አምላክ ከእናቱ ከቅድስተ ቅዱሳን ከደንግል ማርያምጋ ከነቤተሰብህ ዕድሜ ከጤናጋ አብዝቶ ይስጥህ ስላልተፈቀደላት ነው አንድ ቀን ሲገለጽላት ትጠመቃለች የሊዲያን ልቡና የከፈተ እግዚአብሐር አምላካችን ልቡናን ይክፈትላት

  • @saraethiopi9378
    @saraethiopi93782 жыл бұрын

    እግዚአብሔር ይመስገን ቃለህይወት ያሰማልን መምህራችን በጣም ደስ ይላል እግዚአብሔር እዝነ ልቦናችንን ይክፈትልን አሜን ፫❤

Келесі